TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ‼️

በቁጥጥር ስር ስለ ዋሉ ግለሰቦች የፌደራል አቃቤ ህግ በመግለጫው ካነሳቸው #አንኳር ነጥቦች መካከል፦

• ምርመራው ከ5 ወር በላይ ፈጅቷል። የዚህ ምክንያቱም በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦችን አስረን ከማጣራት አጣርተን ለማሰር ስለሞከርን ነው። ማንንም ተጠርጣሪ ሳንይዝ ነው ያጣራንው።

• በቁጥጥር ስር ከዋሉ ገለሰቦች መሀል የተሰጣቸውን ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው ያለአግባብ ሀብት ያከማቹ፣ ሀብት ያሸሹ፣ በሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ የተሳተፉ፣ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የተከሰቱ ብጥብጦች ያስተባበሩ ይገኙበታል።

• በብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አባላት መካከል በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በስውር እስር ቤት ግለሰቦችን በማሰር እና በማሰቃየት ተጠርጥረው የተያዙ አሉ። በአዲስ አበባ ብቻ ከሰባት በላይ እስር ቤቶች ተገኝተዋል።

• በሰብአዊ መብት ጥሰት ጠጠርጥረው ከተያዙ ግለሰቦች መሀል ግለሰቦችን ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት እራሳቸውን እንዲያገሉ ማድረግ እና ማሰቃየት፣ በአንቡላንስ እያፈኑ ሰዎችን መሰወር፣ ህገወጥ መሳሪያዎችን የራሴ ነው ብሎ እንዲፈርሙ ማድረግ፣ የብልት ቆዳዎችን በፒንሳ መሳብ፣ ጫካ ማሳደር፣ ከአውሬ ጋር ማሰር፣ አፍንጫ ውስጥ እስክርቢቶ መክተት፣ ግብረሰዶማዊ ጥቃት መፈፀም፣ ሴቶችን መድፈር የመሳሰሉ አረመኔያዊ ድርጊቶችን ፈፅመዋል

• የሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት በዋናነት የተቀነባበረው የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አባል በሆኑ ግለሰብ ነው።ኬንያ ከምትገኝ ገነት ቶሎሺ ከተባለች ግለሰብ ጋር በመሆን ነበር፡፡

• ሜቴክን በተመለከተ፤ የውጪ ሀገር ግዥዎችን ያለጨረታ መስጠት፣ ግዥ አፈፃፀሙ ከኮርፖሬሽኑ የበላይ አመራሮች ጋር የጥቅም ትስስር ያላቸው ሰዎች የድለላ ስራ ሰርተው የሚከፈላቸውና እነዚህ የውጪ ኩባንያዎችን የሚያመጡት ደላሎች በስጋ ዝምድና ለአመራሩ ቅርብ የሆኑ ናቸው። እነዚህ በድለላ ያሉ ሰዎች በሀገር ውስጥ ካካበቱት ሃብት በላይ ወደ ዉጪ ሃብት አሽሸዋል። ከመደበኛው ዋጋ እስከ 400% ተጨማሪ ዋጋ እየተጨመሪ ግዢ ይፈፀም ነበር።

• የሀገር ውስጥ ግዢም በግልፅ ጨረታ መፈፀም ሲገባው እስካሁን በዚህ መልኩ የተፈፀመ የለም። ከኮርፓሬሽኑ አመራሮች ጋር የዝምድናና የጥቅም ትስስር ካላቸው ሰዎች በብዙ እጥፍ በተጋነነ ዋጋ ይገዛ ነበር። ከአንድ ድርጅት 21 ጊዜ፣ ከሌላው ደግሞ 15 ጊዜ ግጭ ተፈፅሟል። ከአንድ ድርጅት በአንድ ጊዜ ብቻ የ2015 ሚሊዮን ብር ግዢ ያለጨረታ ተፈፅሟል።

• ከተቋሙ ተልዕኮ ውጪ የተፈፀሙ ግዥዎችም አሉ። ከዚህም ውስጥ የመርከብ ግዢ ይገኝበታል። በማይመለከተውም ስራ ገብቶ ወደ
ንግድ ስራ አስገብቷቸዋል።

ምንጭ፦ EPRDF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#FDREDefenseFORCE የህወሓት አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ የ10 ሚልዮን ብር ሽልማት ማዘጋጁትን የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ማስታወቁን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ሌ/ጀነራል አስራት ዴኔሮ እንደተናገሩት የህወሓት አመራሮችን በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሽልማቱ መዘጋጀቱን ገልፀዋል። በዚህም የመከላከያ ሠራዊት በህግ የሚፈለጉትን የህወሓት አመራሮች…
#FDREDefenseForce

መከላከያ ሰራዊት በህግ እየፈለጋቸው የሚገኙት የህወሓት #አንኳር አመራሮች መበታተናቸውን አሳውቋል።

ሰራዊቱ የህወሓት አመራሮች የተደበቁበትን ለጠቆመው 10 ሚሊዮን ብር ማበረታቻ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ጥቆማ ለሚያደርሰው አካል ደህንነቱ ተጠብቆ ማበረታቻው በሚስጥር ይሠጠዋል ብሏል።

ሀገር መከላከያ ሰራዊት እየፈለኳቸው ነው ያላቸውን የህወሓት አንኳር የነበሩትን አመራሮች የተደበቁበትን በአካል መጠቆም እንደሚቻልም ገልጿል።

በተጨማሪ የጥቆማ መቀበያ ስልክ ቁጥሮች ይፋ አድርጓል፦ 09 43 47 13 36 እና 012 5 50 43 48

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Amharic-Executive-Summary-AAIR.pdf
399.8 KB
#Update

በኢትዮጵያ የአፋር እና አማራ ክልሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶች ላይ የተደረገ የምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆኗል።

የምርመራ ሪፖርቱ #አንኳር_ጉዳዮችን በPDF (399.8 KB) ከላይ ያንብቡ።

@tikvahethiopia
#Amhara

ዛሬ በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የውይይት መድረኮች ሲካሄዱ መዋላቸውን ከመንግሥታዊ የዜና አውታሮች የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።

ውይይቶቹ የተመሩት ከፌዴራል እና ከሌሎች የሀገሪቱ ክልል በመጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት ነበር።

በዋነኝነት ትኩረት ያደረገው በክልሉ ያለውን ችግር ለማዳመጥና የመፍትሄ ሃሳቡን ከህዝቡ ለመረዳት ነው ተብሏል።

ባለስልጣናት በነዚህ መድረኮች ላይ ክልሉ በሰላም እጦት በሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ እየከፈለ ስላለው ዋጋና እየደረሰ ስላለው ጫና ሲናገሩ ተደምጠዋል።

መንግሥት ለዘላቂ ሰላም ጥረት እያደረገ መሆኑንና ይህንንም ህዝቡ ሊደግፍ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ጥያቄዎችን በሃይል አማራጭ ለመፍታት መሞከር ውጤት እንደሌለውና ክልሉን ወደ ባሰ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ እንደሚከት ጠቁመው ፤ ሰላማዊ መንገድ መከተል ዓይነተኛ መፍትሄ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ለጥያቄዎች ከትጥቅ ትግል ይልቅ በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋብ።

በተለይ በባህር ዳር ነበረ የውይይት መድረክ የክልሉ ህዝብ በተደጋጋሚ የሚያነሳቸው ፦
የወሰንና የማንነት፣
የፍትሃዊ ተጠቃሚነት
ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በሰላም የመኖር መብት ሌሎች ጥያቄዎች ታውቀው ያደሩ መሆናቸውና በቀጣይ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ መንግስት እየሰራ ነው ብለዋል።

ዛሬ ውይይት እንደተደረገባቸው ከተሰሙት አንዷ በሆነችው ደሴ የተገኙ ተሳታፊዎች ፤ የእርስ በእርስ ግጭቱ እያደረሰ ካለው ጉዳት በተጨማሪ፦
የኑሮ ውድነት
የሥራ አጥነት
የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና ሌሎችም ተዳምረው ህብረተሰቡን ለከፍተኛ እንግልት መዳረጉ ተነስቷል።

የአማራ ህዝብ #አንኳር ጥያቄዎች በተገቢው ጊዜ እና ፍጥነት መመለስ ባለመቻሉ ዛሬ ለተደረሰው የሰላም እጦት ምክንያት መሆናቸውን ተሳታፊዎች አንስተዋል።

በመንግሥትና በታጣቂ ኃይሎች መካከል ሀቅ ላይ የተመሰረተ በእውነትም ሀገርን ከትርምስ ሊያወጣ የሚችል ውይይት ማድረግ እና ክልሉም አሁን ካለበት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማውጣት እንደሚገባ ተነስቷል።

ዛሬ በተመሳሳይ ጊዜ ውይይት ተደርጎባቸዋል ከተባሉ ከተሞች መካከል ባህር ዳር፣ ደሴ፣  ወልድያ፣ ደባርቅ፣ ደብረ ታቦር፣ እንጅባራ፣ ሰቆጣ ከተሞች ይጠቀሳሉ።

በአማራ ክልል ከተሞች በነበሩት መድረኮች ላይ ፦ የሶማሌ ፣  የኦሮሚያ ፣ የሲዳማ ፣ የሐረሪ፣ የቤኒሽንጉል ጉሙዝ ክልሎች ፕሬዜዳንቶች እንዲሁም የአዲስ አበባ ከንቲባ ተገኝተው ነበር።

የሀገር መከላከያ ፣ የገንዝብ ፣ የሥራ እና ክህሎት ፣ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሮችን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል አመራሮችም ተገኝተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

ከዚህ ቀደም በክልሉ ከተሞች መሰል የውይይት መድረኮች ሲዘጋጁ የነበረ ቢሆንም በአንድ ጊዜ በዚህ ልክ ከፍተኛ እና የክልል አመራሮች ወደ ክልሉ ከተሞች ውይይት ሲቀመጡ ይህ የመጀመሪያ ነው።

የአማራ ክልል በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ቦታዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይል እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄዱ ግጭቶች ከግጭቱ ተሳታፊዎች ባለፈ ንፁሃን ሰለባ እያደረጉ፣ ወጥቶ ለመግባት ፣ ለንግድ ፣ ለቱሪዝምም ትልቅ እንቅፋት እየሆኑ እንዳለ በተደጋጋሚ ተነግሯል።

@tikvahethiopia