TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA 3 ጉዳዮች ከዛሬው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ፦ 1ኛ. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከዛሬ የካቲት 8/2014 ጀምሮ ቀሪ የሚሆንበት የውሳኔ ሃሳብ በ63 ተቃውሞ፣ በ21 ድምፀ ታአቅቦ፣ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል። 2ኛ. የመንግስት ሰራተኞች ጡረታ ለመደንገግ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ በሁለት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ እና የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ጡረታ ለማደንገግ የቀረበውን ረቂቅ…
#መንግሥት እና የ #ግል ሠራተኞች ጡረታን ለመደንገግ የቀረበው አዋጅ ምን ይዟል ?

ለመንግሥት ሠራተኞች ፦

• የተሻሻለው የጡረታ ዐዋጅ የጡረታ ዕድሜን ጣራ ' 60 ዓመት ' እንዲሆን እና ጡረተኛው በሕይወት ሳለ የሚያገኘው የጡረታ መጠን ሲያልፍ ለትዳር አጋር 50 በመቶ የጡረታው ተጠቃሚ እንዲሆን ይፈቅዳል።

• የፖሊስና መከላከያ መዋጮ ከግለሰቡ የሚደረገው ሌሎች የግልና የመንግሥት ሠራተኞች እንደሚያዋጡት 7 በመቶ ሆኖ ከመንግሥት አካል የሚደረግለት መዋጮ ግን ወደ 33 በመቶ ከፍ እንዲል ተደርጓል።

ለግል ድርጅቶች ሠራተኞች ፦

• በድርጅቶች ምክንያት ሳይዋጣ የቀረን ገንዘብ በሦስት ወር ውስጥ ገቢ ካልተደረገ በቀጥታ ድርጅቱ ካለው ማንኛውም የባንክ አካውንት ገቢ እንዲደረግበት ያስገድዳል።

• የግል ድርጅት ባለቤቶች በድርጅቱ ሠራተኛ ሆነው በጡረታ ማዕቀፉ ውስጥ እንዳይገቡ አዋጁ አግዷል።

• ከ10 ዓመት በላይ ያገለገለ ሠራተኛ ዕድሜው ለጡረታ በሚደርስበት ጊዜ የዕድሜ ልክ ጡረታ ተከፋይ እንዲሆን አዋጁ ይፈቅዳል።

• የሚሰበሰበው የጡረታ መዋጮም ወደ ኢንቨስትመንት በማስገባት ገቢን ማሳደግ ለጡረተኞች የክፍያ ማሻሻያ የሚያደርግበትን እድል ይፈጥራል።

• አንድ አሰሪ የ ግል ድርጅት ፍቃዱን በሚያድስበት ወቅት የሠራተኞቹን መዋጮ ካላስገባ ፍቃዱ የማይታደስበት አስገዳጅ አንቀጽም ተካቷል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#Amhara #Merawi

በአማራ ክልል ፤ በየጊዜው በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በመንግሥት የፀጥታ ኃይል መከላከያ እና በ " ፋኖ " ታጣቂ ኃይሎች መካከል ግጭቶች ይደረጋሉ።

በእነዚህ ግጭቶችም በሁለቱም በኩል ከሚሞተው የግጭቱ ተካፋይ ባለፈ ንፁሃን ሰዎች ሰለባ እየሆኑ እንዳለ በተደጋጋሚ ተገልጿል።

ምንም እንኳን #መንግሥት ፤ " ከእውነታው ያፈነገጠ እና ሚዛናዊነት የጎደለው " ብሎ ቢያጣጥለውም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮኒሽን  (#ኢሰመኮ) ይፋ አድርጎት በነበረው ሪፖርት በክልሉ ፦

- የአንድ ዓመት ከሰባት ወር #ሕፃንን ጨምሮ በርካታ ሲቪል ሰዎች በድሮን መገደላቸው / የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው።

- በከባድ መሣሪያ ድብደባ ምክንያት #ሲቪል_ሰዎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት መድረሱ።

- በመንግሥት የጸጥታ ኃይል አባላት #ከሕግ_ውጪ የሆኑ ግድያዎች እንደሚፈፀሙ።

- ከዚህ ቀደም ግጭቶች በተካሄደባቸው አካባቢዎች የመንግሥት የጸጥታ አካላት በመንገድ ላይ ወይም ቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ ከያዟቸው በርካታ ሲቪል ሰዎች ውስጥ ፦
" ፋኖን ትደግፋላችሁ "
" ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ "
" መሣሪያ አምጡ "

" የተኩስ ድምጽ ስለተሰማበት አቅጣጫ መረጃ ስጡ " በሚልና ይህንን በመሰሉ ምክንያቶች ከሕግ ውጭ የሆኑ በርካታ #ግድያዎች መፈጸማቸውን በይፋ ማሳወቁ አይዘነጋም።

ከሰሞኑን ዳግሞ በሰሜን ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል፣ ሰኞ ጥር 20/2016 ዓ/ም የነበረውን ውጊያ ተከትሎ በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ገለጻ ፤ በሰሞኑ ተኩስ እሳቸው የሚያውቋቸው ብቻ 15 ወጣቶች መገደላቸውን ተናግረዋል።

ከዚህም ባለፈ ግን ፤ " የሟቾቹን ቁጥር በዚህ ወቅት ለመግለጽ መሞከር የጥቃቱን አድማስ ያሳንዋል እንጂ አይገለጸውም" ብለዋል።

እኚሁ ነዋሪ በግፍ የተገደሉ ንጹሐን ሰዎችን ቁጥር በሂደት እንጂ አሁን ሁሉንም ማወቅ እንደማይቻል ገልጸው ፤ " የዚህ ህዝብ ጭፋጨፋ ግን መቼ ነው የሚያበቃው? " ሲሉ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች፣ የሆስፒታል ሰዎችና የአይን እማኞች በከተማው ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

አብዛኞቹ ነዋሪዎች ግድያው የተፈጸመው በቤታቸው እና በመንገድ ላይ በተገኙ ሰላማዊ ሰዎች ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

አንድ የህክምና ባለሙያ 13ት ሰዎች ከአስፓልት ዳር መገደላቸውን እንደሚያውቁ ተናግረው በአጠቃላይ በከተማዋ በዚያ ዕለት 85 ሰዎች መገደላቸውን አመልክተዋል።

አንድ የአይን እማኝ በርካታ ቀብሮች ላይ መገኘታቸውን ጠቅሰው የሟቾችን ቁጥር " ከ100 በላይ ነው " ብለዋል። ጥቃቱ በተፈጸመ ማግስት ጠዋት ላይ 48 አስከሬን መቆጠራቸውን ተናግረው ፤ " ከማርዘነብ ሆቴል እስከ በረድ ወንዝ ድረስ ግራ እና ቀኝ አስከሬን ብቻ ነበር " ብለዋል።

የሟቾችን ቁጥር 115 ገደማ የሚያደርሱ አንድ የዐይን እማኝ ደግሞ መከላከያ ከተማዋን ከተቆጣጠረ በኋላ ስታዲየም እና ጤና ጣቢያ በተባሉ ሰፈሮች " ከ6 ዓመት ህጻን እስከ 75 ዓመት አዛውንት " ድረስ ግድያ ተፈጽሟል ብለዋል።

የሆስፒታል ሠራተኛ የሆኑት የዐይን እማኝ በከተማዋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ6 ወር ነፍሰ ጡርን ጨምሮ 25 ሰዎች ቆስለው መጥተው " የተረፈ የለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" 24ቱ ሆስፒታል የመጡት ሞተው ነው። አንዲት የ6 ወር ነፍሰ ጡር ሴት ከነ ነፍሷ መጥታ ሆስፒታል እንደደረሰች አርፋለች። አጠቃላይ 25 ነበር የመጡት " ብለዋል።

ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ፤ #በመርዓዊ_አስተዳደር ህንጻ ውስጥ በነበሩት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የፋኖ ታጣቂዎች ሰኞ ጠዋት ድንገተኛ ጥቃት ፈፀመው እንደነበርና ለዚህ ምላሽ " የበቀል እርምጃ " በመወሰዱ ነው ለበርካታ ሰዎች ግድያ ምክንያት የሆነው ብለዋል።

ስለ ግድያው ምን ምላሽ እንዳለቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ  መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር)፣ " ስብሰባ ላይ ነኝ መልሸ ልደውል " ብለዋል።

መንገሻ (ዶ/ር) ይህን ያሉት እንዲያብራሩ የተፈለገውን ጥያቄ በዝርዝር ከሰሙ በኋላ ሲሆን፣ በድጋሚም ስልክ ሲደወል ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

እንዲሁም፣ " እባክዎ ስልክዎን ያንሱና በኮሚዩኒኬሽን በኩል ያለውን የመርዓዊ ጉዳይ ማብራሪያ በመስጠት ኃላፊነትዎን ይወጡ " የሚል የፅሑፍ መልዕክት (SMS) ቢላክላቸውም ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል።

በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
* የክልሉ የኮሚዩኒኬሽን ምክትል፣
* የክልሉና የሰሜን ጎጃም ዞን ኮማንድ ፖስት፣
* የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ስለጉዳዩ ምን ምላሽ እንዳለቸው ለማወቅ እና ሃሳባቸውን ለማካተት ስልክ ቢደውልም ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ኮሚሽን ( #ኢሰመኮ ) ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ፤ " መረጃው ደርሶናል (የመርዓዊ ጉዳይ) ። እያረጋገጥን ነው " ብለዋል።

አክለው ፣ "የጸጥታ ጉዳይ ስለሆነ ትንሽ መንቀሳቀስና መረጃ መሰብሰብ አስቸጋሪ ሊሆን ስለሚችል ሊዘገይ ይችላል። ግን እያጣራን ነው" ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ 1.2 ቢሊዮን የምስኪን ሕዝብን ገንዘብ 4 ዓመታት ሙሉ ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ እየተጠቀመበት ነው። በውላችን መሠረት መኪና አላስረከበንም ” - የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት በስራቸው ከ2,800 በላይ አባላት ያሏቸው ከ40 በላይ የሚሆኑ ሕጋዊ የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት ከ3 ዓመታት በፊት " ከኦክሎክ ትሬዲንግ/ኃላ/የተ/የግ/ ማኀበር " መኪና እንዲቀርብላቸው ቢዋዋሉም መኪናው ሳይቀርብ የውል ገደቡ እንዳለፈ፣…
#ቅሬታ

“ እኔ 1.5 ሚሊዮን ብር ነው #የተጨመረብኝ። እውነት ድርጅቱ ጨምሮበት ነው ወይስ የድሃ እንባ ፈልጎ ነው ? ”- እያለቀሱ ቅሬታ ያቀረቡ ቆጣቢ እናት

2012 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ በኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር አማካኝነት መኪና ለማስመጣት ገንዘብ ሲቆጥቡ የነበሩ ከ40 በላይ በሆኑ ማኀበራት ሥር የሚገኙ ከ2 ሺህ 800 በላይ ቆጣቢዎች፣ ውል የገባላቸውን መኪና አስመጪ ማኀበሩ በውሉ መሠረት መኪናውን እንዳላቀረበላቸው ገልጸዋል።

ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መካከል አንዱ ቆጣቢ፣ “ እኔ በሥነ ስርዓት መረጃ አለኝ። በእኛ ስም እየመጣ እየተሸጠ ነው። ለዚህ እኔ ምስክር ነኝ ” ሲሉ ኦክሎክ ጀነራል ቲሬዲንግን ኮንነዋል።

ሌሎች ቅሬታ አቅራቢዎች በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

➡️ አንድ ቅሬታ አቅራቢ፣ “ ገንዘባችንን ሰጥተን ለማኝ እየሆንን ነው። ገንዘባቸውን ከፍለው እንደገና የጥበቃ ሰራተኛ ሆነው ተጠግተው መኪና ያገኙ ራሱ አሉ ” ብለዋል።

➡️ ሌላኛው አባት በበኩላቸው፣ “ መኪናውን የሚጠብቁ ሁለት ልጆች አሉኝ። ገናኮ ለየትኛው እንደምሰጥ እያሰብኩ ነው ያለሁት” ሲሉ የነበራቸውን ተስፋ አስረድተው፣ “ ጎዳና ላይ ከምታድር ድሃ መቀነቷን ፈትቶ እንደመውሰድ ነው። ችግር ካለ ስብስቦ ሊጠይቀን ይችል ነበር። ግን በስማችን መነገድ ነው የፈለገው ” ብለዋል።

➡️ ሌላኛዋ ቆጣቢ በበኩላቸው ፦

“ ውላችን ከ3 እስከ 6 ወራት፣ ካልሆነ ደግሞ እስከ 1 ዓመት ነበር፣ 60 ሺሕ ከፍለን የሚለው። 25 በመቶ መኪናው አገር ውስጥ ከገባ በኋላ ገንዘብ እንከፍላለን የሚል ነው ውላችን ላይ የነበረው። 60 ሺሕ ከፍለን እያለ 2013 ዓ/ም ላይ 25 ፐርሰንት ክፈሉ ተብሎ የመኪናውን ዋጋ 25 በመቶ ስንከፍል፣ እኔ ተመዝግቤ የነበረው መኪና 520 ሞዴል ነበር። የመኪናው ዋጋ 520 ሺሕ ብር ነበር። 

በመካከል 25 በመቶ ክፈሉ ‘የቻንሲና የሞተር ቁጥር መጥቷል’ ተብሎ ተከፈለ። ነገር ግን ‘ይህን መኪና ፋብሪካው ማምረት ስላቆመ 690 ሺሕ የሚመረተውን መኪና ቀይሪ’ ተብዬ 690 ሺሕ ብር የመኪናውን 25 ፐርሰንት 2013 ዓ/ም ኀዳር ወር ከፍዬ እየጠበኩ ሁለት ዓመታት ተቆጠሩ።

በ2014 ዓ.ም ከ2,800 በላይ አባላት በተገኙበት ኦሮሚያ የባህል አዳራሽ ተሰብስቦ ‘ከጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የመጣሁ ነኝ መኪናችሁን 1 ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ተውስዳላችሁ። እንባችሁ ታብሷል ” ያላቸው አካል እንደነበር ገልጸው፣ ምንም መፍትሄ ስላልተገኘ፣ መንግሥት ይዳኘን " ሲሉ ጠይቀዋል።

➡️ አንዲት እያለቀሱ ቅሬታቸውን ያቀረቡ እናት በመጀመሪያ የነበረውን ውል መሠረት በማድረግ ተስማምተው እንደገቡ ገልጸው፦ “ ሁለት ወራት ጠበቁና 35፣ ‘45 ፐርሰንት ጨምሩ’ አሉን። ያን አድርገን ሳንጨርስ (ተበድረን ያስገባነውን ጉድ) መልሰው ሦስት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ‘400 ሺሕ ብር ጨምሩ፣ አበዳሪ ተገኝቷል በሁለት ወራት ውስጥ ገጣጥመን እናስገባለን’ አሉ። እኔ 1.5 ሚሊዮን ብር ነው የተጨመረብኝ። እውነት ድርጅቱ ጨምሮበት ነው ወይስ የድሃ እንባፈልጎ ነው?። አልገባኝም። #መንግሥት_ይዬን ። ” ሲሉ እያለቀሱ ቅሬታ አቅርበዋል።

➡️ ሌላኛው ቆጣቢ በበኩላቸው፣ “ ትዳራችንን ልናፈርስ ጫፍ ላይ ደርሰናል። አብዛኞቻችን ደግሞ የተሸወድነው የመንግሥት ባለስልጣንና ባንክ ቁጭ አድርጎ ቃል ሲገባልን ነው ” ነው ያሉት።

#TikvahaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia