TIKVAH-ETHIOPIA
1.37M subscribers
54.4K photos
1.34K videos
197 files
3.61K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ኤርሚያስ አመልጋ ከእስር አልተፈቱም! [ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8] መንግስት ክሳቸው አንዲቋረጥ ካደረገላቸው 63 ተከሳሾች ውስጥ እስካሁን ያልተፈታው ኤርሚያስ አመልጋ ብቻ መሆኑ ተገለጸ። ክሳቸው ከተቋረጠላቸው ሰዎች ውስጥ እስካሁን 62ቱ ከእስር መለቀቃቸውን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አስታውቋል። ኤርሚያስ አመልጋ ምህረት ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል አንዱ ቢሆኑም እስካሁን…
62 ግለሰቦች ከእስር ተለቀዋል ?

ዛሬ ጥዋት የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 በሰጠው መረጃ ክሳቸው ከተቋረጠላቸው ሰዎች ውስጥ እስካሁን 62ቱ ከእስር ተለቀዋል፤ የሚቀሩት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ብቻ ናቸው ቢሉም ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሌሎች ግለሰቦችም ከእስር እንዳልተፈቱ አረጋግጧል። የግለሰቦቹ የቅርብ ሰዎች የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት እንደነገሩን ከሆነ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ተቋም ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የሰጠው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በአዲስ አበባ ከተማ የከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሰዓት ማሻሻያ እንደተደረገበት የከተማ አስተዳደሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

በአዲሱ ማሻሻያ ከባድ ተሽከርካሪዎች ጠዋት ከ1-3 ሰአት እንዲሁም ከሰዓት ከ 10:30-12:00 ውጪ ባሉ ሰዓቶች እንዲንቀሳቀሱ ተወስኗል።

እስካሁን በነበረው ህግ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ከባድ ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ብቻ ነበር መንቀሳቀስ የሚፈቀድላቸው።

#MayorOfficeAA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
የብስክሌት ትራንስፖርት መንገድ🤔 በየት በኩል ነው ብስክሌት ተገልጋይ የሚያልፈው ? ለብስክሌት ነው የተሰራው ወይስ ለመኪና ማቆሚያ ? ይህን ነገር የታዘቡት የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሚሰሩትን መልካም ስራዎች እንደራሳችን አድርገን መጠበቅ ካልቻልን በምንፈልገው ያህል ማደግ አንችልም ብለዋል። ህብረተሰቡ ቢያንስ የሚሰሩ ስራዎችን የመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል። ቪድዮው ትላንት ምሽት የቲክቫህ…
መንግስት ሰርቶ ዞር ማለቱ ተገቢ አይደለም!

በአዲስ አበባ ከተማ ጀሞና ለቡ አከባቢ ለብስክሌት መተላለፊያ ተብሎ የተሰራው መንገድ 2 ሳምንት እንኳ ሳይሞላው ቦታ ላይ እየደረሰ ያለው ውድመት አሳዛኝ ነው ሲሉ የቲክቫህ ቤተሰቦች ትዝብታቸውን አካፍለዋል፦

- ብሎኖቹን እየተፈቱ ነው።

- አሽከርሻሪዎች እየገጩ ይጥላሉ።

- በለቡ አከባቢ የባጃጅ ማጠቢያም ሆኗል።

- በግለሰቦች እየተቀሉ ነው።

ይህ ሁኔታ መንግስት ሰርቶ መሄድ ብቻ ሳይሆን አስፈላጊውን ክትትል እንዲያደርግና ህዝቡም ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራት እንዳለበት የሚያሳይ ነው። ሚዲያዎችም በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል።

ሌሎች አስተያየታቸውን ያካፈሉ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ይህ ገንዘብ ወጪ ተደርጎበት የተሰራው ስራ ምን ያህል ታስቦበታል፤ ምን ያህልስ አገልግሎት ይሰጣል የሚለው በጥልቀት ተጠንቶ መሰራት ነበረበት ብለዋል።

ለመኪና እንኳን መንገዱ እንደሚጠብ የሚያነሱት ቤተሰቦቻችን ከተሰራ በኃላ ደግሞ በቂ ግንዛቤ የማስጨበጫ ስራ መስራት ያስፈልግ ነበር ፤ ህብረተሰቡም እንደራሱ ንብረት ሊጠብቅ ይገባው ነበር ሲሉ ገልፀዋል።

በተለይ የብስክሌት ተጠቃሚዎች አስተያየት አካፍሉ @tikvahethiopiaBot

#TikvahFamily

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#NewsAlert

የኢራን ምክትል ፕሬዘዳንት Masoumeh Ebtekar በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] መጠቃታቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።

ከቀናት በፊት የኢራን ምክትል ጤና ጥበቃ ሚንስትር ኢራጅ ሀሪርቺ ኮሮና ቫይረስ [#COVID19] እንዳለባቸው መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙርያ የሚያደርጉትን ድርድር የአሜሪካ መንግሥት ቀደሞ በታዛቢነት አሁን ደግሞ በአደራዳሪነት መግባቱን በመቃወም በአሜሪካ፣ ዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።

የሰልፉ አስተባባሪ እና የዲሲ ግብረ ኃይል ተወካይ አቶ ጣሰው መላከሕይወት ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ዋነኛ ጥያቄያቸው አሜሪካ ከአደራዳሪነት እንድትወጣ ነው። አሜሪካ እንዲሁም የዓለም ባንክ ከአደራዳሪነት ወደ ታዛቢነት እንዲመለሱ እንደሚፈልጉም አክለዋል።

"ሰልፉን የጠራነው የአሜሪካ መንግሥት ቀደም ሲል በታዛቢነት አሁን ደግሞ በአደራዳሪነት ለመግባት ኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ተጽዕኖ እየፈጠረ ስለሆነ፤ ያንን ተጽዕኖ ከኢትዮጵያ እንዲያነሳ ለመጠየቅ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፦

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ክልል የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያትም የነበረ ተጠርጣሪ በህብረተሰቡ ጥቆማ ተይዞ በምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው በተለምዶ ጨው በረንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተያዘው ተጠርጣሪ በሀሰተኛ መንገድ ካዘጋጃቸው፦

- መንጃ ፍቃዶች፣
- የትምህርት ማስረጃዎች፣
- የተለያዩ ማህተሞች ፣
- ፓስፖርቶች፣
- ቲተሮች፣
- የልደት ካርዶችና ሌሎች የተለያዩ ሰነዶች እንዲሁም ለማተሚያነት ከሚጠቀምበት ኮምፒዩተርና የማሸጊያ ማሽን ጋር በህብረተሰቡ ጥቆማ ሊያዝ ችሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የምዕራብ ጎንደር ዞን የቋራ ወረዳ የጸጥታ ሁኔታ...

የምዕራብ ጎንደር ዞን የቋራ ወረዳ የጸጥታ ምክር ቤት በወረዳው ያለውን የጸጥታ ሁኔታ የገመገመ ሲሆን ወረዳው ሰላማዊ የሆነ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን በቀረበው ሪፖርት ማረጋገጥ ተችሏል።

የፀጥታ ምክር ቤቱ የቀረቡትን ሪፖርቶች ከገመገመ በኋላ የወረዳውን ሰላም አጠናክሮ ለማስቀጠል ያመች ዘንድ መከናወን ያለባቸውን ተግባራት እንደሚከተለው አስቀምጧል:-

- ቁልፍና ንዑሳን በሮች እንዲሁም ኬላዎች እንዲጠበቁ

- የከተማ ፖትሮል የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል

- የወረዳው ጥምር ሀይል ተግባሩን ከዚህ እንደቀደመው በቁርጠኝነት እንዲፈጽም

- በኢንቨስትመንት ቀጠና ችግር እንዳይፈጠር ከወዲሁ በእቅድ የተደገፈ ዝግጅት እንዲደረግ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን እነዚህንና ሌሎች ተያያዥ የጸጥታ ተግባር በመገምገም ስብሰባውን አጠናቅቋል።

[የቋ/ወ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የትግራይ ክልል መንግስት 2 ሺህ 332 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ! የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 2 ሺህ 332 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል። ታራሚዎች ይቅርታ የተደረገላቸውም የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) 45ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ነው ተብሏል። #ኤፍቢሲ @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
25 ኤርትራውያንም በይቅርታ ከሚፈቱት ውስጥ ናቸው...

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 2 ሺህ 332 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ ማስታወቁ ይታወቃል በይቅርታ እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው ታራሚዎች መካከል 25 ኤርትራውያን ይገኙበታል።

#MillionHaileseilase
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ሼር #SHARE

የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች፦

COVID-19 በትኩሳት እና ደረቅ ሳል ይጀምራል። ከሳምንት በኋላ የመተንፈስ ችግር ያጋጥማል። በበሽታው የተያዘ ሰው እስከ 14 ቀናት ምንም አይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል። አንዳንድ ሰዎች የበሽታ ምልክት ሳያሳዩ በሽታውን ሊያስተላልፉ ይችላሉ።

ኮሮና ቫይረስ መድሃኒት አለው?

ቫይረሱን ከሰውነት ውስጥ የሚያስወግድ መድሃኒት የለም። ሃኪሞች በሽተኞችን እያከሙ የሚገኙት የታማሚዎችን የበሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ በማድረግ ነው።
ለመተንፈስ የሚረዱ ቁሶችም ጥቅም ላይ ይውላሉ።

እራሴን ከቫይረሱ እንዴት ነው መጠበቅ የምችለው?

የዓለም ጤና ድርጅት የሚከትሉትን እንዲያደርጉ ይመክርዎታል፦

- እጅዎን ይታጠቡ- ቫይረሱን ሊገድሉ በሚችሉ ሳሙናዎች

- በቫይረሱ የተበከሉ ነገሮችን ሊነኩ ስለሚችሉ፤ በእጅዎ ዓይን፣ አፍ እና አፍንጫዎን ከመነካከት ይቆጠቡ።

- ወደ የሚያስነጥሱ፣ የሚያስሉ እና ትኩሳት ወዳለባቸው ሰዎች አይጠጉ። ቢያንስ የ1 ሜትር እርቀት ይፍጠሩ።

- ሲያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍ እና አፍንጫዎን ይሸፍኑ - ከዚያም እጅዎን ይታጠቡ። ይህን ማድረግዎ በቫይረሱ ተይዘው ከሆነ የማሰራጨት ዕድልዎን ያጠባሉ።

በቫይረሱ እርሶ ወይም ሌሎች መያዛቸውን ከተጠራጠሩ፦ እራሰዎን ያግልሉ፤ በቤትዎ ይቆዩ ሌሎችም ተመሳሳይ እንዲያደርጉ የበኩልዎን ይወጡ። 8335 ላይ በመደወል ለማሕብሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በፍጥነት ያሳውቁ።

ምንጭ፦ BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ናይጀሪያ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ሰው የተገኘባት ሶስተኛዋ አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች። የቫይረሱ ተጠቂ የሆነው ግለሰብ ጣሊያናዊ ዜግነት ያለው ሲሆን፥ ናይጄሪያ ውስጥ የሚሰራና ከሶስት ቀን በፊት ከሚላን ወደ ሌጎስ የመጣ ነው ተብሏል።

የናይጄሪያ ጤና ሚኒስቴር ባለስልጣናትም ግለሰቡ ሌጎስ በሚገኝ የሕክምና ተቋም ክትትል እየተደረገለት መሆኑን ገልጸዋል። ከታማሚው ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባሉ ሰዎችን መለየት መጀመራቸውንም ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።

መንግስትም የአስቸኳይ ጊዜ ዘመቻ እቅድ አውጥቶ ወደ ስራ ገብቷልም ነው ያሉት። ከዚህ ቀደም ግብፅ እና አልጄሪያ የቫይረሱ ተጠቂ የተገኘባቸው ሃገራት ነበሩ።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

"የኮሮና ቫይረስ አስጊ የሚባል ደረጃ ላይ ደርሷል" – ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

የኮሮና ቫይረስ አስጊ የሚባል ደረጃ ላይ እና ዓለም አቀፍ ስጋት ሊሆን የሚችልበት አቅም ላይ መድረሱን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገለፁ።

የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አስተያየት የተሰማው በተለያዩ የዓለም ሀገራት እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት ነው። ባለፉት ሁለት ቀናት ከቻይና በበለጠ በሌሎች ሀገራት አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸውም ተጠቁሟል።

በአሁኑ ወቅት ከቻይና ውጭ ኢራን እና ጣሊያን የቫይረሱ መገኛ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፥ ቫይረሱም ከእነዚህ ሃገራት ወደ ሌሎች ሀገራት በሚያቀኑ ሰዎች አማካኝነት እየተሰራጨ ነው ተብሏል። ዶ/ር ቴድሮስ በሰጡት አስተያየት በቀሪው ዓለም እየታየው ያለው ነገር አሁን ላይ ትልቅ ትኩረት የምንሰጠው ነው ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ የዓለም መንግስታት ቫይረሱን ለመቆጣጠር በፍጥነት እና በጥንካሬ ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባም አሳስበዋል። ወቅቱ የፍርሃት ሳይሆን ቫይረሱን የመቆጣጠር እና የሰዎችን ህይወት የምናተርፍበት ጊዜ ነውም ብለዋል ዶክተር ቴድሮስ በንግግራቸው።

#ቢቢሲ #ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ዓለም አቀፍ መረጃ፦ - የሟቾች ቁጥር 2,807 ከፍ ብሏል - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 82,220 ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,807 የደረሰ ሲሆን 82,220 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 32,914 ደርሰዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ዓለም አቀፍ መረጃ፦

- የሟቾች ቁጥር 2,859 ከፍ ብሏል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 83,706

ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,859 የደረሰ ሲሆን 83,706 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 36,636 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ አይ ዲ) ጋር የ30 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ።

የድጋፍ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እና በኢትዮጵያ የዩኤስ አይ ዲ ዳይሬክተር ሲን ጆንስ ተፈራርመውታል።

ድጋፉ ቦርዱ ቀጣዩን ሃገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ተአማኒ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ለማከናወን እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ይውላል ተብሏል።

#ETHIOFM107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

አጫጭር መረጃዎች ከቢቢሲ፦

- ጃፓን እና ኢራቅ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በማሰብ ትምህርት ቤቶችን ዘግተዋል። ይህ በቻይና የተለያዩ አካባቢዎችም ተተግብሯል።

- ሳውዲ አረቢያ ለመንፈሳዊ ጉዞ ማንም አይምጣ ስትል እገዳ የጣለች ሲሆን እገዳው ቀጣዩን የሃጅ ጉዞ ይመልከት አይመልከት አልታወቀም።

- ኢራን ዜጎቿ የሚያደርጓቸውን አላስፈላጊ የአገር ውስጥ ጉዞዎች እንዲሰርዙ ያሳሰበች ሲሆን በመዲናዋ ቴህራን እና በሌሎች ከተሞች የአርብ ፀሎትን ሰርዛለች።

-አውስትራሊያ ከቻይና የሚነሱ ተጓዦች ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ አግዳለች።

- በቫይረሱ 17 ሰው የሞተባት ጣልያን 11 ከተሞችን ዘግታለች።

- ግሪክ ፌስቲቫሎችን በሙሉ ሰርዛለች።

#BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

አስረኛው የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች የጋራ ጉባኤ ዛሬ በሰመራ ከተማ ተጀመረ። በጉባኤው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች፣ የዘጠኝ ክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ፖሊስ ኮሚሽነሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከቲክቫህ ኢትዮ. መከላከያ ሰራዊት አባላት፦

የደቡብ ዕዝ ስታፍ የሰራዊት አባላት በቶጋ ካምኘ የተሰራዉ የሰራዊቱ መናፈሻ ጋርደን እንዳስደሰታቸዉ እና ከስራ መልስ አረፍ ሲሉ ጥሩ ስሜት እንደፈጠረላቸዉ ገልፀውልናል። መናፈሻውን ከላይ በፎቶው ትመለከቱት ዘንድም አጋርተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia