ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
853 subscribers
3.46K photos
103 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ኦርቶዶክሳዊ_የጾታ_ትምህርት
#ክፍል_10
#በዓለማችን_የሚታዩ_የጋብቻ_አይነቶች
በዓለማችን ላይ የሚታዩትን የጋብቻ አይነቶችን የመስኩ ባለሙያዎች አንድ ለአንዲት /Monogamy/ ከአንድ በላይ ጋብቻ /Polygamy/ በማለት #በ2 ታላላቅ መደቦች ይከፍሏቸዋል ።
#ሀ_ከአንድ_በላይ_ጋብቻ/Polygamy/ ፦ ይህ በራሱ በሁለት ይከፈላል ። አንዳንዱ ማህበረሰብ አንድ ወንድ ብዙ ሴቶችን እንዲያገባ ይፈቀድለታል ። ይህ /Polygyny/ ፖሊጂኒ የሚባል ነው ። ለምሳሌ በሙስሊሞች ዘንድ 1 ወንድ ከ 1 ሴት በላይ እስከ 4 ሴት እንዲያገባ ይፈቀድለታል ። ሴቷ ግን ከዚህ ተከልክላለች ። ሁለተኛው አይነት ደግሞ አንዲት ሴት ብዙ ወንዶችን የምታገባበት ነው ። ይህ ፖሊአንድሪ /Polyandry/ ተብሎ የሚጠራው ነው ። በተወሰኑ የሩቅ ምስራቅ ሕዝቦች መካከል የሚፈፀም መሆኑ ጥናቶች ያረጋግጣሉ። ከዚህ ውጭ ቡድናዊ ጋብቻዎች /Group Marriage / የሚፈፀምባቸው የአለማችን የህብረተሰብ ክፍሎች እንደነበሩ ጥናቶች ይጠቁማሉ ። ይህ ማለት ብዙ ወንዶችና ብዙ ሴቶች በአንድ ላይ እየኖሩ የጋራ ባሎችና የጋራ ሚስቶች የሚሆኑበት አይነት ነው ። በዓለማችን በስፋት ተለምዶ የሚገኘው የ1 ወንድ ከ1 በላይ ሴቶችን የማግባት ሥርዓት ነው ። በክርስትና እምነት ድርጊቱ የማይደገፍና በእግዚአብሔርም ዘንድ የተጠላ ቢሆንም በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ እንደምናገኘው በብሉይ ኪዳን ብዙ ሚስቶች የነበራቸው ወንዶች ነበሩ። ብዙ ባል ያገባች ማግኘት ግን ይከብዳል ። ይህ ከጋብቻ ባህርይ ውጪ ነው ።
#ለ_አንድ_ለአንድ /Monogamy/ ጋብቻ አንድ ለአንዲት ፤ አንዲት ለአንድ መሆን እንደሚገባ ተገልጿል ።ለአዳም ብዙ ሴቶች አለመፈጠራቸው ለአንድ ወንድ አንዲት ሴት እንጂ ብዙ ሴቶች ያልተፈቀደ መሆኑን ፤ ለሔዋንም ብዙ ወንዶች አለመፈጠራቸው ለአንዲት ሴት አንድ ባል እንጂ ብዙ ወንዶች ያልተፈቀዱ መሆኑን ያመለክታል ። በሃገራችን ኢትዮጵያ በልዩ ብሔር ብሔረሰቦችና በተለያዩ የእምነት ድርጅቶች የሚፈጸሙ በርካታ የጋብቻ አይነቶች አሉ ። የኦርቶዶክስ ተከታዮች የሚፈጽሟቸው የጋብቻ አይነቶች የሚከተሉት ናቸው ። #1ኛ ሐይማኖታዊ ጋብቻ #2ኛ የሠማንያ ጋብቻ #3ኛ የሲቪል ጋብቻ በመባል ይታወቃሉ ።
#1ኛ_ሃይማኖታዊ_ጋብቻ ፦ ሃይማኖት አለን የሚሉ ክፍሎች እንደየሥርዓተ ሃይማኖታቸው የሚፈጽሙት ነው ። በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት የሚጋቡ በተክሊል ፣ በሥጋወደሙ ወይም እንደ ስርዓቱ በመአስባን ጸሎት እና በቁርባን የሚወሰኑ ናቸው ።
#2ኛ_የሠማንያ_ጋብቻ ፦ ይህ ጋብቻ ዓይነቱና ይዘቱ ሰፊ የሆነ እና በብዙ ሰዎች የሚፈጸም የተለመደ ባሕላዊ የጋብቻ አይነት ነው ።
#3ኛ_የሲቪል_ጋብቻ ፦ በመንግስት በተቋቋመ አካል ፊት ቀርቦ የሚፈጸመው የጋብቻ አይነት ነው ።ይህ እንግዲ በከተሞች የሚፈጸም ነው ። በተለምዶ የመዘጋጃ ቤት ጋብቻ ተብሎ ይጠራል ።
#የመዐስባን_ጋብቻ ፦ መዐስብ ማለት ብቸኛ ፣ ፈት ፣ ጋለሞታ ሚስት የሌለችው ባል የሌላት በሞት ወይም በነውር ምክንያት ተፈትታ ወይም ተፈትቶ በብቸኝነት የሚኖር የምትኖር ማለት ነው ። በመዐስብነት የሚኖሩ ሰዎች የብቸኝነት ኑሮ የሚዘልቁት ሆኖ ባለማግኘታቸው ምክንያት እንዲያገቡ ውሳኔ ላይ በሚደርሱበት ጊዜ ዳግም ያገቡ ዘንድ ይፈቀድላቸዋል ። #መዐስባን ጋብቻ በሚፈጽሙበት ጊዜ የማስተሰሪያ ጸሎት ይጸለይላቸዋል እንጂ ተክሊል አይደረግላቸውም

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#ትምህርተ_ንስሐ (በአቡነ ሺኖዳ)
#የመጨረሻው_ክፍል
#ንስሐ_እንዴት_ይገባል ?
#1ኛ_ከራስ_ጋር_መሆን
ንስሐ መግባት የራስን ፈቃድ ይጠይቃል። ምናልባት ያለህበትን የኀጢአት ባሕርና ጥፋት አልተገነዘብክ ይሆናልና መጀመሪያ ከራስህ ጋር መሆን አለብህ ። ከራሳችን ጋር የሆንን እንደሆነ ድካማችንንና ኀጢአታችንን ለእግዚአብሔር መናገር አይከብደንም ። ማንም ቢሆን በመንፈሳዊ ሕይወቱ በበረታ ቁጥር ሰይጣንም ሊጥለው ከመቼውም የበለጠ ኃይሉን አጠናክሮ ሊፈትነው እንደሚተጋ የተረጋገጠና የማይጠረጠር ነው ።
#2ኛ_ምክንያትንና_ለራስ_ይቅርታ_ማድረግን_ማስወገድ
በንስሐ ሕይወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደርና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም ። ኃጢአትን ከፈፀሙና ከሰሩ በኀላ ለኃጢአት ያበቃ ሌላ ምክንያት ማቅረብና በዚያም አንፃር ለመጽናናት መሞከር በራሱ ኀጢአት ነው ።ስለ ሰራነው ሀጢአት ንስሐ መግባት እንጂ ምክንያት በማበጀት ራስን ነፃ ማድረግ የለብንም ። በዓለም እስካለን ድረስ ሁላችንም ሀጢአትን እንሰራለን ። ወፍጮ ቤት ገብቶ ዱቄት ሳይነካን እንደማንወጣው ሁሉ በዓለምም እስካለን ድረስ እንበድላለን ። ለዚህ ነው አበው ሰው ሆኖ የማይሳሳት፣ እንጨት ሆኖ የማይጨስ ፣ ብረት ሆኖ የማይዝግ የለም የሚሉን ። እግዚአብሔርም ለምን በኀጢአት ወደቅክ አይለንም ለምን አልተነሳህም ነው የሚለን ። ሰለዚህ ንስሐ አባት የሌለን በመጀመሪያ ንስሐ አባት እንያዝ ከዛም ያደረግነውን ሁሉ ዝርዝር አርገን ተናግረን ከሀጢአት የተፈታን ወንዶች የ40 ቀን ህፃን ሴቶች ደሞ የ80 ቀን ህፃን እንሁን ። ሀጢአታችን ምንም ቢበዛም ከእግዚአብሔር ፍቅር ግን አይበልጥም ። የአምላካችን የክርስቶስ ደም ከኀጢአት ሁሉ ሊያነፃን የታመነ ነው ። ማንኛችንም ብንሆን የተወለድንበትን ቀን እንጂ የምንሞትበትን ቀን አናውቅም ። የትኛዋ ቅፅበት የመጨረሻችን እንደሆነች አናውቅምና በቶሎ ንስሐ ገብተን ተዘጋጅተን እንጠብቅ። ስለ #ንስሐ በጥቂቱ ከአቡነ ሺኖዳ መጽሐፍ ላይ ያዘጋጀነው ትምህርት ለዛሬ በዚ አበቃ ነገ ደግሞ ስለ ንስሐ በሌሎች ትምህርቶች እንመለስበታለን ሀሳብ አስተያየት ኢዮአታም ይጠቀሙ

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር
ተከታታይ ትምህርት
#ክፍል_2
@zekidanemeheret
#10ቱ_ትዕዛዛት (ኦሪ ዘፀ 20)
#1.እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ ነኝ ከኔ በቀር ሌሎቹ አማልክት አይሁኑልህ ።
#2.የእግዚአብሔር የአምላክህን ስም በከንቱ አታንሳ ። #3.የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ ።
#4.እናትና አባትህን አክብር ። #5.አትግደል
#6.አታመንዝር
#7.አትስረቅ
#8.በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር
#9.የባልንጀራህን ቤት አትመኝ #10.ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ።
🖊የክርስትና ህግ የፍቅር ህግ ነው ። ቅዱስ ጳውሎስ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈፅሞታል ካለ ቡሃላ ከ10ቱ ትዕዛዛት የተወሰኑትን በመጥቀስ #ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍፃሜ መሆኑን በግልፅ ይናገራል። /ሮሜ 13÷8/ 🖊ጌታችን እንዳስተማረን ፍቅር በሁለት ይከፈላል ። #1ኛ_ፍቅረ_እግዚአብሔር #2ኛ_ፍቅረ_ቢፅ
🖊በሌላ በኩል ደግሞ ከአዎንታዊና አሉታዊ ከመነገራቸው አንፃር በሁለት ይከፈላሉ ።
#1ኛ_ሕግ_በአሉታ_የተነገሩ /አታድርግ/
#2ኛ_ትዕዛዝ_በአዎንታ_የተነገሩ /አድርግ/ ይባላሉ
🖊ከዚህም ሌላ ከአፈፃፀማቸው አንፃር ሲታዩ በሦስት ይከፈላሉ ። #1ኛ_በሐልዩ /በማሰብ/ የሚፈፀሙ ህግ1,3,4 እና 9 #2ኛ_በነቢብ /በመናገር/ የሚፈፀሙ ህግ 2,8
#3ኛ_በገቢር /በማድረግ/ ህግ 5,6,7,10 ናቸው ።
🖊#10ቱ ትዕዛዛት ለሙሴ በተሰጡ ጊዜ በሁለት የድንጋይ ፅላቶች ላይ ተፅፈው ነበር ። እንዲሁም ሁሉ በተለይም እስራኤል ዘነፍስ የምንባለው ለእኛ ለክርስቲያኖች ከልባችን ፅላት ላይ በመንፈስ ልንፅፈው ይገባል። በቤተክርስቲያናችን በፅላቶቻችን ላይ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይገኛል ። ጌታችን ደግሞ ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለው ካለ ቡሃላ ብትወዱኝስ ትዕዛዜን ጠብቁ ብሎ አስተምሯል ። እንዲህ ከሆነ የሚያስፈልገንን ነገር ለመለመን የጌታችን ስሙ ስለተፃፈበት በዙሪያው ተሰብስበን መለመን ያስፈልጋል ። ህጉ ከልባችን ስለማይጠፋ ሕጉን መጠበቅና መፈፀም ይገባናል ።
🖊ለዚህም በቀጣይ እያንዳንዳቸውን በዝርዝር እንማማራለን ።

ይቀጥላል....

