Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
462 subscribers
3.03K photos
184 videos
46 files
2.1K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
#አንኳር_ዜናዎች!
▶️ አልቃሳም ብርጌዶች“ሙጃሂዲኖቻችን ከ “ኢሬዝ” በስተምዕራብ በጋዛ ሰርጥ የሚገኘውን የጽዮናውያን የእግር ሃይል ከርቀት በኢላማ ውስጥ አስገቡት!”ብሏል።

▶️ ክሬምሊን“የሩሲያ የአየር መከላከያ ዘዴን ወደ ሄዝቦላህ መላክን በተመለከተ በዎል ስትሪት ጆርናል ዘገባ ላይ የተነገረው ውሸት ነው” በማለት አጣጥሏል።

▶️ የተባበሩት መንግስታት በዌስት ባንክ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ እና አፋጣኝ እርምጃ ያስፈልገዋል ሲል አሳስቧል።ወሬብቻ!

▶️ የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ተኩስ በአስቸኳይ ማቆም እና ሰብአዊ እርዳታን በጋዛ ለሚገኙ ሲቪሎች ማስተላለፍ አስፈላጊ ነው ያለ ሲሆን፣ጋዛን በተመለከተ የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎችን ተግባራዊ እንድያደረግ እንጠይቃለን፣በተለይ የተኩስ አቁምን፣ ሰብዓዊ ቀውስን ለመፍታት እና የታፈኑትን መመለስን በተመለከተ ብሏል።
በተጨማሪም ግብፅ ፍልስጤማውያንን ወደ ሲና በማፈናቀል የፍልስጤምን ጉዳይ የመፍታት ዘዴን እንደማትቀበል አረጋግጣለች በማለት አክሏል።
በመጨረሻም ፍልስጤማውያንን ለማፈናቀል እና የፍልስጤም መንግስት ምስረታን ለማጥፋት የታቀደው ሴራ አስከፊ መዘዞችን የሚያስከትል ሲሆን በአካባቢው ያለውን ቀውስ የበለጠ ያሰፋዋል ሲል አስጠንቅቋል።

▶️ የኩዌት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጦርነቱን በአስቸኳይ ማቆምና የሰብአዊ እርዳታ ወደ ጋዛ ህዝብ እንዲገባ መፍቀድን በተመለከተ ከሩሲያ ጋር ተመሳሳይነት ያለው አቋም አለን ያለ ሲሆን፣400 ቶን ሰብአዊ እርዳታን የጫኑ 11 አውሮፕላኖችን በጋዛ ላሉ ወገኖቻችን ልከናል ብሏል።በመጨረሻም የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ ያለውን ጦርነት በተቻለ ፍጥነት ለማስቆም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል በማለት አሳስቧል።

▶️ የእስራኤል ጦር የኛ የምህንድስና ቡድን በጋዛ ሰርጥ የተገኙትን ዋሻዎች ለማፍረስ እየሰሩ ነው ብሏል!
አፍራሽ መሀንዲስ! 🙄

▶️ የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት እራሳቸውን እንድከላከሉ 6 ሚሊየን የጽሁፍ መልእክቶችን እና 1.2 ሚሊየን በራሪ ወረቀቶችን በጋዛ ለሚገኙ ሲቪሎች አሰራጭተናል ብሏል!
ድንቄም አዛኝ! 😎

▶️ አል-ቃሳም ብርጌዶች ከቤቴላሂያ በስተሰሜን ምዕራብ በሚገኝ ሕንፃ ላይ በቲፒጂ ዛጎሎች የተጠለፈውን የጽዮናውያን ኃይል ኢላማ አድርገናል ብሏል።

▶️ CNN በመረጃ የተደገፈ ምንጭን ጠቅሶ እንደገለጸው የአሜሪካ ባለስልጣናት ነዳጅ ለሰብአዊነት ሲባል ወደ ጋዛ እንዳይገባ ስጋት አድሮባቸዋል ያለ ሲሆን፣ባይደን እና ከፍተኛ አማካሪዎቹ የአለም ማህበረሰብ ቁጣ እየተባባሰ በመምጣቱ እስራኤልን ወታደራዊ ግቦቿን የማሳካት ችግር እንዳለባት አስጠንቅቀዋል በማለት ዘግቧል።

▶️ አል ቁድስ ብርጌዶች በ"ሱፋ"፣"ሁሊት" እና "ኒር ሻቅ" የተሰበሰበውን ወራሪ ሀይል በሚሳኤል ፈንጅ ደበደብናቸው በማለት አስታውቋል።

▶️ NBC በዩኤስ ባለስልጣናት ላይ ባወጣው መረጃ እስራኤል ጦርነቱን እንዴት እየፈፀመች እንደሆነ በBiden አስተዳደር ውስጥ ባሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል ያለው ስጋት እየጨመረ ሲሆን፣የጋዛ ሰብአዊ ቀውስ እየተባባሰ ሲሄድ የባይደን አስተዳደር በእስራኤል ውስጥ የመቆጣጠር ችሎታ ያሳስበዋል ብሏል።

▶️ አልቃሳም ብርጌዶች ከኤሬዝ በስተ ምዕራብ በነበሩ የጠላት መኪናዎች በጋዛ ኤንቨሎፕ ውስጥ በተሰበሰቡ ከባድ የሞርታር ዛጎሎች ደበደብን ሲል፣ ሒዝቦላህ በበኩሉ በደቡብ ሊባኖስ ርሜይሽ ከተማ ትይዩ በሚታት ቦታ አቅራቢያ በተሰበሰቡ የጠላት ወታደሮች ላይ ኢላማ ያደረግን ሲሆን በጦር ሠራዊታቸው ላይ ጉዳት መድረሱን አረጋግጠናል ብሏል!
እነዚህን እርኩሳኖች በሏቸው አቦ አሏህ ይርዳችሁና!

▶️ የቱርክ መንግስታት ድርጅት #የመጨረሻ ባለው መግለጫው አስቸኳይ የተኩስ አቁም ተፈፃሚ እንድሆን፣ለሲቪሎች ጥበቃ እንድደረግ እና በመላው ጋዛ ሰብአዊ እርዳታ እንዲሰጥ እንጠይቃለን ብሏል።

▶️ ፑቲን ማንኛውም ኖርማል ሰው በጋዛ ውስጥ በደም የተሸፈኑ ሕጻናት ምስሎችን በማየቱ እጅግ ያዝናል፣ይበሳጫልም በማለት የእስራኤልን፣አሜሪካንና ምዕራባዊያንን ጭራቅነት ጠቁሟል።

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በምስራቅ አዘርባጃን ግዛት አደጋ በደረሰባት ሄሊኮፕተር ላይ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና ከበርካታ ባለስልጣናት ጋር #የመጨረሻ እይታ!
#አልጀዚራ

ኢና ሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን !

በጎንደር በግፍ የተገደሉት የመስጂድ ኢማም ሸይኽ ሲራጅ አብድሬ እኚህ ናቸዉ!

በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ደንቢያ ወረዳ አየንባ ቀበሌ የመስጂድ ኢማም የሆኑት ሸይኽ ሲራጅ አብድሬ በግፍ ተገድለዋል::

አላህ(ሱ.ወ) ይዘንላቸዉ። አሚን🤲

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal