TIKVAH-ETHIOPIA
1.4M subscribers
54.8K photos
1.37K videos
198 files
3.65K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#udate አርበኞች ግንቦት 7⬇️

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ የሁሉም ሀሳብ አራማጆች #ለዘለቄታዊ ለውጥ ቁጭ ብሎ መወያየት እንደሚገባ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለፁ።

ሊቀመንበሩ በቦሌ አየር ማረፊያ በሰጡት መግለጫ #የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለመጠበቅ ከመጣር ይልቅ #ትክክለኛ ምርጫ ማካሄድ የሚችል ስርዓትና #ተቋማት መኖራቸውን ማረጋገጥ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ገልፀዋል።

የለውጡ ኃይል የሀገሪቱን ረጅም የመከራ ቀን በመሳጠርም ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጉንም አስታውቀዋል።

ከሁሉ በላይ ሁላችንም ለሀገር ለውጥ #እንወያይ የሚል ሀሳብ አንግቦ ለተግባራዊነቱም መስራቱ መጪው ጊዜ #ብሩህ ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳሰነቃቸውም ገልፀዋል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ከሁሉም ኃይሎች ጋር ተመካክሮ የተገኘውን ይህን እድል መጠቀም እንደሚሻም ነው ያሰትወቁት ።

በፖለቲካ ምክንያት ሰውን እንደጥላት የማየት አስተሳሰብ ከህብረተሰቡ ሊወጣ ይገባል #መረጋጋት ያስፈልጋል ብለዋል ፕሮፌሰሩ።

የሀገሪቱን ዘለቂ ሰላም ለማምጣትና ዲሞክራሲያዊ ባህልን ለማጎልበት ህብረተሰቡ ለመወያየትና ለመደማመጥ የሚቻልበት ሁኔታ መፍጠር አለበት ስለዚህም ለሁሉም ነገር ነገሮችን #ተረጋግቶ ማሰብ ይገባል ብለዋል።

እኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲመጣ ከማድርግ ውጪ ሌላ ዓለማ የለም ይህን ስራ ለመተግበር ግን ብዙ ስራ ይጠይቃል ይህንንም ከሁሉም ጋር በጋራ ለመስራት ፍቃደኛ ነን ብለዋል ሊቀመንበሩ በመግለጫቸው።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ እኛ በህብረ ብሔራዊ ስሜት ሀገርን ለመገባት አስበን ብንመጣም #በብሔር ከተደራጁ አካት ጋርም ቢሆን በዲሞክራሲያዊ መልኩ #ለመወያየት ዝግጁ ነን ብለዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከቡራዩ ከተፈናቀሉ ዜጎች በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ #ተፈናቃይ ዜጎች ቁጥር 1 ሺህ 514 ብቻ ናቸው፡፡ በቡራዩ በአሁኑ ወቅት በተፈጠረው #መረጋጋት በአዲስ አበባ ጊዜያዊ የመጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ከነበሩ 11 ሺህ 902 ያህሉ ወደመጡበት የመኖሪያ ቀያቸው በአዲስ አበባ አስተዳደር አማካይነት ተመልሰዋል፡፡

©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቅርቡ ግጭት በተከሰተባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላለፉት 2 ቀናት በአብዛኛዎቹ #መረጋጋት የታየባቸው ቢሆንም ሆሮ ሊሙና ያሶ በተባሉት ቦታዎች ግን አሁንም የፀጥታ ሥጋት መኖሩን የምሥራቅ ወለጋ ዞን የፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታከለ ቶሎሣ ለኢቲቪ ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው ያለና #ማንነቱን በግልፅ ለመለየት ያልተቻለ የተደራጀ እና የታጠቀ ኃይል ሕዝቡን ሥጋት ውስጥ ከቶታል ያሉት ኃላፊው ችግሩን ለማስቆም መንግሥት አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በቤንሻንጉል ካማሺ ዞን #መረጋጋት እየተፈጠረ ይገኛል ተባለ። በዚህም ድጋፍ ለሚሰፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ነው የተሰማው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቦንጋ እየተረጋጋች ነው‼️

በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ  ከቡና መገኛነት ጋር ተያይዞ በድረ-ገጽ በተላለፈ መረጃ  የተፈጠረው ችግር በመቃለሉ ወደ #መረጋጋት መመለሱን የዞኑ ባህል፣ ቱሪዝምና መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ አስታወቀ፡፡

የመምሪያው ኃላፊ አቶ #አስረስ_አዳሮ ለኢዜአ እንደገለጹት በተፈጠረው ችግር ምክንያት በከተማዋ ላለፉት አምስት ቀናት  ትራስንፖርትና ማህበራዊ አገልግሎቶች ተቋርጠው ነበር፡፡

ይህም የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እንደሚጎዳ የዞኑ አስተዳደር ከወጣቱንና ከሌላውም የህብረተስብ ክፍል ጋር ተወያይቶ  መግባባት ላይ በመድረሱ ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ ከተማዋ ወደ መረጋጋት መመለሷን አስረድተዋል፡፡

የትራንስፖርት አገልግሎትም ጀምሯል፡፡

የቡና መገኛነት ጉዳይ መነሻ ሆኖ ለዓመታት የቆየው የቡና ሙዚየም ስራ አለመጀመር ህዝቡን እንዳስቆጣውም ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለስልጣን የተሰጠው ይቅርታና የቡና ሙዚየም ግንባታ ስራው እንደሚጀምር የሰጠው  መግለጫ ህዝቡን እንዳረጋጋው ተናግረዋል፡፡

ከህዝቡ የተነሱ  ጥያቄዎች ከክልልና ከፌደራል መንግስት ጋር በመነጋገር ምላሽ እንዲያገኙ ለመስራት መስማማት ላይ በመድረሳቸው  የግልና የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደቀድሞ ስራቸው መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡

አካባቢውን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስና መንገዱን ለማስከፈት በተደረገው ጥረት የወጣቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ድርሻ ከፍተኛ እንደነበረ አስታውቀዋል፡፡

ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል አቶ ገብረሚካኤል ወልደማርያም  በሰጡት አስተያየት በታሪክ የሚታወቀው የከፋ ቡና መገኛነት በተለያዩ ተቋማት የተሳሳተ መረጃ በመሰጠቱ ህዝቡን ማስቆጣቱን ተናግረዋል፡፡

ህዝቡ ያነሳቸውን ጥያቄዎች የዞኑ አስተዳደር ኃላፊነት ወስዶ እንደሚያስፈጽም ሃላፊነት በመውሰዱ ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት ወደ ነበረበት መመለሱን ገልጸዋል፡፡

መንግስት የሀዝቡን ጥያቄ በፍጥነት መመለስ እንዳለበትና ጉዳዩ ዳግም ጥያቄ የሚያስነሳ መሆን እንደሌለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ሌላኛው የከተማው ነዋሪ አቶ ረጋሳ ጸጋዬ በበኩላቸው ባለፉት ቀናት የተካሄደው ሰልፍ ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መጠናቀቁን ገልጸው ጥያቄው ተገቢነት ያለው በመሆኑ በመንግስት በኩል ምላሽ ያገኛል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡

“ቡናና ከፋ ከስያሜው ጀምሮ ጥብቅ ቁርኝት ያለው እና ታሪካዊ የሰነድ ማስረጃዎች የሚያረጋግጡ ሆኖ ሳለ የተላለፈው መረጃ መዛባት ለችግሩ ምንጭ ሆኗል “ያሉት ደግሞ አቶ ብርሃኑ  ገብሬ ናቸው፡፡

የዞኑ አስተዳደር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ጉዳዩ የመጨረሻ እልባት እንዲያገኝ ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

 ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአፍሪካ ህብረት‼️

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች አስቸኳይ ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል። በመክፈቻው ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተወዳዳሪ ሆና ለመገኘት አንድ ድምፅ ልታሰማ እንደሚገባ ነው የተናገሩት።

በመጀመሪያቸው በሆነው በህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ንግግራቸው ኢትዮጵያ በጥልቅ መታደስ ውስጥ እንዳለች በማንሳት ባለፉት ሰባት ወራት ውስጥ ለበርካታ ችግሮች ምላሽ የሚሆኑ የማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰዷን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ አዲስ የፖለቲካ ምህዳር እየፈጠረች መሆኗን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን መፍታቷን፣ የመገናኛ ብዙሃንን ነፃነት ማረጋገጧን እና የተዘጉ ድረገፆችን መክፈቷን ለአብነት አንስተዋል። በአሁኑ ወቅትም በሙስና ላይ ሰፊ እርምጃ እየወሰደች እና የፍትህ ስርዓቷን እያሻሻለች እንደምትገኝም ግልፀዋል።

