ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
802 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ትምህርተ_ንስሐ (በአቡነ ሺኖዳ)
#የመጨረሻው_ክፍል
#ንስሐ_እንዴት_ይገባል ?
#1ኛ_ከራስ_ጋር_መሆን
ንስሐ መግባት የራስን ፈቃድ ይጠይቃል። ምናልባት ያለህበትን የኀጢአት ባሕርና ጥፋት አልተገነዘብክ ይሆናልና መጀመሪያ ከራስህ ጋር መሆን አለብህ ። ከራሳችን ጋር የሆንን እንደሆነ ድካማችንንና ኀጢአታችንን ለእግዚአብሔር መናገር አይከብደንም ። ማንም ቢሆን በመንፈሳዊ ሕይወቱ በበረታ ቁጥር ሰይጣንም ሊጥለው ከመቼውም የበለጠ ኃይሉን አጠናክሮ ሊፈትነው እንደሚተጋ የተረጋገጠና የማይጠረጠር ነው ።
#2ኛ_ምክንያትንና_ለራስ_ይቅርታ_ማድረግን_ማስወገድ
በንስሐ ሕይወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደርና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም ። ኃጢአትን ከፈፀሙና ከሰሩ በኀላ ለኃጢአት ያበቃ ሌላ ምክንያት ማቅረብና በዚያም አንፃር ለመጽናናት መሞከር በራሱ ኀጢአት ነው ።ስለ ሰራነው ሀጢአት ንስሐ መግባት እንጂ ምክንያት በማበጀት ራስን ነፃ ማድረግ የለብንም ። በዓለም እስካለን ድረስ ሁላችንም ሀጢአትን እንሰራለን ። ወፍጮ ቤት ገብቶ ዱቄት ሳይነካን እንደማንወጣው ሁሉ በዓለምም እስካለን ድረስ እንበድላለን ። ለዚህ ነው አበው ሰው ሆኖ የማይሳሳት፣ እንጨት ሆኖ የማይጨስ ፣ ብረት ሆኖ የማይዝግ የለም የሚሉን ። እግዚአብሔርም ለምን በኀጢአት ወደቅክ አይለንም ለምን አልተነሳህም ነው የሚለን ። ሰለዚህ ንስሐ አባት የሌለን በመጀመሪያ ንስሐ አባት እንያዝ ከዛም ያደረግነውን ሁሉ ዝርዝር አርገን ተናግረን ከሀጢአት የተፈታን ወንዶች የ40 ቀን ህፃን ሴቶች ደሞ የ80 ቀን ህፃን እንሁን ። ሀጢአታችን ምንም ቢበዛም ከእግዚአብሔር ፍቅር ግን አይበልጥም ። የአምላካችን የክርስቶስ ደም ከኀጢአት ሁሉ ሊያነፃን የታመነ ነው ። ማንኛችንም ብንሆን የተወለድንበትን ቀን እንጂ የምንሞትበትን ቀን አናውቅም ። የትኛዋ ቅፅበት የመጨረሻችን እንደሆነች አናውቅምና በቶሎ ንስሐ ገብተን ተዘጋጅተን እንጠብቅ። ስለ #ንስሐ በጥቂቱ ከአቡነ ሺኖዳ መጽሐፍ ላይ ያዘጋጀነው ትምህርት ለዛሬ በዚ አበቃ ነገ ደግሞ ስለ ንስሐ በሌሎች ትምህርቶች እንመለስበታለን ሀሳብ አስተያየት ኢዮአታም ይጠቀሙ

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#መቼ_እንፈር?

"ወዳጆች ሆይ! ማፈር የሚገባን ኃጢአት ስንሠራ እንጂ #ንስሐ ስንገባ አይደለም፡፡ ኃጢአት ሕመም ነው፤ ንስሐ ደግሞ መድኃኒቱ ነው፡፡ ከኃጢአት ቀጥሎ ሐፍረት አለ፤ ከንስሐ ቀጥሎ ግን በጌታ የኾነ ደስታ አለ፤ነገር ግን ሰይጣን ይህን ቅደም ተከተል አዛብቶብን በኃጢአት ስንደሰት በንስሐም እናፍራለን፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
​​#ምሥጢረ_ንስሐ

#ንስሐ ፦ ነስሐ ተፀፀተ ካለው የተገኘ ሲሆን ፤ ንስሐ ማለት በሠሩት ኃጢአት መፀፀት ፣ ማዘን ፣ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ መወሰን ማለት ነው። ንስሐ ከዘለዓለማዊ ፍርድ የሚያድን ፤ ዘማዊውን እንደ ድንግል ፤ ሌባውን መጽዋች የሚያደርግ በፊት ከተሠራው ኃጢአት ንጹህ አድርጎ ፤ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ የሚያደርግ ምሥጢር ነው ።

#ከንስሐ_በፊት

#መፀፀት
አንድ ክርስቲያን በድፍረትም ይሁን በስህተት “የሠራው በደል” መጻሕፍት በማንበብ ፣ ከመምህራን ተምሮ ፣ የስብከት ካሴት አዳምጦ ፤ ህሊናው ወቅሶት ፣ ወይም በሌላ በአንድ ምክንያት ስህተት መሆኑን ከተረዳ በኋላ ተፀፅቶ ከእግዚአብሔር ለመታረቅ (በደሉን ለማስተስረይ) የሚያደርገው ጉዞ ንስሐ ይባላል።

በሠራው በደል ሳይፀፀት ፤ ለጊዜው ህሊናውን ስለረበሸው ብቻ ንስሐ የሚገባ ሰው ፤ ከንስሐው በኋላ ወደ ቀደመ ሕይወቱ ሊመለስ ይችላል ። ምክንያቱም ፡ ንስሐ የገባው ፡ በሠራው በደል ከልቡ ተፀፅቶ ሳይሆን ፤ በስሜት ተነሳስቶ ነውና ፤

#ኃጢአትን_መጥላት
በበደላችን ከተፀፅትን በኋላ የሰራነውን በደል መጥላትና ወደፊትም መሥራት እንደሌለብን ራሳችንን ማሳመንና ከኃጢዓት መንገድ መራቅ ማለት ነው ።

ከንስሐ በኋላ ስላለው ሕይወት መወሰን
አንድ ምዕመን ንስሐ ከመግባቱ በፊት ለወደፊቱ የሚኖረውን ሕይወት አስቀድሞ መመርመርና መወሰን ይገባዋል የእግዚአብሔን ቃል ስንሰማ ለጊዜው ልባችን ሊነካ ፣ ምን እናድርግ ልንል እንችላለን ። የሐ ሥ 2 ፥ 37።

ነገር ግን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ዓለሙን ወደመምሰል እንደማንመለስ አስቀድመን ራሳችንን መመርመር አለብን። ብዙዎቹ በስሜት ወደ ክርስትና ከገቡ በኋላ ፤ በጊዜያዊ ነገር ተታለው በድንገት ከሃይማኖት መንገድ ወጥተዋልና ።

#በንስሐ_ጊዜ

አንድ ምዕመን ካለፈ በደሉ በንስሐ ታጥቦ በአዲስ ሕይወት ራሱን ለማስተካከልና ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ከወሰነ በኋላ የንስሐ አባት ሊኖረው ይገባል።

ጌታችን “ካህናትን” ራሱን ወክለው መንጋውን እንዲጠብቁ “በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሰረ በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሁን” (ማቴ 8 ፥ ዮሐ 21 ፥ 15 ። ማቴ 16 ፥ 19) በማለት መንጋውን እንዲጠብቁ ሾሟቸዋልና።

አንድ ክርስቲያን በሕይወት ሲኖር ፤ የእግዚአብሔርን መንገድ የሚመራው ፤ ሲሳሳት ንስሐውን ተቀብሎ ቀኖና በመስጠት ከእግዚአብሔር የሚያስታርቀው የንስሐ አባት የግድ ሊኖረው ይገባል።


#ሼር
__
👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
የምንወደው ጓደኛችን ቢሞትብን ለቀናት ሐዘን እንቀመጣለን። ብር ቢጠፋብንም እንዲሁም እንቆጫለን። ዕለት ዕለት ሐጢአት ስንሠራ ግን ጥቂትስ እንኳ አናስብም። #መቼ_ይሆን_የምንነቃው?🤔

ልብስ የተሰጠን ከብርሃናዊ ልብሳችን ስለተራቆትን ነው /ዘፍ. 3፥20/። ታድያ በኃጢአታችን ምክንያት በተሰጠን ልብስ ልባችንን ከፍ ከፍ የምናደርገው ስለምንድ ነው?🤔

ተወዳጆች ሆይ! እስኪ ንገሩኝ ከእኛ መካከል #የሚኖርበትን_ቤት_በቆሸሸ_ቁጥር_የማያጸዳው_ማነው?

ታድያ የእግዚአብሔር ማደርያ የኾነው ሰውነታችንን #በንስሐ_መወልወያ #የምናጸዳው_መቼ_ነው?🤔

ልጆቼ #ንስሐ_ግቡ እንጂ በኃጢአታችሁ ምክንያት በፍጹም ተስፋ አንዳትቆርጡ።

ወዳጄ ሆይ! #ማፈር_የሚገባህ #ኃጢአት_ስትሰራ_እንጂ_ንስሐ_ስትገባ_አይደለም

#ኃጢአት_ሕመም ነው። #ንስሐ_ደግሞ_መድኃኒቱ_ነው። ከኃጢአት ቀጥሎ ህፍረት አለ ፤ ከንስሐ ቀጥሎ ግን በጌታ የኾነ ደስታ አለ። ነገር ግን ሰይጣን ይህን ቅደም ተከተል አዛብቶብን በኃጢአት ስንደሰት በንስሐም እናፍራለን።

☞☞#የቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #መልካም_ምክሮች

@zekidanemeheret