TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.36K videos
198 files
3.63K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኬንያ ናይሮቢ፣ ሞምባሳን ጨምሮ በተለያዩ የኬንያ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች መደረግ ጀምረዋል። በወጣቶች መሪነት እየተካሄዱ ባሉት በነዚህ ሰልፎች ላይ መንግሥት ተጨማሪ ታክስ ለመጣል ያረቀቀውን የፋይናንስ ረቂቅ አዋጅ ሙሉ በሙሉ እንዲተወው እየተጠየቀበት ነው። መንግሥት በረቂቁ ላይ አንዳንድ ማሻሻያ አደረጋለሁ ቢልም ተቃዋሚዎች ግን " የምን አንዳንድ ነው ? ሙሉ ረቂቁን ተወው " የሚል አቋም እንደያዙ…
#Update

በኬንያ ተቃውሞ ሰዎች ተገደሉ።

የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግሥት ያረቀቀውን አዲስ የታክስ ሕግ የተቃወሙ ኬንያውያን የአገሪቱን ፓርላማ ቅጥር ጊቢ ጥሰው ገብተዋል።

ፖሊስ በከፍተኛ ቁጥር የወጡ ተቃዋሚ ወጣቶችን ለመበተን ጥይት እና አስቀሽ ጭስ ተኩሷል።

እስካሁን ድረስ ቢያንስ 5 ሰዎች በጥይት የተመቱ ሲሆን ሁለቱ ሕይወታቸው አልፏል።

ከጥቂት ሰዓታት በፊት የአገሪቱ ም/ ቤት አባላት ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ገጥሞት የነበረውንና በተለያዩ ምርት እና አገልግሎቶች ላይ ተጨማሪ ታክስ የሚጥለውን ረቂቅ ሕግ አጽደቀዋል።

" አዲሱ የቀረጥ ሕግ ኑሯችንን ያስወድድብናል " ሲሉ የቆዩት ኬንያውያን ወጣቶች ከአገሪቱ ፓርላማ ፊት ለፊት የተቃውሞ ድምጻቸውን ለማሰማት በከፍተኛ ቁጥር ወጥተዋል።

ከፖሊስ ቁጥጥር አቅም በላይ የሆኑ አብዛኛዎቹ ወጣቶች የሆኑ ተቃዋሚዎች የፓርላማውን በር ጥሰው ገብተዋል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ የፓርላማ አባላት ከምክር ቤቱ ምድር ቤት ለመደበቅ ሲሯሯጡም ተይተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፥ ተቃዋሚዎች አንደኛውን የፓርላማውን ክፍል በእሳት ማያያዛቸውን ቢቢሲ እና የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update “ ከታገቱ ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም ሰባት ወራት ይሆናቸዋል። እንደቀላል ነገር በወጡበት ቀሩ ” - የታጋች ባለቤት ከ6 ወራት በፊት ወደ ባቱ (ዝዋይ) ለስራ ጉዳይ እየተጓዙ በታጣቂዎች ታገቱ ከተባሉ 6 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች መካከል 3ቱ ቢለቀቁም 3ቱ ግን እንዳልተለቀቁ ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም የሚችለውን ሁሉ…
#Update

“ በታጣቂዎች ከታገቱ 9 ወራት አለፉ፤ ያሉበትን እንኳ አናውቅም። ወደ ማን እንጩህ ? ”- የታጋች ባለቤት

መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም በታጣቂዎች ታግተው የተወሰዱ 3 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች ደብዛቸው እንደጠፋ መሆኑን የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ወደባቱ ለስራ እየተጓዙ በነበረበት ወቅት በታጣቂዎቸ ታገቱ የተባሉት ሠራተኞቹ ያልተለቀቁት አጋቾቹ ገንዘብ ጠይቀው ከ2.8 ሚሊዮን ብር ከተላከ በኋላ እንደሆነ የታጋች ቤተሰቦች ከዚህ ቀደምም ገልጸው ነበር።

አሁንስ ምን አዲስ ነገር አለ ? 

- አቶ ልዑል አስፋወሰን
- አቶ ሰይፉ እንዳለ
- አቶ አብዩ ደገፋው የተባሉ ሠራተኞች በህይወት ይኑሩ አይኑሩ አይታወቅም።

ትላንት ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ 2 የታጋች ቤተሰቦች ስለ 3ቱም ታጋቾች ምንም የሰሙት ፍንጭ እንኳ እንደሌለ ገልጸዋል።

አንዷ የታጋች ባለቤት “ በታጣቂዎች ከታገቱ 9 ወራት አለፉ ፤ ያሉበትን እንኳ አናውቅም። ወደ ማን እንጩህ ? ” ሲሉ ሀዘን ያጀበው ጥያቄ አንስተዋል።

የሰው ልጅ ለ9 ወራት ያህል ያለበት እንኳን አለማወቅ ከባድ ሀዘን መሆኑን ፤ ኤሌክትሪክ ኃይልን በቅርቡ ቢጠይቁም ካቅሙ በላይ እንደሆነበት መግለጹን ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን እየተሰራ እንደሆነ ጥያቄ ያቀረበለት የኤሌክትሪክ ኃይል ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት መግለጹ ይታወቃል።

#TikvahEthiopaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

በቦሊቪያ የተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት ከሸፈ።

ሙከራው ሰዓታትን እንኳን አልቆየም።

የፕሬዜዳንቱን ቤተመንግሥት በኃይል ሰብረው ገብተው የወረሩት ወታደሮች ከቤተመንግሥቱ አካባቢ መሄዳቸው ተሰምቷል።

ፕሬዜዳንት ሉዊስ አርሴ ፤ ወታደሮችን እየመሩ ቤተመንግሥት የገቡትን የሠራዊቱን አዛዥ ጄነራል ጁዋን ጆሴ ዙኒጋን ከስልጣን አውርደው በሌላ ተክተዋል።

አዲሱ የሠራዊት አዛዥ ጆሴ ዊልሶን ሳንቼዝ ሁሉም ቤተመንግሥት የመጡ ወታደሮች ወደ የመጡበት ወታደራዊ ሰፈር /ክፍል እንዲመለሱ አዘዋል።

ይህን ተከትሎም ወታደሮቹ ከስፋራው ለቀው ሄደዋል።

ፕሬዝዳንት አርሴ አዲስ የአየር ኃይል አዛዥ እና የባህር ኃይል አዛዥም ሾመዋል።

ፕሬዝዳንቱ ወታደሮች ቤተመንግሥቱን ሰብረው መግባታቸውን እና መውረራቸውን ተከትሎ ህዝቡ በነቂስ ተደራጅቶ ወደ ጎዳና እንዲወጣና የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እንቅስቃሴውን እንዲያከሽፍ እና ዴሞክራሲውን እንዲያስጠብቅ ጥሪ አቅርበው ነበር።

በዚህም በርካቶች የሀገሪቱን ባንዲራ ይዘው በቤተመንግሥቱ አካባቢ ተሰብሰበው ነበር።

ፕሬዝዳንቱ ሙከራው መክሸፉን ተከትሎ ህዝቡን  በእጅጉ አመስግነዋል።

ወታደሮችን እየመሩ ቤተመንግሥት የገቡት ጄነራል ጁዋን ጆሴ ዙኒጋን ምንም እንኳን የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ ነኝ ብለው በግልጽ ባይናገሩም ፥ " ጥፋት ይቁም ፤ ሀገራችንን ወደ ድህነት መምራት ይቁም፣ ሠራዊታችንን ማዋረድ ይቁም " ሲሉ ተደምጠው ነበር።

ጦሩ ዴሞክራሲን ወደነበረበት ለመመለስ እና የፖለቲካ እስረኞችን ነጻ ለማድረግ እንደሚጥርም ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ዙኒጋን አዲስ የሚኒስትሮች ካቢኔ እንደሚቋቋም ከአሁን በኃላ ሀገሪቱ አሁን ባለው መንገድ እንደማትቀጥልም ገልጻው ነበር።

ጄነራል ዙኒጋን ከሽፏል ከተባለው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በኃላ ቀጣይ ዕጣፋንታቸውን እና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለጊዜው አልታወቀም።

ቦሊቪያ 🇧🇴 ፦ በደቡብ አሜሪካ የምትገኝ ከ12 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖሩባት ሀገር ናት።

#Bolivia
#failedcoup

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

ወታደሮችን እየመሩ የቦሊቪያው ፕሬዚዳንት አርሴ ቤተ መንግስትን በኃይል ሰብረው በመግባትና በመውረር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ያደረጉት ጄነራል ሁዋን ሆዜ ዙኒጋ በሀገሪቱ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው እስር ቤት ገብተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት እና ምክትል ፕሬዜዳንት በጋራ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ። ስራ መልቀቂያውን ያስገቡት ፤ " በፍትህ እና የዳኝነት ሰርዓቱ ለውጥ ለማምጣት ያሰብናቸው ፣ ያቀድናቸው የጀመርናቸው ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች ለማሳካት የሚያስችል ሁኔታ ማግኘት ስላልቻልን ነው " ብለዋል። ሰኞ ሰኔ 17/2016 ዓ.ም የተፃፈው የስራ መልቀቅያ ደብዳቤ በበርካታ የማህበራዊ…
#Update

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ ጥያቄያችን ለመመለስ ቃል ስለገባ የስራ መልቅቅያ ጥያቄያችን ትተነዋል " - የትግራይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንትና ምክትል ፕሬዜዳንት

የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንትና ምክትል ፕሬዜዳንት ያስገቡትን የመልቀቂያ ደብዳቤ እንደተውት አሳወቁ።

ፕሬዜዳንቱና ምክትል ፕሬዜዳንቱ ይፋ ባደረጉት መግለጫ ፤ ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ያቀረቡት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ተከትሎ ሰኔ 18 /2016 ዓ.ም ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ውይይት ማደረጋቸውን ገልጸዋል።

በዚ ውይይት ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች ለመመለስ ቃል በመገባቱ ስራ የመልቀቅ ጥያቄያቸውን እንደተውት አሳውቀዋል።

ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች ምን እንደሆኑ በግልፅ ያላብራሩ ሲሆን ከላይ እስከ ታች የሚገኘው የፍርድ ቤት አካል ስራውን ተረጋግቶ እንዲሰራ መልእክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዜዳንቱና  ምክትል ፕሬዜዳንቱ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ተከትሎ የወረዳና የዞን ፍርድ ቤቶች ስራ የማቆም አድማ መምታት ጀምረው ነበር

ከክልሉ ፕሬዜዳንት ከተደረገው ውይይት በኃላ ችሎቶች ተከፍተው አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል በአካል ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

ከመቐለ ውጪ በመላው ክልል ያሉ ፍርድ ቤቶች መደበኛ አገልግሎት መስጠት መቀጠላቸው የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የፕሮቶኮል ሹም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa በሀዋሳ ከተማ የስፓርት ውርርድ ( #ቤቲንግ ) ቤቶች እየታሸጉ / እየተዘጉ ይገኛሉ። ይህ ተከትሎ የስፖርት ውርርድ ቤት ባለቤቶች " እንዴት የንግድ ፈቃድ እያለን ይዘጋብናል ? " ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል። እነዚህ የስፖርት ውርርድ ቤቶች ከወራት በፊት በተለያዩ ምክኒያቶች ተዘግተው የቆዩ ሲሆን በቅርቡ ተከፍተው ነበር። አሁን ላይ ተመልሰው መዘጋት/መታሸግ መጀመራቸው…
#Update

" የስፖርት ውርርድ ቤቶችን የመዝጋትና የመክፈት አሰራር አድሎአዊነት የተንጸባረቀበት ነው " - ቅሬታ አቅራቢዎች

" የተከፈቱ ቤቶች ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ህጋዊ ደብዳቤ ያመጡ ናቸው " - የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ

በቅርቡ በሀዋሳ ከተማ ያሉ የስፖርት ውርርድ ቤቶች  " ህጋዊ አይደሉም ፣ በብዛት  የተከፈቱበት አካባቢም የትምህርትና የመኖሪያ ሰፈር ነው " በሚል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ቢዘጉም ከቀናት ቆይታ በኋላ ግን የተወሰኑት ተከፍተዉ ስራ ጀምረዋል።

ይህንን ተከትሎ ፥
- ለምን ሁሉም በህግና ስርአት እየሰራ እና ግብርም እየከፈለ እያለ በከፊል ተከፍቶ በከፊል ይዘጋል ?
- ቤቶቹን የመዝጋትና የመክፈት ስራን የሚሰራዉ የከተማው ፖሊስ አሰራሩ አድሏዊነት የታየበት ነው፤
- ገንዘብ ሰጥተው የሚያስከፍቱ ሰዎችም እንዳሉ እየተሰማን ነው ሲሉ የስፖርት ውርርድ ቤታቸው የተዘጋባቸዉ ግለሰቦች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ የከተማዉ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ፥ አሁን ላይ ተከፍተዉ ወደስራ የተመለሱት ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ህጋዊ ደብዳቤ ያቀረቡ መሆናቸዉን ገልጸዋል።

በተጨማሪም " ለሀገር ፈጽሞ ጥቅም የማይሰጠዉ የቨርቹዋል አሰራር አሁንም እንደተከለከለ ነው። ካሁን በፊት እንደህግ ያስቀመጥነዉ የመኖሪያ ቤትና የትምህርት ቤቶች ዙሪያ የተጣለዉ ክልከላ ዛሬም ቀጥሏል " ብለዋል።

ከዚህ ውጭ አከፋፈቱን በተመለከተ የሚነዛዉ ስም ማጥፋት አግባብ አለመሆኑን ገልጸዉ ማንኛዉም አካል ህጋዊ ሆኖ ከመጣ ድርጅቱን ማስከፈት እንደሚችል ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የ2016 ዓ/ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የ2016 ዓ/ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና እና የዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና መቼ ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል። የትምህርት ሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራር ፥ የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት ይፋ እንደሚደረግ…
#Update

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኳል።

የተማሪዎቹ ውጤት ዛሬ ለተቋማቱ መላኩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል።

በዚህም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

የዘንድሮው የመውጫ ፈተና ለ57 የመንግሥት እና ለ124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በ244 የቅድመ ምረቃ መርሐግብሮች መሰጠቱ ይታወቃል።

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቴፒ #አሽከርካሪዎች ° “ ከቴፒ ቡና ጭነን ለመውጣት ተከልክለን ከቆምን ወር ሊሞላን ነው ” - አሽከርካሪዎች ° “ ክልል ኮሚቴ አቋቁቁሞ ነገሩን እያጣራ ነው ”- ቡናና ሻይ ባለስልጣን የጫኑትን ቡና ይዘው እንዳይንቀሳቀሱ በመከልላቸው ያለምንም መፍትሄ ከሦስት ሳምንታት በላይ ለመቆም እንደተገደዱ አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረዋል። “ ለሥራ የምንወጣው ቤተሰቦቻችንንም ለማስተዳደር…
#Update

“ አሁንም ድረስ ቡና ጭነው የቆሙ ተሽከርካሪዎች አሉ ” - አሽከርካሪዎች 

“ የቆሙት ተሽከርካሪዎች በወንጀል ተጠርጣሪዎች ናቸው ” - ቡናና ሻይ ባለስልጣን

ከቴፒ የጫኑትን ቡና ይዘው እንዳይወጡ ከዚህ ቀደም ተከልክለዋል ከተባሉት 24 ተሽከርካሪዎች መካከል 3ቱ አሁንም እንዳልተለቀቁ አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡ አንድ አሽከርካሪ፣ “ አሁንም ቡና ጭነው የቆሙ ተሽከርካሪዎች አሉ። ደቡብ ምዕራብ ቦንጋ ከተማ በቡናና ሻይ ባለስልጣን ግቢ ውስጥ አቁመዋቸዋል ” ብለዋል።

ሌሎችም አሽከርካሪዎች፣ በበኩላቸው ይህንኑ ሀሳብ ተጋርተው፣ ተሽከርካሪዎቹ ቦንጋ የቆሙት ቴፒ ከወጡ በኋላ ቡናው ' Commercial ነው ’ ተብሎ መሆኑን አስረድተዋል።

የተለቀቁት ተሽከርካሪዎችም ቢሆኑ የተለቀቁት ከአንድ ወር መጉላላት በኋላ በመሆኑ በኑሮ ላይ ከባድ ጉዳት እንደገጠማቸው አስረድተው፣ “መጨረሻ ላይ ቡናው Local ነው ተብሎ ተለቀቅን፣ በዚህ ጉዳይ ሲጀመር መጠየቅ ያለበት ሹፌር አልነበረም” ብለዋል።

ከአሽከርካሪዎቹ በኩል ለተነሳው ለዚህ ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ጥያቄ ያቀረበላቸው የቡናና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የግብይት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሻፊ ዑመር፣ “ ስንመረምር 3ቱ መኪና Local ብለው የጫኑት የExport ቡና ሆነ ” ብለዋል።

“ ስለዚህ የExport ቡና መሸጥ ህገ ወጥ ነው። አገርን ዶላር ማሳጣት ነው። 3ቱ መኪና እዛው ቆመው ነው ያሉት በፓሊስ እጅ ነው ” ሲሉ ተናግተዋል።

አቶ ሻፊ “ አሁን ላይ የቆሙት ተሽከርካሪዎች በወንጀል ተጠርጣሪዎች ናቸው ” ብለው “ እንደዚህ ያደረጉ አካላትም ለህግ እንዲቀርቡ ለደቡብ ምዕራብ ደብዳቤ ፅፈናል ” ሲሉ አክለዋል። 

ትክክለኛ የችግሩ ምንጭ ማነው ? በማለት ላቀረብነው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አቶ ሻፊ፣ “በሁሉም Side አለ” ብለዋል።

“ ላኪዎቹ የ Local አስመስለው Exportable ቡና ሲገዙ በጥሩ ዋጋ ስለሚሸጡ። ለአገር አያስቡም። አቅራቢው ደግሞ ቡናን በአፈርና ውሃ እያሸ ወደ Local እንዲገባ ስለሚያደርግ ችግር አለበት” ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው፣ “አሽከርካሪዎቹም ቢሆኑ እያወቁ ነው የተሻለ ዋጋ ስለሚከፈላቸው ቴፒ ሂደው የሚጭኑት። ሲጀመር የExports ቡና ማከማቻ፣ Localን ወደ Export የሚለየው አዲስ አበባ ነው። ቴፒ የሚያስሄዳቸው ነገር የለም” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፥ " በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በሽረ እንዳስላሰ ከተማ የነበሩ ተፈናቃዮች ከሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቄያቸው ሰሜን ምዕራብ ዞን ፀለምቲና ማይ ፀብሪ እንዲመለሱ የማድረግ ስራ ተጀምሯል " ሲል አሳውቋል። ከ3 ዓመት በላይ በእንዳስላሰ ሽረ ከተማ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው ለመጓዝ ዝግጁ እንዲሆኑ አርብ ማታ ተነግሯቸው…
#Update

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፥ ከትላንትና ጀምሮ በጦርነት ምክንያት ከቤትን ንብረታቸው ተፈናቅለው እስካሁን በመጠለያ የነበሩ የሰሜን ምዕራብ ዞን ፀለምቲና ማፀብሪ ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ መጀመሩን አሳውቋል።

ከማይ ዓይኒ፣ ከማይ አንበሳ፣ ከመድኃኔዓለም እና ውሕደት ከተባሉ ቀበሌዎች የተፈናቀሉ ከአንድ ሺሕ አምስት መቶ በላይ ተፈናቃዮች ትላንት ተመልሰዋል።

ዛሬም ማይ ፀብሪን ጨምሮ የፀለምቲ ወረዳ ስድስት ቀበሌዎች ተፈናቃዮች ተመልሰዋል።

አንዳንድ ቃላቸውን ለቪኦኤ የሰጡ ተመላሾች ህዝቡ " እንኳን ደህንና መጣችሁ ! " ብሎ በመልካም ሁኔታ እንደተቀበላቸው ፤ ታጣቂዎች ግን እስካሁን እንዳልወጡ፣ ትጥቅም እንዳላወረዱ ይህ ስጋት እንዳሳደረባቸው ገልጸዋል።

ይህ አካባቢ ጦርነቱን ተከትሎ በአማራ ክልላዊ መንግሥት ስር የጠለምት ወረዳ አስተዳደር ተብሎ ነበር።

የጠለምት አማራ ወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ አለቃ አለነ አሰጋ ፤ " የጠለምት ወረዳ አስተዳደር የጸጥታ መዋቅር፣ ከዛሬ 3 ቀናት በፊት በግዳጅ ሥራ እንዲያቆም ተደርጓል " ብለዋል።

አለቃ አለነ ፥ በሥራ ላይ የቆየው ፖሊስ እና የጸጥታ መዋቅሩ ወደ ዓዲኣርቃይ አካባቢ መንቀሳቀሳቸውን ገልጸዋል።

እርሳቸው ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ግን ከአካባቢው አለመልቀቃቸውን ጠቁመዋል።

በአካባቢው የጸጥታ ስጋት መኖሩን ጠቁመው፣ መንግሥትም ይህንኑ ተገንዝቦ፣ ነዋሪው ኅብረተሰብ የራሱን የጸጥታ መዋቅር እንዲዘረጋ ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል፡፡

አለቃ አለነ የጠለምት የወሰንና የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንደመሆናቸው በአካባቢው ላይ ያላቸውን የወሰን እና የማንነት ጥያቄውን በቦታው ላይ እያሉ ማቅረባቸውን እንደሚቀጠሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ፌደራል መንግሥት የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው የትግራይ እና አማራ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈናቃዮች ወደቦታቸው ከተመለሱ በኃላ ከነዋሪው ህብረተሰብ ጋራ በመሆን የጋራ አስተዳደር ከአቋቋሙ በኋላ የሚነሳው ጥያቄ በሕዝበ ውሳኔ / ሪፈረንደም ምላሽ ቢያገኝ የተሻለ እንደሆነ መግለጹ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ፍርዱ ለሚዲያ 16 ዓመት ከተባለ በኃላ ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዳለ ሰምቻለሁ " - ጸጋ በላቸው " ጉዳዩ ለቢሮዉም ሆነ ለኔ አዲስ ነው " - ወ/ሮ ወይንሸት ብርሀኑ በሀዋሳ ከተማ የዳሽን ባንክ ሰራተኛ ከሆነችዉ ጸጋ በላቸዉ ጋር በተያያዘ በጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ  የነበረው ኮንስታብል የኃላመብራት ወ/ማርያም " ለብዙዎች አስተማሪ ይሆናል " በተባለ መልኩ የ16 አመት ጽኑ እስራት…
#Update

" ውሳኔዉ መስተካከሉ አስደስቶኛል ጥንካሬም ሆኖኛል " - ጸጋ በላቸዉ

" የይግባኝ ዉሳኔዉን ተከትሎ ፍርዱ ወደ 10  መቀነሱ ልክ አልነበረም " - የክልሉ ዋና ዐቃቤ ህግ


• ግለሰቡ በ14 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንዲቀጣ ተፈርዷል።

በሀዋሳ ፥ የዳሽን ባንክ ሰራተኛዋን ጸጋ በላቸዉ ላይ የጠለፋ ወንጀል የፈጸመዉ የጸጥታ አባሉ ምክትል አስር አለቃ የኋላመብራቱ  ወልደማርያም የጠየቀው ይግባኝ ተቀባይነት አግኝቶ ፍርዱ ከ16 አመት ወደ 10 መውረዱ ተሰምቶ ነበር።

በወቅቱ በዉሳኔዉ ያዘነችዉ ተበዳይ ጸጋ በላቸዉ ቅሬታ ውስጥ መግባቷን በመግለጽ ፍርድ ቤቱ ያሳለፈዉ ውሳኔ አግባብ አለመሆኑንና ቅጣቱ በጣም እንዳሳመማት ገልጻ  ቅሬታ ማቅረቧን መዘገባችን ይታወሳል።

ይህን የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሳኔ በመቃወም ይግባኝ የጠየቀዉ የክልሉ ዐቃቤ ህግ ቅጣቱ መውረዱ ከህግ አንጻር አግባብ አይደለም ብሎ በመከራከር የቅጣት ማቅለያውን ውድቅ በማድረግ ቅጣቱ ተስተካክሎ የ14 አመት ከ6 ወር ውሳኔ ተሰጥቷል።

በዚህ የፍርድ ሂደት አስተያየቷን በመልእክት ያጋራችን ወይዘሪት ጸጋ በላቸዉ በፍርዱ መስተካከል  ደስታ እንደተሰማትና ይህም  ጥንካሬ  እንደሚሰጣት ገልጻልናለች።

" እንደኔ አይነት ጉዳት የደረሰባችሁ እህቶች ሁሉ ወደህግ በመሄድ መጠየቅን አትፍሩ " የምትለው ጸጋ ፥ ከመጀመሪያውም በህግ ላይ እምነት እንደነበራት ተናግራለች።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ኃላፊው አቶ ማቶ ማሩ ፥ " ምንም እንኳን ሚዲያዎች ለዚህ ኬዝ የሰጡት ትኩረት ጉዳዩን ታዋቂ ቢያደርገውም ክልሉ ለሴት ልጅ ጥቃት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ በመሆኑ በርካታ ጠንካራ ውሳኔዎች ተላልፈዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይህ የጸጋ በላቸዉ ኬዝ ማህበረሰቡን ያስተምራል ለተጎጅዋም ፍትህ ይሰጣል ብለን ስንከታተለዉ የነበረ ጉዳይ ከመሆኑ በላይ ድርጊቱን የፈጸመዉ ግለሰብ ማህበረሰብ ይጠብቃል ተብሎ ኃላፊነት የተሰጠዉ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተነው ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ ማቶ ከወራት በፊት የተሰጠውን የይግባኝ ውሳኔ ህጋዊ ድጋፍ የለውም ብሎ በመቃወም የክልሉ ዐቃቤ ህግ ፍርዱ እንዲስተካከል የጣረው ለዚህ ነበር  ብለዋል።

ቅጣቱ ከ10 ወደ 14 አመት መስተካከሉን ገልጸው " እንደክልል በዚህ አመት ብቻ ከ256 በላይ ሴቶችንና ህጻናትን የተመለከተ ኬዝ በትኩረት ይዘን እየሰራንበት ነው በተወሰኑት ላይም አስተማሪና  ጠንካራ ውሳኔዎች እየተሰጡ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaHawassa

@tikvahethiopia