ለፓን አፍሪካኒዝም ራእይ በመገዛት ከኤርትራ ጋር የነበረንን ግጭት ያለአንዳች ጥፋት መፍትሄ በመስጠት ቋጭተናልም ብለዋል። ይህንንም ተከትሎ በአፍሪካ ቀንድ አንፃራዊ ሰላም እና #መረጋጋት መምጣቱን ነው ያነሱት።

ይህም በመሆኑ በአከባቢው ሰላም፣ ብልፅግና እና ተስፋ እየመጣ ነው በማለትም ኤርትራ ላይ ላይ ተጥሎ የነበረው ማአቀብ መነሳትን በማሳያነት አንስተዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት/ኢጋድ ላደረጉት የማያቋርጥ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በካቢኔዋ የሴቶች እኩልነትን ማሳካት መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አንስተዋል።

ርእሰ ብሄሯን እና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ፕሬዚዳንትን ሴት ማድረጓን በማንሳት፥ ሴቶችን ወደ ውሳኔ ሰጪነት ማምጣቱ ለብዘሃነት ሲባል ሳይሆን ትክክለኛ ተግባር ስለሆነ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፍሪካ የኢኮኖሚ ትስስር መፍጠር እንዳለባት በገልፅ፥ ኢትዮጵያ የበኩሏን ድርሻ ለመወጣት ቪሳን በመዳረሻ የአውሮፕላን ማረፊያ የመስጠት አገልግሎትን ለሁሉም የህብረቱ አባል ሀገራት ዜጎች መጀመሯን አስታውቀዋል።

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ወደ አፍሪካ ህብረትነት ከተሸጋገረ በኋላ ተቋሙ ብዙ ስኬቶችን ቢያስመዘግብም መድረስ ከሚገባበት ቦታ አንፃር ብዙ እንደሚቀረው አንስተዋል።

የምንፈልግፍበት ቦታ ለመድረስ ግን በአፍሪካ ውጤታማ፣ ጠንካራ፣ ግልፅ እና ዴሞክራሲያዊ መንግስታት እንደሚያስፈልጉ ነው የጠቆሙት።

አሁን የተጀመረው የአፍሪካ ህብረትን የማሻሻል ሂደት ወሳኝ መሆኑን በመግለፅም፥ ይህ ሂደት ከመነሻው የተሳካ እንዲሆን አስተዋፅኦ ላደረጉት ለሩዋንዳው ፕሬዚዳንት እና ለወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ፖል ካጋሜ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የፋይናንስ ጉዳይ የማሻሻያው አብይ ጉዳይ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ ህብረቱ በፋይናንስ ራሱን መቻሉን ማረጋገጥ ይገባናል ብለዋል።

የአፍሪካ ሀገራት አህጉራዊውን የነፃ ንግድ ስምምነት እና ያለባቸውን የፋይናንስ ግዴታዎች በመወጣት ህብረቱ በፋይናነስ ራሱን ችሎ እንዲቆም ማድረግ እንደሚገባም ነው የጠቆሙት።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በድሬዳዋ አስተዳደር ሰሞኑን ችግር በተፈጠረባቸው አካባቢዎች መደበኛ እንቅስቃሴ መቀጠሉን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ አስታውቋል። ላለፉት አራት ቀናት ችግር የተፈጠረባቸው አካባቢዎች ዛሬ ሙሉ ለሙሉ ወደ #መረጋጋት ተመልሰዋል። መደበኛና የንግድ እንቅስቃሴም ወደ ወትሮ ሁኔታ ተመልሷል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማዕከላዊ ጎንደር ዞን‼️

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጭልጋ፤ በምስራቅና ምእራብ ደንቢያ ወረዳዎች ሰሞኑን ተከስቶ የነበረው ግጭት ወደ #መረጋጋት እየተመለሰ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የግጭቱ ዋነኛ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ 53 ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ሲውሉ 29 የጦር መሳሪዎች መያዛቸውም ተገልጿል።

የመምሪያው ሃላፊ ኮማንደር እንየው ዘውዴ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የፀጥታ መዋቅሩ ከሀይማኖት አባቶችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመቀናጀት ባደረገው ጥረት ግጭቶቹን መቆጣጠር ተችሏል፡፡

“በአሁኑ ወቅት በአካባቢዎቹ ሰላምና መረጋጋት እየሰፈነ ነው” ያሉት ሃላፊው ህብረተሰቡ አብሮ የመኖር ባህሉንና እሴቱን በመጠበቅ ለአካባቢው ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የጸጥታ መዋቅሩ የአካባቢውን ሰላም ከማስከበር ጎን ለጎን የግጭቱ ጠንሳሽና ተዋናይ ነበሩ የተባሉ 53 ተጠርጣሪ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል በአሁኑ ወቅት ህግ ፊት ለማቅረብ አስፈላጊውን መረጃ የማጠናቀር ስራ መጀመሩን ተናግረዋል።

በግጭቱ ታሳታፊ ከነበሩ ግለሰቦችም 29 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መያዛቸውን የጠቆሙት ኮማንድሩ 490 የተለያዩ ጥይቶችና 18 የጥይት ሳጥኖች በጸጥታ ሃይሉ እጅ መግባታቸውን ገልጸዋል።

እንደ ኮማንደሩ መግለጫ በግጭቶቹ ምክንያት በርካታ ዜጎች የህይወትና የንብረት ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የጸጥታ ሃይሉ ህግ የማስከበር ተልእኮውን አጠናክሮ መቀጠሉን የተናገሩት ኮማንደሩ የሰላሙ ባለቤት ህዝቡ እራሱ በመሆኑ የጀመረውን የተቀናጀ ጥረት እንዲቀጥልም አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሽ ከተማ እየተረጋጋ ቢሆንም፤ የሸቀጣ ሸቀጥና የእህል አቅርቦት ማነስ በአፋጣኝ እንዲፈታላቸው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ካማሽ ከሦስት ወራት በኋላ ወደ ሰላምና #መረጋጋት እየተመለሰች መሆኗንም መስክረዋል። በመንገድ እጦት በአሶሳ ከተማ የተከማቸው ከ4 ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር፣ ዘይት፣ ዱቄትና ሌሎችም ሸቀጣሸቀጦች ሰሞኑን ወደ ካማሽ ዞን እንደሚጓጓዙ የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታውቋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮሚያ ክልል #መረጋጋት በሚታይባቸው አካባቢዎች ለመሰብሰብ ከታቀደው ገቢ በላይ መሰብሰቡን እንዲሁም ግጭት በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች የታቀደውን ያህል ገቢ መሰብሰብ #አለመቻሉን የክልሉ የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ...

•በተረጋጉ አካባቢዎች ካቀደው እስከ 163 በመቶ
•ባልተረጋጉ ስፍራዎች ካቀደው እስከ 43 በመቶ ገቢ ሰብስቧል

ምንጭ፦ EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ #ሰላምና #መረጋጋት ለማምጣት የየተቋማቱ ኃላፊዎችና መምህራን ሥራቸውን በአግባቡ እየተወጡ #አለመሆኑ ተገለጸ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር #ጣሰው_ወልደሀና እንዳሉት፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ ለውጥ ለማምጣት ህዝቡ ተቃውሞዎች ሲያደርግ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ተሳታፊዎች ነበሩ፤ ለውጡ ከመጣ በኋላም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ መንግሥትና የየተቋማቱ ኃላፊዎችና መምህራን ሥራቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ሁከቶቹ ተበራክተዋል ብለዋል፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚታዩትን የሰላም መደፍረስ ምክንያት የሚያጠና ቡድን ማዋቀሩን በመጥቀስ፤ በቀጣይ ለሚሠራቸው ሥራዎች አንድ ሚሊዮን ብር መመደቡንም ገልጸዋል፡፡ ሰላም ከሌለ ልማትና የመኖር ነፃነት ስለማይኖር በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችም ሆኑ መምህራን ለሰላም ዘብ መቆም እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
BBC አማርኛ ~ ስለቴፒ ከተማ ግጭት‼️

በቴፒ ከተማ ከትናንት በስቲያ ጥር 22/2011 ዓ.ም በተነሳ #ግጭት ሰባት ሰዎች #መሞታቸውን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #የሽዋስ_አለሙ ለቢቢሲ ገለፁ።

ግጭቱን ተከትሎም ጥር 5/2011 ዓ. ም የዓመቱን ትምህርት መስጠት የጀመረው የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ ትምህርት #መቋረጡን ተሰምቷል።

ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገው በዩኒቨርሲቲው ቴፒ ግቢ ተማሪ እንዳለው ከትናንት በስቲያ ግጭቱ ሲፈጠር መስጊድ ሰፈር (ባጃጅ ሰፍር) አካባቢ ከጓደኞቹ ጋር ወጣ ብሎ ነበር።

"በድንገት አካባቢው በግርግር ተናወጠ፤ በተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ማን ለማን እንደሚተኩስ አይታወቅም፤ ቀውጢ ተፈጠረ" ይላል።

በወቅቱም እነርሱም ራሳቸውን ለማዳን መንደር ለመንደር እየተሹለከለኩ ወደ ግቢያቸው እንዳመሩ ይናገራል።

በጊዜው በቴፒ ካምፓስ የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ችግር አጋጥሞ ስለነበር በግቢው ውስጥም ውጥረት ነግሶ ነበር ይላል። ምክንያቱ ምን እንደነበር እርግጠኛ ባይሆንም በከተማው ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ሳቢያ ምግብ አብሳዮቹ በሥራ ገበታቸው ላይ ባለመገኘታቸው መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል።

አካባቢው #ከተረጋጋም በኋላ በርካታ ቤቶች ወደተቃጠሉበት ስፍራ እንደሄዱና 'ጀምበሬ' እየተባለ የሚጠራው ሰፈር ሙሉ በሙሉ #መውደሙን እንደተመለከተ ተናግሯል።

በዩኒቨርሲቲው የ3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ይህ የዓይን እማኝ እንደሚለው በአካባቢው በየዓመቱ ችግር እንደሚነሳ በማስታወስ አሁንም በግጭቱ ምክንያት ትምህርት #ተቋርጧል

በሚዛን ቴፒ አካባቢ የቆየ የመዋቅር ጥያቄ ነበር የሚሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የቴፒ ከተማ ነዋሪ እንደገለፁት በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በግምት የአንድ ትልቅ ቀበሌ 1/3ኛ የሚሆን ሰፈር ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

"ከዚህ በፊት ቴፒ በሸካ ዞን ሲተዳደር ቆይቷል፤ ሕዝቡ ያንን በመቃወም በዞኑ መተዳደር አንፈልግም የሚል ጥያቄ በማቅረቡ እርሱን ሰበብ ተደርጎ ጉዳዩ ወደ ብሔር ግጭት አመራ" ይላሉ።

ህዝቡ የተለያየ ኮሚቴ አዋቅሮ ለጥያቄው መልስ ለማግኘት እየተጠባበቀ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ባልታሰበ ሁኔታ ሌሊት ላይ ጥቃት መፈፀሙን ይናገራሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት ጥቃቱ ከትናንት በስቲያ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድንጋይ በመወራወር ተጀምሮ በመንገድ ዳር ያሉ የሚከራዩ ቤቶችን #በማቃጠል ነው የተጀመረው።

ጥቃቱ ቀን ጋብ ብሎ ከቆየ በኋላ ሌሊት ከ9:00 ሰዓት በኋላ በርካታ ቤቶች እንደተቃጠሉና ንጋት ላይ ወደ #ጫካ ሸሽተው የነበሩት የሰፈሩ ነዋሪዎች ደርሰው ለማጥፋት ሲሞክሩ እንደነበር ይናገራሉ።

ሰዎች በተኙበት ቤቶችና መጋዘኖች ተቃጥለዋል፤ አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል የሚሉት መምህሩ፤ "በወቅቱ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ እርስ በርስ እየተጠራሩ ወደ ጫካ ሸሹ፤ ይሁን እንጂ አዛውንቱ የጓደኛዬ አባት አገር ሰላም ብለው በተኙበት በስለት ተገድለዋል" ይላሉ።
"የእኔ ቤተሰቦች ንብረታቸው ተዘርፏል፤ ቤታቸው ወድሟል" ሲሉ በሃዘን ይገልፃሉ።

ትናንት በቴፒ ከተማ በየመንገዱ ላይ የሚቃጠሉ የመኪና ጎማዎች፤ በቁጣ የተነሱ ወጣቶችና ነበር የሚታየው፤ የተኩስ ድምፅም ይሰማ ነበር።

በአንፃሩ ዛሬ የከተማው ነዋሪዎች በግጭቱ የሞቱትን ሰዎች ለመቅበር በተለያየ ቦታ ተበታትነው ስለሚገኙ በአንፃሩ #መረጋጋት ይታይበታል ብለዋል።

በወቅቱ ሕዝቡ የፀጥታ ኃይሎች #ጣልቃ ይገባሉ ብሎ ቢጠባበቅም ግጭቱን ለማስቆም ምንም እርምጃ ባለመወሰዱ ጉዳት መድረሱንና ችግሩ ከተከሰተ በኋላ ከስፍራው መድረሳቸውን ተናግረዋል።

መምህሩ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ትምህርት የጀመረው ዘግይቶ ቢሆንም አሁንም በዚሁ ግጭት ምክንያት በቴፒ ካምፓስ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን ይገልፃሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት ለተማሪዎቹ ደህንነት ሲባል ተማሪዎች በግቢው ውስጥ እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን በዩኒቨርስቲው ሁለት ግቢዎች ውጥረትና ስጋት ይታያል።

የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳረ አቶ የሽዋስ አለሙ በበኩላቸው #ራስን_በራስ የማስተዳደር የቆየ ጥያቄ ቢኖርም የአሁኑ ግጭት መነሻ ግን ተቋርጦ የነበረ የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመር ነው ይላሉ።

አስተዳዳሪው እንዳሉት በግጭቱ 7 ሰዎች ሲሞቱ 100 የሚጠጉ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 1500 ሰዎችም ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

የፌደራል፣ የክልልና የመከላከያ የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው #ፀጥታ ለማስፈን እየሰሩ መሆናቸውን አስተዳዳሪው ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ BBC አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጨፌ ኦሮሚያ 9ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው እለት ማካሄድ #ጀምሯል። ጨፌው ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባው የክልሉን መንግስት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም እንደሚገመግም ይጠበቃል። እንዲሁም በክልሉ ያለው #ሰላም#መረጋጋት እና የህግ የበላይነትን ማስከበር ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚመክርም ተገልጿል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንገዱ ተከፍቷል...

ትናንት ተዘግቶ የዋለው የአዲስ አበባ-ደሴ መንገድ ዛሬ ተከፍቷል። በአካባቢው #መረጋጋት የሚታይ ሲሆን፣ በታጣቂዎች ቁልፍ የተነጠቁ ተሽከርካሪዎች አልፎ አልፎ መንገድ ዘግተው/ቁመው ይታያሉ።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉሙዝ
(ትኩረት‼️)

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፓዊ ወረዳ ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና የሰው ሕይወት እየጠፋ፣ አካል እየጎደለና ንብረት እየተዘረፈ መሆኑን ነዋሪዎች ለአብመድ አስታውቀዋል፡፡

ከቀናት በፊት በዳንጉር ወረዳ በጫኝና አውራጆች መካከል በተነሳ ግጭት የተጀመረው አለመረጋጋት ወደተለያዩ አካባቢዎች #መስፋፋቱን ነው ነዋሪዎቹ ያስታወቁት፡፡

ከፓዊ ወረዳ ሕዳሴ ቀበሌ አስተያዬታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ‹‹እረኞች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ከብቶቻችንም እየተነዱ እየተወሰዱ ነው፡፡ ትናንት ገበያ መውጣት አልቻልንም፤ ዛሬም #በዓሉን ለማክበር ተቸግረን ፍርሃት ውስጥ ነን›› ብለዋል፡፡

ማምቡክ መንደር 49 አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ደግሞ ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ዛሬ ገበያ ነበር፤ ገና ከመቆሙ በጠዋቱ ተበትኗል፡፡ በጫካው ውስጥ ተኩስና ቀስት ማስወንጨፍ አለ፡፡ ከዳንጉር አካባቢ ነው የግጭቱ መሠረት ያለው፤ መንግሥት በፍጥነት ሊደርስልን ይገባል፡፡ ሰዎች በየጫካው እየሞቱ ነው›› ብለዋል፡፡ በዛሬው ዕለትም የሀገር መከላከያ ሠራዊት በቦታው መድረሱንም ገልጸዋል፡፡

የቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት በበኩሉ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ተከስቶ የነበረዉ የፀጥታ ችግር አንጻራዊ #መረጋጋት ላይ መሆኑን ለአብመድ አስታውቋል፡፡ ሚያዝያ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ አይሲካ ቀበሌ በአሽከርካሪ እና ጫኝና አውራጅ ሥራ በተሠማሩ ወጣቶች መካከል ግጭት መፈጠሩ ተነግሮ ነበር፡፡

አሁን ላይ ችግሩን የፈጠሩ ግለሰቦች #በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን እና ተጨማሪ የሰዉ ሕይወት #እንዳይጠፋ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አድጎ አምሳያ ለአብመድ ገልጸዋል፡፡ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል እና የክልሉ የፀጥታ ኃይል በጋራ በመሆን ችግሩ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ እየሠራ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ

የሀዋሳ ከተማ ሰላም ቀድሞ ወደነበረበት እየተመለሰ ይገኛል። በከተማይቱ የንግድ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴም እየተጀመረ ነው። ካለፉት ቀናት በእጅጉ የተሻለ መረጋጋት እና ሰላም በከተማዋ መስፈኑን በስልክ ያነጋገርናቸው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል።

#ወንዶገነት

በወንዶ ገነት ከተማ አርብ ዕለት ተከስቶ በነበረው ግጭት ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን የሚታወስ ሲሆን ትናንት ቅዳሜም በወንዶ ገነት ውጥረት ነግሶ ነው የዋለው። ይሁን እንጂ ዛሬ እሑድ በከተማው መረጋጋት እንደሚታይ አንድ የአይን እማኝ ለቢቢሲ ገልፀዋል “የትራንስፖርት አገልግሎት ጀምሯል። ሱቆችም ከሞላ ጎደል ተከፍተዋል። የጸጥታ ኃይል አስከባሪዎች በስፋት በከተማዋ ሲንቀሳቀሱ ነው የዋሉት።
/BBC/

#ይጋለም

ከተማዋ ወደ ቀድሞ እንቀስቃሴ አልተመለሰችም፤ ሆኖም ግን ካለፉት ሁለት ቀናት የተሻለ #መረጋጋት አለ። ዛሬ ላይም ቢሆን በይርጋለም ከተማ የደህንነት ስጋት መኖሩን ለBBC የተናገሩ የከተማዋ ነዋሪ፤ በዚሁ ምክንያት በርካታ የንግድ ተቋሟት በራቸውን ዝግ አድርገው እንደዋሉ ገልፀዋል።

#ሀገረሰላም

በስልክ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ዛሬ ካለፉት ሁለት ቀናት የተሻለ ሰላም እና መረጋጋት እንደታየ ገልፀዋል፤ ስጋቶች ግን አሁንም አሉ ብለዋል። የመከላከያ ሰራዊት በከተማው ይገኛል በየቦታውም ቅኝት ሲያሰርግ ውሏል ሲሉ የዛሬውን ሁኔታ አስረድተዋል።

#አለታወንዶ

የዛሬው ዉሎ ከትላንትና እና ከትላንት በስቲያ ከነበረው እጅጉ የተሻለ እና መረጋጋት የታየበት እንደነበር ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በሲዳማ ዞን የኢንተርኔት አገልግሎት አልተጀመረም!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ካርቱም

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) የሚመሩት ልዑክ ካርቱም ገብቷል፡፡ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በማኅበራዊ ገጹ እንዳስነበበው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት ልዑክ ዛሬ ወደ ሱዳን ያቀናው በሱዳን የሽግግር መንግሥትን በይፋ ለመመሥረት በሚከናወነው ሥነ-ሥርዓት ለመታደም ነው፡፡

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሐሰን ኦማር አልበሽር መንግሥት የሦስት አስርት ዓመታት ቆይታው በሕዝባዊ ተቃውሞ ተናግቶ ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሲመሠረት ሱዳን ወደ ቀውስ እንደምትገባ ብዙዎች ገምተው ነበር፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያና የአፍሪካ ሕብረት ባደረጉት ተከታታይ ጥረት ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱና ሲቪል የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሳተፉበት የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በዚህም #ሱዳን ወደ #መረጋጋት እንደምትገባ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ የሽግግር መንግሥቱ ምሥረታ ላይ ለመገኘትም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) የሚመሩት ልዑክ ዛሬ ጠዋት ካርቱም ገብቷል፤ ደማቅ አቀባበልም ተደርጎለታል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia