Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
486 subscribers
3.15K photos
218 videos
46 files
2.15K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
በህንድ የአእምሮ ጤና እክል ያለባት ወጣት መለኮታዊ ኃይል አላት በሚል በመመለክ ላይ ትገኛለች

በታሚል ናዱ ግዛት የሂንዱ ከተማ በሆነችው ቲሩቫናማላይ ውስር ሚስጥራዊ ኃይል አላት የተባለችው ግለሰብ የአእምሮ የጤና ችግር ላይ ብትሆንም የሕንድ ማህበረሰብን ግን እያመለካት ይገኛል።

ህንዳውያን በርከት ያሉ አምላክ እና አማልክቶች ያሏቸው ሲሆን የሂንዱ አማልክቶች ሚስጥሮች እና እውነተኛ ህይወት ላይ በርካታ አወዛጋቢ ጉዳዮች ይነሳሉ። ከነዚህ መካከል ቶፒ አማ የምትባለው ኮፍያ የምታደርገው ሴት ብዙ ጊዜ ‘ሲድዳ’ እየተባለች በቅፅል ስም ትጠራለች። ይህችው ግለሰብ አዳኛችን ናት በማለት መመለክ ላይ ትገኛለች። አማኞች ፍፁም የሆነች ብሩህ ፍጡር ናት ይሏታል። ነገር ግን ዓለማዊ አመለካከት ላላቸው ሰዎች የህክምና እርዳታ የምትፈልግ የአእምሮ እክል ያለባት ሴት ናት።

ለአማኞች የሚታየቸው በቲሩቫናማላይ ጎዳናዎች ውስጥ ስትንቀሳቀስ ማንም በማይረዳው ጥንታዊ የታሚልኛ ቋንቋ ስትናገር ሲያዩ፣ ሌሎች ደግሞ ቤት የሌላት ምስኪን ሴት ያለ አላማ ስትቅበዘበዝ እና ስታጉረመርም ትውላለች ይላሉ። ሁሉም ነገር የአመለካከት ጉዳይ በመሆኑ ልዩነቶች መስተናገዳቸው ግድ ሆኗል።ቶፒ አማ የቲሩቫናማላይ ምልክት ከመሆኗ እና ብዙ ተከታዮችን ከመሳቧ በፊት የነበራት ህይወት እንቆቅልሽ ሆኖ በመቆየቱ ለታዋቂነቷ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

ሁለት ወጥ ቃላቶችን እንኳን በአንድ ላይ አሰካክታ መናገር አለመቻሏን መለኮታዊ ኃይል ቢኖራት ነው ብለው ህንዳውያኑ እንዲያስቡ አስገዷቸዋል። በህንዳውያኑ የማህበራዊ ድህረ ገፅ ተጠቃሚዎች ዘንድ ቶፒ አማ ከተማዋን እየዞረች የጠጣችውን የቡና ትራፊ የተባረከ መስዋዕት ነው በማለት ሰዎች አንስተው ሲቀምሱ ይታያል። በሌላ በኩል ይህችኑ ሴት የአዕምሮ ጤና ችግር ያለባት ፣ የቆሸሸ ልብስ የለበሰች ፣ ሰውነቷ ከመታጠብ የራቀ እና በአንዳች እክል ውስጥ እንዳለች ማስተዋል ይችላል።

አንድ የኤክስ ተጠቃሚ ባጋራው ፅሁፍ አንዳንዶች በአእምሮ ህመም እየተሰቃየች ነው ብለው የሚያስቡ እና እርዳታ ትሻለች የሚል ሰዎች ቢኖሩም ስለ እርሷ ውዳሴ የሚያቀርቡና የሚዘምሩ በርካቶች መሆናቸውን ፅፏል።ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ ጥበቧ ካልተገለጠልህ እሷን ማግኘት የሚችሉት የታደሉት ብቻ ናቸው ሲሉም አማኞች ይደመጣሉ።

አስደናቂው ጉዳይ የአእምሮ እክል ላይ የምትገኘው ቶፒ አማ በአብዛኛው አምላኪዎቿን ችላ ብላ የእለት ውሎዋብ ስታሳልፍ አንዳች ምስጢራዊ ኃይል እየተገለጠላት ነው ብለው የሚያስቡ አሉ። በዚህም የተነሳ በሄደችበት ቦታ ሁሉ በርካቶች ይከተሏታል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal