Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
469 subscribers
3.05K photos
188 videos
46 files
2.11K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
ባዶ እጃችንን ምንም ሳንይዝ ዱንያን ተቀላቀልን ፤ በዱንያም ላይ በሁሉም ነገሮች እና ጉዳዮች ላይ እየታገልን ቆየን ፤ ዱንያን ለቀን ስንሄድ ደግሞ እንደ አመጣጣችን ባዶ ሆነን ዱንያን ለቀን እንሄዳለን ፤ ከዛም በታላቁ ጌታ ፊት ቆመን ስለ ሁሉም ነገር ሂሳብ እንተሳሰባለን።

ጌታችን ሆይ ያማረ ኻቲማን ወፍቀን 🥹 🤲

ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
"ዱዓዬ እጣፈንታዬን ለመቀየር በቂ አልነበረም ማለት ነው?" የሚሉ ከርታታ ልቦች አሉ። በህይወት ልዩ መልኮች እንቅፋት የተመቱ ልቦች። በህመም፣ በእዳ፣ በትዳር አለመሳካት፣ በሁኔታዎች መዘበራረቅና ግራመጋባት የሚዋኙ ስሜቶችም እንዲሁ። ምን ያህል ጌትዬን ተለማምጠናል? … ከአለሙ ሁሉ እስኪያስቀድመን፣ ከጠያቂዎች ሁሉ እስኪመርጠን። እርሱ የሚለማመጡትን ይወዳል። የሚወደውን ደግሞ ይመርጣል።

ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
ለ አላህ እንጅ የማይነገሩ ንግግሮች...
ወደ እሱ እንጅ የማይላኩ እሮሮዎች...
በእሱ ፊት እንጅ የማይወርዱ እንባዎች አሉ።.....ለርሱ እያንሾካሾካችሁ ያ......ረብ በሉ

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ለፈገግታ

ድሮ ነው አሉ...አንዲት ግብፃዊት አዛውንት በሐጅ ላይ በሚደረገው የጠጠር መወርወር(ጀመራት) ስርዓት ላይ ጠጠር እየወረወሩ:-
"ያዝ አንተ ው*ሻ" ይላሉ።
ይህን ያየ አንድ ወጣት በተረጋጋ ድምፅ:-
"እናቴ እንዲህ መሳደብ አይፈቀድም!" ይላቸዋል።
እናትም ቀበል አድርገው :-"አንተን ይመለከትሃል? ወይስ ዝምድና አላቹህ?"😁

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን ረሂመሁሏህ በህይወታቸው ለመጀመሪያ ግዜ አፕልን (🍎) ያዩበትን አጋጣሚ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፦
---------

እኔና የዒልም ጓደኞቼ ሆነን ሸይኽ ዐብድራህማን ኢብን ናስር አሰዕዲ ዘንድ የኢብኑ ረጀብን قواعد الفقهية  እንቀራ ነበር። ኪታቡ ትንሽ ጠጠር ይል ነበር! ቢሆንም  እርሳቸው ዘንድ ይሄንን ኪታብ ለመማር የጀመርነው ብዙ ተማሪዎች ነበርን ግን ከግዜ ወደ ግዜ የተማሪው ቁጥር በጣም እየቀነሰ መጥቶ ሸይኹ ዘንድ እኔ ብቻ እስክቀር ደረስኩ።  አልሃምዱሊላህ ኪታቡን እርሳቸው ዘንድ ጨረስኩት። በጨረስን በንጋታው ሸይኹን ካገኘኋቸው፣ ከዘየርኳቸውና ሰላም ካሉኝ በኋላ  እጃቸውን ወደ ኪሳቸው አስገብተው የሆነ ከዚህ በፊት አይቼው የማላውቀውን የፍራፍሬ አይነት ሰጡኝ 🫴🏻 🍎

ያሸይኽ አልኳቸው ምን የሚደረግ ነው? ልጥበሰው? ልቀቅለው አልኳቸው እርሳቸውም "አይ ይሄ ቱፋህ (አፕል) ይባላል ዝም ብለህ ቆርጠህ ተመገበው"አሉኝ ይላሉ


ሁሉንም አላህ ይዘንላቸው፤ ነገም ያቺ ያማረችዋን የጀነት ፍራፍሬ ከሚበሉትና ከምንጯም ከሚጎነጩት ደጋግ ባሮቹ  ያድርጋቸው። አላህ እኛንም የነሱን መልካም ፈለግ ተከታዮች ያድርገን። 🤲

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ለሰው ልጆች የደስታና የፈገግታ ሰበብ እንጂ ለአንድም ሰው የመከፋትና የማዘን ምንጭ አትሁን! ማስደሰትን እንኳ ባትችል ማንንም ለመጉዳት አታስብ!!
ከአፈር ተፈጥረን ፤ አፈር ላይ ስንረማመድ ኖረን ፤ ከዛ ሁላችንም ከ አፈር በታች እንገባለን። አንደኛው ከሌላኛው በምንም አይበልጠውም። ለአላህ ባለው ፍራቻ እና በመልካም ስራ ብቻ እንጂ።

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ኢብኑል-ቀይም "በዳኢዕ አልፈዋኢድ" በተሰኘው ኪታባቸው ከኢማም ኢብኑ ዐቂል የተያዘ ወርቃማ ንግግርን አስፍረዋል:-
"አንድ ሰው "የነቢዩ አካል ያረፈበት ስፍራ(ሑጅራህ) ይበልጣል ወይንስ ከዕባ? ሲል ጠየቀኝ።እኔም እንዲህ መለስኩ:-
"በጥያቄህ ለማወዳደር የፈለከው ካዕባን እንዲሁ ከቀብራቸው ስፍራ(ሑጅራ) ጋር ከሆነ ካዕባ ይበልጣል።ነገር ግን በሑጅራው የእሳቸውﷺ አካል እያለ ከሆነ ግን በፍፁም ወላህ።ዐርሽና ተሸካሚዎቹ፤አደም የኖሩባት ኤደን ጀነት፤ተሽካርካሪ ፈለኮችም ጭምር ከሑጅራው ጋር አይወዳደሩም።ምክኒያቱም በሑጅራው ከፍጥረተ ዓለሙ ጋር ቢለካ የሚመዝን አካል አርፏል።"

عليه افضل الصلاه والسلام اللهم صلي وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى اله وصحبه اجمعين

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Video
ቁርአን ለሰይዳችንﷺ ክብርና ልቅና ለመሳል በሚከብድ መልኩ የተለየ ቦታ ሰጥቶ እናገኛለን።ይህንም በአንድ ታሪካዊ ምሳሌ እንግለፀው:-

ሰይዳችንﷺ ማር በጣም ይወዱ ነበር።በለት ተለት ተግባራቸው ከሚፈፅሟቸው ተግባሮች አንዱ ከዐስር ሰላት በኃላ ባለቤቶቻቸውን እየተዟዟሩ መዘየር ነበር።ልክ ሲመሽም ወደ አንዷ ባለቤታቸው በመሄድ ያድራሉ።

ታዲያ የምዕምናን እናት የሆኑት ዓኢሻህ እና ሐፍሳህ አንድን ነገር ያስተውላሉ።ሰይዳችንﷺ ከዐስር ሰላት በኃላ እየተዟዟሩ ሲዘይሯቸው ከሌሎቹ በተለየ መልኩ እናታችን ዘይነብ ቤት ይቆዩ ነበር።ሲያጣሩም ዘይነብ ጋር ሲቀመጡ እናታችን ዘይነብ ሁሌ ማር እንደምትሰጣቸው አወቁ።የዚህ ጊዜም በጋራ አንድ ውጥን ወጠኑ።ሁለታቸውም ቤት ሲመጡ "መጋፊር" የተሰኘ ጣፋጭና ጠረኑ መጥፎ የሆነን ፈሳሽ የሚያወጣ አትክልት እንደበሉ ለመንገር ተስማሙ።
ሰይዳችንﷺ የሐፍሳና የዓኢሻህ ቤት በገቡበት ሰዓት ሁለቱም "የመጋፊር" አትክልት እንደበላ ሰው አይነት ጠረን እንደተሰማቸው ገለፁ።
ሰይዳችንምﷺ:-"አይደለም! ዘይነብ ማር አጠጥታኝ ነው።"ሲሉ ገለፁ።ነገር ግን ነገሩ ከአንድም ሁለት ሰው ስላነሳው ጥርጣሬ ገባቸው።
በቀጣዩ ቀንም ዘይነብ ቢንቱ ጀሐሽ ቤት ከገቡ በኃላ ማር እንደማይበሉ በመግለፅ ራሳቸውን ቆጠቡ።

ይህ ክስተት ከሴቶች ተፈጥሯዊ የቅናት ባህሪ አንፃር ሲታይ ተራ ነገር ነው።በሺህ ቤቶችም የሚከሰት የተለመደ ተግባር ነው።ነገር ግን ቁርአን ይህን ጉዳይ እንደ ተራ ነገር አልተወውም።ይህ እና መሰል ተግባር ከሰይዳችንﷺ  ጋር ፈፅሞ መደረግ የሌለበት መሆኑን አጥብቆ ገለፀ።የምዕምናን እናት የሆኑትን ዓኢሻህና ሐፍሳህን የሚወቅስ አንቀፆችም ወረዱ።በአንቀፆቹም ከዚህ ተግባራቸው የማይመለሱ ከሆነ አሏህ፣ጂብሪል፣ሌሎች መልአክት እንዲሁም ደጋግ ምዕመናን ረዳቱ ከሆኑት ሰው ጋር ፀብ እንደገቡ ገለፀ።

إِن تَتُوبَا إِلَى اللَّهِ فَقَدْ صَغَتْ قُلُوبُكُمَا ۖ وَإِن تَظَاهَرَا عَلَيْهِ فَإِنَّ اللَّهَ هُوَ مَوْلَاهُ وَجِبْرِيلُ وَصَالِحُ الْمُؤْمِنِينَ ۖ وَالْمَلَائِكَةُ بَعْدَ ذَٰلِكَ ظَهِيرٌ

ወደ አላህ ብትመለሱ ልቦቻችሁ በእርግጥ ተዘንብለዋልና (ትስማማላችሁ)፡፡ በእርሱም ላይ ብትረዳዱ አላህ እርሱ ረዳቱ ነው፡፡ ጂብሪልም ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ ረዳቶቹ ናቸው፡፡

ይህን ክስተት በደምብ አስተውል።የሁሉ በቂ የሆነው የፍጡራን ሁሉ አምላክ የሆነው አሏህ፤እንዲሁም የመልአክት አለቃ የሆነው ጂብሪልና ደጋግ የአሏህ ባሪያዎች በአንድ ጎን፤ዓኢሻህ እና ሐፍሳህ ደግሞ በሌላ ጎን እንደሚያደርግ የተገለፀው ይህ ክስተት በብዙሐን ቤቶች የሚከሰትና እንደተራ የሚታይ ክስተት ነው።

ይህ ጥብቅና ዛቻን ያዘለ መለኮታዊ መልእክት የርሳቸው ክብርና ልቅና ምን ያክል የከበደ እንደሆነ የሚገልፅ ነው።የሳቸው ስብእና ድምበር ለማድረግ በሚከብድ መልኩ እጅጉን የተለየ መሆኑ በዚህ አንቀፅ ይታያል።ለርሳቸው ክብር የሰማያት ግርዶሽ ተገልጦ ጅብሪልን ያንቀሳቀሰና እስከ እለተ ትንሳኤ ድረስ የሚነበብን አናቅፅት ወርደዋል።ትንሽ አድርገን ያየናት "የማር ጠብታ" ይህን ከፈጠረ፤የእሳቸውን ትዕዛዝ የሚያጣጥል፤ክበራቸውን የሚዳፈር እንዲሁም አባትና እናቱ ቢገለፁበት በሚከፋው እጅግ የወረደ ቃላት የሚገልፅ ሰው ቦታው የት ይሆን?

ኢማም አዝ-ዘመኽሸሪይ አንቀፁን ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ።
" ኃያሉ አምላካችን አሏህ ብቻውን በቂ ከመሆኑ ጋር ከርሱ በኃላ፤ጂብሪልና ደጋግ አማኞች እንዲሁም  የቁጥራቸው ብዛት፤ሰማያትን ያጣበቡ መልአክት እርሱን በጠላ ሰው ላይ አንድ ሆነዋል።ታዲያ ይህ ሁሉ ረዳት ያለው ሰው የሁለት እንስቶች በሐሳብ ማበር ምን ሊያደርገው ይችላል?"

محمد بشر وليس كالبشر
بل هو ياقوتة والناس كالحجر

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ጥሩ የሩሕ ጓደኛ መፈለግ በጣም ጥሩ ነገር ነው። ጥሩ ጓደኛ መሆን ደግሞ ግዴታ ነው።
"ለወላጆች በጎ መዋል ትላልቅ ወንጀሎችን ያስምራል"

ኢማም አህመድ ኢብኑ ሀንበል ቀደሰላሁ ሩሁሁ
"እውቀት ሁሉም ሊያገኘው ማይችል የአላህ ስጦታ ነው "
ኢማሙ አህመድ
"በድህነት ላይ ሰብር ማረግ ታላላቆች እንጂ ማያገኙዋት ደረጃ ነች"

ኢማሙ አህመድ ኢብኑ ሀንበል
"በሰደቃ ላይ መመፃደቅ ሀራም ነው
ምንዳውንም ያበላሻል"

ኢብኑ ነቂብ አል ሻፍዒይ ረሂመሁሏህ