ቅንጭብጭብ
7.3K subscribers
410 photos
9 videos
3 files
498 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
ውድ የ ቅንጭብጭብ ወዳጆቼ ከታላቅ ይቅርታ ጋር ሠሞነኛ በሆነ አጋጣሚ ሠሞኑን ማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ ላልኖር ሥለምችል ቅንጫቢ ፖሥት አይኖርም።

ሐሣብ አሥተያየታችሁ አይለየን . . . .

በመጪው ሣምንት ሐሙስ ከሠዓት እሥክንገናኝ ቸር ሠንብቱልኝ. . .

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅ!
#አሜን

@kinchebchabi @kinchebchabi

ለአሥተያየት እና ጥቆማ @bcrAzykid


ሠናይ ሣምንት. . .
ደግ ደጉን የምንሠማበት የአገራችን #ኢትዮጲያ ትንሣኤዋን የምናይበት የምሥራች የምንሠማበት ያድርግልን

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!


@kinchebchabi #ቅንጭብጭብ
ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለደብረታቦር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፡፡

ክፈት በለው በሩን የጌታውን
ክፈት በለው በሩን የጌታውን
እዛ ማዶ ሆ
ጭስ ይጨሳል ሆ
አጋፋሪ ሆ
ይደግሳል ሆ
ያችን ድግስ ሆ
ውጬ ውጬ ሆ
በድንክ አልጋ ሆ
ተቀምጬ ሆ
ያቺ ድንክ አልጋ ሆ
አመለኛ ሆ
ካላንድ ሰው ሆ
አታስተኛ ሆ
ሆያ ሆዬ ጉዴ
ጨዋታ ነው ልማዴ
ሆያ ሆዬ ጉዴ
ሙልሙል ሙልሙል ይላል ሆዴ...

ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ
ሆያ ሆዬ ሆሆሆሆሆ
የቡሄ ለታ ሆሆሆሆ
ችቦ ሲወጣ ሆሆሆሆ
ከእማምዬ ቤት ሆሆሆሆ
ሙልሙሉ ይውጣ ..ሆሆሆሆ

ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ
ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ

አመት አውዳመት ድገምና አመት
ድገምና

የአባቢዬን ቤት ድገምና አመት ድገምና ሰላም ይሙላበት የማምዬን ቤት ድገምና ፍቅር ይሙላበት ድገምና ክበር በንስሀ ከበር በፀሎት የእነ አባቢዬን ቤት እግዜር ይግባበት ክበር በንስሀ ክበር በፀሎት የእማምዬን ቤት
እግዜር ይግባበት

በፈረስ አፍንጫ አይገባም ትንኝ የ #ቅንጭብጭብ ጌታ አግዜር ይስጥልኝ።

#አሜን ለራሴ😂
በፈረስ አፍንጫ አይገባም ትንኝ የ #ቅንጭብጭብ ወዳጅ እግዜር ያቆይልኝ።

አመት አመት ያድርሠን በቸር በሠላም በፍቅር ሣይለየን በጤና ለአመቱ በሠላም ያድርሠን።

#ቅንጭብጭብ @kinchenchabi

🎆🌠🎆መልካም በዓል🎆🌠🎆


#B_crAzy_kid 2፡20😂

Join us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጲያ
#አሜን_በሉ!

ሕይወት አስቸጋሪ ብትሆንና የሰራኸው ሁሉ ባይሳካ እንኳን "አሜን" በል! ምክንያቱም የተሻለ ቀንና አዲስ የሕይወት ምእራፍ ዛሬ ስለተሰጠህ ያልተሳካልህና አስቸጋሪ የሆነብህን ሁሉ በዛሬው አዲስ ቀን መቀየርና ማስተካከል ትችላለህና።

ፍቅረኛሽ ጥሎሽ ቢሄድና እሱን መመለስ ወይም መታረቅ የማይቻልበት ሁኔታ ቢፈጠርም "አሜን" በይ! ምክንያቱ እሱ ያንቺ አይደለም ማለት ነው። አንቺ የአቅምሽን ጥረሻል፤ሁኔታዎች ግን ሊመለስ እንደማይችል ነገሩሽ።

ዋው ... ዛሬ ደሞ እንዴት ደስ የሚል አዲስ ቀን በሕይወትሽ ላይ ተጨመረልሽ? ምናልባትኮ ዛሬ ውስጥሽ በደስታ ከተሞላና ከውስጥሽ ያሉትን የቅሬታ ስሜቶች ሁሉ ካባረርሻቸው የተባረከና ያንቺ የሆነውን የሂወት አጋርሽን የምታገኚበት ቀን ይሆንልሻል። ታዲያ ይሄ አሜን አያስብልም?

ከስራ ብትባረርም "አሜን" በል። ዛሬ ለአንተ አዲስ አማራጭንና ምናልባትም ትናንት ተቀጥረህ ትሰራበት ከነበረው ስራ የተሻለ ዛሬ ታገኛለህና አሜን በል። ይህኛው ስራህም ከባለፈው የበለጠና ከራስህ አልፈህ ሌሎችንም የምትቀጥርበት ሊሆን ይችላል።

ለዶክተሮችበጣም ያስቸገረና የማይድን የመሰላቸው ህመም ቢያሰቃይሽም አንቺ ግን እያመመሽ እንኳን ህመሙንረስተሽ "አሜን" በይ! ያኔ የዓለም ሁሉ ፈጣሪ ሁሉን ቻይ አምላክ ለዶክተሮቹ የከበዳቸውን ሁሉ ይቀይረዋል አይቻልም ያሉትን ሁሉ ይለውጠዋል። ሕይወትሽም አዲስ ይሆናል።

🙏 ለወዳጅዎ ያካፍሉ 🙏

Join.us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#ኢትዮጵያዬ.... ገስግሺ ወደፊት

ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ መድኃኒትን የሀገር በቀል እውቀት ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማጣመር እየሞከረች ነው።
ዕፀ ደብዳቤና ሌሎች መጻሕፍቶችሽ ለዛሬ መድሀኒት ናቸውና ይውጡ ያገልግሉ...
ሐኪም አበበች ሽፈራውና ሌሎች የዕፅ አዋቂዎች ትኩረት የተነፈጉ የባሕል ሐኪሞችሽ ዛሬ ተባብረው አለምን አፉን ያሲዙልኝ ዘንድ እርሱ ይራዳቸው።

#አሜን
#ኢትዮጵያ
#Bcrazykid

የኮሮና ቫይረስን በሳይንሳዊ ምርምር በተደገፈ የሀገር በቀል እውቀት ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማቀናጀት ቫይረሱን ለማከም የተሰራው መድሃኒት መሰረታዊ የምርምር ሂደት በማለፍ ተደጋጋሚ የቤተ ሙከራ ሞዴሊንግ ሂደቶችን በስኬት አልፏል፡፡

ምርምሩ የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ መከሰቱ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጪ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ተደጋጋሚ የምርመር ሂደት አልፎ ወደ ምርት እና ቀጣይ የእንስሳት ፍተሻ እና ክሊኒካል ፍተሻ ስራዎች እንዲሸጋገር ተደርጓል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር ኢንጂ.)፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰና ከኢትዮጵያዊያን የባህል ሃኪሞች ጋር እና የህክምና ተመራማሪዎች ጋር በመሆን የሀገር በቀል እውቀቶችን በሳይንሳዊ ሂደቶች በማሳለፍ ለዘመን አመጣሹ ኮሮና ቫይረስ( ኮቪድ -19) ወረርሽኝ ህክምና የተዘጋጀውን መድሃኒት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችላቸውን ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።

መድሃኒቱ የመከላከል አቅም የሚጨምር፣ መርዛማነት የሌለው እና አዋጭነቱ የተረጋገጠ ነው፡፡

የምርምር ሂደቱ ተጠናቅቆ ወደ ምርት ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን ዝርዝር መረጃዎችን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ይሰጣል፡፡

@kinchebchabi @kinchebchabi