ቅንጭብጭብ
7.5K subscribers
408 photos
9 videos
1 file
497 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

የአፍ መሸፈኛ ማስክ አትጠቀሙ!!

የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ በርካታ የጤና ተቋማት እንደገለጹት የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ የሚያስፈልገው ለሚከተሉት ብቻ ነው 👇
.
👉 ምልክቱ ለታየባቸው፤
👉 ለኮሮና በሽተኛ አስታማሚዎች፤
👉 ለሕክምና ባለሙያዎች፤
.
🔵 ምልክቱ ላልታየበት ሰው የአፍ መሸፈኛ ለብሶ መሄድ ይልቁንም ጉዳት አለው
.
👉 አፍ ላይ ለቫይረስ ምቹ የትንፋሽ እርጥበት ይፈጥራል፤
👉 ማስኩን ለማስተካከል ፊታችንን እንድንነካካ ይገፋፋል፤
👉 ለሚያስፈልጋቸው ባለሙያዎች እጥረት ይፈጥራል፤
👉 የሐሰት የደኅንነት ስሜት በመፍጠር ከጥንቃቄ ያዘናጋል፤
👉 ለስግብግብ ነጋዴ ብዝበዛ ክፉኛ ይዳርጋል፤
.
አንድን ነገር ጥቅም እና ጉዳቱን ሳናውቅ እንደፋሽን ማድረግ አይጠቅምም።
ሐኪሞች «አትልበሱ» እያሉ መልበስ ከጉዳት በስተቀር ጥቅም የለውም።
.
የተሻለው አማራጭ አንድ ወይ ሁለት ማስክ ገዝቶ ምልክቱ ሲታይብን ወደሐኪም ቤት ስንሄድ እንድንለብሰው በቦርሳችን ማስቀመጥ ነው። ለማስክ መግዣ የምንጨፈጭፈውን ብር ሳኒታይዘር ወይም አልኮልገዝቶ አዘውትሮ መጠቀም ይሻላል።

ንክኪዎችን መቀነስ
እጅን በሳሙና በአግባቡ መታጠብ
#ሲያስነጥሱ አፍዎን ይሸፍኑ
ፊትን ከመነካካት መቆጠብ
የጋራ መገልገያዎችን በአልኮል ማፅዳት

ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር #8335 ይደውሉ

ሼር በማድረግ ላልሰማ አሰሙ!
#ኮሮናቫይረስ #ኮቪድ19

@kinchebchabi @kinchebchabi