TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Amhara

#እቅድ፦ 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመዝገብ

#እስካሁን_የተመዘገቡት ፦ 2,937,556 ተማሪዎች

በአማራ ክልል ለዘንድሮ ዓመት ትምህርት ይመዘገባሉ ተብለው ከታሰቡት 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎች መመዝገብ የተቻለው 2,937,556 ተማሪዎችን እንደሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ይህ ከቅድመ መደበኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ሲሆን ካለፉት ዓመታት ሲነፃፀር እቅዱ አጥጋቢ እንዳልሆነ አመልክቷል።

የሚጠበቀውን ያህል ተማሪዎች እንዳይመዘገቡ ከሆነበት ምክንያቶች አንዱ በክልሉ ውስጥ በልዩ ልዩ ቦታዎች ያለው የትጥቅ ግጭት መሆኑ ተነግሯል።

አንዳንድ ዞኖች እስካሁን ጭራሽ ምዝገባም ያልጀመሩ ሲሆን እነዚህም የምዕራብ አማራ አካባቢዎች ፣ ምስራቅ ጎጃም ፣ ምዕራብ ጎጃም ደብረማርቆስ ፣ ሰሜን ጎጃም እንደሆኑ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

በክልሉ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ተፅእኖ አሳድሮብናል ያለው ትምህርት ቢሮ አንፃራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች ላይ የተማሪ ምዝገባ መከናወኑን አመልክቷል። አንዳንድ ዞኖችም የተሻለ አፈፃፀም አስመዝግበዋል ሲል አክሏል።

አሁንም የምዝገባ ቀኑ ያልተገደበ ሲሆን ዞኖች ጎን ለጎን የመማር ማስተማር ስራውን እና ምዝገባውን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው ማለቱን ቪኦኤ ዘገቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#Amhara #Oromia

ከ5 ዓመታት በላይ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ሳቢያ ወደ አማራ ክልል በመሸሽ ተጠልለው የሚገኙና ገና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ተፈናቃዮችን ኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ቄየዎቻቸው የመመለስ ሥራ ለመስራት ሰሞኑን ባህር ዳር ከተማ ላይ ተደረገ በተባለ የጋራ ውይይት ስምምነት ላይ መደረሱን የሁለቱም ክልሎች የኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ፣ "የታሰበው በጸጥታ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ከክልላችን ተፈናቅለው አማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮችን መልሦ የማቋቋም ሥራ ነው" ብለዋል።

አክለውም፣ "በጸጥታ ምክንያት ከኦሮሚያ ወደ አማራ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎችን ለመመለስ አብይ ኮሚቴው በሚቀጥለው ሳምንት ተገናኝቶ መሪ ዕቅዱን ያወጣል" ሲሉ አስረድተዋል።

የአማራ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድወሰን አሰፋ በበኩላቸው፣ "ሁለታችን ተቀናጅተን ለመስራት የሚቀጥለው ሰኞ ቀጠሮ ይዘናል። በዛ መሰረት ታይም ቴብሉን እናስቀምጣለን  መቼ ይመለሱ? መቼ ወደዛ እናጓጉዝ? የሚለው በቅዳችን ነው የሚመለሰው" ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ለአብነትም በሰሜን ሸዋ ዞን #ደራ_ወረዳ ከአሥር በላይ ቀበሌዎች፣ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ታጣቂ ቡድኑ በንጹሐን ላይ ግድያ እየፈጸመ መሆኑን ነዋሪዎች እንደገለጹ፣ ይህ በእንዲህ እንያለ ተፈናቃዮች ቢመለሱ ለደኅንነታቸው ምን ዋስትና ይኖራቸዋል ? የሚል ጥያቄ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርቧል።

አቶ ወንድወሰን ለዚሁ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " የጸጥታ ችግር እያለ እኛም እዲመለሱ አናደርግም። በኦሮሚያ ክልል በኩልም የጸጥታ ችግሩ አስተማማኝ ደረጃ ሳይዘልቅ ተመላሾቹ ለዳግም ችግር የሚጋለጡበትን  መገድ ሁለታችንም አንሰራም" ብለዋል።

አክለውም፣ " ሰሜን ሸዋ አካባቢ ያለው የጸጥታ ችግር ወጣ ገባ የሚል ነው እናተም እደምታውቁት አማራ ክልልም የጸጥታ ችግር አለ። ይህን በዘላቂ መፍትሔ ይሰጠዋል ብለን ነው የምናስበው፣። ሆሮ ጉድሩ ያለውም ቢሆን አሸባሪው ሸኔ  ወጣ ገባ እያለ ችግር ሊፈጥር ይችላል " ብለው፣ በቅድሚያ የጸጥታውን ችግር የምረጋግጥ ሥር እንደሚከናወን አስረድተዋል።

አቶ ሀይሉ አዱኛ በበኩላቸው፣ " የጸጥታው ችግር በተረጋገጠባቸው አካባቢዎች የማስፈሩም መልሶ የማቋቋሙም ሥራ ይሰራል። የጸጥታ ችግር ያልተረጋገጠበት አካባቢዎች ደግሞ እያረጋገጥን ነው መልሰን የምናቋቁመው፣ ዛሬ መልሰን ችግር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ በተሞላበት አኳኋን ነው የሚሰራው " ሲሉ ተናግረዋል።

የሁለቱም ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በገለጹት መሠረት፣ ተፈናቃዮችን ወደነበሩበት ኦሮሚያ ክልል ከመመለስ በፊት ይህን ሥራ ለማስኬድ የተዋቀረው አብይ ኮሚቴ መረጃዎችን ያጠራል።

ያንብቡ - https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-10-27

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአማራ ክልል የሚገኙ የ10 ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዜዳንቶች በቅርቡ ከክልሉ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ አኳያ የመማር ማስተማር ሂደትን ማስቀጠል ይቻል እንደሆነ ውይይት እንዳደረጉ ቪኦኤ ዘግቧል። የክልሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዋና ፀሀፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል፤ የዩኒቨርሲቲዎቹ ፕሬዜዳንቶች ባደረጉት ውይይት ወቅታዊው የክልሉ የፀጥታ ችግር በቅርቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ…
#Amhara

በአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዋና ጸሐፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን፤ የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎችን አቋም በተመለከተ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የነበረው መረጃ " #የተሳሳተ ነው " አሉ።

ከሰሞኑን በአማራ ክልል ስላሉ ዩኒቨርሲቲዎች ምንድነው የተባለው ?

ከቀናት በፊት ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ የፎረሙን ዋና ጸሐፊ የሆኑትን ዶ/ር አስማረ ደጀንን ዋቢ በማድረግ ባወጣውና ቲክቫህ ኢትዮጵያም ባጋራው ዘገባ ፤ በአማራ ክልል የሚገኙ የ10 ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች ከክልሉ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ አኳያ የመማር ማስተማር ሂደትን ማስቀጠል ይቻል እንደሆነ ውይይት ካደረጉ በኃላ ሁኔታው #በቅርቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማስቀጠል የሚያስችል እንዳልሆነ የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

በተጨማሪ ዶ/ር አስማረ ደጀን ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል፤
*  ተማሪዎች ገብተው ግጭቶች በሚመጡበት ጊዜ ዩኒቨርሲቲዎች ኃላፊነት እንደማይወስዱ፤

* ዩኒቨርሲቲዎች ለ2016 የሚሆን የምግብ አቅርቦት ማዘጋጀት የነበረባቸው ቢሆንም አቅራቢዎቹ ከቦታ ቦታ ፤ ምርት ካለበት ቦታ ሄደው ተዘዋውረው መግዛት ስላልቻሉ የምግብ ግብአቶች በጠቅላላው ተማሪን ሊያስጠራ የሚችል እንዳልሆነ ገልፀዋል።

ፎረሙ ትምህርት ሚኒስቴር " ለ2016 ትምህርት በአሁን ሰዓት ተማሪዎችን ጥሩ እያለ ነው " ብሎ ለፀጥታው ኃላፊነት የሚወስድ አካል ከሌለ ይህን ማድረግ #እንደሚያስቸግር ነው የገለፀው።

ከዚህ ባለፈ የፎረሙ አባልና የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ፤ በአካባቢው የቀጠለው አለመረጋጋት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ እንደማያስችል ከተስማሙት የፎረሙ አባላት እንደሆኑ ገልጸዋል።

ያለው ሁኔታ ካልተሻሻለ በስተቀር አሁን ባለው ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ግቢ ውስጥ ተማሪ ማስገባት በእጅጉ ፈታኝ እንደሚሆንና ለልጆችም ደህንነት በጣም አስጊ መሆኑን ፕሬዜዳንቱ ለጣቢያው ተናግረዋል።

ይህ መረጃ ከተሰራጨ ከቀናት በኃላ የፎረሙ ዋና ጸሐፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዛሬ በሰጡት ቃል " ሰሞኑን የተሰራጨው መረጃ በአማራ ክልል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ያልተባለና ስህተት ነው " ብለዋል።

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ለመቀበል አመች ሁኔታዎችን እየተጠባበቁ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በክልሉ የሚገኙ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን መጥራት መጀመራቸውንም ገልጸው፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች ጥሪ ማስተላለፉን ለአብነት አንስተዋል፡፡

"አብዛኞቹ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን እየጠሩ ነው" ያሉ ሲሆን " ብዙ ተማሪዎችን በአንድ ጊዜ ለመጥራት ግን የግብዓት ችግር ለተቋማቱ እንቅፋት ሆኗል " ብለዋል።

ዶ/ር አስማረ፤ በክልሉ በተፈጠረው የሰላም እጦት ግብዓት አቅራቢዎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ለማቅረብ የተቸገሩ ቢሆንም ዩኒቨርሲቲዎች የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየሠሩ መሆኑን አሳውቀዋል። በየአካባቢው ያሉ አቅራቢዎች ግብዓት እንዲያቀርቡ እየተደረገ ነው ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎችን ተቀበሉ በሚልበት ጊዜ የማይቀበሉበት ምክንያት እንደሌለም ገልጸዋል።

" ክልሉ ያጋጠመው የጸጥታ ችግር እየተሻሻለ ከመጣ ተቋማቱ ተማሪዎቻቸውን ወዲያው ይጠራሉ፤ ተማሪዎችን አይጠሩም የተባለው ስህተት ነው፤ አልተባለምም " ሲሉ ተናግረዋል።

አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ግብዓት ለማግኘት ከመቸገራቸው ውጭ የመማሪያ ክፍሎችን አጽድተዋል፣እድሳት የሚያስፈልጋቸውንም አድሰው ለትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ዝግጁ ሆነዋል ሲሉ ለክልሉ ሚዲያ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara በአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዋና ጸሐፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን፤ የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎችን አቋም በተመለከተ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የነበረው መረጃ " #የተሳሳተ ነው " አሉ። ከሰሞኑን በአማራ ክልል ስላሉ ዩኒቨርሲቲዎች ምንድነው የተባለው ? ከቀናት በፊት ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ የፎረሙን ዋና ጸሐፊ የሆኑትን ዶ/ር አስማረ ደጀንን ዋቢ በማድረግ ባወጣውና ቲክቫህ…
#Amhara

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ2ኛ እስከ 6ኛ ዓመት የህክምና ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ ከሆኑ ረጅም ግዜ እንደሆናቸው በመግለፅ መፍትሔ እንዲፈለግላቸው ጥሪ አቀረቡ።

ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት በአማራ ክልል በተፈጠረው ችግር ለሦስት ወራት (ለ12ኛ ክፍል ፈተና 1 ወርን ጨምሮ) ቤት መቆየታቸውን ገልጸዋል።

"እስካሁን ማንም ስለእኛ የሚናገር የለም፣ ብዙ እየተሰቃየን ነው" ያሉት ተማሪዎቹ፤ "በተስፋ መቁረጥ የተነሳ የተለያዩ አላስፈላጊ ነገሮች ውስጥ እየገባን ነው" ብለዋል።

ተማሪዎቹ፦
-በኮቪድ-19 ምክንያት ለ11 ወራት፣
-በትግራይ ጦርነት ለ3 ወራት፣
-በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና አንድ ወር፣
-አሁን ደግሞ ለሦስት ወራት ቤት መቆየታቸውን ገልጸዋል።

"በሰባት ዓመት መመረቅ የነበረብን፥ አሁን በግቢው ከዘጠኝ ዓመት በላይ እንድንቆይ ተደርገናል " ብለዋል።

" ጎንደርና ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ አቻ ጓደኞቻችን ትምህርታቸውን ቀጥለዋል፣ እኛ በጣም ወደኋላ ቀርተናል" ሲሉም ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ከፍተኛ የስነ-ልቦና ቀውስ ውስጥ መግባታቸውንና ብዙ እየተሰቃዩ መሆኑን ያስረዱት ተማሪዎቹ፤ የሚማሩት ትምህርት እንደሌሎች ዲፓርትመንቶች ለአንድ ቀን እንኳን ሊካካስ የሚችል እንዳልሆነ ገልጸዋል።

የህክምና ስርዓተ ትምህርት ልዩ በመሆኑ ጉዳያቸው በልዩ መልኩ እንዲታይ፣ ከተቻለ ቶሎ ወደነበሩበት ዩኒቨርሲቲ እንዲመለሱ፣ ካልሆነም እንደ ትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደሌሎች የተሻለ ሠላም ወዳለባቸው ዩኒቨርሲቲዎችቦታ ተመድበው ትምህርታቸውን እንዲጨርሱ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎችን ጥያቄ ይዞ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አመራሮችን ለማነጋገር ባለፉት ሳምንታት ጥረት አድርጓል።

ስማቸውን የማንገልፀው የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር በተማሪዎች የተነሳው ችግር በእርግጥም ትክክል እንደሆነ አረጋግጠውልናል።

ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በጉዳዩ ላይ አለመወያየቱንና እስካሁን ምንም የተላለፈ ውሳኔ አለመኖሩን ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሴኔትም ሆነ ትምህርት ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ የሚሰጡትን ምላሽ ያደርሳችኋል።

በሌላ በኩል፤ በክልሉ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ሌሎች ተማሪዎች የሚማሩባቸው ተቋማት ጥሪ ለማድረግ ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነ በሚዲያ ከማስነገር በዘለለ እስካሁን ጥሪን በተመለከት ምንም ፍንጭ እንደሌለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ፤ በሌሎች ክልሎች የሚማሩ ጓዶቻቸው ትምህርት እየተከታተሉ ቢሆንም እነሱ ግን እስካሁን ሳይጠሩ የዓመቱ 3ኛ ወር መግባቱን አመልክተዋል።

" በበፊቱ የሰሜኑ ጦርነት ስቃያችንን ያየን እንዲሁም 1 አመት የተጨመረብን እጅግ አሳዛኝ ተማሪዎች ነን " ያሉት ተማሪዎቹ " በቅርቡ በአማራ ክልል በተከሰተው ጦርነት ሌላ ችግር ውስጥ ገብተናል " ሲሉ አስረድተዋል።

ሌላ 2ኛ አመት እንዳይጨመርብን የክልሉን ሰላም ተረጋግጦ ወደ ትምህርት ገበታችን እንድንመለስ ይደረግ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በጦርነት ውስጥ ላሉ ጓደኞቻቸውም ተጨማሪ አመት ተጨምሮ ችግርና ብሶት ውስጥ ገብተው ተስፋ እንዳይቆርጡ ክልሉ ሰላም እንዲሆን ጥረት እንዲያረግ ጥሪ አቅርበዋል።

