Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
465 subscribers
3.04K photos
187 videos
46 files
2.1K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
#የአልቃሳም_ብርጌዶች_ቃልአቀባይ #አቡ_ዑበይዳህ #የዛሬ_መግለጫ!
ሙጃሂዶቻችን የጽዮናውያንን አረመኔያዊ ጥቃት መጋፈጣቸውን ቀጥለዋል፤ወረራውን ከጀመረ ጀምሮ #335 የጽዮናውያን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ላይ ኢላማ መደረጉን  የመዝገብን ሲሆን፣
የታለሙት ተሽከርካሪዎችም የወታደር አጓጓዦች፣ታንኮች እና ቡልዶዘሮች ሲሆኑ ባለፉት 72 ሰዓታት ውስጥ ብቻ #33 የጽዮናውያን መኪኖችን ኢላማ አድርገናል ብሏል።
አቡ ዑበይዳህ አያይዞም በጽዮናዊቷ ላይ በተለያዩ ኢላማዎች የሚሳኤል ጥቃቶችን ማደረሱንም የቀጠልን ሲሆን፣በቤቴ ሀኖን የሚገኘውን የጠላት እግረኛ ጦር ቡድን በፀረ-ሰው መሳሪያ አጥቅተናል፤በተጨማሪም ባለፉት ሶስት ቀናት ውስጥ በጠላት ሃይሎች ላይ ጠንካራ ዘመቻ አድርገን ከዜሮ ርቀት ላይ በቦምብ እና መትረየስ በማጥቃት #አምስት የጠላት ጦር ተሸካሚ ወታደሮችን ገድለናል ብሏል!
“ሙጃሂዶቻችን በጦር ሜዳ ያሳዩት ጀግንነት ከአረመኔ ወራሪ ሃይል ጋር እየተጋፈጥን በመሆኑ በዓለም ላይ ላለ ነፃ ሰው ሁሉ የሚያኮራ ነው!” ያለው ቃልአቀባዩ አቡ ዑበይዳህ በጋዛ ፈጣን ድል ለማግኘት የጠላትን እቅድ አክሽፈን የእኛ ሙጃሂዶች በቦታቸው ተቀምጠዋል፤ጠላት አሁንም እውነተኛ ኪሳራውን እየደበቀ ነው፣ እኛም ከወራሪ የጠላት ሃይሎች ጋር እየተፋለምን ነው ብሏል።
የአልቃሳም ብርጌድ ቃል አቀባይ አቡ ዑበይዳህ እንደተናገረው ጠላት ጦርነቱን በማራዘም የሚቆጥረው በደል እና እልቂት ነው፣ እናም ጦርነቱ የቱንም ያህል ቢቆይ ትግሉን ለመቀጠል ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን ብሏል!
#ጠላት_የተቀበለው_ጊዜያዊ_እርቅ_የመሬት_ዘመቻ_ከመጀመሩ_በፊት_ስናስቀምጠው_የነበረው_እና_ጠላት_በወቅቱ_ውድቅ_ያደረገውን_ስምምነት_ነው” ያለው አቡ ኡበይዳህ፣በተወረረው ዌስት ባንክ ላሉ ወገኖቻችን ታጋዮች ሰላምታ እንሰጣለን፤ህዝባችንን ለመደገፍና ወረራውን ለመቃወም ለወጣው የሀገራችን ብርታት ለሆነው ሁሉ ሰላምታ እናቀርባለን!
በተለይም #በየመን ላሉ ወንድሞቻችን ሰላምታ እናቀርባለን!#በሊባኖስ የሚገኙትን ወንድሞቻችንን በሰሜን ግንባር ወራሪውን ለከበቡት እና ቦታውን ለሚያወድሙ ወንድሞቻችንም ሰላምታ እናቀርብላቸዋለን ብሏል አቡዑበይዳህ!
“በመላው የፍልስጤም ግዛት ለወራሪው ያለው ተቃውሞ እንዲጠናከርና #በዮርዳኖስ ያሉ ወንድሞቻችን ህዝባዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን!በዓለም ላይ ያሉ ነፃ ሰዎች ሁሉ ጠላትንና ጥቅሞቹን በየቦታው እንዲያምታቱ እና በሁሉም መንገድ እንዲያደናግሩ እንጠይቃለን”ብሏል በመግለጫው!
“እሮብ እለት ሙጃሂዶቻችን ከጃባሊያ በስተምስራቅ ከሚገኙት ዋሻዎች ውስጥ የአንዱን መሿለኪያ ቀዳዳ ሲከፍቱ የጽዮናውያን ሃይል ሊያፈነዳው ሞክሮ ብርቱ ጉዳት ደርሶበታል ያለ ሲሆን፣የቃሳም ቡድን ማክሰኞ ጠዋት ስድስት ግለሰቦችን ባቀፈው የጠላት እግር ቡድን ላይ ፀረ-ሰው መሳሪያ ጋር ኢላማ ማድረጉን እና  አንድ ሙጃሂድ በ #10 ሜትር ርቀት ላይ #ስምንት የጽዮናውያን ወታደሮች ከጦር አጓጓዥ ተሽከርካሪ ላይ ወርደው ከረንቲሲ ሆስፒታል በስተምስራቅ ሙትና ቁስለኛ አድርጓቸዋል ብሏል!
በተጨማሪም ሙጃሂዲኖቻችን በዘይቱን ሰፈር በሚገኝ ህንጻ ውስጥ ለመመሸግ በዝግጅት ላይ የነበሩ በርካታ የጠላት እግረኛ ወታደሮችን በማጥቃት ሙት እና ቁስለኛ አድርገዋቸዋል ብሏል!
አቡ ዑበይዳህ አያይዞ ሙጃሂዶቻችን ዛሬ ጎህ ሲቀድ ከዜሮ ርቀት ሀይ ዘይቱን ሰፈር የሚገኘውን ህንጻ ለመውረር የወጣውን የጽዮናውያን ሃይል አጥቅተው አንድ ወታደር በግንቡ ላይ ተቀምጦ ሳለ መርካቫን የተሰኘ ታንክ አውደመዋል ብሏል!
#አሏሁ_አክበር!
#አልጀዚራ_ቀጥታስርጭት!

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1