TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ፍጹም ሀሰተኛ / የውሸት ይዘት ነው ተጠንቀቁ " - የጠ/ሚ ጽ/ቤት

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገውን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) እንደሰረዘው ተደረጎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

የጠ/ሚ ጽ/ቤት ያወጣው መግለጫ አስመስሎ አንድ የተቀነባበረ የጠ/ሚ ጽ/ቤት አርማ ያለበት መግለጫ በስፋት እየተዘዋወረ ይገኛል።

ይኸው መግለጫ ፦

- ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ከተለየችው ' ክልል ' ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) እንደሰረዘችው ፤
- ኢትዮጵያ ከዩኬ፣ ከG7 እና ከሌሎች ሀገራት ጋር ተወያይታ የሶማሌላንድን ሉዓላዊ ሀገርነት የምትደግፍበት ማስረጃ እንዳላገኘች
- የኢትዮጵያ መንግሥት ከአሁን በኃላ ህጋዊ ያልሆነ ስምምነት ከሶማሌላንድ ጋር እንደማያደርግ
- ኢትዮጵያ ፤ የሶማሌላንድ ጉዳይ የሶማሊያ ስለሆነ ፖለቲካዊ ችግራቸውን በአንድ ሀገር ጥላ ስር እንዲፈቱ እንደምትተው ... የሚገልጽ ነው።

ይህ ግን ፍጹም ሀሰተኛና መግለጫው የተቀነባበረ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ምን አለ ?

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፤ ከሶማሌላንድ ጋር ስለተፈጸመው የመግባቢያ ስምምነት በኦንላይን እየተዘዋወረ እና እየተሰራጨ ያለው መረጃ ፍጹም ሀሰተኛ / የውሸት ይዘት ስለሆነ ህዝቡ እንዲጠነቀቅ መክሯል።

በሀገር ውስጥ ፣ በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች መግለጫም ሆነ መረጃ የሚሰጠው በይፋዊ የጽ/ቤቱ ገጾች / ቻናሎች ላይ ብቻ እንደሆነ አመልክቷል።

ሁሉም ሰው የጽ/ቤቱን ይፋዊ አርማ በመጠቀም ከሚሰራጩ  እንደዚህ አይነት የውሸት መረጀዎች / ይዘቶች እራሱን እንዲጠብቅ አደራ ብሏል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ላለፉት ስድስት ቀናት በመላ አገሪቱ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ተጠናቋል። 57 የመንግሥት እና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ማስፈተናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከመውጫ ፈተናው ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በተለይ ከተነገርን ይዘት እና ከተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው…
#MoE

የ2016 ዓ/ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የ2016 ዓ/ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና እና የዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና መቼ ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።

የትምህርት ሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራር ፥ የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በጣም ከዘገየ እስከ ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል ብለዋል፡፡

የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቅ ከመጀመራቸው በፊት ይፋ እንደሚደረግ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

#TikvahEthiopia

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ላለፉት ስድስት ቀናት በመላ አገሪቱ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ተጠናቋል። 57 የመንግሥት እና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ማስፈተናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከመውጫ ፈተናው ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በተለይ ከተነገርን ይዘት እና ከተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው…
#MoE

ትናንት የተሰጠው የፋርማሲ ትምህርት የመውጫ ፈተና ተሰርዞ በድጋሚ ይሰጣል ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናው " የቴክኒክ ችግር " አጋጥሞት እንደነበር ገልጿል።

ተማሪዎች በበኩላቸው ቀደም ብሎ ፈተናው ወጥቶ በወረቀት እትም እና በPDF መሰራጨቱንና ተማሪዎችም ሰርተው መግባታቸውን አመልክተዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ግን ፈተናው " የቴክኒክ ችግር " ስላጋጠመው ፈተናው በድጋሜ  በድጋሜ ቅዳሜ ሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጠዋት ከ3:00 ሰዓት ጀምሮ እና ከሰአት ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ ይሰጣል ብሏል።

ምን አይነት የቴክኒክ ችግር እንደሆነ በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

ለፈተናው ተቀምጠው የነበሩ የፋርማሲ ተማሪዎች በየተፈተኑበት የፈተና ጣቢያ በሰዓቱ በመገኘት በድጋሜ የሚሰጠውን ፈተና እንዲወስዱ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ተማሪዎች ምን አሉ ?

የጥዋቱም ይሁን የከሰዓቱ ፈተና ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ እንዴት እንደሆነ ባይታወቅም ወጥቶ ተማሪዎች በበድን ሰርተውት እንደገቡ ገልጸዋል።

ሌላው ፈተናው ከብሉፕሪነቱ ጋር እንደማይጣጣም ፤ ትምህርቱንም የሚመዝን ፈተና እንዳልወጣ አመልክተዋል።

የባለፉት ፈተናዎችን እንዳዩና የዚህ አይነት ፈተና ግን እንዳልነበር ጠቁመው ፈተናው ማስተካከያ እንዲደረግበት አሳስበዋል።

የ2016 ዓ/ም ፈተና ትላንት መጠናቀቁ ይታወሳል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " የዘንድሮው ፈተና ከ220 በላይ ፕሮግራሞች ያለምንም ችግር Smoothly ነው የተሰጠው " ብሎ ነበር።

" ከፈተናዎቹ ጋር የተያያዘም ምንም አይነት Issue አላጋጠመንም፤ አንድም ቅሬታ ለትምህርት ሚኒስቴር አልደረሰም " ሲል ነበር ያስረዳው።

ሚኒስቴሩ ይህን ቢልም  ፤ በተለይ ከተነገርን ይዘት እና ከተዘጋጀው ብሉፕሪንት ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው ፦
- የማኔጅመንት
- የማርኬቲንግ ማኔጅመንት
- የሀይድሮሊክና ውሃ ሃብት
- የቬተርነሪ ሜድስን
- የኸልዝ ኢንፎርማቲክስ ተማሪዎች ተማሪዎች ቅሬታ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#Amhara

የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል ምን አለ ?

- ይህ የ ' ሰላም ካንውስል ' በአማራ ክልል ውስጥ የተፈጠረውን አለመስማማት እና አለመግባባት ተከትሎ የተከሰተውን የእርስ በእርስ ጦርነት በሰላም ለመቋጨት መንግሥትን እና ታጥቀው ጫካ የገቡ የፋኖ አባላትን ለማደራደርና ለማወያየት ይቻል ዘንድ ለመመቻቸት የተሰየመ ነው።

- ድርሻው መንግሥት እና የፋኖ አባላትን ለድርድር፣ ለውይይት እንዲበቁ ማመቻቸት ብቻ ነው።

- ያለ ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ደረጃ ፣ በየትኛውም ቦታ ፣ በየትኛውም አደራዳሪ የመንግሥት ኃይሎች እና በጫካ የሚገኙ የፋኖ ወንድሞቻችን ቢያስን ዘላቂ ተኩስ ለማቆም ንግግር እና ድርድር እንዲያደርጉ ይህ ካውንስል ተሰይሟል።

- በጦርነት እንጨራረሳለን እንጂ አንሸናነፍም።

- የአማራ ህዝብ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ ምስቅልቅል ውስጥ ይገኛል።

- ግጭቱ አጠቃላይ ሀገሪቱን ለከፍተኛ ጉዳት እና ወደባሰ የድህነት አረንቋ እየከተታት ይገኛል።

- ለዚህ ግጭት መነሻ የአማራ ህዝብ ለዘመናት ሲጠይቃቸው የነበሩ ጥያቄዎች በሰለጠነ ንግግር እና ድርድር አለመፈታታቸው ወይም ደግሞ የሚፈቱበትን ሂደት የሚያመለክት ግልጽ ፍኖተ ካርታ አለመቀመጡ ነው።

የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ተብለው የተለዩት ፦
° የተዛባ ትርክት ማረቅና ማስተካከል
° ህገመንግስት ይሻሻልልን
° የወሰን እና ማንነት ጉዳይ
° ፍትሃዊ የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ውክልና ጉዳይ
° በሌሎች ክልሎች የሚኖሩ የአማራ ህዝብ ጉዳይ
° የአዲስ አበባ የመልካም አስተዳደር እና አድሏዊ አሰራር ችግር አለመቀረፉ
° በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ንጹሃን የአማራ ተወላጆች ለሚደርስባቸው ግድያ እና መፈናቀል ተጠያቂነት አለማስፈን ጉዳይ .. የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

- እነዚህ ጥያቄዎች በቅንነት በሀገሪቱ ጥላ ስር በንግግር እና በድርድር ሊፈቱ የሚገባቸው እንጂ ወደ ጦርነት የሚያስገቡ አልነበሩም።

- የክልሉ መንግሥት በህዝብ ዘንድ ያለው ቅቡልነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ሄዷል።

- ክልሉም ከችግሩ ሚያወጣው ፣ የተደራጀ የፖለቲካ እሳቤ የሚፈጥርለት ምሁር የመከነ እስከሚስል ደርሷል።

- ላለፉት ዓመታት የኢኮኖሚን ችግር የሚቀርፍ የማሻሻያ ድጋፍ ይደረጋል ሲባል በተለያዩ አጀንዳዎች በመወጠር እና የደህንነት ስጋት ውስጥ እንዲወቅ ሆኖ በከፋ የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ውስጥ ይገኛል።

- ከ ' ህወሓት ' ጋር የተደረገው ስምምነት በአግባቡ ሳይተገበርና የአማራ ህዝብ ህልውና ስጋት ዋስትና ሳይበጅለት ቀርቶ ነው የክልሉ የጸጥታ ችግር ተባብሶ ከ2015 ሀምሌ መጨረሻ አንስቶ በነፍጥ የታገዘ ግጭት የጀመረው። በዚህ ምክንያት ለአንድ አመት የሚጠጋ ጊዜ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነበር።

- ለአንድ አመት በተጠጋው ጦርነት የክልሉ ህዝብ መከራ እና ምስቅልቅል ህይወት ውስጥ ይገኛል።

- በአሁን ጊዜ በርካታ የክልሉ አካባቢዎች በመንግስት እና የአማራን ህዝብ ጥያቄ ለማስመለስ ጫካ ገብተናል ባሉ ' ፋኖዎች ' መካከል በሚካሄድ በትጥቅ የታገዘ ጦርነት ፦
ንጹሃን ተገድለዋል።
ከ12 እስከ 13 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።
ከ3.6 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ከትምህርት ገበታቸው ውጭ ሆነዋል።
የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ክፉኛ ተጎድቷል።
የግል እና የመንግስት ተቋማት ከቦታ ቦታ ለመጓጓዝ ባለመቻላቸው አገልግሎት አሰጣት ክፉኛ ተዛብቷል።
ነፍሰጡር እናቶች በአግባቡ የአምቡላንስ አገልግሎት አያገኙም።
እናቶች እና ህጻናትን ጨምሮ ከጦርነት ተሳትፎ ውጭ የሆኑ ዜጎች ለከፋ የስነልቦና ጫና ተዳርገዋል።
እጋታ ተስፋፍቷል።
ዜጎች ያለ ከልካያ በጠራራ ጸሀይ ይዘረፋሉ፤ ይገደላሉ።
ታላላቅ ፕሮጀክቶች ተስተጓጉለዋል።
ህዝቡ ለሁለት ወገን ግብርና ቀረጥ ይከፍላል።

ይህ ጦርነቱ ካመጣቸው መዘዞች መካከል ነው።

- ችግሩን ለመቅረፍ በአዲስ አበባ እና ከባህር ዳር ከህብረተሰቡ የተውጣጣ ክፍል ውይይት አድርጓል። በውይይቶቹ የሀገሪቱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና የሲቪል አመራሮችም ተገኝተው ነበር።

- ጦርነቱ አሸናፊነት የሌለው የእርስ በእርስ ጦርነት ስለሆነ በንግግር በውይይት በድርድር ይፈታ የሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል።

- በክልል ፣ በሀገር ደረጃ በየትኛውም መንገድ ይሁን የአማራን ህዝብ ጥቅም ይዤ ነው የምዋጋው ከሚል ኃይል ጋር ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ድርድር እንዲደረግ የመፍትሄ ሀሳብ ተቀምጧል።

- መንግሥት አሸናፊ የሌለው ይሄ አውዳሚ ጦርነት በንግግር እና ድርድር ለመፍታት " ፍቃደኛ ነኝ ነገር ግን ፋኖ አደረጃጀቱና መሪው ብዙ ነው ለመደራደር አንድ መሆን አለባቸው " በማለቱ የድርድሩ ደረጃ ጊዜ ፣ ቦታ እና ተደራዳሪዎች ተለይተው ለንግግር እና ድርድር እንዲበቁ ይህ 15 አባላት ያሉት የሰላም ካውንስል ተመርጧል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የደቡብ ክልል ፈርሶ እንደ አዲስ የተዋቀሩት #ሁሉም አዳዲስ ክልሎች በጀት የሚደለደልላቸው በነበረው የድሮ ቀመር እንደሆነ ተገልጿል። ገንዘብ ሚኒስቴር #አዲስ_ቀመር የማዘጋጀት ምንም ስልጣን እንደሌለው ይህ ስልጣን የፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደሆነ አመልክቷል። የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የ2017 በጀት ረቂቅን ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባብራሩበት ወቅት ስለ አዳዲሶቹ ክልሎች…
የበጀት ጉዳይ !

" ' ቀመሩ እኔን ተጠቃሚ እያደረገኝ አይደለም ' የሚሉ ክልሎች እየመጡ ነው " - አቶ አገኘሁ ተሻገር

የፌዴሬሽን ም/ቤት በተለይም ከአዳዲሶቹ ክልሎች የድጎማ በጀት ቀመሩ እንዲሻሻል ጥያቄ እየቀረበለት መሆኑን የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናግረዋል።

አቶ አገኘሁ ፥ " ' ቀመሩ እኔን ተጠቃሚ እያደረገኝ አይደለም ' የሚሉ ክልሎች እየመጡ ነው ይሄ ቀመር እየጠቀመን ስላልሆነ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያሻሽልልን የሚል ጥያቄ እየተነሳ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

በመሆኑም ም/ቤቱ ጉዳዩን በልዩ ትኩረት ተመልክቶ እምርጃ መውሰድ እንዳለበት አስገንዘበዋል።

ይህ ካልሆነ ግን ፍትሃዊ እኩል የመልማት እድል ማረጋገጥ እንደማይቻል ተናግረዋል።

ለመጨረሻ ጊዜ የክልሎች የበጀት ድጎማ ቀመር የተሻሻለው በ2010 ዓ/ም ነበር። በወቅቱ 3 ዓመት ይቆያል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ፦
- የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ
- የግብርና እና የቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ መረጃዎች አለመሟላት ቀመሩን ለማሻሻል እንቅፋት ሆኗል።

ያለፉት 30 ዓመታት የበጀት ድጎማ ቀመር ለ9 ጊዜ ተሻሽሏል። የመጨረሻው ማሻሻያ 2010 ላይ ነበር።

በቅርቡ በድጎማ በጀት ቀመር  ዙሪያ በተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ፤ የደቡብ ክልል ፈርሶ እንደ አዲስ የተዋቀሩት ሁሉም አዳዲስ ክልሎች በጀት የሚደለደልላቸው በነበረው የድሮ ቀመር እንደሆነ ገልጸው ነበር።

ሚኒስቴሩ አዲስ ቀመር የማዘጋጀት ምንም ስልጣን እንደሌለው በመግለጽ   " ይህ ስልጣን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው " ሲሉ ተናግረው ነበር።

በአዳዲሶቹ ክልሎች ከበጀት ጋር በተያያዘ ፤ " የበጀት እጥረት " የሚሉ ጥያቄዎች እንደሚነሱ ይታወቃል።

የመንግሥት ሰራተኞች ደሞዝ መዘግየትና በአግባቡ አለመክፈልም በስፋትም ከአዳዲሶቹ ክልሎች የሚነሱ ጉዳዮች ናቸው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በአዲስ አበባ ፤ እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ የክረምት ወቅቱ ሳይጠናከር ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ከተማው አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። እስካሁን ባለው የፒያሳ እና የአራት ኪሎ መስመር እንዲሁም ከሜክሲኮ እስከ ሳር ቤት ያለው ተጠናቆ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተመርቋል። ከዚህ ቀደም ፦ - ከ4 ኪሎ - ፒያሳና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ…
#AddisAbaba

" በትልቅ ቁጠባ በ33 ቢሊዮን ነው እየተተገበረ ያለው " - ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፥ የከተማው 5ቱ ኮሪደር ስራ እየተተገበረ ያለው በ33 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህን የተናገሩት ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ነው።

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ፥ መጀመሪያ ላይ የ5ቱም ኮሪደር ስራ ሲጠና ኮንሰልታንቶችና አጥኚው ቡድን መንገድ እና የመንገድ መሰረተ ልማት የሚፈጀው ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ እንደገለጹ አስረድተዋል።

" ይህ እንግዴ በወቅቱ ጥናት ነው በዚህ ተለዋዋጭ ገበያ " ያሉት ከንቲባዋ " እስካሁን ድረስ የተጠኑትን 5 ኮሪደሮች እየተገበርን ያለነው በ33 ቢሊዮን ነው " ብለዋል።

በ33 ቢሊዮን ብር እየተተገበረ ያለው ስራም " ትልቅ ቁጠባ የተተገበረበት ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

ስራው ብክነትን በመከላከል፣ የሚወጣውን ወጪም አስፈላጊ ነገር ላይ ብቻ እንዲሆን እየተደረገ ነው ብለዋል።

አንዳንድ በከተማው አስተዳደር የሚሰሩ ስራዎችም ለኮንትራክተሮች እንዳልተሰጡ የተናገሩት ከንቲባዋ ፥ ለአብነት የሜክሲኮ መንገድ በኮንትራክተር ሳይሆን በራስ አቅም መሰራቱን ገልጸዋል።

#TikvahEthiopia
#AddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኳል። የተማሪዎቹ ውጤት ዛሬ ለተቋማቱ መላኩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል። በዚህም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። የዘንድሮው የመውጫ ፈተና ለ57 የመንግሥት እና ለ124 የግል ከፍተኛ የትምህርት…
#ExitExam

የግል የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት መቼ ይፋ ይሆናል ?

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2016 ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ውጤት ሰኔ 21/2016 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

በተመሳሳይ ጊዜ በአንድ ላይ የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤት ግን እስካሁን ይፋ አልተደረገም።

ይህን ተከትሎ የግል ተፈታኞች በርካታ ጥያቄዎችን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አድርሰዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልገሎት ዴስክን ጠይቀናል።

" ከግል ተፈታኞች ውጤት ጋር በተያያዘ ያልተጠናቀቁ ነገሮች በመኖራቸው ውጤቱ ይፋ አለመደረጉን " የዴስኩ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" ቀሪ መጠናቀቅ ያለባቸው ጉዳዮች እንዳለቁ የግል ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ይደረጋል " ብለዋል።

የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ገበየሁ በበኩላቸው ፥ " ከግል ተፈታኞች አጠቃላይ መረጃ እና ክፍያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሲጠናቀቁ ውጤቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚለቀቅ " ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ማኅበሩ 178 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በአባልነት ይዟል፡፡

የግል ተቋማት ተማሪዎች የፈተና ውጤት ለተቋማቱ አለመላኩን ከተቋማት በኩል ባገኘነው መረጃ የተረዳን ሲሆን ከሰሞኑን የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ተልኳል፣ እየተላከ ነው ፣ ውጤት ሊለቀቅ ነው " የሚሉ መረጃዎች ሀሰተኛ እንደሆነ ተገንዝበናል።

በሌላ በኩል ፥ በዚሁ ጉዳይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተማሪዎች ተወካይ አነጋግሯል።

ይኸው ተወካይ በውጤት ጉዳይ ከተማሪዎች ጫና ሲበዛ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር እንደሄደና አንድን ኃላፊ እንደጠየቀ የተሰጠው ምላሽም ፥ " ለመፈተኛ ይከፈል የተባለውን በክፍያ (በተማሪ 500 ብር) አጠቃለው ያልፈጸሙ ተቋማት አሉ " የሚል እንደሆነ ገልጿል።

ክፍያውን ሙሉ በሙሉ የከፈሉ እንዳሉ ሁሉ ያልከፈሉ በመኖራቸው ውጤቱ እንደዘገየ እንደተነገረው አስረድቷል።

ተማሪዎች የፈተናው ውጤት መዘግየቱ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳሳደረባቸው ተረድተናል።

ተማሪዎቹ ፥ " ያልከፈለውን አለማስፈተን ነው እንጂ የሚጠበቀውን ክፍያ ከፍሎ የተፈተነን ተማሪ ውጤት ማዘግየት እና ተማሪውን በጭንቀት ማሰቃየት ፍጹም ተገቢ አይደለም " ብለዋል።

ውጤታቸው በፍጥነት እንዲላክና እንዲገለጽ ሌላው ጉዳይ እነሱን የሚመለከት ባለመሆኑ ይህን ያህል ውጤት በመጠበቅ ለጨነቁ እንደማይገባቸው አስገንዝበዋል።

ዘንድሮ 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ማስፈተናቸው ይታወቃል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR " ... ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል " - የም/ቤት አባል የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? አቶ አብርሃም በርታ (የተ/ም/ቤት አባል) ፦ " ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እና አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጡት ሪፖርት ሙስና በሀገራችን ከአመት አመት እየጨመረ መምጣቱን ያሳያሉ። ይህን ስር የሰደደ መንግሥታዊ ሌብነት ወይም ሙስና…
የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና የተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አበባው ደሳለው ፦

" የመንግስት ኃላፊዎች በተለያየ ጊዜያት በተደጋጋሚ ስለ ሀገራዊ ምክክር እና ስለ ሽግግር ፍትህ ሲያነሱ ይደመጣል።

ነገር ግን ከሀገራዊ ምክክር እና ከሽግግር ፍትህ በፊት መቅደም ያለባቸው ነገሮች አሉ። ከነዚህ ውስጥ አንደኛውና ዋነኛው የእምነት ግንባታ ነው።

መንግስት በህዝብ ዘንድ እምነት አልገነባም ብለን እናስባለን። ይሄም የሚገናኘው ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር ነው።

ባለፉት 10 ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ሰበብ በማድረግ የመንግስት ኃይሎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል።

ከነዚህ ጥሰቶች ውስጥ የጅምላ ግድያ፣ በሰብዓዊ / ባልታጠቁ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል። በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች።

ጥቂቱን ለመጥቀስ በመርዓዊ ፣ በጅጋ ፣ በደብረ ኤልያስ ፣ በፍትኖተ ሰላም፣ ደብረሲና አካባቢ ፣ ጎንደር እና ወሎም እንዲሁ ተፈጽሟል።

ይህንንም የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ተቋማት የዘገቡት የአይን እማኞችም የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው።

ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጾታዊ ጥቃት፣ ድብደባ ፣ ዘረፋ ፣ ንብረት ማውደም ፣ የሲቪል ተቋማት በጤና ፣ በትምህርት ተቋማት ላይ ውድመት እንደደረሰ በርካታ ምስክሮች ገልጸዋል።

ሌላው የሰብዓዊ መብት ችግር በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ምክንያት በርካታ ፖለቲከኞች የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ታስረዋል።

ከዚህ ባለፈ ጋዜጠኞች፣ አንቂዎች፣ አጠቃላይ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በተለይ በአማራ ክልል አማራዎች በጅምላ ለወራት በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ።

የምክር ቤት አባላትን ስናነሳ የምክር ቤት አባላችን አቶ ክርስቲያን ታደለ የመንግስት ወጪ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆኖ መንግስትን ከምዝበራ ያዳነ በሰላማዊ ትግልም በእጅጉ የሚያምን ሰው ነው አንድ አመት ለሚሞላ ጊዜ በእስር እየማቀቀ ያለው።

ሌሎችም በለውጡ ከእርሶ ጋር አብረው የሰሩ እንደ አቶ ዮሐንስ ቧያለው ፣ ዶ/ር ካሳው ተሻገርና አቶ ታዬ ደንደአ ያሉም ለውጡ ስህተት ፈጽሟል በትክክለኛው ጎዳና እየሄደ አይደለም ብለው ስለሞገቱ ብቻ ለወራት ታስረዋል።

ከዚህ የከፋው ግን የት እንኳን እንደታሰረ የማይታወቅ አንድ የአብን አባላችን ነው ሀብታሙ በላይነህ ይባላል።

ሀብታሙ በላይነህ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ነው። እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ መምህር ነው። ላለፉት 4 ወራት የት እንደገባ አይታወቅም። ይህን ጉዳይ ቤተሰቡም እኔም ለተለያየ የመንግስት ኃላፊዎች አቤት ብለናል ምላሽ አላገኘንም። ዛሬ እርሶ ምላሽ ይሰጡናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፤ እንማጸናለን።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ልክ እንዳበቃ ህጋዊ አሰራሩ ይቀጥላል ብለን እንገምት ነበር ነገር ግን አዋጁ አብቅቶ በኮማንድ ፖስቱ እየተዳደርን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።

የጅምላ እስር አሁንም አለ፣ ህገመንግስቱ በትክክል እየሰራ አይደለም። በደረቅ ወንጀል የተከሰሱ ሰዎች ብቻ መጠየቅ ሲገባቸው አሁንም በፖለቲካ አመለካከታቸው ዜጎች በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ።

ስለዚህ ህብረተሰቡ ስለ ሽግግር ፍትህና ስለ ሀገራዊ ምክክር መንግስት ሲያወራ ይመነው ? እምነት አልገነባንም።

በጅምላ የታሰሩ፣ የህሊና እስረኞች ቢፈቱ፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መርምረው አጥፊዎች ተጠያቂ እዲሆኑ ቢደረግ ያኔ እምነት መገንባት ይቻላል።

መንግስት ምን እቅድ አለው እምነት ለመገንባት ? የህሊና እስረኞችን ለመፍታት እና የጅምላ ግድያና ሌሎች ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማቆም ምን ወስኗል ? "

#TikvahEthiopia
#HoPR

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrAbiyAhmed ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኑሮ ውድነትን በተመለከተ ለተጠየቀው ጥያቄ ምን መለሱ ? " የኑሮ ውድነት የበርካታ ሀገራት ፈተና ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በአንዳንድ ሀገራት ከ60 በመቶ በላይ የደረሰ የዋጋ ንረት እየተመዘገበ ነው፡፡ በኢትዮጵያም የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ መንግስት በርካታ ኢንሸቲቮችን ቀርጾ እየሰራ ነው፡፡ በተለይ የሌማት ትሩፋት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት…
ስለ ኑሮ ውድነት ...

" ልማትን የሚያፋጥን መንግስት እዛው ላይ እያለ የኑሮ ውድነትን መቆጣጠር በጣም ፈታኝ ነው " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ስለ ኑሮ ውድነት ምን አሉ ?

" የኑሮ ውድነት ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የሁሉ ዓለም ዋነኛ አጀንዳ ነው።

የኑሮ ውድነት የበርካታ ሀገራት ስብራት፣ ጭንቀት ፣ ውጥረት እንደሆነ መገንዘብ ይገባል። የተለየ ለኢትዮጵያ ብቻ የሆነ ችግር አይደለም።

በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚሰሩ የፋይንናንስ ባለሞያዎችን ለማነጋገር ሞክረናል።

ችግሩን ምን ብናደርግ ነው የምንፈታው ? ብለን።

ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ሁኔታ ልማትን የሚያፋጥን መንግስት እዛው ላይ እያለ የኑሮ ውድነትን መቆጣጠር በጣም ፈታኝ ነው።

የኮሪደር ልማት ፣ ህዳሴ ግድብ ምናምን እያልን እዛው ላይ እያለ ኑሮ ውድነትን መቆጣጠር ያስቸግራል ፤ ምክንያቱም በርከታ ሀብት ስለሚፈስ።

ኢንፍሌሽንን ለመቀነስ አንዱ መንገድ እየተፋጠነ ያለውን ልማት መግታት ነው ልማቱን ብንገታው በሌላ መንገድ ከኑሮ ውድነት ያላነሰ የስራ አጥነት ችግር ስላለ አንደኛውን ብንፈታው አንደኛው ቁስል መልሶ ጠልፎ ስለሚይዘን ይሄን ባላንስ አድርጎ ልማትም ሳናስቆም ስራ አጥነትንም ለመቀነስ እየሞከርን ኢንፍሌሽን መቀነስ ቀላል ጉዞ አልነበረም።

የብዙ አማካሪዎች ፣ የሞያተኞችም ምክር የነበረው ያለው መፍትሄ አንድ ብቻ ነው በፍላጎት እና አቅርቦት መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ ነው።

ይህን ለማድረግ ደግሞ ምርታማነትን ማሳደግ ነው። "

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና የተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አበባው ደሳለው ፦ " የመንግስት ኃላፊዎች በተለያየ ጊዜያት በተደጋጋሚ ስለ ሀገራዊ ምክክር እና ስለ ሽግግር ፍትህ ሲያነሱ ይደመጣል። ነገር ግን ከሀገራዊ ምክክር እና ከሽግግር ፍትህ በፊት መቅደም ያለባቸው ነገሮች አሉ። ከነዚህ ውስጥ አንደኛውና ዋነኛው የእምነት ግንባታ ነው። መንግስት በህዝብ…
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ታሳሪዎች ምን አሉ ?

" 4 ኪሎ ተቀምጦ ' ጉዞ ወደ 4 ኪሎ'  ከሚሉ 4 ኪሎ ተቀምጠው ጉዞ ወደ ፓርላማ እያሉ በሰላም ቢታገሉ ችግር የለብኝም " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፦

" እስረኛ መፍታት ላይ እኛ እንታማለን ? ' እንዴት እስረኛ ትፈታለህ ? ' ተብለን ስንገመገም እና ስንወቀስ እንዳልነበረ።

ያልፈታነው ጉድ አለ እንዴ ? እስር ቤቱን በሩን ከፍተን ነው የለቀቅነው። በዚህ እንኳን አንታማም።

ከዚህ ፓርላማ የታሰሩት ወንድማችንን በተመለከተ (አቶ ክርስቲያንን ማለታቸው ነው) ሁሉም ተቃዋሚ የሚታሰር ከሆነ ጠያቂዬ (አቶ አበባውን ማለታቸው ነው) ለምን አልታሰሩም ?

ጠያቂዬ ተቀምጠው እየጠየቁ ነው እዚህ።

እርሶን የሚያስቀምጥ እሳቸውን የሚያሳስር ነገር ካለ ልዩነት አለ ማለት ነው። ልዩነቱን ግን እኔ ዳኛ አይደለሁም። ወንጀለኛ ናቸው ፣ ጥፋተኛ ናቸው ልል አልችልም። የፍትሕ ስርዓቱ አይቶ መርምሮ ፈትሾ ፍርድ ይስጥ።

የግል ምኞትህ ያሉኝ እንደሆነ እርሶም እርሳቸውም ከእርሶ ጎን ተቀምጠው ባያቸው ደስታውንም አልችለውም።

በሰላማዊ መንገድ 4 ኪሎ ተቀምጦ ' ጉዞ ወደ 4 ኪሎ'  ከሚሉ 4 ኪሎ ተቀምጠው ጉዞ ወደ ፓርላማ እያሉ በሰላም ቢታገሉ ችግር የለብኝም።

የግል ጥላቻ የለኝም። የግል መግፋትም የለብኝም።

ህግ ከፈታቸውና ከኛ መካከል ቢሆኑ ደስታውን አልችለውም። ነገር ግን ሁላችንም ማወቅ ያለብን ፦
- የፓርላማ አባል መሆን
- ጋዜጠኛ መሆን
- ሚኒስትር መሆን
- ማዕከላዊ ኮሚቴ መሆን ከወንጀል እና ከጥፋት አይታደገንም። አለማጥፋት ነው።

የኔ ዋስትና አለማጥፋት ነው። ካጠፋው እመጣለሁ ያለመከሰስ መብቴ ይነሳል እጠየቃለሁ።

እዚህ አካባቢ ላይ መቀመጥ ለማንኛውም ጥፋት ዋስትና አድርገው ፤ ዝም ብሎ መንገደኛ ይነሳና ዩትዩብ ከፍቶ ጋዜጠኛ ነኝ የሚለው እንደዛ ትክክል አይደለም።

ጋዜጠኛም ህግ አለው ፣ ወታደርም ቢሆን ህግ አለው መጠየቅ አለበት ፣ ሚኒስትርም ህግ አለው።

በዚህ አግባብ ማየት ካልቻልን ስራችንን ቆርጠን ጥለነው በኋላ የማንጠግነው ነገር ይፈጠራል። "

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia