Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
462 subscribers
3.03K photos
184 videos
46 files
2.1K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
#አልጀዚራ_ሰበር!
የእስራኤል ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን“የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በጋዛ ሰርጥ ላይ ለአንድ ሳምንት ያህል በሀማስ የተያዙትን ሰዎች ለማወቅ ሲበሩ ነበር!”ሲል አስታወቀ!!
ሀማስማ ጉድ ችሏል!

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
#አልጀዚራ_ቀጥታ
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የእስራኤልን ጥቃቶች ባስቸኳይ ማስቆም አስፈላጊ ስለመሆኑ አንድ ወጥ የአረብ አቋም ዛሬ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይተላለፋል ያለ ሲሆን፣የግብፅ፣የጆርዳን፣የሳዑዲ አረቢያ፣የኤሜሬትስ፣የኳታር እና የፍልስጤም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ አማን ውስጥ ከአሜሪካ አቻዎቻቸው ጋር እየተገናኙ መሆኑን አስታውቆ የእስራኤልን ጥቃት ማቆም፣ እርዳታ መግባት እና መፈናቀልን በተመለከተ የአረቦች አቋም ሊናወጥ ወይም ሊሸሽ አይችልም ብሏል።
#የአልቃሳም_ብርጌዶች_ቃልአቀባይ #አቡ_ዑበይዳህ #የዛሬ_መግለጫ!
ሙጃሂዶቻችን የጽዮናውያንን አረመኔያዊ ጥቃት መጋፈጣቸውን ቀጥለዋል፤ወረራውን ከጀመረ ጀምሮ #335 የጽዮናውያን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ላይ ኢላማ መደረጉን  የመዝገብን ሲሆን፣
የታለሙት ተሽከርካሪዎችም የወታደር አጓጓዦች፣ታንኮች እና ቡልዶዘሮች ሲሆኑ ባለፉት 72 ሰዓታት ውስጥ ብቻ #33 የጽዮናውያን መኪኖችን ኢላማ አድርገናል ብሏል።
አቡ ዑበይዳህ አያይዞም በጽዮናዊቷ ላይ በተለያዩ ኢላማዎች የሚሳኤል ጥቃቶችን ማደረሱንም የቀጠልን ሲሆን፣በቤቴ ሀኖን የሚገኘውን የጠላት እግረኛ ጦር ቡድን በፀረ-ሰው መሳሪያ አጥቅተናል፤በተጨማሪም ባለፉት ሶስት ቀናት ውስጥ በጠላት ሃይሎች ላይ ጠንካራ ዘመቻ አድርገን ከዜሮ ርቀት ላይ በቦምብ እና መትረየስ በማጥቃት #አምስት የጠላት ጦር ተሸካሚ ወታደሮችን ገድለናል ብሏል!
“ሙጃሂዶቻችን በጦር ሜዳ ያሳዩት ጀግንነት ከአረመኔ ወራሪ ሃይል ጋር እየተጋፈጥን በመሆኑ በዓለም ላይ ላለ ነፃ ሰው ሁሉ የሚያኮራ ነው!” ያለው ቃልአቀባዩ አቡ ዑበይዳህ በጋዛ ፈጣን ድል ለማግኘት የጠላትን እቅድ አክሽፈን የእኛ ሙጃሂዶች በቦታቸው ተቀምጠዋል፤ጠላት አሁንም እውነተኛ ኪሳራውን እየደበቀ ነው፣ እኛም ከወራሪ የጠላት ሃይሎች ጋር እየተፋለምን ነው ብሏል።
የአልቃሳም ብርጌድ ቃል አቀባይ አቡ ዑበይዳህ እንደተናገረው ጠላት ጦርነቱን በማራዘም የሚቆጥረው በደል እና እልቂት ነው፣ እናም ጦርነቱ የቱንም ያህል ቢቆይ ትግሉን ለመቀጠል ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን ብሏል!
#ጠላት_የተቀበለው_ጊዜያዊ_እርቅ_የመሬት_ዘመቻ_ከመጀመሩ_በፊት_ስናስቀምጠው_የነበረው_እና_ጠላት_በወቅቱ_ውድቅ_ያደረገውን_ስምምነት_ነው” ያለው አቡ ኡበይዳህ፣በተወረረው ዌስት ባንክ ላሉ ወገኖቻችን ታጋዮች ሰላምታ እንሰጣለን፤ህዝባችንን ለመደገፍና ወረራውን ለመቃወም ለወጣው የሀገራችን ብርታት ለሆነው ሁሉ ሰላምታ እናቀርባለን!
በተለይም #በየመን ላሉ ወንድሞቻችን ሰላምታ እናቀርባለን!#በሊባኖስ የሚገኙትን ወንድሞቻችንን በሰሜን ግንባር ወራሪውን ለከበቡት እና ቦታውን ለሚያወድሙ ወንድሞቻችንም ሰላምታ እናቀርብላቸዋለን ብሏል አቡዑበይዳህ!
“በመላው የፍልስጤም ግዛት ለወራሪው ያለው ተቃውሞ እንዲጠናከርና #በዮርዳኖስ ያሉ ወንድሞቻችን ህዝባዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን!በዓለም ላይ ያሉ ነፃ ሰዎች ሁሉ ጠላትንና ጥቅሞቹን በየቦታው እንዲያምታቱ እና በሁሉም መንገድ እንዲያደናግሩ እንጠይቃለን”ብሏል በመግለጫው!
“እሮብ እለት ሙጃሂዶቻችን ከጃባሊያ በስተምስራቅ ከሚገኙት ዋሻዎች ውስጥ የአንዱን መሿለኪያ ቀዳዳ ሲከፍቱ የጽዮናውያን ሃይል ሊያፈነዳው ሞክሮ ብርቱ ጉዳት ደርሶበታል ያለ ሲሆን፣የቃሳም ቡድን ማክሰኞ ጠዋት ስድስት ግለሰቦችን ባቀፈው የጠላት እግር ቡድን ላይ ፀረ-ሰው መሳሪያ ጋር ኢላማ ማድረጉን እና  አንድ ሙጃሂድ በ #10 ሜትር ርቀት ላይ #ስምንት የጽዮናውያን ወታደሮች ከጦር አጓጓዥ ተሽከርካሪ ላይ ወርደው ከረንቲሲ ሆስፒታል በስተምስራቅ ሙትና ቁስለኛ አድርጓቸዋል ብሏል!
በተጨማሪም ሙጃሂዲኖቻችን በዘይቱን ሰፈር በሚገኝ ህንጻ ውስጥ ለመመሸግ በዝግጅት ላይ የነበሩ በርካታ የጠላት እግረኛ ወታደሮችን በማጥቃት ሙት እና ቁስለኛ አድርገዋቸዋል ብሏል!
አቡ ዑበይዳህ አያይዞ ሙጃሂዶቻችን ዛሬ ጎህ ሲቀድ ከዜሮ ርቀት ሀይ ዘይቱን ሰፈር የሚገኘውን ህንጻ ለመውረር የወጣውን የጽዮናውያን ሃይል አጥቅተው አንድ ወታደር በግንቡ ላይ ተቀምጦ ሳለ መርካቫን የተሰኘ ታንክ አውደመዋል ብሏል!
#አሏሁ_አክበር!
#አልጀዚራ_ቀጥታስርጭት!

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
#Breaking!
ኒው ዮርክ ታይምስ የእስራኤል ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው እስካሁን ባለው ሂደት #ኢራን:
√185 ሰው አልባ አውሮፕላኖች፣   √36 ክራይዝ ሚሳኤሎች እና
√110 ከመሬት ወደ ላይ የሚወነጨፉ ሚሳኤሎችን አስወንጭፋለች!
- አብዛኛወቹ በቀጥታ ከ #ኢራን ሲሆኑ ጥቂቶቹ ከየመን እና ከኢራቅ የተላኩ ናቸው!
#አልጀዚራ

@ https://t.me/Xuqal
“ተዋጊዎቻችን እና እኛ የያዝናቸው Sukhoi 24 አውሮፕላኖች ተልእኳቸውን ለመወጣት ምቹ ሁኔታ ላይ ናቸው!”
የኢራን ጦር አየር ሃይል አዛዥ
#አልጀዚራ

@ https://t.me/Xuqal
የኢራን ባለስልጣን ለሮይተርስ እንደተናገሩት የሄሊኮፕተር አደጋውን ተከትሎ የፕሬዚዳንቱ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ህይወት አደጋ ላይ ነው።
#አልጀዚራ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በምስራቅ አዘርባጃን ግዛት አደጋ በደረሰባት ሄሊኮፕተር ላይ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና ከበርካታ ባለስልጣናት ጋር #የመጨረሻ እይታ!
#አልጀዚራ

ኢና ሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን !

በጎንደር በግፍ የተገደሉት የመስጂድ ኢማም ሸይኽ ሲራጅ አብድሬ እኚህ ናቸዉ!

በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ደንቢያ ወረዳ አየንባ ቀበሌ የመስጂድ ኢማም የሆኑት ሸይኽ ሲራጅ አብድሬ በግፍ ተገድለዋል::

አላህ(ሱ.ወ) ይዘንላቸዉ። አሚን🤲

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
“በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ እና በቀላሉ ሊደረስበት በማይችል ተራራማ አካባቢ የፍለጋው ስራ ቀጥሏል!
- ተጨማሪ የነፍስ አድን ቡድኖች ወደ አደጋው ቦታ እየላክን ነው!”

የኢራን መንግስት ቃል አቀባይ!
#አልጀዚራ

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
#BREAKING
የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሁሰይን አሚር አብዱላሂ እና አብሯቸው የነበረው የልዑካን ቡድን በሙሉ በሄሊኮፕተር አደጋው መሞታቸውን የኢራን መንግስት ቴሌቭዥን አስታውቋል!
#አልጀዚራ

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal