ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
7.08K subscribers
1.29K photos
8 videos
37 files
262 links
የዲ.ን ዮርዳኖስ አበበ ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
ንስሓ  ማለት ምን ማለት ነዉ?                                                                                                         ንስሃ የቃሉ ፍች እና ማብራሪያ ማዘን፣መፀፀት፣መቆጨት፣መቀጣት፣ቀኖና መቀበል፣ስለተሰራዉ ኃጢአት ካሳ መክፈል፣የሰሩትን በደል እና ጥፋት ማመን ነዉ።በተጨማሪ ሌላ ጊዜ ከፈጣሪ ጋር የሚያጣላዉን እና ሰማያዊ የዘላለም ህይወት ሊያሳጣዉ የሚችል ኃጢያት ላለመፈፀም የመጨረሻ ዉሳኔ የሚደርስበት የመደምደሚያ ሃሳብ ነዉ።


1/ንስሓ ወደ እግዚአብሄር መመለስ ነዉ                                                                                        የእግዚአብሔር ሰዉ ነቢዩ ሚልክያስ እንደተናግረው "ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከስርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል።ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ"በማለት ከ እግዚአብሔር ሕግ በመተላለፍ እና ተዛዙን በማፍረስ ለበደሉት ሰወች የንስሓ ጥሪ እንዳቀረበላቸው እንመለከታለን።(ሚል 3 ፥ 7 )

ጠቢቡ ሰለሞን "ኃጢአቱን የሚሰዉር አይለማም፤የሚናዘዝባት እና ተሚተዋት ግን `ምህረትን ያገኛል "በማለት ስለ ኃጢአት ግልጸኝነትና ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለሚሆንልን ምህረት ተናግሯል።(ምሳሌ28፥13)                                                                       #ጌታችን_መድሃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በምሳሌ ሲናገር በኅጢአት ወድቆ በንስሓ ስለተመለሰው የሰው ልጅ ኅጥያቱን ተመራምሮ እና በልቡ ተጸጽቶ ወደ ሰማያዊ አምላክ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ዉሳኔ ላይ ቢደርስ የምህረት እና የችርነት አባት እግዚአብሔርም በደስታ እና በፍቅር እንዴት እንደሚቀበለዉ ተመዝግቦ እናገኛለን።(ሉቃ 15፥  )

2/ንስሓ #ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅን ያመለክታል                                      #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳዉሎስ ለቆሮንቶስ ሰወች በጻፈላቸዉ መልእክቱ ስለዚህ ሲናገር "እንግዲህ #እግዚአብሔር ስለኛ እንደሚማለድ ስለ #ክርስቶስ መለዕክተኞች ነን #ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን እንለምናችኋለን"ሲል ተናግሯል።(2ቆሮ 5፥20)

3/ ንስሓ ክርስቲያን ከኃጢአት እንቅልፍ የሚነቃበት ደወል ነዉ                                              ክርስቲያን ኃጢአትን በሰራ ጊዜ በመንፈሳዊ ህይወቱ እና በክርስቲያናዊ ስነምግባሩ ማንቀላፋቱን የምናስተዉልበት ምልክት ነዉ።"የሰው ልጅ ኃጢአተኛ መሆን ሲጀምር በክርስቲያናዊ ህይወቱ የነበሩት እሴቶች ሁሉ ከሱ ጨርሰዉ ስለሚጠፉ ኃጢአት የሚያሰራው የክፉ መንፈስ ባለቤት የሆነዉ ሰይጣን በኃጢአት የማደንዘዝ መርፌ አይምሮውን ስለሚያሳጣው የቆመበትን ስፍራ እና የወደቀበትን ጉድጓድ ፈጽሞ ሊያዉቀዉ አይችልም እና በንስሓ ደወል እንድንቀሰቅሰው ያስፈልጋል።                                                                                          4/ንስሓ በኃጢአት ምክንያት ወድቆ የነበረ ክርስቲያን ወደ መንፈሳዊ ህይወቱ መመለሱን ያመለክታል                                                                                                           የኃጢአት ደዌ ያደረበት ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በንስሓ ህክምና ፈውስ ካላገኘ በመጨረሻ የሚገጥመው እድል የነፍስ ሞት ነው።ሓዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር "አንተ የተኛህ ንቃ ከሙታንም ተነሳ #ክርስቶስም ያበራልሃልና "ሲል ተናግሯል(ኤፌ5፥14)።                                                                                                                            #ወንጌላዊ_ቅዱስ_ዩሃንስም "እኛ...ከሞት ወደ ህይወት እንደተሻገርን እናውቃለን"በማለት ስለ ህይወት መንገድ መስክሯል

ሰይጣን ከሚዋጋቸው የድኅነት መንገዶች ውስጥ ንስሓን የሚያክል የለም ምክንያቱም ንስሐ ጠላት ዲያብሎስ የክርስቲያኖችን ሕይወት ለማጥፋት የገነባውን የኃጢአት ሕንፃ ሁሉ #በእግዚአብሔር ቸርነት እንዳልነበረ በማድረግ ስለሚያፈርስበት ነው። ከዚህ የተነሳ የሰው ልጅ ንስሐ እንዳይገባ ቢገባም ቶሎ እንዳይሆን የተቻለውን ከማድረግ ፈፅሞ አያርፍም። ጠላት ዲያብሎስ ሰዎችን በኃጢአት ለማቆየት ወይም ንስሐ የሚገቡበትን ጊዜ ለማራዘም ከሚጠቀምባቸው የንስሐ መሰናክሎች መካከል ፦                                                              1/ እንቅፋት መፍጠር፦ ድንገተኛ ፈተናዎች ወይም አጋጣሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ ብቻ እንቅፋት በመፍጠር ያሰናክላቸዋል።

2 / ኃጢአተኛው ራሱን ከእርሱ የበለጠ ኃጢአት ሠሩ ከሚላቸው ጋር በማነፃፀር የተሻለ እንደሆነ እንዲገምትና ንስሓም እንደማያስፈልገው ራሱን ማሳመን፥ ማንም ክርስትያን ከሌላው ጋር ኃጢአቱን ሊያነጻጸር አይገባም ።

3/ ከሥጋ ድካም የተነሣ በአካባቢ ተጽእኖ መመራት#ቅዱስ_ጳውሎስ "ይህን ዓለም አትምሰሉ" በሏል ሮሜ 12፥2 ዓሳ ትንሽ ሲሆን ማዕበል በሚያናውጠው ባሕር ውስጥ ይዋኛል ክርስቲያንም እንዲህ ፈተናን ተቋቁሞ ለንስሓ መብቃትና መንፈሳዊ ህይወት መኖር ይገባዋል።

4 /መዘግየት ፦ ዲያብሎስ ንስሓ እንዳንገባ የሚዋጋን በቀጥታ አይደለም ነገር ግን የተለያዩ ስውር ፈተናዎችንና ምክንያቶች እየደቀነ ንስሐ እንዳንገባ ያዘገየናል። መዘግየት ከሚያስከትለው አደጋ መካከል አንዱ ለንስሐ የተዘጋጀውን ልቡና መለወጥና ለንስሓ ያለውን ዕድል ማጥፋት ነው። ኃጢአት ወዲያው ካልተቀጨና ከቀጠለ ሥር ይሰዳል ሱስ ሆኖ ይዋሀደንና ከዚያም ለንስሓ የተዘጋጀውን ጸጸትና ፍላጎት ሊያጠፋው ይችላል።

5/ ተስፋ መቁረጥ ፦ሰይጣን በኃጢአት ከመውደቃችን በፊት የእግዚአብሔርን ቸርነትና ይቅርታ በማሰብ ኃጢአት እንድንሠራ ያደርገናል ከሠራነው በኋላ ደግሞ ሎቱ ስብሓት የእግዚአብሔርን ፍርድ ኩጣን የተሞላ እንደሆነ ያሳስበናል ንስሐ እንዳንገባም ተስፋ ያስቆርጠናል።                                   6/ ተነሳሒው ራሱን በማድነቅ በመመጻደቅ ኃጢአተኛ እንዳልሆነ እንዲያስብ በማድረግ፦ ሰው መልካም ነው ብሎ የሚገምተው የራሱ ሕይወት በኃጢአት የተዳደፈ መሆኑን ካላመነ በቀር ሊለወጥ አይችልም። በሕይወቱ ውስጥ መንፈሳዊ ለውጥ ከሌለ ደግሞ ስለ ንስሐ አያስብም፤ ንስሐም አይገባም ስለዚህ ራሱን አይመረምርም ።

7/ በልቡና ውስጥ #ፈሪሃ_እግዚአብሔር አለመኖሩ#ቅዱስ_ይስሐቅ እንዳለው #ፈሪሃ_እግዚአብሔር ከሌለ ንስሐ መግባት የለም ብሏል አንዳንድ ሰዎች በፍቅር ሰበብ #ፈሪሃ_እግዚአብሐርን ከልቡናቸው ፈጽመው ያስወግዳሉ። በዚህ ጊዜም ስለ ንስሐ ህይወታቸው ግድ የለሽ ይሆናሉ በኃጢአት ይወድቃሉ። ከኃጢአት የተነሳም ፍርሃትን አውጥቶ በመጣል ወደ ንስሓ የሚያቀርበውን #የእግዚአብሔርን_ፍቅር ያጣሉ።
መኰንኑም ደኅንነቷን በሰማ ጊዜ ያዛት ሃይማኖቷንም እንድትተው አስገደዳት አይሆንም ባለችውም ጊዜ አንበሶችና ድብ ከሚያድሩበት እንዲጨምሩዋት አዘዘ። እነርሱም ሰገዱላትና የእግሮቿን ትቢያ ላሱ። ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው መኰንኑና ወገኖቹ አመኑ አንድ አምላክ በሚሆን በ #አብ#ወልድ#መንፈስ_ቅዱስ ስም ተጠመቁ በ #ክርስቶስም መንጋዎች ውስጥ ሆኑ።

እርሷ ቅድስት ጤቅላም ክብር ይግባውና የ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ወንጌልን በማስተማር ቅዱስ ጳውሎስን እያገለገለችው ኑራ በሰላም አረፈች።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስቷ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አንጢላርዮስ

በዚህችም ቀን የቀራጮች አለቃ የነበረ ቅዱስ አንጢላርዮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ አስቀድሞ በማንም ላይ ርኅራኄ የሌለው ነበረ በአንዲትም ዕለት ድኆች በአንድ ቦታ እያሉ በአንጻራቸው አልፎ ሲሔድ በአዩት ጊዜ ስለርሱ እንዲህ አሉ።

ይህ ባለጸጋ በድኆች ላይ ምንም ምን ርኅራኄ የሌለው ነው ከእነርሱም አንዱ እኔ ሔጄ ከእርሱ ምጽዋት ተቀብዬ ብመጣ ምን ትሰጡኛላችሁ አላቸው እነርሱም አንተ ከእርሱ ምጽዋትን ካገኘህ ያልከውን እንሰጥሃለን አሉት በዚህም ነገር ከተከራከሩ በኋላ ወደ አንጢላርዮስ ቤት ሒዶ ምጽዋትን ለመነው አንጢላርዮስም ከመሶቡ እግር የደረቀ ለከት ዳቦ አንሥቶ በመበሳጨት ወርውሮ የድኃውን ራስ ፈቃው ድኃውም ወደ ባልንጀሮቹ ተመልሶ ያንን ለከት አሳያቸው።

በዚያቺም ሌሊት አንጢላርዮስ በሕልሙ ራእይን አየ እርሱ በፍርድ አደባባይ ቁሞ ሳለ የጠቆሩ ሰዎች ስለ ክፋቱ ብዛት ሲከራከሩት ብርሃን የለበሱ ሰዎች ደግሞ ከዚች ለከት ዳቦ በቀር በርሱ ዘንድ ያደረገውን ምጽዋት አላገኘንም ብለው ሲያዝኑ በሚዛንም በመዘኑዋት ጊዜ ከኃጢአቱ ሁሉ ተስተካከለች። በዚያንም ጊዜ ነቃ በልቡም ሳልወድ የሠራሁት ይህን ያህል ጠቃሚ ከሆነ ወድጄ ብሠራውማ እጥፍ ድርብ የሆነ ዋጋ የማገኝ አይደለምን አለ።

ከዚህም በኋላ ተነሥቶ ገንዘቡን ጥሪቱን ሁሉ አውጥቶ ለድኆችና ለችግረኞች መጸወተ። ገንዘቡንም ሁሉ ከጨረሰ በኋላ ከሩቅ ቦታ ድኆች መጥተው ምጽዋትን ለመኑት እርሱም ገንዘቡን ሁሉ እንደ ጨረሰ ነገራችውና እጅግ አዘኑ እንዳዘኑም አይቶ እንዲሸጡት ፈቀደላቸው እነርሱም ሸጡትና የሽያጩን ገንዘብ ተከፋፈሉ።

በተሸጠበትም እንደባሪያ እያገለገለ ኖረ የጌታው ባሮችም በሚያሳዝኑት ጊዜ ብርሃናዊ ሰው ተገልጦ አትዘን የተሸጥክበትን ዋጋ እኔ ተቀብዬዋለሁ እነሆ በእጄ ውስጥ አለና ይለዋል።

ከዚህም በኋላ አስቀድሞ ከነበረበት የመጡ ሰዎች ሥራውን በገለጡበት ጊዜ በሥውር ሸሽቶ ወደ ከተማው በር ደረሰ በሩን የሚጠብቀውም ዲዳና ደንቆሮ ነበር። አንጢላርዮስም በሩን ክፈትልኝ በአለው ጊዜ ከአፉ በእሳት አምሳል ወጥቶ በረኛውን ነካው ያን ጊዜ አንደበቱ ተፈታ ጆሮዎቹም ሰሙ በሩንም ከፍቶለት ወደ በረሀ ሔደ በዚያም ገድሉን ፈጽሞ አረፈ።

ሰዎችም በአጡት ጊዜ ወደ በሩ መጡ በረኛውም የሆነውን ሁሉ ነገራቸው ከቅድስናውና ከተአምራቱም የተነሣ እጅግ አደነቁ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አንጢላርዮስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ዮሐንስ_ዘደብረ_ጽጌ

በዚህችም ቀን ደግሞ የደብረ ጽጌ አባ ዮሐንስ አረፈ። ይህም ቅዱስ አብዝቶ ከመጾሙ ተግቶም ከመጸለዩ የተነሣ ሥጋው ጠውልጎ እንደ ደረቀ ምድር ሆነ። በአንዲትም ቀን በጋን የመላ ውኃ በአፈሰሱበት ጊዜ ከሥጋው ድርቀት ብዛት የተነሣ ከእርሱ ምንም አልነጠበም።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም)
አባ እልመፍርያንም አስተዋይነቱን የአንደበቱን ጣዕም የተደራረበ አገልግሎቱንም ተመልክቶ ጳጳስዋ ለሞተባት ለአንዲት አገር ጵጵስና ሊሾመው ወደደ። ጳጳሳትንና ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትንም በእሑድ ቀን ሰበሰባቸው አባ አትናስዮስንም አቅርበው እንዲህ አሉት ለዕገሌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ልትሆን ዛሬ #መንፈስ_ቅዱስ ጠርቶሃል አሉት። እርሱም ሰምቶ አለቀሰ እንዲተዉትም አልቅሶ አማላቸው እንደማይተውትም በአወቀ ጊዜ እርሱ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት አትናስዮስ እንደሆነ ነገራቸው የአመጣጡንም ምሥጢር ገለጸላቸው።

በዚያን ጊዜ አባ አልመፍርያን ደነገጠ አክሊሉንም ከራሱ ላይ አውልቆ በምድር ላይ ወደቀ ለረጅም ጊዜ እንደ ሞተ ሆነ በተነሣም ጊዜ እንዲህ ብሎ ጮኸ ወንድሞቼ የማደርገውን እስቲ ንገሩኝ ዛሬ እሳት ከሰማይ ወርዶ እንዳያቃጥለኝ ምድርም አፍዋን ከፍታ እንዳትውጠኝ እፈራለሁና ጌታዬ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት አትናስዮስ ውኃ እየቀዳ የፈረሶችና የበቅሎዎች ጉድፍ እየጠረገ በቤቴ ውስጥ እንደ ባርያ ሊአገለግል አግባብ ነውን ወዮልኝ ወዮልኝ።

ጳጳሳቱና የተሰበሰቡት ሁሉ በሰሙ ጊዜ ከእግሩ በታች ወድቀው ሰገዱለት እጆቹንና እግሮቹንም ሳሙ ሊቀ ጳጳሱም ያማሩ የክህነት ልብሶችን ያለብሱት ዘንድ መስቀሎችንና አርዌ ብርቱን ያመጡ ዘንድ በመንበር ላይም ያስቀመጡት ዘንድ አዘዘ።

ከዚያም በኋላ ጳጳሳቱ ከመንበሩ ጋር ተሸከሙት ሦስት ጊዜ አክዮስ አክዮስ አክዮስ እያሉ ይህም ይገባዋል ማለት ነው ቤተ ክርስቲያኑን አዙረው ወደ መቅደስ አስገቡት ።

ከዚህም በኋላ መቀደሻ ልብስ ለብሶ መሥዋዕቱን አክብሮ ቀድሶ አቈረባቸው እነርሱንም ሀገራቸውንም ባረከ ለዚያችም አገር ምንኛ መጠን የሌለው ደስታ ሆነ ተባለ ።

በማግሥቱም አባ እልመፍርያን ተነሥቶ በቅሎ አስመጣ ለጒዞ የሚያሻውን ሁሉ አዘጋጀ አባ አትናስዮስንም በበቅሎ አስቀምጦ እርሱ በእግሩ ተከተለው ጳጳሳቱና ኤጲስቆጶሳቱ ሁሉም ከአባ እልመፍርያን ጋር አጅበዉ ወደ አንጾኪያ አገር ወሰዱት አባት አትናስዮስም አባ እልመፍርያንን አንተም በበቅሎ ላይ ተቀመጥና በአንድነት እንሒድ አለው። አባ እልመፍርያንም ጌታዬ ለእኔ አይገባኝም አንተ በእግርህ ወደ አገሬ እንደመጣህ እንዲሁ እኔም በእግሬ ወደ አገርህ አደርስሃለሁ አለው።

የአንጾኪያ አገር ጳጳሳትም የሊቀ ጳጳሳት አትናስዮስን መምጣት በሰሙ ጊዜ ከሕዝብ ሁሉ ጋር ሊቀበሉት ወጡ በታላቅም ክብር ተቀብለው ወደሹመቱ መንበር አስገቡት። ለአባ እልመፍርያንም ሁለተኛ ወንበር አድርገው በክብር አስቀመጡት በዚያችም ቀን ፈጽሞ ደስ አላቸው ተሰናብተውትም ወደ ሀገራቸው በፍቅር አንድነት ተመለሱ። ይህም አባት አትናስዮስ በጎ አኗኗርን ኖረ መንጋውንም በትክክል በእውነት ጠበቀ በጎ ጒዞውንም ፈጽሞ በሰላም አረፈ ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_እስጢፋኖስ_ካልዕ

በዚችም ቀን በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በአንጾኪያ አገር የሰማዕታት መጀመሪያ ሁኖ ሌላው እስጢፋኖስ በሰማዕትነት አረፈ ።

ይህም የፋሲለደስ ወንድም ለሆነ የኒቆምዮስ ልጅ ነው በወገንም የከበረ ነው አባቱም ከአንጾኪያ ታላላቆች ወገን ሁኖ በወርቅ በብር በወንድ ባሮች በሴት ባሮች እጅግ የበለጸገ ነው ክብር ይግባውና #ክርስቶስንም እጅግ ይፈራዋል ይወደዋልም ለድኆችና ለችግረኞች አብዝቶ ይመጸውታል በሰው ሁሉ ዘንድ ተወዳጅ ነው ።

ይህንንም ቅዱስ እስጢፋኖስን በወለዱት ጊዜ በበጎ ተግሣጽ በምክር አሳደጉት በጀመሪያም የዳዊትን መዝሙር ከዚያም የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትን የ #መንፈስ_ቅዱስ ዕውቀት በላዩ እስቲመላ ድረስ አስተማሩት ።

ሁለተኛም ሥጋዊ ጥበብ ፈረስ መጋለብን ጦር መወርወርን በፍላፃ መንደፍን በቅዱስ ፋሲለደስ ቤት ሁኖ ከቅዱሳን ፊቅጦርና ገላውዴዎስ ጋር ተማረ ለፋሲለደስ የወንድሙ ልጅ ነውና ስለዚህም የፋሲለደስ ልጅ ይባላል ።

ዘመዶቹም ሁሉ #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ናቸው በሕጉ በትእዛዙ በአምልኮቱ ሁሉ የጸኑ ናቸው ። ከውስጣቸውም ክብር ይግባውና ከ #ክርስቶስ የፍቅር ትኲሳት ልቡን የሚያቀዘቅዝ ወደ ቀኝ ቢሆን ወደ ግራም ፈቀቅ የሚል የለም ።

#ጌታችንም ለእርሱ ያላቸውን የፍቅራቸውን ጽናት በአየ ጊዜ ዓለም ሳይፈጠር ያዘጋጀላቸውን መንግሥቱን ሊአወርሳቸው ወደደ ። ከዚህም በኋላ የግብጽ አገር ወደ ሆነ የፍየል ጠባቂ በጦርነት ምክንያት ወደ መለመሉት ስሙ አግሪጳዳ ወደ ሚባል ሰው ሰይጣን መጥቶ አደረበት ወደ አንጾኪያም በደረሰ ጊዜ የመንግሥት ፈረሶች ባልደራስ አደረጉት ።

የአንጾኪያም ንጉሥ በሞተ ጊዜ መንበሩ ከንጉሥ ተራቆተ በአንዲት ዕለትም የንጉሡ ሴት ልጅ በቤቷ ደርብ ስትመላለስ ሲዘፍን አየችው እርሱም ለፈረሶች ክራርና መሰንቆ ሲመታላቸው እንደሚዘፍን ሰው ሁነው ያሽካኩ ነበር ። ስለዚህ ወደደችውና ባል አድርጋ አነገሠችው ስሙንም ዲዮቅልጥያኖስ ብላ ሰየመችው ።

ያን ጊዜ በዘመኑ ለተደረገ ዓመፅና ግፍ ወዮ ምን ዓይነት ዓመፅና ግፍ ነው ። ክብር ይግባውና #ክርስቶስን ከካደው በኋላ ጣዖታትን አመለከ በ #ክርስቶስም ያመነውን ሁሉ ገደለ እንደ ነጣቂዎች አራዊትም የሰውን ሥጋ የሚበላ ደማቸውንም የሚጠጣ ሆነ ። የተመረጡ የመንግሥት ልጆችን ሁሉ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች በተናቸው ከእነርሱ ውስጥ በችንካሮች ቸንክሮ የገደላቸው አሉ በማረጃ አርዶ የገደላቸው በጦር ወግቶ በእሳትም አቃጥሎ የገደላቸው አሉ አሥሮ አፋቸውንም በልጓም ለጉሞ ወደ ግብጽ አገሮች እስከ ሰደዳቸው ድረስ ልቅሶና ዋይታም በአንጾኪያ አገር እስከመላ ድረስም ባል ስለ ሚስቱ ሚስትም ስለ ባልዋ እናትና አባት ስለ ልጆቻቸው ልጆችም ስለ ወላጆቻቸው ሰዎችም ሁሉ ስለ ወገኖቻቸው የቅዱሳን ሰማዕታትም ሥጋቸው በሀገሩ ጥጋጥግ የወደቀ ሆነ ። ለጠባቂዎች ገንዘብ ሰጥተው በሥውር ወስደው ከሚቀብሩአቸው በቀር ቀባሪ የላቸውም ።

ይህም ቅዱስ እስጢፋኖስ የምስክርነት አክሊልን ይሰጠው ዘንድ ወደ #እግዚአብሔር ሲጸልይ ኖረ ።

የመጀመሪያዪቱ ቀን ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በግዛቱ ውስጥ ላሉ አገሮች ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት እንዲዘጉ የጣዖት ቤቶች እንዲከፈቱና እንዲአመልኳቸው እነርሱ በጦርነት ውስጥ ድል አድራጊነትን ይሰጡናልና ይህንንም ትእዛዝ የሚቃወምና እምቢ የሚል ቢኖር ንብረቱ ይወረስ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ ይሠቃይ ርኅራኄ በሌለው አሟሟት እስኪሞት ብሎ የሚያዝ የአዋጅ ደብዳቤ ጻፈ ።

የመንግሥቱን ታላላቆች ሁሉ ሕዝቡንም ታላቁንም ታናሹንም ሰበሰባቸው ። ይቺ የረከሰች ደብዳቤም በተሰበሰቡት ፊት ትነበብ ዘንድ አዘዘ ቅዱስ እስጢፋኖስም በሰማ ጊዜ ስለ ቀናች ሃይማኖት በ #ክርስቶስ ፍቅር እሳትነት ልቡ ነደደ ።

ዲዮቅልጥያኖስንም ተመለከተው እንደ ኢምንትም አደረገው። እንዲህም አለው ንጉሥ ሆይ አጵሎንን ያመልኩ ዘንድ የምታዝ ይቺን የረከሰች ደብዳቤ በመጻፍህ የምታሳየው ይህ ዓመፅ ምንድን ነው ይህንንም ሁሉ ያጠፋው ዘንድ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አለ ይህንንም ብሎ ይችን የረከሰች ጽሑፍ በያዘ ወታደር ላይ ተወርውሮ ነጠቀውና ቀደዳት በጣጥሶም ጣላት ።
ንጉሣችንና አባታችን ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስም የእረፍት ዘመኑ ሲደርስ #እግዚአብሔር_አምላክ ቃል ኪዳኑን ለዘላለም እንደሚያፀናለት ነግሮት በዚህች በተባረከች #በጥቅምት_19 ቀን በክብር አሳረፈው።

መቃብሩንም አስቀድሞ እነደነገረው በዛው በተቀደሰ ዋሻ ውስጥ አደረገለት። እናም ዛሬ ድረስ ቦታው በክብር ተጠብቆ ይኖራል። ምእመናንም ቃል ኪዳኑን በማሰብ "ማረኝ ይምርሐ" እያሉ መቃብሩን ይዞራሉ። ያንን ከሰማይ የወረደለትን #መስቀልም በቤተመቅደሱ የሚያገለግሉት ካህናት አባቶች ቦታውን ለመሳለም የሚመጣውን ሕዝበ ክርስቲያን በበዓል ቀን ይባርኩበታል፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባት ይምርሐነ ክርስቶስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_በርቶሎሜዎስና_ሚስቱ

ዳግመኛም በዚህች ቀን በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ቅዱስ በርቶሎሜዎስና ሚስቱ በሰማዕትነት አረፉ።

እሊህ ቅዱሳንም የግብጽ ምዕራብ ከሆነ ፍዩም ከሚባል አገር ናቸው ክርስቲያኖችም እንደሆኑ በመኰንኑ ዘንድ ወነጀሏቸው መኰንኑም ልኮ አስቀረባቸውና ስለ ሃይማኖት ጠየቃቸው እነርሱም ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በፊቱ ታመኑ።

መኰንኑም ጥልቅ ጒድጓድ እንዲቆፍሩላቸው በዚያም እንዲጨምሩአቸውና በሕይወታቸው እንዲደፍኑባቸው አዘዘ። መኰንኑም እንዳዘዘ አደረጉባቸው በዚህም ምስክርነታቸውን ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕታቱ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#የጳውሎስ_ሳምሳጢን_ውግዘት

በዚችም ቀን ስለ ጳውሎስ ሳምሳጢ በአንጾኪያ አገር የቤተ ክርስቲያን የአንድነት ስብሰባ ተደረገ። ይህ ጳውሎስም ከአንጾኪያ አገሮች በአንዲቱ አገር ኤጲስቆጶስነት በተሾመ ጊዜ ክፉ ዘርን ሰይጣን በልቡ ውስጥ ዘራበት አካላዊ ቃልን አካል እንደሌለ የ #ክርስቶስም ጥንት መገኛው ከ #ማርያም እንደሆነ እርሱም አለምን ያድንበት ዘንድ #እግዚአብሔር የፈጠረው እንደሆነ ከመለኮትም ጋር ያልተዋሐደ በላዩ ወርዶ በ #እግዚአብሔር ፈቃድ አደረበት እንጂ ብሎ የሚያምን ሆነ በ #ወልድም ቢሆን በ #መንፈስ_ቅዱስም ቢሆን የሚያምን አልሆነም።

ስለዚህም ኤጲስቆጶሳት አንድነት ተሰበሰቡ የእስክንድርያ አባ ዲዮናስ የሮሜ አባ ዲዮናስዮስ እሊህ ሊቃነ ጳጳሳት ስለ እርጅናቸው ከዚያ ደርሰው ከእርሳቸው ጋር ሊሰበሰቡ አልቻሉም ነገር ግን መልእክትን ጻፉ።

የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስም እንዲህ የሚል መልእክትን ጻፈ። የ #እግዚአብሔር ልጁም ቃሉም የሆነ #ክርስቶስ በመለኮቱም ከእርሱ ጋር ትክክል የሆነ እርሱም ከሦስቱ አካላት አንዱ #ወልድ ስለእኛ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል #ማርያም ያለ ዘር ስጋንና ነፍስን ነሥቶ ፍጹም ሰው የሆነ በመለኮቱ ከ #አብ#መንፈስ_ቅዱስ ጋር ትክክል ሲሆን እንደእኛ ፊጹም ሰው ሁኗል ከተዋሕዶውም በኋላ ያለ መለያየትና ያለ መቀላቀል ሁለቱ ባሕርያት አንድ ሁነዋል ከብሉይና ከሐዲስ መጻሕፍት ምስክሮችን ጠቅሶ እያስረዳ ጽፎ ይቺንም መልእክት ከሁለት ምሁራን ቀሳውስት ጋር ላካት።

በዚያንም ጊዜ አሥራ ሦስቱ ኤጲስቆጶሳትና እሊህ ሁለቱ ቀሳውስት ጉባኤ አድርገው ይህን ጳውሊ ሳምሳጢን አቅርበው የአባ ዲዮናስን መልእክት በፊቱ አነበቡ። ዳግመኛም #ክርስቶስ#እግዚአብሔር ልጁም ቃሉም የሆነ የጌትነቱ ነጸብራቅ ነው የሚለውን የሐዋርያ ጳውሎስን ቃል በመጥቀስ እርሱ ከ #አብ#መንፈስ_ቅዱስ ጋር በትክክልነት እንደሚኖር አስረዱት እርሱ ግን ቃላቸውን አልተቀበለም።

ከዚህም በኋላ በእርሱ ትምህርት የሚያምኑትን ሁሉ አው*ግዘው ከምእመናን ለይተው አሳደዱት። ለምእመናንም ሥርዓትን ሠሩ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ከስሕተት ይጠብቀን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘጸይለም

በዚችም ቀን የጸይለም አገር የከበረ አባት ዮሐንስ አረፈ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ከሀገሩ ታላላቆች ወገን ናቸው የአባቱም ስም አብርሃም የእናቱም ስም ሣራ ነው እነርሱም ልጆች ስለ ሌሏቸው ብዙ ዘመን ወደ #እግዚአብሔር እየለመኑ ኖሩ።

በአንዲትም ዕለት ሁለት መነኰሳት ወደ እነርሱ እንግድነት መጡ እነርሱም በክብር ተቀብለው አሳደሩአቸው። እሊህ መነኰሳትም አብርሃምን ልጅ የለህምን አሉት እርሱም እንባውን እየአፈሰሰ አባቶቼ ልጅ የለኝም አሁንማ እኔ አረጀሁ የሚስቴም የልጅነቷ ወራት አለፈ ብሎ መለሰላቸው። እሊህ መነኰሳትም ስለ እርሳቸው ጸለዩላቸው ባርከዋቸውም ጎዳናቸውን ተጓዙ።

ከጥቂትም ቀን በኋላ ቅድስትሳራ ፀነሰች ደስ የሚያሰኝም ልጅን ወለደች ስሙንም ዮሐንስ ብለው ሰየሙት በእርሱም ደስ አላቸው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት እየአስተማሩ አሳደጉት።

ዐሥራ ሰባት ዓመትም በሆነው ጊዜ ወደ መምህሩ ቤት መነኰሳት መጡ ዮሐንስም ከእርሳቸው ጋር እንዲወስዱት ለመናቸው እነርሱም አባትህን እንፈራለንና እኛ አንወስድህም አሉት። መነኰሳቱም ወደቦታቸው እየሔዱ ሳሉ ወደ መረጠው ጎዳና ይመራው ዘንድ ዮሐንስ ተነሥቶ ወደ #እግዚአብሔር ጸለየ ከመምህሩም ቤት ወጥቶ ሊደርስባቸው ወዶ መነኰሳቱን በኋላቸው ተከተላቸው ወደ ታላቅ ወንዝም ደረሰ ብቻውንም መሻገር ፈርቶ ቆመ ከዚያም ሳለ ዓረቦች ከግመሎቻቸው ጋር መጡ ያሻገሩትም ዘንድ ለመናቸው እነርሱም ከእርሳቸው ጋር አሻገሩት አንወስድህም ወደአሉት መነኰሳት ወደ ገዳማቸው በ #እግዚአብሔር ፈቃድ ደረሰ።

ከእርሳቸውም አንዱ አባ ስምዖን የሚባለው ዮሐንስን ወስዶ ደቀ መዝሙሩ አድርጎ ከሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር አኖረው።

አባ ስምዖን የሚሞትበት ጊዜ እንደቀረበ በአወቀ ጊዜ ልጆቹን ጠርቶ ከሞትኩ በኋላ በእናንተ ላይ የሚሆነውን #እግዚአብሔር ያሳየኝን እነግራችሁ ዘንድ ልጆቼ ኑ አላቸውና ከእናንተ አንዱን ጅብ ነጥቆ ይወስደዋል። ሁለተኛው ወደ ዓለም ተመልሶ ይባክናል። የሦስተኛው ግን ዜናው በዓለሙ ሁሉ ይሰማል አላቸው።

ከዚህም በኋላ አረጋዊው ስምዖን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ተመልክቶ ልጄ ሆይ በክርስቶስ ፍቅር ጽና ለብዙዎች አባት ልትሆን እርሱ መርጦሃልና አለው። አባ ስምዖንም ከአረፈ በኋላ በሦስተኛው ቀን አንዱ ረድዕ ወደ ዓለም ተመልሶ ሚስት አገባ ሁለተኛው ወዴት እንደ ደረሰ አልታወቀም። አባ ዮሐንስም ብቻውን ቀረ ፈጽሞ አዘነ በልቡ እንዲህ አለ የጓደኞቼን ወሬ እጠይቅ ዘንድ ከገዳም ወጥቼ ልውረድ ይህንንም ብሎ ከገዳሙ ወጥቶ ሲወርድ የጸይለም ጦረኞች ተቀበሉት ደም ግባታቸው ከሚአምር ከሁለት ሴቶች ጋር አሥረው ወሰዱት በጒዞም ላይ እያሉ ለእንስሶቻቸውና ለራሳቸው የሚጠጡት ውኃ አጡ። አባ ዮሐንስም ከዚህ በረሀ ውስጥ ፈጣሪዬ ውኃን ቢአወጣላችሁ ትለቁኛላችሁን አላቸው አዎን አሉት። በዚያንም ጊዜ አባ ዮሐንስ በስመ #አብ #ወወልድ#መንፈስ_ቅዱስ ብሎ በምድር ላይ አማተበ ውኃም ፈልቆላቸው ጠጥተው ረኩ።
#ጥቅምት_21

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ አንድ በዚህችም ቀን #እመቤታችን_ተአምራትን_አድርጋ_ሐዋርያው_ማትያስን ከእሥራት ቤት ያወጣችበት፣ #የነቢይ_ኢዩኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ፣ የማርታና የማርያም ወንድም #የቅዱስ_አልዓዛር ሥጋው ከቆጵሮስ አገር የፈለሰበት፣ የቅዱስ አባት #አባ_ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም እረፍት ነው፣ ታላቁ ጻድቅ #አቡነ_አላኒቆስ ዕረፍታቸው ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#እመቤታችን_ለሐዋርያው_ቅዱስ_ማትያስ_ያደረገችለት_ተአምር

በዚህችም ቀን እመቤታችን #ማርያም ተአምራትን አድርጋ ደቀ መዝሙር ማትያስን ከእሥራት ቤት አዳነችው።

የከበሩ ቅዱሳን ወንጌልን በዓለም ዞረው ይሰብኩ ዘንድ ዕጣ ሲጣጣሉ ለቅዱስ ማትያስ ዕጣ የደረሰው ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ነበር፡፡ ይህችም ሀገር እስኩቴስ የተባለች ሩሲያ እንደሆነች የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

ቅዱስ ማትያስም እነዚህ ሰውን የሚበሉ ሰዎች አገራቸው እንደደረሰ ዐይኑን አውልቀው አሠሩት፡፡ ምግባቸውም የመጻተኛ ሰው ሥጋ ነው፡፡ በልማዳቸው መሠረት መጻተኛን ሰው ገና እንደያዙት ዐይኖቹን ዐውልቀው በእሥር ቤት ያኖሩታል፡፡ እስከ 30 ቀንም ድረስ ሳር እያበሉ ያስቀምጡትና በ30ኛው ቀን አውጥተው አርደው ይበሉታል፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ማትያስንም በልማዳቸው መሠረት ዐይኖቹን አውልቀው አሠሩት፡፡ ሐዋርያውም በእሥር ቤት ሆኖ በዚያ ላይ ዐይኖቹን ታውሮ ሳለ በጭንቅ ወደ #ጌታችንና ወደ #እመቤታችን ይለምን ነበር፡፡ ነገር ግን እመብርሃንና ልጇ #መድኃኔዓለም 30ኛው ቀን ሳይፈጸም ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስን ወደ እርሱ ላኩለት፡፡ ቅዱስ ማትያስም ዐይኑን ፈወሱለትና ማየት ቻለ፡፡

እንድርያስም በተዘጋው በር በተአምራት ገብቶ አሥርቤቱ ውስጥ ያሉ እሥረኞችን በስውር አውጥቶ ከከተማው ውጭ ካስቀመጣቸው በኋላ ሁለቱ ሐዋርያት ተመልሰው ሰውን ለሚበሉት ሰዎች ተገለጡላቸው፡፡ እነርሱም ይዘው በአንገታቸው ገመድ አግብተው ለ3 ቀን በሀገራቸው ጎዳናዎች ላይ ሁሉ ጎተቱዋቸው፡፡ ሁለቱም ሐዋርያት በጸሎታቸው ከእሥር ቤቱ ምሰሶ ሥር ውኃ አፈለቁና ውኃው ሀገራቸውን ሁሉ እስኪያጥለቀልቅና ሰዎቹንም እስከ አንገታቸው ድረስ እስከሚደርስ ሞላ፡፡ ሁሉም በተጨነቁ ጊዜ ሁለቱ ሐዋርያት በፊታቸው ተገለጡና ‹‹በጌታችን እመኑ ትድናላችሁ›› በማለት ወንጌልን ሰብከውላቸው አሳመኗቸው፡፡ ምሥጢራትንም ሁሉ ገለጡላቸው፡፡ ደግሞም የአራዊት ጠባይን ከሰዎቹ ያርቅላቸው ዘንድ ወደ #ጌታችንና ወደ ተወደደች እናቱ ከጸለዩ በኋላ በ #አብ#ወልድ#መንፈስ_ቅዱስ ስም አጠመቋቸው፡፡ ያ የአውሬነት ጠባያቸውም ጠፍቶላቸው የዋህ፣ ቅንና ሩኅሩኆቸ ሆኑ፡፡ ሐዋርያትም ሃይማኖትን እያስተማሯቸው 30 ቀን አብረዋቸው ከተቀመጡ በኋላ አገልጋይ ኤጲስ ቆጶሳትን፣ ካህናትንና ዲያቆናትን ሾመውላቸው ወደ ሌላ ሀገር ሄዱ፡፡

ለሐዋርያት ሞገሳቸው ጣዕመ ስብከታቸው የኾነች ክብርት #እመቤታችን ለእኛም ትለመነን!

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ኢዩኤል_ነቢይ

ዳግመኛም በዚህችም ቀን የነቢይ ኢዩኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። ይህም የእስራኤልን ልጆች የሚያስተምርና የሚገሥጻቸው ነበር ስለ #ክርስቶስም በኢየሩሳሌም መኖርና ማስተማር ትንቢት ተናገረ። ደግሞም ስለ መከራው በሐዋርያትና በሰባ ሁለቱ አርድእት በሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት ላይ የ #መንፈስ_ቅዱስን መውረድ እንዲህ ሲል ተናገረ።

ከዚህ በኋላ በሥጋዊ በደማዊ ሰው ሁሉ ከመንፈሴ አሳድርበታለሁ ሴቶች ልጆቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ ትንቢትን ይናገራሉ አለቆቻችሁ ሕልምን ያልማሉ ጎልማሶቻችሁም ራእይን ያያሉ። ሁለተኛም እንዲህ አለ ያን ጊዜ ከተራራው ማር ከኮረብታውም ወተት ይፈሳል በቤተ #እግዚአብሔር አጠገብ ካሉ ከይሁዳ አገሮች ሁሉ ምንጩ ከላይ ወደታች ይፈሳል።

ሙታን በሚነሡ ጊዜ ስለሚሆነው የፍርድ ሰዓት እንዲህ አለ ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ የከዋክብትም ብርሃናቸው ይጠፋል። የትንቢቱንም ወራት አድርሶ #እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነብዩ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አልዓዛር የማርታና የማርያም ወንድም

በዚችም ቀን ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው የቅዱስ አልዓዛር ሥጋው ከቆጵሮስ አገር የፈለሰበት ሆነ።

ከክርስቲያን ነገሥታትም አንዱ ሥጋው በቆጵሮስ እንዳለ በሰማ ጊዜ ከቆጵሮስ ደሴት ወደ ቊስጥንጥንያ አፈለሰው። ሊአፈልሱትም በወደዱ ጊዜ በከበረ የደንጊያ ሣጥን ውስጥ ሁኖ በምድር ውስጥ ተቀብሮ አገኙት በላዩም እንዲህ የሚል ጽሑፍ ነበረ ይህ በመቃብር ውስጥ አራት ቀን ከኖረ በኋላ ከሙታን ለይቶ ላስነሣው ክብር ይግባውና የ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ወዳጁ የሆነ የቅዱስ አልዓዛር ሥጋ ነው።

ይህንንም በአዩ ጊዜ ደስ ተሰኙበት ተሸክመውም ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ወሰዱት ካህናቱም ሁሉ ወጥተው በታላቅ ክብር በመዘመርና በማመስገን ተቀበሉት በአማረ ቦታም አኖሩት በዚችም ቀን በዓልን አደረጉለት።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አልዓዛር ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘኢየሩሳሌም

በዚህችም ቀን ለከበረች አገር ኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳሳት የሆነ ቅዱስ አባት አባ ዮሐንስ #እግዚአብሔርን በሚወድ የንጉሥ ሰይፈ አርዕድ ደግሞ ቈስጠንጢኖስ ለሚባል ልጁ በሆነ በንጉሣችን በዳዊት ዘመን አረፈ።

ይህም ቅዱስ ከምስር አገር ታላላቆች #እግዚአብሔርን የሚፈሩ የክርስቲያኖች አባቶች ልጅ ነው። የዲቁና መዓረግንም ለመሾም እስከ ተገባው ድረስ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማሩ በበጎ አስተዳደግ አሳደጉት። ከዚህም በኋላ በዲቁናው ሹመት አገልግሎቱን በአሳመረ ጊዜ የቅስና መዓረግ የሚገባው ሁኖ ቅስና ተሾመ።

በጾም በጸሎት #እግዚአብሔርንም በመፍራት የተጠመደ ሁኖ ድኆችንና ችግረኞችን የሚወዳቸው የሚረዳቸው ሆነ ያን ጊዜ የሐዋርያት የሆነች የጵጵስና ሹመት የምትገባው ሁና በከበረች አገር በኢየሩሳሌም በ #እግዚአብሔር ፈቃድ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ ሕዝቡንም በፈሪሀ #እግዚአብሔርና በትሕትና የሚያስተምራቸው ሆነ።

እነርሱም ስለ ቅድስናው እጅግ የሚወዱት ሆኑ መልኩና የአንደበቱ አገላለጥ እንደ #እግዚአብሔር መልአክ ያማረ ነበር። በሹመቱም ጥቂት ዘመናት ከኖረ በኋላ ከመንበረ ሢመቱ እስከ አራቀው ድረስ በላዩ ሰይጣን ምክንያትን አመጣ።

ይህም እንዲህ ነው በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በአባ ማርቆስ ዘመን በግዛቱ ውስጥ ያሉ እስላሞች ስለ ዐመፁበት የኢትዮጵያ ንጉሥ ፈጅቷቸው ነበርና ስለዚህ በግዛቱ ውስጥ በሚኖሩ እስላሞች ላይ ክፉ እንዳያደርግ ለኢትዮጵያ ንጉሥ መልእክት እንዲልክ ሊቀ ጳጳሳት አባ ማርቆስን የምስር ንጉሥ አዘዘው።

አባ ማርቆስም ወደ ኢትዮጵያ ንጉሥ ስለሚላኩ ሰዎች ከመኳንንቱ ከኤጲስ ቆጶሳቱና ከሀገር ታላላቆች ሽማግሌዎች ጋር ተማክሮ እሊህን ብሩሀን ከዋክብት የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስን የምስር ኤጲስቆጶስ አባ ሳዊሮስን በእውቀታቸው በአስተዋይነታቸውና በቅድስናቸው መረጡአቸው ወደ ኢትዮጵያ ንጉሥም ይሔዱ ዘንድ ግድ አሏቸው።