የትምህርት ዘመን ካሌንደር መዛባት የሚፈጥረውን ቀውስ ባለፉት ዓመታት ታይቷል ያሉት ተማሪዎቹ በክልሉ ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ ለማድረግ ካልቻሉ ሌላ መፍትሄ ይፈለግ ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎችን ቅሬታ በተመለከተ የሚመለከታቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አካላት ለማነጋገር ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም ለጊዜው አልተሳካም።

@tikvahethiopia
#Amhara

“ ወደ 270 በሚደርሱ ተቋማት መድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎቻቸው ላይ ዘረፋ ተከስቷል ” - አቶ አብዲልከሪም መንግስቱ

በአማራ ክልል በየወቅቱ በሚያገረሸው የፋኖ እና የመከላከያ የተኩስ ልውውጥ ሳቢያ አብዛኛዎቹ ነፍሰጡሮች ወደ ህክምና ተቋማት ሄደው አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውን፣ በጤና ተቋማት ላይም የንብረት ዘረፋና ውድመት መፈጸሙን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከክልሉ ጤና ቢሮ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ በአሁኑ ኮንፍሊክት እኛ የምናውቀው ወደ 270 በሚደርሱ ተቋማት መድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎቻቸው ላይ ዘረፋ ተከስቷል። በኢንተርናል ኮፍሊክቱ ማለት ነው። ይሄ ዳሜጅ ሳይሆን የመድኃኒትና የህክምና መሳሪያ መወሰድ ነው ” ብለዋል።

ዘረፋው የተፈጸመው ግጭት በሚስዋልባቸው የተለያዩ አካባቢዎች መሆኑን፣ ክልሉ ባለው መረጃ መሠረት እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ) ድረስ ወደ 7 የሚሆኑ የጤና ተቋማት መውደማቸውንም አክለዋል።  

በሌላ በኩል ፤ በክልሉ ነዋሪዎች በሚስተዋለው የጸጥታ መደፍረስ ሳቢያ እናቶችና ሕጻናት ሕክምና ማግኘት እንዳልቻሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል።

ቅሬታውን በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳላቸው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ከብዱልከሪም በበኩላቸው “የመንገድ መዘጋጋቶች አሉ። እንዲሁም ደግሞ ማህበረሰቡ ሥጋት ውስጥ ከመኖሩ ጋር ተያይዞ፣ ከግጭቱ ጋር ተያይዞ እናቶች በፈለጉት ሰዓት ጤና ጣቢያ ሂዶ ለመውለድ የመቸገር ነገር አለ” ብለዋል።

አክለውም፣ ሕጻናትም በተመሳሳይ በፈለጉት ጊዜ ክትባት ማግኘት እንዳልቻሉ፣ ጤና ኤክስቴንሽኖች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ማህበረሰቡን ተደራሽ ማድረግ እንዳልቻሉ አስረድተዋል።

“ እናቶች በጤና ተቋም ከመውለድ አኳያ ከ50% ያልበለጠ ነው። አብዛኛዎቹ አሁን ቤት ውስጥ የመውለድ ነገር አለ ” ያሉት ኃላፊው፣ ከፍተኛ በሆነ የደም መፍሰስ ምክንያት እናቶች ለሕልፈተ ሕይወት እንደሚዳረጉ፣ ቁጥራዊ መረጃ ለመስጠት ግን ጥናት ማድረግ እንደሚጠይቅ ተናግረዋል።

በጸጥታው ችግር ሳቢያ ወደ ጤና ጣቢያ ሂደው መውለድ ያልቻሉ ነፍሰጡሮች ምን ያህል ናቸው ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ  “ በጤና ተቋማት እየወለዱ ያሉ እናቶች በአንደኛው ሩብ ዓመት 45 ፐርሰንት ናቸው ” ብለዋል።

“ ስለዚህ ቀሪው 65 ፐርሰንት የሚሆነት እናቶች ከችግሩ ጋር በተያያዘ በቤታቸው እየወለዱ ያሉበት ሁኔታ እንዳለ ሪፓርቶቻችን ያሳያሉ ” ሲሉም አክለዋል።

ክልሉ ካሉት የጤና ተቋማት የሕክምና አገልግሎት እየሰጡ ያሉት ምን ያህል ናቸው ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ በክልሉ ፦
* ከ100 በላይ ሆስፒታሎች፣
* 917 ጤና ጣቢያዎች
* ከ3500 በላይ ጤና ኬላዎች፣
* ከ4000 በላይ የግል ጤና ተቋማት እንዳሉ፣ ግጭቱ ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ አልፎ አልፎ የአገልግሎት መቆራረጥ እንደሚያጋጥም፣ ሙሉ ለሙሉ የተቋረጠ አገልግሎት ግን እንደሌለ አስረድተዋል።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ ነው።

@tikvahethiopia
#Amhara #Merawi

በአማራ ክልል ፤ በየጊዜው በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በመንግሥት የፀጥታ ኃይል መከላከያ እና በ " ፋኖ " ታጣቂ ኃይሎች መካከል ግጭቶች ይደረጋሉ።

በእነዚህ ግጭቶችም በሁለቱም በኩል ከሚሞተው የግጭቱ ተካፋይ ባለፈ ንፁሃን ሰዎች ሰለባ እየሆኑ እንዳለ በተደጋጋሚ ተገልጿል።

ምንም እንኳን #መንግሥት ፤ " ከእውነታው ያፈነገጠ እና ሚዛናዊነት የጎደለው " ብሎ ቢያጣጥለውም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮኒሽን  (#ኢሰመኮ) ይፋ አድርጎት በነበረው ሪፖርት በክልሉ ፦

- የአንድ ዓመት ከሰባት ወር #ሕፃንን ጨምሮ በርካታ ሲቪል ሰዎች በድሮን መገደላቸው / የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው።

- በከባድ መሣሪያ ድብደባ ምክንያት #ሲቪል_ሰዎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት መድረሱ።

- በመንግሥት የጸጥታ ኃይል አባላት #ከሕግ_ውጪ የሆኑ ግድያዎች እንደሚፈፀሙ።

- ከዚህ ቀደም ግጭቶች በተካሄደባቸው አካባቢዎች የመንግሥት የጸጥታ አካላት በመንገድ ላይ ወይም ቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ ከያዟቸው በርካታ ሲቪል ሰዎች ውስጥ ፦
" ፋኖን ትደግፋላችሁ "
" ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ "
" መሣሪያ አምጡ "

" የተኩስ ድምጽ ስለተሰማበት አቅጣጫ መረጃ ስጡ " በሚልና ይህንን በመሰሉ ምክንያቶች ከሕግ ውጭ የሆኑ በርካታ #ግድያዎች መፈጸማቸውን በይፋ ማሳወቁ አይዘነጋም።

ከሰሞኑን ዳግሞ በሰሜን ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል፣ ሰኞ ጥር 20/2016 ዓ/ም የነበረውን ውጊያ ተከትሎ በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ገለጻ ፤ በሰሞኑ ተኩስ እሳቸው የሚያውቋቸው ብቻ 15 ወጣቶች መገደላቸውን ተናግረዋል።

ከዚህም ባለፈ ግን ፤ " የሟቾቹን ቁጥር በዚህ ወቅት ለመግለጽ መሞከር የጥቃቱን አድማስ ያሳንዋል እንጂ አይገለጸውም" ብለዋል።

እኚሁ ነዋሪ በግፍ የተገደሉ ንጹሐን ሰዎችን ቁጥር በሂደት እንጂ አሁን ሁሉንም ማወቅ እንደማይቻል ገልጸው ፤ " የዚህ ህዝብ ጭፋጨፋ ግን መቼ ነው የሚያበቃው? " ሲሉ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች፣ የሆስፒታል ሰዎችና የአይን እማኞች በከተማው ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

አብዛኞቹ ነዋሪዎች ግድያው የተፈጸመው በቤታቸው እና በመንገድ ላይ በተገኙ ሰላማዊ ሰዎች ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

አንድ የህክምና ባለሙያ 13ት ሰዎች ከአስፓልት ዳር መገደላቸውን እንደሚያውቁ ተናግረው በአጠቃላይ በከተማዋ በዚያ ዕለት 85 ሰዎች መገደላቸውን አመልክተዋል።

አንድ የአይን እማኝ በርካታ ቀብሮች ላይ መገኘታቸውን ጠቅሰው የሟቾችን ቁጥር " ከ100 በላይ ነው " ብለዋል። ጥቃቱ በተፈጸመ ማግስት ጠዋት ላይ 48 አስከሬን መቆጠራቸውን ተናግረው ፤ " ከማርዘነብ ሆቴል እስከ በረድ ወንዝ ድረስ ግራ እና ቀኝ አስከሬን ብቻ ነበር " ብለዋል።

የሟቾችን ቁጥር 115 ገደማ የሚያደርሱ አንድ የዐይን እማኝ ደግሞ መከላከያ ከተማዋን ከተቆጣጠረ በኋላ ስታዲየም እና ጤና ጣቢያ በተባሉ ሰፈሮች " ከ6 ዓመት ህጻን እስከ 75 ዓመት አዛውንት " ድረስ ግድያ ተፈጽሟል ብለዋል።

የሆስፒታል ሠራተኛ የሆኑት የዐይን እማኝ በከተማዋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ6 ወር ነፍሰ ጡርን ጨምሮ 25 ሰዎች ቆስለው መጥተው " የተረፈ የለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" 24ቱ ሆስፒታል የመጡት ሞተው ነው። አንዲት የ6 ወር ነፍሰ ጡር ሴት ከነ ነፍሷ መጥታ ሆስፒታል እንደደረሰች አርፋለች። አጠቃላይ 25 ነበር የመጡት " ብለዋል።

ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ፤ #በመርዓዊ_አስተዳደር ህንጻ ውስጥ በነበሩት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የፋኖ ታጣቂዎች ሰኞ ጠዋት ድንገተኛ ጥቃት ፈፀመው እንደነበርና ለዚህ ምላሽ " የበቀል እርምጃ " በመወሰዱ ነው ለበርካታ ሰዎች ግድያ ምክንያት የሆነው ብለዋል።

ስለ ግድያው ምን ምላሽ እንዳለቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ  መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር)፣ " ስብሰባ ላይ ነኝ መልሸ ልደውል " ብለዋል።

መንገሻ (ዶ/ር) ይህን ያሉት እንዲያብራሩ የተፈለገውን ጥያቄ በዝርዝር ከሰሙ በኋላ ሲሆን፣ በድጋሚም ስልክ ሲደወል ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

እንዲሁም፣ " እባክዎ ስልክዎን ያንሱና በኮሚዩኒኬሽን በኩል ያለውን የመርዓዊ ጉዳይ ማብራሪያ በመስጠት ኃላፊነትዎን ይወጡ " የሚል የፅሑፍ መልዕክት (SMS) ቢላክላቸውም ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል።

በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
* የክልሉ የኮሚዩኒኬሽን ምክትል፣
* የክልሉና የሰሜን ጎጃም ዞን ኮማንድ ፖስት፣
* የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ስለጉዳዩ ምን ምላሽ እንዳለቸው ለማወቅ እና ሃሳባቸውን ለማካተት ስልክ ቢደውልም ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ኮሚሽን ( #ኢሰመኮ ) ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ፤ " መረጃው ደርሶናል (የመርዓዊ ጉዳይ) ። እያረጋገጥን ነው " ብለዋል።

አክለው ፣ "የጸጥታ ጉዳይ ስለሆነ ትንሽ መንቀሳቀስና መረጃ መሰብሰብ አስቸጋሪ ሊሆን ስለሚችል ሊዘገይ ይችላል። ግን እያጣራን ነው" ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia
#Amhara

ዛሬ በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የውይይት መድረኮች ሲካሄዱ መዋላቸውን ከመንግሥታዊ የዜና አውታሮች የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።

ውይይቶቹ የተመሩት ከፌዴራል እና ከሌሎች የሀገሪቱ ክልል በመጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት ነበር።

በዋነኝነት ትኩረት ያደረገው በክልሉ ያለውን ችግር ለማዳመጥና የመፍትሄ ሃሳቡን ከህዝቡ ለመረዳት ነው ተብሏል።

ባለስልጣናት በነዚህ መድረኮች ላይ ክልሉ በሰላም እጦት በሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ እየከፈለ ስላለው ዋጋና እየደረሰ ስላለው ጫና ሲናገሩ ተደምጠዋል።

መንግሥት ለዘላቂ ሰላም ጥረት እያደረገ መሆኑንና ይህንንም ህዝቡ ሊደግፍ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ጥያቄዎችን በሃይል አማራጭ ለመፍታት መሞከር ውጤት እንደሌለውና ክልሉን ወደ ባሰ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ እንደሚከት ጠቁመው ፤ ሰላማዊ መንገድ መከተል ዓይነተኛ መፍትሄ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ለጥያቄዎች ከትጥቅ ትግል ይልቅ በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋብ።

በተለይ በባህር ዳር ነበረ የውይይት መድረክ የክልሉ ህዝብ በተደጋጋሚ የሚያነሳቸው ፦
የወሰንና የማንነት፣
የፍትሃዊ ተጠቃሚነት
ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በሰላም የመኖር መብት ሌሎች ጥያቄዎች ታውቀው ያደሩ መሆናቸውና በቀጣይ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ መንግስት እየሰራ ነው ብለዋል።

ዛሬ ውይይት እንደተደረገባቸው ከተሰሙት አንዷ በሆነችው ደሴ የተገኙ ተሳታፊዎች ፤ የእርስ በእርስ ግጭቱ እያደረሰ ካለው ጉዳት በተጨማሪ፦
የኑሮ ውድነት
የሥራ አጥነት
የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና ሌሎችም ተዳምረው ህብረተሰቡን ለከፍተኛ እንግልት መዳረጉ ተነስቷል።

የአማራ ህዝብ #አንኳር ጥያቄዎች በተገቢው ጊዜ እና ፍጥነት መመለስ ባለመቻሉ ዛሬ ለተደረሰው የሰላም እጦት ምክንያት መሆናቸውን ተሳታፊዎች አንስተዋል።

በመንግሥትና በታጣቂ ኃይሎች መካከል ሀቅ ላይ የተመሰረተ በእውነትም ሀገርን ከትርምስ ሊያወጣ የሚችል ውይይት ማድረግ እና ክልሉም አሁን ካለበት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማውጣት እንደሚገባ ተነስቷል።

ዛሬ በተመሳሳይ ጊዜ ውይይት ተደርጎባቸዋል ከተባሉ ከተሞች መካከል ባህር ዳር፣ ደሴ፣  ወልድያ፣ ደባርቅ፣ ደብረ ታቦር፣ እንጅባራ፣ ሰቆጣ ከተሞች ይጠቀሳሉ።

በአማራ ክልል ከተሞች በነበሩት መድረኮች ላይ ፦ የሶማሌ ፣  የኦሮሚያ ፣ የሲዳማ ፣ የሐረሪ፣ የቤኒሽንጉል ጉሙዝ ክልሎች ፕሬዜዳንቶች እንዲሁም የአዲስ አበባ ከንቲባ ተገኝተው ነበር።

የሀገር መከላከያ ፣ የገንዝብ ፣ የሥራ እና ክህሎት ፣ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሮችን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል አመራሮችም ተገኝተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

ከዚህ ቀደም በክልሉ ከተሞች መሰል የውይይት መድረኮች ሲዘጋጁ የነበረ ቢሆንም በአንድ ጊዜ በዚህ ልክ ከፍተኛ እና የክልል አመራሮች ወደ ክልሉ ከተሞች ውይይት ሲቀመጡ ይህ የመጀመሪያ ነው።

የአማራ ክልል በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ቦታዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይል እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄዱ ግጭቶች ከግጭቱ ተሳታፊዎች ባለፈ ንፁሃን ሰለባ እያደረጉ፣ ወጥቶ ለመግባት ፣ ለንግድ ፣ ለቱሪዝምም ትልቅ እንቅፋት እየሆኑ እንዳለ በተደጋጋሚ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
#Amhara

በአማራ ክልል በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ከቱሪዝም የሚያገኙት ገቢ በመቀነሱ መነኮሳት ለመፈናቀል መገደዳቸውንና ገዳሙ የሀይቅ ውሃ ሙላት ሥጋት ላይ በመሆኑ ተጀምሮ የነበረውን ግንባታ ማስኬድ አለመቻሉን በባሕር ዳር ጣና ሀይቅ የሚገኘው የመስቀል ክብራ አንጦንስ አንድነት ገዳም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የገዳሙ እመምኔት እማሆይ ወለተ ሥላሴ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገው ነበር።

ምን አሉ ?

መነኮሳት እየተፈናቀሉ ነው። የምንተዳደው በቱሪስት ገቢ ነበር በጸጥታው ችግር ቆሟል።

በወቅታዊ ችግር ምክንያት ቱሪስት የሚባል ነገር የለም። ፍሰቱ ቁሟል። የእርሻ ቦታም የለንም። ገቢ የምናገኘው ሁሌም የቱሪስት እጅ ጠብቀን ነው።

የዕደ ጥበብ ሥራዎቻችንን ሰዎች ለበረከት እያሉ ይገዙ ነበር ይሁን እንጂ ላለፉት 6 ወራት በከፋ ችግር ውስጥ ነን።

ቀና ብንል ሰማይ ነው፣ ዝቅ ብንል ምድር ነው። በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው።

በገዳሙ 40 መነኮሳት ነበሩ ፤ ነገር ግን 5 መነኮሳት በመፈናቀላቸው በገዳሙ የቀሩት 35 መነኮሳት ብቻ ናቸው። አሁንም ያሉት መነኮሳት ይሰደዳሉ የሚል ሥጋት አለኝ።
 
አጣዳፊ ችግራችን / የሚያስፈልገን የዕለት ቀለብ / የዕለት ጉርስ የዓመት ልብስ ነው። ከዚህ አልፎ የዕደ ጥበብ ውጤቶቻችን ገበያ ላይ ለማዋል ቢችሉ ከድጋፍ ጠባቂነት እንወጣለን።

በሌላ በኩል ፤ ገዳሙ በጣና ውሃ ሙላት በተለይ በክረምት ወቅት ትልቅ ስጋት ስለሚጋርጥበት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲና በባህልና ቱሪዝም በኩል Proposal ተሰርቶ ዙሪያውን ግንባታ ተጀምሮ እንደነበር፣ ነገር ግን ግንባታ ከሚያስፈልገው 300 ሜትር የተገነባው 65 ሜትር ብቻ መሆኑን፣ በአጠቃላይ ለግንባታው ወጪ ከ12 ሚሊዮን በላይ እንደሚያስፈልግ፣ በዚህም ሁሉም ሰው ርብርብ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

የመስቀል ክብራ አንድነት ገዳም በ1314 በፃድቁ አቡነ ዘዮሐንስ የተመሰረተና አቡኑ ለ35 ዓመታት ሲያገለግሉበት የቆዩ ገዳም መሆኑ ተነግሯል።

መረጃው የተዘጋጀው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#Amhara

በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ አይሱዚ በተባለው የጭነት ተሽከርካሪ ላይ ሰኞ ዕለት ተፈፅሟል በተባለ የድሮን ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ተናግረዋል።

ለደህንነቴ ስለምሰጋ ስሜን አትጥቀሱብኝ ያሉ በርካታ ሟቾች ዘመዶቼ ናቸው ያሉ ነዋሪ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፤ በጭነት ተሽከርካሪ ላይ የነበሩት አብዛኞቹ ቤተክርስቲያንን ልጅ ክርስትና አስነስተው ወደ መኖሪያ ቤት እየተመለሱ የነበሩ ናቸው ብለዋል።

እኚሁ ነዋሪ ምን አሉ ?

- ጥቃቱ ከደረሰባቸው ውስጥ የኔ ዘመዶች ይገኙበታል። ሳሲት ከተማ ክርስትና ላይ ውለው ሲመለሱ ነበር።

- ከሰላ ድንጋይ ወደ ሳሲት ጦርነት እየቀረበ ሲመጣ ሙሉ ቤተሰብ የነበራቸውን የራሳቸውን ተሽከርካሪ ተጠቅመው ወደ ትውልድ ቄያቸው ሲጓዙ ነው ጥቃት የተፈፀመው።

- ከ40 በላይ ሰዎች ነበሩ ነው የተባለው ፤ መኪናው በአካባቢው የነበረውን ጦርነት በመሸሽ ላይ የነበሩ ሰዎችንም ጭምር እያሳፈረ ነው የሄደው።

- የእኔ ቤተሰቦች፦ የአክስቴ ልጆች እህትና ወንድም የነበሩ፣ በወንድምየው ወገን 7 ልጆች ነበሩ አንድ ላይ (እስከነ ሚስቱ) አቶ ምሳው ይባላል፣ እህቱ ሸዋለፋ ትባላለች እሷ እስከነልጇ ነበረች አጠቃላይ 6 ቤተሰብ ነው ያለቀው። በሌላ በኩል፤ የአባቴ ወገን፣ ዘመዶች፣ አክስቶቼ ነበሩ ፤ ቄስ ንጉሴ እስከነባለቤታቸው አጠቃላይ 8 ቤተሰብ፣ ክርስትና አንሺ የነበረው የባልየው ወንድም ዘየደ እስከነ ሹፌሩ፣ ጎረቤታቸው አቶ ማመዬ አጠቃላይ የአጎቴና የአክስቶቼ ልጆች የስጋ ዘመዶቼ አልቀዋል።

- በጥቃቱ አስከፊነት ምክንያት ማንነታቸው ሳይለዩ የተቀበሩ አሉ። ወደ ጤና ተቋማት ሄደው የሞቱም አሉ።

- ጥቃቱ በይበልጥ በግራ በኩል ነው ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው።

- ክርስትና የተነሳው ህፃን በአያቱ እቅፍ ውስጥ የነበረ ሲሆን ከአያቱ ጋር በህይወት መትረፍ ችሏል። ወላጆቹ ግን ህይወታቸው አልፈዋል።

- ቦታው ከጦርነት ቀጠና 15 ኪ/ሜ ይርቃል። ማንም እዛ ጥቃት ይፈፀማል ብሎ አልገመተም።

- ጥቃቱ ማህበረሰቡን ያስደነገጠ ነው። ከዚህ ቀደም በአካባቢው እንደዚህ አይነት ነገር ስላልነበር።

- ስትጓዙ ተጠንቀቁ። አንዳንድ ተሽከርካሪዎች ላይ አትጓዙ። ትራንስፖርት መጠቀም ከባድ ሆኗል።

- መንግሥት ህዝብን ለማስተዳደር እስከተመረጠ ድረስ የመረጠው ህዝብ ላይ እንዲህ ያለው ጥቃት ማድረስ የማይጠበቅ ነው። ተዋጊና ተዋጊ ምንም አይነት ጉዳት ቢደርስ ሁለቱም አስቦበት ነው። ሰላማዊ ሰዎች ላይ እንዲህ ያለው ጥቃት ሲደርስ መንግሥት ኃላፊነቱን ቢወስድ።

- መንግሥት ጉዳዩን በቅርበት አይቶ የተፈፀመውን ጥቃት ቢመረምርልን የሚል መልዕክት አለኝ።

ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት በመከላከያ እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል " ሰላድንጋይ " ላይ ግጭት እንደነበር አሁን ላይ ግን እንደሌለ መከላከያም በከፍተኛ ቁጥር ወደ ስፍራው ገብቶ አካባቢውን እንደተቆጠር ተነግሯል።

ይህን የሰሜን ሸዋ ጉዳይ በተመለከተ እስካሁን በመንግሥት በኩል የተሰጠ ምንም ምላሽ የለም። መገናኛ ብዙሃን ምላሽ ለማግኘት ጥረት ቢያደርጉም እንዳልተሳካ አሳውቀዋል።

ነገር ግን ከወራት በፊት መንግሥት ፦
- ድሮን የታጠቀው አለኝ ለማለት ሳይሆን ልክ እንደሌለው ማሳሪያ ጥቅም ላይ ለማዋል እንደሆነ ፣
- የፀጥታ ኃይሉ ድሮ በንፁሃን ላይ እንደማይጠቀም ፤
- ድሮ ጥቅም ላይ የሚውለው ለስብስብ ኢላማ እንደሆነ በዚህም ከመንግሥት ጋር የገጠመው የታጣቂው ስብስብ ዒላማ ሲገኝ እንደሚመታ
- ህዝብ ላይ ድሮን እንደማይጣል ፣ መንደር ላይ እንደማይተኮስ ፣
- የታጣቂ ኃይሎች ምርጥ ኢላማ ሲገኝ እንደሚተኮስ
- ድሮን ጥቅም ላይ ሲውል ለህዝብ ጥንቃቄ እንደሚደረግ አሳውቆ ነበር።

@tikvahethiopia
#Amhara

የአቶ ዮሐንስ ቧያለውን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱን የአማራ ክልል ምክር ቤት አሳወቀ።

የአማራ ክልል ምክር ቤት በ6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባዔ የክልሉ ም/ቤት አባል የነበሩት የአቶ ዮሐንስ ቧያለውን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።

አቶ ዮሐንስ ከወራት በፊት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

የቀድሞው የአማራ ክልል ባለልስጣን ለረጅም ጊዜ በተለያየ የስልጣን እርከን ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን በኃላ ላይ ከመንግሥት ጋር መቃቃር ውስጥ ገብተው ነበር።

ከወራት በፊትም በአማራ ክልል ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ ለእስር መዳረጋቸው መነገሩ ይታወሳል።

@tikvahethiopia