ቅንጭብጭብ
7.18K subscribers
413 photos
9 videos
5 files
502 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
#ቅንጭብጭብ
© #እርቃን_ገላዎች
#BcrAzyKid

ሴቶች ሰለጠኑ
መለመላቸውን አደባባይ ወጡ
በእርቃን ዘንጠው ከአደባባይ ዋሉ
ሠለጠንን ብለው ክብራቸውን አጡ
ላያደርሳቸውም እውር ተከተሉ
ማንነትን ጣሉ ሴቶች ሠለጠኑ።

ነሐሴ 5 2009
ሌሊት 8:04

Join us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ
© #እርቃን_ገላዎች
#BcrAzyKid

ወንዶችም አረፉ

አንባቢ ሆይ #አረፉ የሚለውን ሞቱ አልያም ስለደከማቸው እረፍት አደረጉ ብለህ እንዳትረዳው።

አረፉ/እርፍና/እርድና
አራዳ ሆኑ ከሚለው የመጣ ቃል ነው።


ወንዶችም አረፉ
እርድና ነው ብለው ቀበቶን ዘለፉ
ሡሪ አወረዱ እርፍና መስሏቸው
ቀደው ለጣጠፉ ሠክረው ተዘረፉ
እትት ብትት room ይዘው ነፉ
አዳርን በጭዌ ከቺክ ጋር ከነፉ
ሌሊቱን በደስታ በርካታ
አመቱን በሃዘን እንዲሁ ከነፉ
ጠንቀቅ ባለማለት ህይወትን ቀጠፉ
ሴቲት ሞተር ጭና ወንዶች ይኸው ጠፉ

ነሐሴ 05 2009
ሌሊት 8፡46

ለአስተያየት @bcrAzykid ይጠቀሙ።

join us
@kinchechabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#Bcrazykid
በእምነት ኢትዮጵያዊው


ይድረስ

~ በየሚዲያውና በየመንገዱ አብይ ተመረጠ ብላችሁ ጮቤ ለምትረግጡ እና
ለክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

~ በቅድሚያ እንኳን ደስ ያሎት ማለት ተገቢ ነውና፤ ለሹመቱ #እንኳን_ደስ_ያሎት #መልካም_የስራ_ዘመን ተመኘሁ

~ በተጨማሪም "ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል" የሚለውን ተረት እንዳይሠሙ፤ የተሰጠዎትን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ በአደራነት ብቻ ሳይሆን በማሳሰቢያነትም ጭምር ይያዙልኝ።

~ የዶ/ር አብይን መመረጥ ተከትሎ ብዙዎች ሲንጫጩ ጮቤ ሲረግጡ አየሁ ድንገት ከከተማ እየወጣሁ ነበር መኪናው ውስጥ ወሬው ስለመመረጥዎና ስለ ነገ ነው

ፐ! ወሬው ደምቆ የገባው ሁሉ የመሠለውን ይሰነዝራል...

- ኮማንድ ፖስቱን ያነሳልናል
- የራሱን ኮሚቴ ያዋቅራል
- ጥሩ አድርጎ ይመራል የተማረ ነው
- የታሠሩትን ይፈታል. . . ኧረ የማይሉት የለም

፨ ቆይ እነዚህን ነገሮች ለማድረግ ጠ/ሚ መሆን ብቻ በቂ ነው እንዴ???


'ንጃ አይመስለኝም!

ወደ ግለ ምልከታዬ ስመጣ ግን ለኔ ማንም ይሁን ማን ብዙም ለውጡ አልታየኝም

ይቺን ምሳሌ በደንብ አጢኑልኝ

~ ሁለት ብርጭቆ አስቀምጡ
አንዱን በንፁህ ውሃ
ሌላኛውን ባልጠራ(በድፍርስ) ውሃ ሙሉት

ቀጥሎም
1 ማንኪያ አፈር በንፁህ ውሃ ውስጥ ጨምሩ
1 ማንኪያ ጥርት ኩልል ያለ ውሃ በድፍርሱ ውሃ ውስጥ ጨምሩበት

አሁን ለውጡን ተመልከቱት

ንፁህ የነበረው ውሃ እየደፈረሰ (እየቆሸሸ) ነው።
ቀድሞውንም ድፍርስ የነበረው ግን ለውጥ አያመጣም 1 አይደለም 2/3 ማንኪያ የጠራ ውሃ ቢደረግበት አይጠራም። . . .


፨ አሁንም ለኔ የሚታየኝ የእነዚህ የውሃ ውጤት ነው።

~ ዶ/ር አብይ ጠ/ሚ ስለሆኑ ብቻቸውን ለውጥ ማምጣት ይቸግራቸዋል። ምን አልባትም ካሉበት አቋም እንዳይሽመደመዱ እሰጋለሁ።

~ አደራ ዶ/ር ቅድሚያ ኢትዮጵያዊነትና ሰብዓዊነት ይበሉልን።
~ በእርሶ የስልጣን ዘመን ደግሞ በተራቸው እነ በዳሳ እነ ገመቹ ሁንዴሳና ኡርጌሳ ህንጣ በህንጣ የሚደርቡበት እንዳይሆን ይልቁንስ አንድ ህዝብ አንድ ኢትዮጵያ ብለው አንድ የምንሆንበት በብሔር በክልል በጎሳ ሳንለያይ እኩል የምንታይና የምንኖርበት እንደሚሆን ተስፋ አለኝ።

አደራ ብለናል። አሳስበናልም!!!

በእምነት ነኝ
ኢትዮጵያዊው
(የማይታይ ፊርማ አለው።)

ሼር በማድረግ ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አድርሱልኝ።

አስተያየትዎን እና ምልከታዎን comment የሚለውን በመጫን ያድርሱን
፨ ያልገባው ሰው ኮመንት ላይ እንዲንጫጫ አልተፈቀደም!

Join.us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

የቀድሞ አብዮት አህመድ
የአሁኑ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ሆነው ቃለ መሃላ ፈፀሙ።
ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግር ተካሄደ

አሹ! #ይበል የሚያሰኝ ነው።

ይሄን ተከትሎም ንግግር አደረጉ ህዝብ አፉን ከፍቶ ሰማው እንደ ገደል ማሚቶ አስተጋባው፤ ንግግሩ ለምን ተወደደ?!

ምክንያቱ ግልፅ ነው...
በየመሃከሉ #ኢትዮጵያ የሚል ስትጠራው ሆነ ስትሠማው ማር ከመላስና ከማጣጣም በላይ ጥፍጥጥጥ የሚል ጣፋጭ ቃል አለ'ኣ

#እመኑኝ
~ የህዝባችን የልብ ትርታው #ኢትዮጵያ የሚል ነው ስለዚህ ኢትዮጵያ በተባለ ቁጥር ህዝቤ ልቡ ቀጥ ትላለች፤ እጅ ይሠጣል እንደ ጨው ሟምቶ እንደ ቅቤ ቀልጦ ይፈሳል

ይህን የተረዱት ጠ/ሚ/ዶ/ር ዐቢይ አህመድም የልባችንን ትርታ ቀጥ አድርገው ዋሉ። ያሉትንም እንደ ገደል ማሚቶ ስናስተጋባላቸው ዋልን። ይሁን ይሁን ክሽን ብሎ የጣፈጠ ንግግር ድንቅ በሆነ አገላለጽ ሥለ ኢትዮጵያችን የተቀነቀነ ጥዑም ዜማም ስለነበር ደጋግመን ሠማን...

~ እኔ ግን አሁንም እሠጋለሁ!!! የቀደመውን ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ ጽሁፍ ላይ እንዳሠፈርኩት ለውጥ ያመጣሉ ማለት ቸገረኝ...
ግን ደግሞ የራሳቸውን አሻራ ያሳርፋሉ ትንሽም ብትሆን የለውጥ ፍንጭ ያሳያሉ ብዬ ተስፋ አደረግሁ...
ለማንኛውም

~ "ምን ምንነቱን ነብር ዥንጉርጉርነቱን አይለቅም!" ነበር የሚባለው

~ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እንዳሏችሁ
ምንም የሚቀየር ነገር የለም...!

እንደዛ ነው እንግዲ ...ነብር ዥንጉርጉርነቱን አይለቅም።

አከተመ!

•፨• በዚህ አጋጣሚ አርአያ ሆነዋልና ለቀድሞ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ እጅግ የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳቸው።
ገና 24 ሰዓት ሳይሞላ የቀድሞ ጠ/ሚ ነበሩ ማለት ጀመርንኮ ሆ!
(ለካ ነበር እንዲህ ቅርብ ነው።)

፨ እንዲሁም ለአዲሡ ጠ/ሚ/ዶ/ር ዐብይ አህመድ እንኳን ለዚህ አበቃዎ በቃል ያነበቡትና በስራ የሚያሳዩን ተመሣሣይ ሆኖ ዳግም ከአሁኑ በበለጠ መልኩ እናወድስዎ ዘንዳ ምኞቴ ነውና ተስፋዬንም ጣልኩብዎ #አደራ #አደራ በሉልኝ

፨ በተጨማሪም በአንድ ወቅት መርገፍ ያለው ባንዲራ ክልክል ነው ብሎ ለቀማኝ ፖሊስ ዛሬ የቀድሞው ጠ/ሚ ለአዲሡ ጠ/ሚ የሰጡት ባንዲራ ባለ መርገፍ ነው በሉልኝ። አደራ

24/07/10
#Bcrazykid
በእምነት ኢትዮጵያዊው

Join.us
@kinchebchabi @kinchebchabi

አስተያየታችሁን comments የሚለውን በመጫን አደርሱን
#B ዛሬ ልደቴ ነው፤
አዎ ድፍን ፳፪ አመቴ።

#Bcrazykid
የቤቱ አባወራ ®
እኔ #ጎፈሬው በእምነት ተሾመ (#Bcrazykid)በጎፈሬነት ለሐገር አቀፍ ውድድር ቀርቤያለሁና የሚከተለውን ሊንክ በመንካት #Vote እንድታደርጉኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ።
#እኔ_ጎፈሬ_ነኝ!

https://www.wishpond.com/lp/2390399/entries/177585260

ሊንኩን በመጫን - ድምፅዎን ይሥጡኝ

ድምፅ ለመሥጠት
1, ሊንኩን ተጭነው በ opera/browser ይክፈቱ
2. ከፎቶው በታች Email ያስገቡና #Vote የሚለውን ይጫኑ
3 #send_confirmation የሚለውን ይጫኑ
4 የ Email አድራሻችሁን በመክፈት confirm በሉ

ጓደኞቻችሁ ድምፅ እንዲሰጡኝ #ሼር
አመሰግናለሁ

https://www.wishpond.com/lp/2390399/entries/177585260
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

፨ ጠላት ሀገር እንኳን በዚህ መልኩ አይዘረፍም!

• አዲስ አበባ ውስጥ 7 ግፍ የሚፈፀምባቸው ድብቅ እስር ቤቶች ተገኙ።
- « በአዲስ አበባ ዜጎች ከሰባት ወደማያንሱ ስውር ማሰቃያ ስፍራዎች ‘በአምቡላንስ እየተጓጓዙ!’ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ይፈጸምባቸው ነበር »
በእነዚህ እስር ቤቶች ዉስጥ
- ሴቶች ይደፈራሉ
- ወንዶች ግብረሰዶም ይፈፀምባቸዋል
- ወንዶች ብልታቸዉ ላይ ሀይላንድ ይንጠለጠልባቸዋል
- አይናቸውን ታስረው በጫካ ይጣላሉ

• ፖሊስ ጣቢያ፣ ማረሚያቤት እና ስውር እስር ቤቶች ውስጥ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በአሌክትሪክ ሾክ ማድረግ፣ ብልትን በፒንሳ መሳብ፣ ዛፍ ላይ ሰቅሎ ለረጅም ጊዜ ማቆየት፣ ጫካ ውስጥ እርቃንን ማሳደር፣ ጥፍር መንቀል፣ በብልት ላይ ውሃ ማንጠልጠል፣ አይናቸው ከታሰረ በኋላ ከከተማ አውጠቶ ጫካ ውስጥ መጣል፣ አልፎ አልፎ ከአውሬ ጋር በማሰር ማሰቃየት ሲደረግ ነበር።

• የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን በተመለከተ፦
ከ2004 እስከ 2010 ድረስ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን 37 ቢሊየን ብር የውጭ ግዢ ፈፅሟል።
እነዚህ ግዢዎች ዓለም አቀፍ ጨረታ ሳይፈፀምባቸው የተከናወኑ ናቸው። ግዢዎቹ በጥቅም በተሳሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት መሀከል የተከናወነ ነው።

• "የሰኔ 16 ቱ የቦምብ ጥቃት የተቀናበረው በብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኦሮሞ ስለሆኑ በኦሮሞ ቢገደሉ ተብሎ ነው በሙከራው ኦሮሞዎች እንዲሳተፉ የተደረገው።"

• ሜቴክ ከ2004-10 ዓ.ም ከ 37 ቢሊዬን (2.5 ቢሊዬን ዶላር) የውጭ ግዢ ያለጨረታ ከውኗል።
የሐገር ውስጥ ግዢ ሙሉ ለሙሉ ያለጨረታ ተከናውኗል። የሐገር ውስጥ ግዢም በግልፅ ጨረታ መፈፀም ሲገባው እስካሁን በዚህ መልኩ የተፈፀመ የለም። ከኮርፓሬሽኑ አመራሮች ጋር የዝምድናና የጥቅም ትስስር ካላቸው ሰዎች በብዙ እጥፍ በተጋነነ ዋጋ ይገዛ ነበር። ከአንድ ድርጅት 21 ጊዜ፣ ከሌላው ደግሞ 15 ጊዜ ግጭ ተፈፅሟል። ከአንድ ድርጅት በአንድ ጊዜ ብቻ የ2015 ሚሊዮን ብር ግዢ ያለጨረታ ተፈፅሟል።

• ከተቋሙ ተልዕኮ ውጪ የተፈፀሙ ግዥዎችም አሉ። ከዚህም ውስጥ የመርከብ ግዢ ይገኝበታል። በማይመለከተውም ስራ ገብቶ ወደ ንግድ ስራ አስገብቷቸዋል

# ከተገዙ አውሮፕላኖች መሀከል አንደኛው አውሮፕላን የት እንደገባ አልታወቀም!

• በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ተጠርጣሪዎች 36 በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

• በአጠቃላይ እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ የሜቴክና ደህንነት አመራሮች ቁጥር 63 ሲሆን እስካሁንም ያልተያዙ በሐገር ውስጥና ከሐገር ውጭ የተደበቁ አሉ።

፨ ከአቃቤ ሕግ መግለጫ
- ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ብርሃኑ ጸጋዬ
ህዳር 3 2011 ዓ.ም

#ኢትዮጵያ
#Bcrazykid

Join 👉 @kinchebchabi
ለመፃፍ እየፈለኩ እጄን የያዘኝ የማደርገው ግራ የገባኝ ልፍስፍስ ያልኩበት አማራጭ ያጣሁበት ባወራ ምን ልጠቅም ብዬ ዝም ብዬ በውስጤ ያረርኩበት እና የክልሉ መንግሥት ሆነ ሕዝብ ከሰብዓዊነት የዘቀጠ ነገር የታየበት

የጌዴኦ ሕዝቦች መፈናቀል እና በረሃብ ማለቅ ነው። ይሄ ኹሉ ሕዝብ ተርቦ ሜዳ ወድቆ እንዴት በሚሊየን በተመደበ ገንዘብ የዘመን መለወጫ ልናከብር ነው ይባላል??? (ደቡብ - ጌዴኦ)

ኧረ እየተሳሰብን - ኧረ እንደሰው እየተሰማን - ነግ በኔ ነው
የጌዴኦ ሕዝቦች ተፈናቅለዋል! ተርበዋል እናቶች ጡት ደርቆባቸው የሚያጠቡት አጥተዋል...

ከለገጣፎ ሲፈናቀሉ መንግሥት መረጃ የለኝም
ከጌዴኦ ሲፈናቀሉ የሚዲያ ሽፋን የለም
ተረኛ ደግሞ #ሱሉልታ ነው ሊያፈናቅሉ ውጡ ማለት ጀምረዋል...

ሕዝብ እያየ ዝም መንግሥት እየሰማ ዝም

አንድም ሰው አይፈናቀልም ተብሎ አልነበር እንዴ?!
የሚያወራ ብቻ ሳይሆን የሚሰማ የውጪውን ሳይሆን ቀድሞ የቤቱን የሚሰራ መንግሥት እፈልጋለሁ!!!
አከተመ!!!

#ኢትዮጵያ
#Bcrazykid
ቅንጭብጭብ
#B ዛሬ ልደቴ ነው፤ አዎ ድፍን ፳፪ አመቴ። #Bcrazykid የቤቱ አባወራ ®
#B ዛሬም ልደቴ ነው፤
አዎ ድፍን ፳፫ አመቴ

#Bcrazykid
የቤቱ አባወራ ®

(ማነው መልካም ልደት የሚለኝ፤ መልካም የሚመኝልኝ 😊)
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#ኢትዮጵያዬ.... ገስግሺ ወደፊት

ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ መድኃኒትን የሀገር በቀል እውቀት ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማጣመር እየሞከረች ነው።
ዕፀ ደብዳቤና ሌሎች መጻሕፍቶችሽ ለዛሬ መድሀኒት ናቸውና ይውጡ ያገልግሉ...
ሐኪም አበበች ሽፈራውና ሌሎች የዕፅ አዋቂዎች ትኩረት የተነፈጉ የባሕል ሐኪሞችሽ ዛሬ ተባብረው አለምን አፉን ያሲዙልኝ ዘንድ እርሱ ይራዳቸው።

#አሜን
#ኢትዮጵያ
#Bcrazykid

የኮሮና ቫይረስን በሳይንሳዊ ምርምር በተደገፈ የሀገር በቀል እውቀት ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማቀናጀት ቫይረሱን ለማከም የተሰራው መድሃኒት መሰረታዊ የምርምር ሂደት በማለፍ ተደጋጋሚ የቤተ ሙከራ ሞዴሊንግ ሂደቶችን በስኬት አልፏል፡፡

ምርምሩ የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ መከሰቱ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጪ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ተደጋጋሚ የምርመር ሂደት አልፎ ወደ ምርት እና ቀጣይ የእንስሳት ፍተሻ እና ክሊኒካል ፍተሻ ስራዎች እንዲሸጋገር ተደርጓል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር ኢንጂ.)፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰና ከኢትዮጵያዊያን የባህል ሃኪሞች ጋር እና የህክምና ተመራማሪዎች ጋር በመሆን የሀገር በቀል እውቀቶችን በሳይንሳዊ ሂደቶች በማሳለፍ ለዘመን አመጣሹ ኮሮና ቫይረስ( ኮቪድ -19) ወረርሽኝ ህክምና የተዘጋጀውን መድሃኒት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችላቸውን ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።

መድሃኒቱ የመከላከል አቅም የሚጨምር፣ መርዛማነት የሌለው እና አዋጭነቱ የተረጋገጠ ነው፡፡

የምርምር ሂደቱ ተጠናቅቆ ወደ ምርት ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን ዝርዝር መረጃዎችን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ይሰጣል፡፡

@kinchebchabi @kinchebchabi