ቅንጭብጭብ
7.63K subscribers
408 photos
9 videos
1 file
497 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#ኮሮና_ቫይረስ ❗️

የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች / Possible Symptoms ዋና ምልክቶች

※ ትኩሳት (Fever)
※ ሳል (Cough)
የምግብ መፈጨት ችግር (Digestive Problem)
※ ማስመለስ (Vomiting)
※ ተቅማጥ (Diarrhea)
※ የምግብ ፍላጎት መቀነስ (Loss of Apetite)
የነርቭ ምልክት (Nerve Symptoms)
※ የራስ ህመም (Head Ache)
የእይታ ችግር (Vision Problems)
※ የአይን ማቃጠል ወይም መለብለብ ናቸው።

የቫይረሱ መተላለፊያ መንገዶች፦

በቻይና የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ (Coronavirus) ወረርሽኝ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ወደ ጤነኛ ሰው በሚከተሉት መንገዶች ይተላለፋል፦
※ በበሽታው የተያዘ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ወቅት በአየር ይተላለፋል።
※ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ከተነካካን ወይም እጅ ለእጅ ከተጨባበጥን (ሰላምታ)።
※ ቫይረሱ ያለበትን ዕቃ ወይም ቁስ ከነካን በኋላ አፋችንን፣ አፍንጫችንን ወይም አይናችንን ከነካን በቫይረሱ በቀላሉ እንያዛለን።

ቫይረሱን ለመከላከል ምን ማድረግ አለብን?

ለኮሮና ቫይተስ የሚሆን ክትባት እስካሁን አልተሰራም፤ ለኮሮና ቫይረስ ኢንፌክሽንን ለመከላከል የሚረዳን ልክ ጉንፋን እንዳይዝዎት የሚያደርጉትን አይነት ጥንቃቄ ያድርጉ፦
※ እጅዎን ለብ ባለ ውሃ እና ሳሙና ይታጠቡ ወይም ከአልኮል የተሰሩ የእጅ ሳኒታይዘሮች (Hand Sanitizer) ይጠቀሙ።
※ ህዝብ በተጨናነቀባቸው ቦታዎች ላለመሄድ ይሞክሩ
※ በሽታው ቢኖርብዎትም ባይኖርብዎትም አፍና አፍንጫዎን የሚከልል ማስክ ያድርጉ
※ አፍዎን፣ አፍንጫዎንና አይንዎን በፍጽም በእጅዎ ወይም በጣትዎ አይንኩ።
※ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ያለዎትን ቅርርብ (ንክኪ) ይቀንሱ።

አጠቃላይ መረጃ
★ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር = 4,474
★ Total Confirmed Cases = 4,474
★ አጠቃላይ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች = 107
★ Total Deaths = 107
★ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር = 63
★ Total Recovered = 63
በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ስርጭት በሃገር (Confirmed Cases by Country/Region)
※ ቻይና (Mainland China) = 4,409
※ ሆንግ ኮንግ (Hong Kong) = 8
※ ታይላንድ (Thailand) = 8
※ ማኩዋ (Macua) = 6
※ ማሊዢያ (Malaysia) = 4
※ አውስትራሊያ (Australia) = 5
※ ሲንጋፖር (Singapore) = 5
※ ታይዋን (Taiwan) = 5
※ ጃፓን (Japan) = 4
※ አሜሪካ (US) = 5
※ ፈረንሳይ (France) = 3
※ ደቡብ ኮሪያ (South Korea) = 4
※ ቬትናም (Vetnam) = 2
※ ካምቦዲያ (Cambodia) = 1
※ ካናዳ (Canada) = 1
※ ኔፓል (Nepal) = 1
※ ጀርመን (Germany) = 1
※ ኮትዲቫር (Ivory Coast) = 1

ለሌሎች #SHARE ያድርጉ!
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#ሼር_ይደረግ!!!

#አንሸበር_እንጠንቀቅ
_______

ኮሮና ቫይረስ አፍሪካን ማመስ ከጀመረ ሰነባብቷል...
ዛሬ በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድ ጃፓናዊ ተገኝቷል። (ገና ሊቀጥል ይችላል!)

አሁን ላይ ዓለምን እያዳረሰ ያለው የቫይረሱ ወረረሽኝ ኢትዮጵያም ውስጥ ተገኘ ብሎ ያለቅጥ መሸበር አይጠቅመንም!።

#መረጃ_ስለ #ኮሮና_ቫይረስ

ኮሮና ቫይረስን መጨነቅ እና መፍራት ሳይሆን በእውቀት መራመድ ያቆመዋል!
በውሃን ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽንለመዋጋት በስፍራው ከሚንቀሳቀስ ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዴት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ እንዴት በዕለት ተዕለት የህይወት እርምጃ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ማስቆም እንደሚቻል የተሰጠ መረጃ!

ከሮና ቫይረስ የአፍንጫ እርጥበት እና አክታ የሚያስከትል ሳል ያለው አይደለም፡፡ በተቃራኒው አፍንጫ የማያረጥብ እና ደረቅ ሳል የሚያስከትል በመሆኑ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡

ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ ...ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣት ቫይረሱን ይገድበዋል፡፡ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡

በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/ Snow አትመገቡ! < የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡

1. ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም። ማንኛውንም አይነት ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡
< በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው፡፡

< አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ ተጠቂ አትሆኑም፡፡

2. ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12 ሠዓታት በህይወት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደ እጀታዎች፣ በሮች፣ የቤት ዕቃዎችን፣ የአውቶቡስ የባቡር ወይም የትራም መደገፊያ እጀታዎችን ወይም ምሰሶዎችን ከነካችሁ በኋላ እጃችሁን በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡

3. ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሙሉ ዘወትር በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡ በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ጸሐይ ላይ ብታሰጡዓቸው ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ይገድለዋል፡፡ በቫይረሱ የመጠቃት ምልክቶች #ምን ምንድን ናቸው?

1. ቫይረሱ መጀመሪያ መቀመጫውን ጉሮሮ ላይ በማድረግ የጉሮሮ ብግነት እና የጎሮሮ ድርቀት ስሜት ያስከትላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት ከ3-4 ቀን በሰው ላይ ሊቆይ ይችላል::

2. ቫይረሱ በመተንፈሻ ቱቦ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመጠቀም ወደ ትራኪያ ከወረደ በኋሊ መቀመጫውን ሳምባ ውስጥ ያደርጋል፡፡

ሳምባን በማጥቃት ኒሞንያ/ የሳምባ ብግነት ያስከላል፡፡ ይህ ምልክት የሚታይባችሁ ሁሉ በፍጥነት ወደ ህክምና ሂዱ!! በቫይረሱ ላለመያዝ ምን ማድረግ ይገባል?

1. የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ቀጥታ ከንክኪ ጋር የተያያዘ ሲሆን ቫይረሱ ያረፈባቸውን ቁሳቁሶች እና ልብሶች ወዘተ... መጠቀም ዋነኛ መተላለፊያው መንገዱ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም ነገር ከነኩ በኋላበተደጋጋሚ እጅን በደምብ መታጠብ ዋነኛ መከላከያ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡

< ቫይረሱ በሰው እጅ ላይ በሕይወት መቆየት የሚችለው 10 ደቂቃ ያህል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአስር ደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ነገር ሊከናወን ይችላል፡- አይንን ማሸት፣ አፍንጫን መንካት፣ ጣቶችን ወደ አፍ መውሰድ ወይም [እንደ ጥፍር የመመጥመጥ ክፉ ልማድ] ቫይረሱን በቀላሉ ወደ ጉሮሮ እንዲሄድ ሊያደርገው ይችላል፡፡

< ስለዚህ ለራሳችሁና ለባልንጀራችሁ (ለሌላው ሰው) ደህንነት ስትሉ በጣም በተደጋጋሚ እጆቻችሁን ታጠቡ፡፡

2. አፍ እና ጉሮሮን ጸረ-ተሕዋስ መድሀኒቶችን በመጠቀም መጉመጥመጥ ቫይረሱን ሊያስወግድ ወይም ወደ ጉሮሮ የሚሄዱትን መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ አፍን መጉመጥመጥ ወደ ጉሮሮ ወደ ትራኪያ አልፎም ወደ ሳምባ ቫይረሱ የሚያደርገውን ጉዞ ሊያግደው ወይም ሊቀንሰው ይችላል፡፡

3. የኮምፒውተራችሁን ኪ-ቦርድ እና ማውዝ በጸረ- ተህዋስ በሚገባ አጽዱ።

ተጨማሪ...
ምን እናድርግ?
______

1 #እጃችንን_እንታጠብ
አዘውትረን በሳሙና እና በውሃ ለሀያ ሴኮንድ እጆቻችንን አዘውትረን እንታጠብ።

2 #መጨባበጥ_ይቅር

3 #ሰው_ከሚሰበሰብበት_እንራቅ

4 #እንሸፈን
በሚያስለን ወይንም በሚያስነጥሰን ግዜ ፊታችንን በክንዳችን ወይም በመሸፈኛ እንሸፍን።

5 #ፊታችንን_አንነካካ

6 #የጋራ_መገልገያዎችን_አንነካካ
ብዙ ሰው የሚነካካቸውን ነገሮች ማለትም የበር እጀታዎች፣ የደረጃ መደገፍያዎች እና የመሳሰሉትን አንነካካ። ምናልባት ከነካን እጅን በሳሙና መታጠብን አንርሳ።

7 #ነጻ_የስልክ_መስመር
የበሽታው ምልክቶች ከታዩብን #8335 ነጻ የስልክ መስመር መደወል አንርሳ።

አስታውሱ!
ወረርሽኙን ማቆም ባንችል እንኳን ፍጥነቱን መቀነስ እንደምንችል አንዘንጋ።

______ #በተለይም

#ወጣቶች በበጎ ፈቃድ በየቦታው ተደራጅታችሁ ከጤና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ህብረተሰቡን እናግዝ።

#የእምነት_ተቆማት የስብከት እና የአምልኮ መርሐ ግብሮቻችሁን ለምእመናኖቻችሁ ጤና ቅድሚያ በመስጠት ላልተወሰኑ ጊዜያት ብታስተላልፏቸው።

#መንግስት ቫይረሱ ብሔራዊ አደጋ መደመሆን እንዳይሸጋገር የላቦራቶሪ እና የለይቶ ማቆያዎች አቅሙን በአፋጣኝ መገንባት ቢችል ....

መረጃውን ሼር በማድረግ የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ #SHARE it!
(© ከተለያየ ድረ ገፅ የተሰበሰበ)

Join us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይበል የሚያሰኝ ውሳኔ... (ከመንግሥት የተሰጠ መግለጫ)

መጋቢት 7 ቀን ከተወሰኑት ውሳኔዎች በተጨማሪ፦

1. ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ መንገደኞች ሁሉ በራሳቸው ወጪ ለዚሁ ዓላማ በተወሰኑ ሆቴሎች ውስጥ ለ14 ቀናት ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ።

2. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 ሀገራት የሚያደርገውን በረራ በጊዜያዊነት እንዲያቆም።

3. መንግሥት የሀይማኖት ተቋማት እና የአምልኮ ስፍራዎች ላይ የምዕመናን መሰባሰብ በጊዜያዊነት መቋረጡን የሚደግፍ ሲሆን፣ የኮቪድ19 ቫይረስን ስርጭት ለመግታት ያስችል ዘንድ ንክኪን በማያስከትሉ ሌሎች አማራጮች አምልኮ ቢካሄድ ይመረጣል።

4. ማረሚያ ቤቶች ጊዜያዊ ማቆያቸውን እና ሌሎች ስፍራዎችን በመጠቀም ጭምር መተፋፈግን እንዲያስቀሩ። በተጨማሪም፣ አዲስ ታራሚዎች ወደ ማረሚያ ቤት ከመግባታቸው በፊት የኮሮና ቫይረስ ምርመራን እንዲያካሂዱ። ታራሚዎችን መጠየቅ ለተወሰነ ጊዜ የተከለከለ ሲሆን፣ በቀላል ጥፋት ምክንያት ማረሚያ ቤት የገቡ ወይም የእርምት ጊዜያቸው የተቃረበ ታራሚዎች እንዲፈቱ።

5. የውጪ ዜጎችን መተናኮል ተቀባይነት የሌለው እና ኢትዮጵያዊ ያይደለ ጥፋት ነው። ሕዝቡ ቫይረሱ ዘርና ዜግነትን የማይለይ መሆኑን ተገንዝቦ፣ የውጪ ዜጎች ላይ ጣት ከመቀሰር እና ከማግለል ይልቅ፣ ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሰረት ቫይረሱን የመከላከል እርምጃዎችን መውሰድ ይኖርበታል።

6. ላለፉት ቀናት የማስተባበር ሥራን ሲሰሩ የነበሩ ወጣቶችም፣ የበጎ ፈቃድ ሥራዎቻቸውን ሲቀጥሉ በተመሳሳይ መልኩ ራሳቸውን እንዲጠብቁ እና ቫይረሱን የመከላከያ እርምጃዎችን ተፈጻሚ እንዲያደርጉ።

7. ኮሚቴው ወሳኝ የነፍስ አድን ሥራዎችን በቂ መገልገያዎች እና መሣሪያዎች ሳይኖሯቸው በማከናወን ላይ የሚገኙትን የሕክምና ባለሙያዎች ያመሰግናል። ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ፣ ኮሚቴው በትምሕርት ላይ ያሉትን ጨምሮ፣ ሁሉም የሕክምና ባለሙያዎች ለብሔራዊ ግዳጅ እንዲዘጋጁ ጥሪውን ያቀርባል።

8. የመጀመሪያው ዙር በአሊባባ አማካኝነት በጃክ ማ የተበረከቱት የምርመራ ቁሶች፣ የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎች እንዲሁም ቫይረሱን የተመለከቱ መመሪያዎች ስብስብ እሁድ መጋቢት 13፣ 2012 ይደርሳሉ። ከዚህ አንጻር፣ ኮሚቴው በመላው ኢትዮጵያ እንዲሁም እንዲደርሳቸው ለታሰበላቸው የአፍሪካ ሀገራት ለማሰራጨት ቅድመ-ዝግጅት እያካሄደ ይገኛል።

9. የጭፈራ ቤቶች እና የመጠጥ ቤቶች ቫይረሱን የመከላከል እና ስርጭቱን የመግታቱ አካል ሆነው፣ በጊዜያዊነት ሥራቸውን ያቆማሉ።

10. ይህንን አሳሳቢ የጤና ሁኔታ በመጠቀም ከገበያ ዋጋ ከፍ ባለ መጠን በመሸጥ ትርፍ ለማጋበስ በሚሞክሩ ግለሰቦች እና የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱ ይቀጥላል።

11. ክልሎች ከፌደራል መንግሥት ድጋፍ እየተደረገላቸው፣ ዝግጁነታቸውን ብቁ ለማድረግ በመሥራት ላይ ይገኛሉ።

#ኢትዮጵያ
#ኮሮና #ኮቪድ19

@kinchebchabi @kinchebchabi
ዓውደ ኢትዮጵያዎች ከደም ልገሳ በኋላ የተነሱት ወቅታዊ ሁኔታን ያገናዘበና ማህበራዊ ፈቀቅታን (ርቀት) የጠበቀ የሕብረት ፎቶ 👏👌

#ኮሮና_ቫይረስ #ኮቪድ19
@awdeethiopia ገጽ የተወሰደ

Join us
@kinchebchabi @kinchebchabi