@zekidanemeheret
ለሌሎችም ማጋራትን አይርሱ
👉ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ክርስቲያናዊ_ሥነምግባር
#ክፍል_10
#8 በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር
@zekidanemeheret
🖊ይህ ቃል የሚሰራው በሐሰት ለሚመሰክር ብቻ አይደለም ሐሰትንም ለሚቀበል ነው። ማቴ ፰÷፵፩
ምሳ ፲፪÷፳፪ ፤ ፩ነገ ፳÷፲፫ ፤ መሳፍ ፲፱÷፭
🇪🇹ምስክርነት ምን ማለት ነው ? በሐሰት መመስከርስ እንዴት ነው ?
🖊 #ምስክርነት ማለት በዳኛ ፊት ወይም በባለሥልጣን ፊት ወይም በአስታራቂ ሽማግሌዎች ወይም ስለ ሥነ ስርዓት ጉዳይ በተሰየመ ጉባኤ ፊት የቀረበውን ሙግትና ክርክር በትክክል ለመፍረድና ለመወሰን የሚረዳ የቃል ማረጋገጫና ሌሎችም መረጃዎችን የሚያመለክት ነው ። በእውነት የሚቀርበው ምስክርነት በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ ያስመሰግናል። ነገር ግን ሰዎች በልዩ ልዩ ጥቅም ተገዝተው ወይም ባልንጀራን አለአግባብ ለመጥቀም ወይም ለመጉዳት ሲባል እውነቱን ነገር በመሸሸግ ሐሰት ነገር በመፍጠር ያልተነገረውን ተነገረ ያልተደረገውን ተደረገ በማለት በመሐላም ሆነ ያለ መሐላ የሚቀርበው የውሸት ማስረጃ ሁሉ የሐሰት ምስክርነት ይባላል። በኀብረተሰቡ ውስጥ እውነትና ሐቅ ጠፍቶ ፍርድ ጎድሎ ድሀ ተበድሎ ሰዎች ሁሉ ጊዜያቸውንና ኃይላቸውን ገንዘባቸውንም በክርክርና በጠብ እንዳያጠፋና ሰላማቸውን እንዳያጡ በፍቅርና በደስታ እንዲኖሩ በማሰብ እግዚአብሔር "በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር" የሚለውን ትእዛዝ እንድንጠብቀው ሰጥቶናል።
🖊ይህን ትዕዛዝ መተላለፍ ትልቅ በደል ነው ።
#በመጀመሪያ መስካሪው እውነት እመሰክራለው ብሎ የገባውን ቃል ኪዳን ወይም መሐላ አፍርሶ ውሸት በመናገሩ ፣
#2ኛ ዳኛውን በማሳሳት የሐሰት ፍርድ በማስፈረዱ ፣
#3ኛ የተፈረደበትን ሰው ሳያጠፋ በማስቀጣቱ በደሉ ብዙ ነው።
🖊ይህ ትዕዛዝ ቀጥታ ምስክሮችን ብቻ የሚመለከት አይደለም ። ልዩ ልዩ የሐሰት መረጃዎችን በማዘጋጀት ፡ ሰነዶችንና መዝገቦችን በማጭበርበርና በማዘዋወር አስመስሎ በመፈረምና በተሰረቁ ማኀተሞች በመጠቀም እንደዚሁም ሌሎች ይኽን የመሰሉ በተንኮል የተቀናበሩትን ሁኔታዎች በማመቻቸት የሚያስፈርዱትንና የሚፈርዱትንም ሁሉ ይመለከታል።
🖊ስለዚህ ምስክርነታችን ሁሉ #በእውነት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት ።
@zekidanemeheret

ይቀጥላል.....

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ተጨማሪ👇👇👇ለማግኘት
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ፍኖተ_ቅዱሳን
#ክፍል_2
(በቀሲስ ደጀኔ ሽፍራው)
#10ሩ_ማዕረጋተ_ቅድስና
መንፈሳዊ ህይወት የቅድስና ኑሮ እንደ መሆኑ መጠን በጥምቀት ጀምሮ ደረጃውን የጠበቀ እድገት ያለበት ሕይወት ነው ።ከዚህም በሃላ እግዚአብሔርን በፍፁም ልቡናቸው ሰውነታቸውና ሕዋሳቶቻቸው እያመሰገኑ አሰረ ፍኖቱን የሚከተሉ ሰዎች ከቅድስና ወደ ከበረ ቅድስና ከሚኖሩበት መንፈሳዊ ኃይል ወደ ሌላ ታላቅ መንፈሳዊ ኃይል ይሸጋገራሉ ። እነዚህ የቅዱሳን የመንፈሳዊ ጉዞአቸው የእድገት ደረጃዎች 3 ናቸው ። እነዚህም #ወጣኒነት (ንፅሀ ስጋ) ፣ #ማዕከላዊነት (ንፅሀ ነፍስ) እና #ፍፁምነት (ንፅሀ ልቡና ) በመባል ይታወቃሉ ። በእነዚህ በእያንዳንዳቸው ስር ደግሞ የተለያዩ ማዕረጋት አሉ ።በንፅሀ ስጋ 3 በንፅሀ ነፍስ 4 በንፅሀ ልቦና 3 ሲሆኑ በጠቅላላው #10ሩ ማዕረጋተ ቅዱሳን በመባል ይታወቃሉ ።
#ንፅሀ_ሥጋ /ወጣኒነት/
ይህ ደረጃ ወጣንያን በባሕርዩ ፍፁም ከኾነው እግዚአብሔር ፍፁም ፀጋን ተቀብለው ለመክበር ቁርጥ ተጋድሎ የሚጀምሩበት ሕይወት ነው ። በዚህም ጊዜ ጠላት የተባለ ሰይጣን የተጋድሎ ሕይወታቸውን የሚያቀጭጭ ፈተና ያመጣባቸዋል ። እነርሱ ግን በፍፁም ተጋድሎ በእግዚአብሔር ፀጋ ከአንዱ ማዕረግ ወደ ሌላው ይሸጋገራሉ ።
#1ኛ #ጽማዌ ፦ ዝምታ ማለት ነው ። ይኸውም አውቆና ፈቅዶ በመናገርና በመቀባጠር ከሚመጣው ኃጢአት መቆጠብ ነው ።ይህን የመጀመሪያውን ደረጃ በዝምታ ማለፍም ታላቁን የሰይጣን ፆር /እሳትን / በተጋድሎ ማጥፋት ነው ።አንደበት እሳት ነውና።
#2ኛ #ልባዌ ፦ ልባዊ ማለት ልብ ማድረግ ፣ ማስተዋል ማለት ነው ። ጌታ በወንጌል "መስማትንስ ትሰማላቹ ነገር ግን አታስተዉሉም " ይላቸው የነበረው ማስተዋል ታላቅ ማዕረግ ስለሆነ ነው ።
#3ኛ #ጣዕመ_ዝማሬ ፦ይህ ደግሞ ሳይሰለቹና ሳይቸኩሉ ምስጢርና ትርጓሜውን እያወጡ እያወረዱ በንቁ ሕሊና ማመስገንና መጸለይ ማለት ነው ። አንድ ሰው የሚፀልየውን ፀሎትና የሚያቀርበውን ምስጋና በትርጓሜና በምስጢር በውሳጣዊ ልቡናው እያዳመጠ የሚያደርሰው ከሆነ ተመስጦን ገንዘብ ማድረግ ይቻለዋል ። ጸጋ መንፈስ ቅዱስንም እየተጎናፀፈ ከዚህ ከስጋዊ አለም ማምለጥ ይቻለዋል።
... ይቀጥላል ...

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
5ቱ የዝሙት ብልቶች
--------------------------------
#1ኛ ዝሙተኛ ጆሮ ፡- የሰው ገመና ያዳምጣል ፣ ዘፈን ያዳምጣል …
#2ኛ ዝሙተኛ ዓይን ፡- የታቃራኒ ጾታን ኣካል ይመለከታል ፣ ጸያፍ ትዕይንቶችን ይመለከታል …
#3ኛ ዝሙተኛ እግር ፡- ወደ መጠጥ ቤት ይገሰግሳል ፣ ወደ ሲኒማ ቤት ይገሰግሳል ፣ ወደ ጭፈራ ቤት ይገሰግሳል ፣ ወደ ጠንቋይ ቤት ይገሰግሳል ….
#4ኛ ዝሙተኛ እጅ ፡- የተቃራኒ ጾታን አካል ይዳብሳል ፣ ጉቦን ትቀበላለች ፣ የሰውን ነፍስ ታጠፋለች …
#5ኛ ዝሙተኛ ምላስ ፡- ዘፈንን ታወጣለች ፣ ስድብን ታወጣለች ፣ የተወገዙ እጾችን ታጣጥማለች ፣ ኣመጻን ታነሳሳለች ፣ የሰውን ስም ታጠፋለች …….
የእነዚህ የዝሙት ብልቶች ስብስብ በስጋና በመንፈስ የተበላሸ ኣካልን ይፈጥራሉ ፡፡ ዘመናችን ወደየት እየሄደ እንደሆነ በምንሰማውና በምናየው ነገር ማረጋገጥ ይቻላል ፡፡ ትልቁም ፣ ትንሹም ፣ ጤነኛውም ፣ በሽተኛውም ወሬው ዝሙትና ዝሙት ነው ፡፡ የወሬ ማሳመሪያው ዝሙት ነው ፡፡ የነገር መጀመሪያው ዝሙት ነው ፡፡ መዝናኛው የዝሙት ወሬ ነው ፡፡ ሁሉም ነገር ዝሙትን እና ሴሰኝነትን ይሸታል ፡፡
አሁን ላይ እያየነው ላለነው መቅሰፍት አንዱና ዋነኛው ምክንያቱም ይሄው ነው።
የወጣቱ ኣለባበስ የተቃራኒ ጾታን ቀልብና ልብ ካልማረከ የለበሰ ኣይመስለውም ፡፡ አንዳንዱ ወንድ ጅንስ ሱሪውን በማጥበብ የውስጥ ልብሱን በማሳየት እና በማሳጠር ባቱን ወጥሮ እና ቁርጭምጭምቱን ገልጦ በመሄድ እህቱን አልያም ግብረ ሰዶማዊ ወንድሙን መስሏል ፡፡ አንዳንዶቹ ሴቶች ደግሞ ከላይ እስከ ታች ድረስ ሰውነታቸውን ወጣጥረው ሊፈነዳ ያለ ልብስና በመልበስ አጭር ቀሚስ በመልበሰ የኣካላቶቻቸውን ብልቶች በማሳየት የለበሱ- ራቁተኛ ሆነዋል ፡፡
ይህ እንደ ሰሃራ በረሃ የተራቆተ አለባበስ የትውልዱን ግብረ ገብነት ላጭቶ ወደ እንስሳነትና ኣውሬነት እያሸጋገረ ነው ፡፡ ምግብ ሲሰነብት እንደሚበላሸው ሁሉ ትውልድም ዘመናትን ሲቆይ እየተበላሸ መጥቶ ከመጥፋት ላይ ደርሷል - 8ኛው ሺህ ፡፡ በኣለባበስ ስርዓትና እና በግብረ ገብነት የተራበ ትውልድ መጨረሻው የምድጃ እንጨት ነው ፡፡
ዓይንን ፣ ጆሮን ፣ ምላስን ፣ እግርን ፣ እጅን በመንፈሳዊው ምርመራ ማስመርመርን እናስቀድም !
ከቤት ተነስተን ወደቤተክርስትያንም ሆነ ወደ ማንኛውም ቦታ ስንሄድ ኣሳፋሪ እና አሸማቃቂ አለባበሳችንን እንፈትሽ !

👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
💠 የክርስትና ስም ለምን ያስፈልጋል ?

ጥቂት የማንባል ሰዎች ከነ መሰየሙም የክርስትና ስማችንንም የማናስታውስ ልንኖር እንችላለን፡፡ የክርስትና ስም አንድ የሚጠመቅ
ሰው በሚያጠምቀው ካህን የሚሰጠው ወይም የሚጸድቅለት ስያሜ ነው፡፡ ይህንን ስም ቤ/ክ ዝም ብላ ለህጻናቱ የምትለጥፍ የሚመስላቸው ሰዎች ቀላል አይደሉም፡፡ በጥምቀት ግዜ ቤ/ክን ልጆቿን ስትቀበል እንዲሁ አይደለም ተገቢ ስም አውጥታ ከመንፈስ ቅዱስ በጥምቀት
ዳግመኛ ወልዳ ቅበዐ ሜሮን ቀብታ የሚንከባከብ የክርስትና አባት እናት ሰይማ በመስቀሉ ቃል አስገብታ ቅዱስ ስጋና ደሙን መግባ ነው፡፡ የክርስትና ስም መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ክርስቲያናዊ ትውፊት አለው፡፡ ብዙ ነብያት እና ቅዱሳን ካላቸው መጠሪያ ሰም በተጨማሪ እራሱ አምላካችን አዳዲስ ስም ሲያወጣላቸው እናያለን

ለምሳሌ፡-
አብራምን 👉 አብርሃም
ያይቆብን 👉 እስራኤል
ስምዖንንን 👉 ጴጥሮስ
ሳኦልን 👉 ጳውሎስ እያለ ሲጠራቸው

ለምን በአዲስ ስም መጥራት እንደፈለገ አንዳች ነገር ልንገነዘብ ይገባል፡፡

...ዓላማውስ ምንድን ነው?

#1ኛ .ቋሚ የቅዱሳን መታሰቢያ እንዲሆን፡- በት.ኢሳ 56:5 አምላክ ለቅዱሳን የማይጠፋ ስም እና የዘለዓለም መታሰቢያ እንደሰጣቸው እናነባለን፡፡ስለዚህ በተለያዩ ቅዱሳን ላይ የነበረውን ፀጋ እና በረከት ለመካፈልና እንዲሁም እንደነሱ የበረታን እንድንሆን በስማቸው እንሰየማለን የጌታችንንም ስሙን ዘርፍ በማድረግ እንዲሁ እንጠቀምበታለን፡፡

#2ኛ .ለተጠማቂውም በረከት እንዲሆንለት፡- በምሳ 10:6 የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው ይላል፡፡ ስለዚህ በስማቸው በመሰየም ከላይ እንደገለጽነው መታሰቢያቸውን እና በረከታቸውን ለመካፈል ሲረዳን ይህን ጸጋ ለማግኘት በቅዱሳን ስም በመሰየም የክርስትና ስም ይወጣልናል፡፡

#3ኛ .መጠሪያ ስም ነው፡-ላለመሰደድ
በቀድሞው ስርአት የክርስትና ስም ለሁልጊዜውም መጠሪያ ነበር፡፡ ከግራኝ መሐመድ መነሳት አስቀድሞ የነበሩ ምዕመናን በክርስትና ስማቸው ነበር የሚጠሩት፡፡ ነገር ግን
መከራው ሲበዛባቸው ከርስታቸው ሲሉ ተለዋጭ ስም በማውጣት መጠቀም ጀመሩ ከዛን ግዜ ጀምሮ ይህ ነገር እየተስፋፋ መጥቶ ከነ ጭራሹ ለመለወጥ በቃ፡፡

🛑 የማይገባ የክርስትና ስም

በአምላክ ስም በቀጥታ መጠራት አይገባም አማኑኤል፣ ኤልሻዳይ፣ ኢየሱስ እነዚህ ስሞች ለሠው ልጆች መጠናችን ስላልሆኑ መጠቀም የለብንም፡፡ በዚህ ምትክ ገብረ አምላክ፣ሣህለ ሥላሴ፣ ፍቅርተ ክርስቶስ፣ ዘአማኑኤል በማለት መሰየም ይቻላል፡፡

💠 በቅዱሳንም ስም በቀጥታም ሆነ ዘርፍ እየተደረለት መሰየም ይቻላል፡፡ ለምሳሌ፡- ዘማርያም፣ ዘሚካኤል፣ አጸደ ማርያም፣ ተክለ
ሐይማኖት ወዘተ... ስለዚህ ስርአቱን በመጠቀም ከሚገኘው በረከት ተሳታፊዎች እንድንሆን አምላክ ይርዳን፡፡ መልዕክቱን ለሌሎች ለማድረስ እባካችሁ ተጋሩት፡፡

#ሼር
_______

👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#የዘንባባ_ቀለበት_የማሰራችን_ምሳሌ

#1ኛ/ ጌታ ለአዳም "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" ያለውን የተስፋ ቃል (ቃል ኪዳን) ለማስታወስ

#2ኛ/ ጌታ ለእመቤታችን የገባላት የምህረት ቃል ኪዳን ተምሳሌት በመሆኑ፤

#3ኛ/ ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት በመሆኑ ይህንንም ለማሰብ ነው

#4ኛ/ አንድም ጌታ አዳምን ከሰይጣን ግዞት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም ከሰይጣን ግዞት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከኃጢአት አውጣን ማረን ለንስኃ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን ስንል ለጌታ ዳግም ላናጠፋ ቃል የምንገባበት በመሆኑ ዘንባባ በጣታችን በቀለበት መልክ እናስራለን፡፡

እንኳን ለሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳችሁ

@zekidanemeheret
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

#ጥያቄ 👇👇👇👇👇👇👇👇
#ፈጣሪ_ለሰው_ልጅ_የታዘለለትን_እንዲያገኝ_አስቀድሞ_ይወስናል?
#በኅጢአት_ስንወድቅ_ለምን_ዝም_ይላል?

#መልስ👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇

#እግዚአብሔር_የተወሰኑ_ሰዎችን_ለመንግሥቱ_ሌሎችን_ደግሞ_ለገሃነም_ወስኗልን? ✞

"...አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኗልና፡፡" ሮሜ. 8:29 የሚለውና ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ገጸ ንባቦችን በመያዝ የቅድመ ውሳኔ (Predestination) ትምህርትን የሚያስተምሩ ካልቪኒስቶች አሉ፡፡ እኚህ ወገኖች “የሰው ዕድል ፈንታው ጽዋዕ ተርታው ከጻድቃን ወይም ከኩንኖች መሆን አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተወሰነ ነው” በማለት ይናገራሉ፡፡ በዚህም የሰው ነፃ ፈቃድንም ገደል የሚከት ትምህርት ያስተምራሉ፡፡ ይህ የቅድመ ውሳኔ (Predestination) ትምህርት ከመጽሐፍ ቅዱስ አላማ ጋር የሚጋጭ ስህተቶችን የያዘ ነው፡፡

#1_አስቀድሞ_ሁሉን_ማወቅ_ወይስ_አስቀድሞ_መወሰን?

እግዚአብሔር ዓለምን ከመፍጠሩ በፊት እስከ ዓለም ፍጻሜ ሊሆን ያለውን ነገር ምንም ሳይሰወርበት ሁሉን ያውቃል፡፡ አንድ ሰው ከቅዱሳን ወገን አልያም ከኃጥአን ወገን እንደሚሆን አስቀድሞ ያውቃል /ሮሜ.8፡28-30/፡፡ ሆኖም ግን የተወሰኑትን ለመንግሥተ ሰማያት የተወሰኑትን ደግሞ ለገሃነም ለኩነኔ አልፈጠራቸውም፡፡ #እንዲህ_ቢሆንስ_ኖሮ_እግዚአብሔር_አንድስ_እንኳ_ይጠፋ_ዘንድ_እንደማይፈልግ_ባልተናገረ_ነበር /2ጴጥ.3፡9/፤ የዓለም ሕዝብ በሙሉ ለድኅነት መጥራት ባላስፈለገ ነበር /ማቴ.28፡19፣ ሮሜ.8፡19/፤ ሰዎች ሁሉ ይድኑ እውነትንም ያውቋት ዘንድ ባልወደደ ነበር /1ጢሞ.2፡4/፡፡ በመሆኑም ሰው ከእግዚአብሔር በተቀበለው ነጻ ፈቃዱ ተጠቅሞ ወይ ርትዕት በሆነች የሕይወት መንገድ ይጓዛል አሊያም የሞት መንገድ በምትሆን በኃጢአት መንገድ ይሄዳል፡፡ ድኅነት ለሁሉም የተሰጠ ቢሆንም የሰው ድኅነቱ በራሱ መሻትና የነጻ ፈቃድ ምርጫ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ሄሬኔዎስ የተባለ አባትም፡- “ጥቂቶች በተፈጥሮ ክፉ ቢሆኑ ሌሎችም መልካም ቢሆኑ መልካሞቹ ስለ መልካምነታቸው መልካም ሠሩ ተብለው ምስጋና የተገባቸው አይሆኑም፡፡ ሲፈጠሩ እንዲህ ሆነው ነውና፡፡ ክፉዎቹም ስለ ክፋታቸው ነቀፌታን ባላገኛቸው ነበር፡፡ ጥንቱንም ሲፈጠሩ እንዲህ ሆነዋልና” ብሏል /Iraneus, Book IV, Chap.37/፡፡

#2ኛ.#እግዚአብሔር_አያዳላም_ፍርዱ_ርቱዕ_ነው!

እግዚአብሔር የተወሰኑ ሰዎችን ለመንግሥተ ሰማያት ሌሎችን ደግሞ ለገሃነም አስቀድሞ ወስኗል ማለት ክብር ምስጋና ለስም አጠራሩ ይሁንና እግዚአብሔር ያዳላል እንደማለት ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ግን “#አምላካችሁ_እግዚአብሔር_የአማልክት_አምላክ_የጌቶች_ጌታ_ታላቅ_አምላክ_ኃያልም_የሚያስፈራም_በፍርዱም_የማያዳላ_መማለጃም_የማይቀበል_ነው” /ዘዳ.10፡17/፤
“እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንደማያዳላ በእውነት አየሁ” /ሐዋ.10፡34/ ፤ “ከእግዚአብሔር ዋጋችሁን እንደምትቀበሉ ታውቃላችሁ ለክርስቶስ ትገዛላችሁና የሚበድል ግን ፍዳውን ያገኛል እርሱም አያደላለትም” ይላል /ቈላ.3፡23/፡፡

#3_አስቀድሞ_መወሰን_አለ_ከተባለ_ትእዛዛት_ለምን_ተሰጡ?

እግዚአብሔር የተወሰኑትን ሰዎች ለመንግሥተ ሰማያት የተወሰኑትን ደግሞ ለገሃነም ፈጠረ ከተባለ ሰዎች በአእምሮ ጠባይ መሪነት፣ በሥነ ፍጥረት አስተማሪነት፣ በሕገ ልቡና አዋቂነት መልካም ሥራ መሥራት ሲያቅታቸው በየዘመናቱ ነቢያትን፣ ነገሥታትን፣ ካህናትን እያስነሣ መላኩ (ሎቱ ስብሐትና) ለከንቱ ነውን? ሐዋርያትና ሊቃውንት እንዲሁም ሰባክያን ለትምህርት ለተግሳጽ መላካቸው ምን ፋይዳ አለው /ማቴ.28፡19፣ 2ቆሮ.5፡8/?

#ይቀጥላል

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

🕊👉 @zekidanemeheret
#የዘንባባ_ቀለበት_የማሰራችን_ምሳሌ

#1ኛ/ ጌታ ለአዳም "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" ያለውን የተስፋ ቃል (ቃል ኪዳን) ለማስታወስ

#2ኛ/ ጌታ ለእመቤታችን የገባላት የምሕረት ቃል ኪዳን ተምሳሌት በመሆኑ፤

#3ኛ/ ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት በመሆኑ ይህንንም ለማሰብ ነው

#4ኛ/ አንድም ጌታ አዳምን ከሰይጣን ግዞት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም ከሰይጣን ግዞት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከኃጢአት አውጣን ማረን ለንስኃ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን ስንል ለጌታ ዳግም ላናጠፋ ቃል የምንገባበት በመሆኑ ዘንባባ በጣታችን በቀለበት መልክ እናስራለን፡፡

እንኳን ለሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳችሁ

https://t.me/zekidanemeheret