ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
7.08K subscribers
1.29K photos
8 videos
37 files
262 links
የዲ.ን ዮርዳኖስ አበበ ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
ንስሓ  ማለት ምን ማለት ነዉ?                                                                                                         ንስሃ የቃሉ ፍች እና ማብራሪያ ማዘን፣መፀፀት፣መቆጨት፣መቀጣት፣ቀኖና መቀበል፣ስለተሰራዉ ኃጢአት ካሳ መክፈል፣የሰሩትን በደል እና ጥፋት ማመን ነዉ።በተጨማሪ ሌላ ጊዜ ከፈጣሪ ጋር የሚያጣላዉን እና ሰማያዊ የዘላለም ህይወት ሊያሳጣዉ የሚችል ኃጢያት ላለመፈፀም የመጨረሻ ዉሳኔ የሚደርስበት የመደምደሚያ ሃሳብ ነዉ።


1/ንስሓ ወደ እግዚአብሄር መመለስ ነዉ                                                                                        የእግዚአብሔር ሰዉ ነቢዩ ሚልክያስ እንደተናግረው "ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከስርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል።ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ"በማለት ከ እግዚአብሔር ሕግ በመተላለፍ እና ተዛዙን በማፍረስ ለበደሉት ሰወች የንስሓ ጥሪ እንዳቀረበላቸው እንመለከታለን።(ሚል 3 ፥ 7 )

ጠቢቡ ሰለሞን "ኃጢአቱን የሚሰዉር አይለማም፤የሚናዘዝባት እና ተሚተዋት ግን `ምህረትን ያገኛል "በማለት ስለ ኃጢአት ግልጸኝነትና ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለሚሆንልን ምህረት ተናግሯል።(ምሳሌ28፥13)                                                                       #ጌታችን_መድሃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በምሳሌ ሲናገር በኅጢአት ወድቆ በንስሓ ስለተመለሰው የሰው ልጅ ኅጥያቱን ተመራምሮ እና በልቡ ተጸጽቶ ወደ ሰማያዊ አምላክ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ዉሳኔ ላይ ቢደርስ የምህረት እና የችርነት አባት እግዚአብሔርም በደስታ እና በፍቅር እንዴት እንደሚቀበለዉ ተመዝግቦ እናገኛለን።(ሉቃ 15፥  )

2/ንስሓ #ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅን ያመለክታል                                      #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳዉሎስ ለቆሮንቶስ ሰወች በጻፈላቸዉ መልእክቱ ስለዚህ ሲናገር "እንግዲህ #እግዚአብሔር ስለኛ እንደሚማለድ ስለ #ክርስቶስ መለዕክተኞች ነን #ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን እንለምናችኋለን"ሲል ተናግሯል።(2ቆሮ 5፥20)

3/ ንስሓ ክርስቲያን ከኃጢአት እንቅልፍ የሚነቃበት ደወል ነዉ                                              ክርስቲያን ኃጢአትን በሰራ ጊዜ በመንፈሳዊ ህይወቱ እና በክርስቲያናዊ ስነምግባሩ ማንቀላፋቱን የምናስተዉልበት ምልክት ነዉ።"የሰው ልጅ ኃጢአተኛ መሆን ሲጀምር በክርስቲያናዊ ህይወቱ የነበሩት እሴቶች ሁሉ ከሱ ጨርሰዉ ስለሚጠፉ ኃጢአት የሚያሰራው የክፉ መንፈስ ባለቤት የሆነዉ ሰይጣን በኃጢአት የማደንዘዝ መርፌ አይምሮውን ስለሚያሳጣው የቆመበትን ስፍራ እና የወደቀበትን ጉድጓድ ፈጽሞ ሊያዉቀዉ አይችልም እና በንስሓ ደወል እንድንቀሰቅሰው ያስፈልጋል።                                                                                          4/ንስሓ በኃጢአት ምክንያት ወድቆ የነበረ ክርስቲያን ወደ መንፈሳዊ ህይወቱ መመለሱን ያመለክታል                                                                                                           የኃጢአት ደዌ ያደረበት ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በንስሓ ህክምና ፈውስ ካላገኘ በመጨረሻ የሚገጥመው እድል የነፍስ ሞት ነው።ሓዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር "አንተ የተኛህ ንቃ ከሙታንም ተነሳ #ክርስቶስም ያበራልሃልና "ሲል ተናግሯል(ኤፌ5፥14)።                                                                                                                            #ወንጌላዊ_ቅዱስ_ዩሃንስም "እኛ...ከሞት ወደ ህይወት እንደተሻገርን እናውቃለን"በማለት ስለ ህይወት መንገድ መስክሯል

ሰይጣን ከሚዋጋቸው የድኅነት መንገዶች ውስጥ ንስሓን የሚያክል የለም ምክንያቱም ንስሐ ጠላት ዲያብሎስ የክርስቲያኖችን ሕይወት ለማጥፋት የገነባውን የኃጢአት ሕንፃ ሁሉ #በእግዚአብሔር ቸርነት እንዳልነበረ በማድረግ ስለሚያፈርስበት ነው። ከዚህ የተነሳ የሰው ልጅ ንስሐ እንዳይገባ ቢገባም ቶሎ እንዳይሆን የተቻለውን ከማድረግ ፈፅሞ አያርፍም። ጠላት ዲያብሎስ ሰዎችን በኃጢአት ለማቆየት ወይም ንስሐ የሚገቡበትን ጊዜ ለማራዘም ከሚጠቀምባቸው የንስሐ መሰናክሎች መካከል ፦                                                              1/ እንቅፋት መፍጠር፦ ድንገተኛ ፈተናዎች ወይም አጋጣሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ ብቻ እንቅፋት በመፍጠር ያሰናክላቸዋል።

2 / ኃጢአተኛው ራሱን ከእርሱ የበለጠ ኃጢአት ሠሩ ከሚላቸው ጋር በማነፃፀር የተሻለ እንደሆነ እንዲገምትና ንስሓም እንደማያስፈልገው ራሱን ማሳመን፥ ማንም ክርስትያን ከሌላው ጋር ኃጢአቱን ሊያነጻጸር አይገባም ።

3/ ከሥጋ ድካም የተነሣ በአካባቢ ተጽእኖ መመራት#ቅዱስ_ጳውሎስ "ይህን ዓለም አትምሰሉ" በሏል ሮሜ 12፥2 ዓሳ ትንሽ ሲሆን ማዕበል በሚያናውጠው ባሕር ውስጥ ይዋኛል ክርስቲያንም እንዲህ ፈተናን ተቋቁሞ ለንስሓ መብቃትና መንፈሳዊ ህይወት መኖር ይገባዋል።

4 /መዘግየት ፦ ዲያብሎስ ንስሓ እንዳንገባ የሚዋጋን በቀጥታ አይደለም ነገር ግን የተለያዩ ስውር ፈተናዎችንና ምክንያቶች እየደቀነ ንስሐ እንዳንገባ ያዘገየናል። መዘግየት ከሚያስከትለው አደጋ መካከል አንዱ ለንስሐ የተዘጋጀውን ልቡና መለወጥና ለንስሓ ያለውን ዕድል ማጥፋት ነው። ኃጢአት ወዲያው ካልተቀጨና ከቀጠለ ሥር ይሰዳል ሱስ ሆኖ ይዋሀደንና ከዚያም ለንስሓ የተዘጋጀውን ጸጸትና ፍላጎት ሊያጠፋው ይችላል።

5/ ተስፋ መቁረጥ ፦ሰይጣን በኃጢአት ከመውደቃችን በፊት የእግዚአብሔርን ቸርነትና ይቅርታ በማሰብ ኃጢአት እንድንሠራ ያደርገናል ከሠራነው በኋላ ደግሞ ሎቱ ስብሓት የእግዚአብሔርን ፍርድ ኩጣን የተሞላ እንደሆነ ያሳስበናል ንስሐ እንዳንገባም ተስፋ ያስቆርጠናል።                                   6/ ተነሳሒው ራሱን በማድነቅ በመመጻደቅ ኃጢአተኛ እንዳልሆነ እንዲያስብ በማድረግ፦ ሰው መልካም ነው ብሎ የሚገምተው የራሱ ሕይወት በኃጢአት የተዳደፈ መሆኑን ካላመነ በቀር ሊለወጥ አይችልም። በሕይወቱ ውስጥ መንፈሳዊ ለውጥ ከሌለ ደግሞ ስለ ንስሐ አያስብም፤ ንስሐም አይገባም ስለዚህ ራሱን አይመረምርም ።

7/ በልቡና ውስጥ #ፈሪሃ_እግዚአብሔር አለመኖሩ#ቅዱስ_ይስሐቅ እንዳለው #ፈሪሃ_እግዚአብሔር ከሌለ ንስሐ መግባት የለም ብሏል አንዳንድ ሰዎች በፍቅር ሰበብ #ፈሪሃ_እግዚአብሐርን ከልቡናቸው ፈጽመው ያስወግዳሉ። በዚህ ጊዜም ስለ ንስሐ ህይወታቸው ግድ የለሽ ይሆናሉ በኃጢአት ይወድቃሉ። ከኃጢአት የተነሳም ፍርሃትን አውጥቶ በመጣል ወደ ንስሓ የሚያቀርበውን #የእግዚአብሔርን_ፍቅር ያጣሉ።