TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC የግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፦ በቤተ ክርስቲያኗ በሀገራዊ እንዲሁም በወቅታዊ ዐበይት ጉዳዮች ላይ ለተከታታይ ቀናት ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ ነገ ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡00 ሰዓት እንደሚሰጥ ተነግሯል። #የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተክርስቲያን #ኢትዮጵያ…
#ኢትዮጵያ

ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ እና የግብረ ሰዶማዊነትን #ኃጢአት በተመለከተ አጀንዳ አድርጎ መወያየቱ ተሰምቷል።

በዚህም፥ የቅድስት ቤተ ክርስቲያኗን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ #ዓለም_አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር የሆነ መግለጫ እንዲሰጥ ወስኗል።

#EOTCTV

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የ4 አብያተ ክርስቲያናትና ሚኒስትሪዎች ሠርተፍኬት #እንዲሰረዝ መወሰኑን አሳውቋል።

ሠርተፍኬታቸው የተሰረዘው ፦

1ኛ. ጋድስ ላይት ግሎሪ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ነብይ ኢዮብ ጭሮ

2ኛ. ገዥዋ ዓለም አቀፍ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መጋቢ ካሳ ኪራጋ

3ኛ. የሰማይቱ ጽዮን ማኅበርተኞች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መጋቢ ሚስጥሩ መዝገቡ

4ኛ. የእግዚአብሔር መንግስት እውነት ዓለም አቀፍ ሚኒስትሪ መጋቢ  ቢንያም ሽታዬ ... ናቸው።

ውሳኔው የተለለፈባቸው በስህተት ትምህርትና ልምምዶች ምክንያት ነው።

ካውንስሉ እነዚህ አካላት የተሰጣቸውን የሕግ ከለላ በመጠቀም ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮና ጤናማ ሥነ ምግባር ውጭ የሆነ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበሩ ገልጿል።

ከዚህ ተግባራቸው ይመለሱ ዘንድም አስፈላጊውን ትምህርትና ምክር ሲሰጥ ቆይቷል።

ይሁን እንጂ ምክሩ ተቀበለው ሕዝብን ከሚያሳስት ተግባራቸው #ለመመለስ ፈቃደኛ ሆነው ባለመገኘታቸው ሠርተፍኬታቸው እንዲሰረዝ ወስኗል።

(ካንውስሉ ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ሬሜዲያል

" በበዓል ቀናት ሆነ ማግስት የሚወጣ የፈተና ሰሌዳ አግባብነት የለውም " - የፌዴራል መጅሊስ

የሬሜዲያል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ቅሬታ አስነስቷል።

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የሪሚዲያል ተማሪዎች የፈተና መርግብር፤ ፈተናው ከሰኔ 3-10/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ያሳያል።

የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 3 እስከ 6/2016 ዓ.ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 6-10/2016 ዓ.ም ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

ይህ የፈተና ፕሮግራም ግን ከ #ኢድ_አል_አድሃ (አረፋ) በዓል ጋር የሚጋጭ በመሆኑ በእስልምና እምነት የከታዮች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል።

እንዲህ ያለ ቅሬታ ሲፈጥር ይህ የመጀመሪያ አይደለም ። ከዚህ ቀደም መሰል ሁኔታዎች ተፈጥረው እንደነበር አይዘነጋም።

የዘንድሮ የሬሜዲያል ፈተና ቀንን በተመለከተ የፌዴራል መጅሊስ ለሃሩን ሚዲያ በሰጠው ቃል ፤ " በበዓል ቀናት ሆነ ማግስት የሚወጣ የፈተና ሰሌዳ አግባብነት የለውም " ሲል ተቃውሟል።

የመጅሊሱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ከማል ሀሩን ፥ " የተማሪዎች የመፈተኛ የጊዜ ሰሌዳ የሙስሊሙን በዓላት ታሳቢ አድርገው መውጣት አለባቸው " ያሉ ሲሆን "  የበዓል ቀናትን ታሳቢ ያላደረገ የፈተና የጊዜ ሰሌዳ አወጣጥ አግባብነት የሌለውና በተማሪዎች የስነልቦና አልፎም የፈተና ውጤታቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

#ኢትዮጵያ
#ሬሜዲያልፈተና
#ሀሩን

@tikvahethiopia
Anti Money laundering law Amharic from COM to HPR (1).pdf
494.2 KB
#ረቂቅ_አዋጅ ፦ " በወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ "

#የሕዝብተወካዮችምክርቤት #ኢትዮጵያ
#AntiMoneyLaunderingLaw

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

የ2016 የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።

ጥዋት የኢድ ሶላት ስነስርዓት በተለያዩ ከተሞች ተከናውኗል።

ከኢድ ሶላት በኃላ ምዕመኑን በየቤቱ ፣ ከዘመድ አዝማዱ፣ ከወዳጆቹ ጋር በመሆን በዓሉን እያከበረ ነው።

#ኢድአልአድሃ #አረፋ

መልካም በዓል

ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Asset Recovery draft proc. Amharic from COM to HPR (1).pdf
#ኢትዮጵያ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ፤ " ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ስለማስመለስ " ምን ይላል ?

➡️ #ማንኛውም_ሰው በቀጥታ ሆነ #በተዘዋዋሪ ያለው ንብረት ወይም የኑሮ ደረጃው አሁን ላይ ባለበት ወይም አስቀድሞ በነበረበት ስራ ወይም በሌላ መንገድ ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ የማይመጣጠን እንደሆነ እና የንብረቱን ወይም የኑሮ ደረጃውን ምንጭ በተመለከተ ምክንያታዊ የሆነ የወንጀል ጥርጣሬ በኖረ ጊዜ የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ ወይም ያለው ንብረት እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ለፍርድ ቤት ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ #ይወረሳል

➡️ ህጋዊ ገቢ እንዳለው የሚያስረዳ የተመዘገበበት ስርዓት የሌለው ወይም ገቢው እነስተኛ በመሆኑ #ከግብር_ነጻ የሆነ ሰው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያለው ንብረት ወይም የኑሮ ደረጃው ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ የማይመጣጠን እንደሆነ የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ ወይም ያለው ንብረት እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ለፍርድ ቤት ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ ይወረሳል፡፡

➡️ " በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ያፈራው ንብረት " ማለት ፦

° በራሱ ስም የሚገኝ ንብረት፣

° በራሱ ስም ባይሆንም ለራሱ ጥቅም ሲያዝበት ወይም ሲቆጣጠረው የነበረው ንብረት ፣

° የተጠቀመው ወይም ደግሞ ያስወገደው ንብረት፣

° በሽያጭ ፣ በስጦታ ወይም በማንኛውም ሁኔታ #ያስተላለፈውን ንብረት ይጨምራል፡፡

➡️ ዐቃቤ ሕግ " #ምንጩ_ያልታወቀ_ነው " ብሎ የጠረጠረውን ማንኛውንም ንብረት ዝርዝር እና የተገኘበትን አግባብ የሚያሳይ መግለጫ እንዲያቀርብ በፅሁፍ ጥያቄ የቀረበለት ማንኛውም ሰው ጥያቄው በደረሰው በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ለዐቃቤ ህግ ዝርዝር ማስረጃዎችን በማያያዝ በፅሁፍ ማቅረብ ይኖርበታል።

➡️ የንብረቱን ምንጭ እንዲያስረዳ የተጠየቀው ሰው የንብረቱን ምንጭ ለማስረዳት የሚያቀርበው ማስረጃ ሀጋዊ መሆን አለበት።

ተጨማሪ ....

☑️ አንድ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ አውጥቶ የሚሰራ ነጋዴ ወይም ድርጅት ሕጋዊ ገቢው ተብሎ የሚገመተው ለተገቢው ባለስልጣን በወሩ ወይም በአመቱ ከንግዱ ያገኘሁት ብሎ ያሳወቀው የገቢ መጠን ሲሆን ወይም ተገቢው ታክስ የተከፈለባቸው ገቢዎች ሆነው ሲገኙና የታክስ ደረሰኝ ሲቀርብ ሲሆን ከዚህ ውጪ ህጋዊ ታክስ ያልተከፈለባቸው ገቢዎች ከህጋዊ ገቢ ውጪ ያፈራው ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ተብሎ ሊወሰን ይችላል።

☑️ ምንጩን ሲያስረዳ " ከውጪ የተላከለኝ ገንዘብ ነው " የሚል ማንኛውም ግለሰብ ገንዘቡ በሕጋዊ መንገድ #በባንክ_ሥርዓት ውስጥ ያለፉ ግብይቶች ወይም ክፍያዎች ስለመሆናቸው በተገቢው የባንክ ደረሰኝ አስደግፎ ማቅረብ የሚገባው ሲሆን ከዚህ ውጪ ያለው ግን እንደ ምንጩ ያልታወቀ ገቢ ተደርጎ ይቆጠራል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ #ምንጩ_ያልታወቀ_ንብረት ክስ የሚቀርብበት ጊዜ እና የገንዘብ መጠን ተደንግጓል፡፡

በዚህም አዋጁ ወደኋላ 10 ዓመታት ተመልሶ የሚሠራ ሲሆን ይህንንም ለመክሰስ የ5 ሚሊዮን የገንዘብ ገደብ ተቀምጧል፡፡

ይህ የገንዘብ ገደብ የተቀመጠበት ዋነኛው ምክንያት በአሁኑ ወቅት ላይ በሀገሪቱ ያለውን የሰው ሃይል ፣ የመክሰስ አቅም እና የፋይናንስ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት አነስተኛ የሃብት መጠን ያላቸውን ግለሰቦች በመተው ከፍተኛ ንብረት ያላቸውን ተጠያቂ ለማድረግ እንደሆነ ተብራርቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ሕጉ ወደኋላ (10 ዓመታት) ተመልሶ እንደመስራቱ በሀገሪቱ #ኢኮኖሚ#ማሕበራዊ እና #የፋይናንስ_ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ ያደርሳሉ ተብሎ የሚገመቱትን ግለሰቦችና ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶችን ተጠያቂ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ተብራርቷል።

አዋጁ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ተጠያቂነት ያለምንም የገንዘብ መጠን ተፈጻሚ ይደረጋል።

ስለ ረቂቅ አዋጁ አጭር ማብራሪያ ⬇️
https://t.me/tikvahethiopia/88313

ረቂቅ አዋጁ⬇️
https://t.me/tikvahethiopia/88314

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM