ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
802 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!

☞በተደጋጋሚ ከእህቶቻችን የወር አበባን አስመልክቶ ጥያቄ ስለመጣ እነሆ በድጋሚ ስለ ወር አበባ ፃፍንላችሁ
እስከመጨረሻው ድረስ ተከታትላችሁ ያልገባችሁን እንድትጠይቁን ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን !

~~~መልካም ንባብ~~

🔰 #የወር_አበባ # 🔰

#ጥያቄ#፦

👉በወር_አበባ ጊዜ መስቀል
መሳለም፣ መጽሐፍ ቅዱስ እና ሌሎች ጸሎት መጽሀፍትን ማንበብ ይቻላል?
እንዲሁም ወደ ቤተክርስትያን መሄድ ይቻላል ?

#መልስ#፦

👉የወር አበባ በሴቶች ላይ በየወሩ የሚታይ የደም መፍሰስ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን አስተምህሮ “ደመ ጽጌ፣ አበባ ደም” በመባል ይጠራል፡፡ አሰያየሙም የወንድ ዘር ካላገኘ ከማህጸን ግድግዳ ፍራሽ ጋር በደም መልክ ስለሚፈስና የኋለኛው ማንነቱ ደምነት ስለሆነ ነው፡፡ ይህም ማለት አገልግሎቱን የጨረሰ፣ ያረጀ፣ ቆሻሻ ማለት ነው፡፡ ይህ በየወሩ ዑደትን ተከትሎ የሚሄደው የዘር ፍሳሽ በስነ ህይወት ትምህርት ኦቫሪ (ከዘር ከረጢት) የሚለቀቅ የወንድ ዘር ካላገኘ ኦቫ (ሴቴ ዘር) ጋር እየተቀላቀለ የሚወርድ ነው፡፡

👉የወር አበባ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በሁለት ከፍለን ነው መመልከት ያለብን፤ በዘመነ ኦሪትና ዘመነ አዲስ ኪዳን በማለት፡፡ በርግጥ በዘመነ ኦሪት የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት ነበር፡፡ ለዚህም ማስረጃነት በመጽሃፍ ቅዱስ ዘሌ 18÷19፣ 20÷18 ያሉ ጥቅሶች “በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች” እና “ባለ መርገም ሴት” በማለት ሲገልጸው፤ ባንጻሩ ደግሞ ከወር አበባዋ ነጻ የሆነችውን ሴት “ከርኩሰትዋ ነጽታ” በማለት የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት መሆኑን ይጠቁማል፡፡ በዘመነ አዲስ ደግሞ የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት መሆኑ ቀርቷል፡፡
ርኩሰት አይደለም፤ ርኩስም አያሰኝም፡፡ በብሉይ ኪዳን አዳምና ሄዋን በገነት
በነበሩ ጊዜ ዕጸ በለስን በልተው እግዚአብሔርን በደሉ፤ እግዚአብሔርም ሄዋንን ደመ ዕጸ በለስን አፍስሰሻልና “ወበከመ አድመውኪያ ለእንትኩ ዕጽ ከማሁ ድምዊ ለለወርኁ፡፡” በማለት ደሟ በየወሩ እንዲፈስ ፈጣሪ ፈረደባት፡፡ ስለዚህ የሄዋን ደም መፍሰስ መነሻው መርገም ነው፡፡ በአዲስ ኪዳን ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈጸመው ቤዛነት መርገምነቱና ርኩስነቱ
ተወግዷል፡፡

👉የወር አበባ በዚህ ዘመን ርኩሰት ወይም መርገም ባይሆንም እድፍ (ቆሻሻ) ነው፡፡ እድፍና ርኩሰት ልዩነት አላቸው፡፡ ርኩሰት ውስጣዊ ነው፤ በንስሃ እንጂ በውሃ አይጠራም፡፡ እድፍ ደግሞ ግዘፍ አካል ያለው፣ የሚታይና ውሃ የሚያነጻው ነው፡፡ የወር አበባ በሴቶች ባህሪ ሳለ እንደ ቆሻሻ አይቆጠርም፣ ከሰውነት ሲወገድ ግን ይቆጠራል፡፡ ይህንን ለማስረዳት ምሳሌ መሆን ከሚችሉት ውስጥ ዛህል (ንፍጥ)፣ ሽንት፣ ምራቅ፣ ዓይነምድርና ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል፡፡

👉ወር አበባ ርኩሰት ባለመሆኑ መስቀል ከመሳም፣ ከመጸለይ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን ከማንበብና ከመድገም አያግድም፡፡ ነገር ግን ከሩካቤ፣ ከመጠመቅ፣ ከመቁረብና ቤተ መቅደስ ከመግባት ይከለክላል፡፡

🔶ከሩካቤ:-

👉ሩካቤ በወር አበባ ጊዜ ከሚከለከሉ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ በወር አበባ ጊዜ
የሚደረግ ግንኙነት የህክምና ባለሙያዎች ሳይቀር ለአባላዘር፣ ለልዩ ልዩ በሽታዎችና ለኢንፌክሽን ሊያጋልጥ እንደሚችል በመናገር እንዳይፈጸም
ይመክራሉ፡፡ በመንፈሳዊው አስተምህሮ ስንመለከተው ደግሞ የሰው ልጅ ዘር
ቅዱስ በሆነው በእግዚአብሔር አምሳል በመፈጠሩ፣ ይህንን የተከበረ ዘር፣ እዳሪ
ወይም ቆሻሻ ከሆነ ደም ጋር ማዋሃድ ኃጢያት እንደሆነ ይቆጠራል፡፡

👉በመጽሐፍ ቅዱስ ሴት ልጅ በወር አበባዋ ጊዜ እንዳለች የሚፈጸምን ሩካቤ
“እርሷም በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች ኃፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ ወደ እርሷ
አትቅረብ” ዘሌ 18÷19፣ ዘሌ 20÷18።
በዚህም ምክንያት በወር አበባ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ በኦሪትም ይሁን በአዲስ ኪዳን ክልክል ነው፡፡

🔶ከመጠመቅ:-

👉ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ “ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ
አሁን ያድነናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፡፡ ለእግዚአብሔር በጎ ህሊና ልመና ነው እንጂ” 1ኛ ጴጥ 3÷21 በማለት ተናግሯል፡፡ ስለዚህ ጥምቀት ስጋዊ እድፍን ማስወገጃ ስላልሆነ፣ ከመጠመቅ በፊት ተጣጥበው እንጂ ከእድፍ ጋር ለመጠመቅ መቅረብ ተገቢ አይደለም፡፡ የወር አበባም ከላይ
እንደተመለከተው ከሰውነት ሲወጣ እድፍ (ቆሻሻ) በመሆኑ፣ ከዚህ የቤተ
ክርስቲያን ስርዓት ውጪ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

🔶ቤተመቅደስ መግባት፡-

👉ሴት በወር አበባዋ ጊዜ የምትከለከለው ነገር ቤተመቅደስ መግባትን ነው፡፡ይህም የሆነው በርኩሰት ምክንያት ወይም በኦሪት ሕግ ምክንያት ሳይሆን በቤተመቅደስ መፍሰስ ያለበት ደም አማናዊ የሆነው የክርስቶስ ደም ብቻ በመሆኑ ነው!ይህ ስርዓት ለሴቶች ብቻ ሳይሆን ለወንዶችም ነው፡፡ አንድ ወንድ እየነሰረው ወይምየሆነ ነገር አካሉን ቆርጦት ደም እየፈሰሰው ከሆነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባትየለበትም!ምክንያቱም በቤተ መቅደስ ከክርስቶስ ደም ውጪ ሌላ ነገር መፍሰስ ስለሌለበት ነው፡፡

👉**በወር አበባ ላይ ሳለች ሴት ወደ ቤተመቅደስ አትግባ ማለት ቤተ ክርስቲያን አትሂድ ማለት ሳይሆን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዳ የመጀመሪያውን ቅጽር (አጥር) ከገባች በኋላ በመጠለያ ውስጥ በመሆን ትጸልይ፣ጠበል ትጠጣ፣ ትማር ወይም ማንኛውንም አይነት መንፈሳዊ ስራዎችን ሰርታ ትመለስ ማለት ነው፡፡

🔶ከመቁረብ፡-

👉ሴቶች ከወር አበባ ሳይነጹ ሥጋ ወደሙ መቀበል አይችሉም፡፡ ይህንን ስርዓት ተላልፈው ወደ ሥጋ ወደሙ እንዲቀርቡ ያደረገ ዲያቆንም ይሁን ቄስ ከክህነቱ እንዲሻር ፍትሕ ነገስት ይደነግጋል፡፡ “ከግዳጅዋ ያልነጻችውን ሴት በደሟ ወራት ከቤተ ክርስቲያን አግብቶ ሥጋውን ደሙን ያቀበለ ከክህነቱ ይሻር፡፡” ፍትነገ 6፣ ዘሌ 7፡19
ይህ ሥርዓት በሴቶች ላይ ብቻ ሳይሆን ወንዶችም ህልመ ለሊት በሚያጋጥማቸው ሰዓት እንዳይገቡ ይከለከላል፡፡

👉ቤተ ክርስቲያን የገነት ምሳሌ ናት፡፡ ሔዋን ከአዳም ጋር በገነት ለሰባት ዓመታት ስትኖር የወር አበባ አታይም ነበር፡፡ ቤተ መቅደስ የገነት ምሳሌ መሆኗ የተሟላ እንዲሆን የወር አበባ የምታይ ሴት ወደ ቤተ መቅደስ አትገባም፡፡
ይቆየን !
:
💥ትምህርቱ ከተመቻችሁ እስኪ በ👍 አሳዩን
:
:
☞ የእናንተ አስተያየት ብዙ እንድንሰራ ይጠቅመናልና አስተያየታችሁን አትንፈጉን
ለጥያቄ እና አስተያየት ኢዮአታም ኢዮአታም ኢዮአታም


✿መልካም ደስ የሚል የተባረከ
ለሊት ይሁንላችሁ !✿

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
++++++++++++++

" #ምሥጢሬን_ላካፍላችሁ "

የዕለቱ ባለታሪክ -
" ሰላም እኅት ወንድሞቼ ! ዩኒቨርሲቲ የ 3ኛ ዓመት ተማሪ ነኝ ። መጠጥ ካልጠጣን እያሉ ብዙ ጓደኞቼ ያስቸግሩኛል። እኔ ግን መጠጥ መጠጣት ኃጢያት መሆኑን ደጋግሜ እነግራቸዋለው። እነርሱም መጠጥ ኃጢያት አይደለም ብለው ይከራከሩኛል። ለመሆኑ ማንኛችን ልክ ነን? "

#መልስ - እዚህ ላይ ሁላችንም ልናስተውል የሚገባው ነገር አለ። ይኸውም ጥቅስ እየጠቀሱ "ኃጢያት ነው ፤ አይደለም፡፡" የሚለው ክርክር ወይም እንካ ሰላንቲያ ምንም አይጠቅምም ፤ ይህንንም ከተገነዘብን በኋላ አንድ ነገር እንመልከት ። ከመጠጥ በስተጀርባ የሚመጣውን ችግር ። "ጉዳት እና ጅራት ከወደ ኋላ ነዉ ።" እንዲል ።

እንኳን እኛ ደካሞች ከቁጥር የማንገባው ቀርቶ በመንፈሳዊ ሕይወት ታላላቅ የሚባሉ ሰዎች በመጠጥ ምክንያት ሲወድቁ ታይተዋል። ከዚህ ላይ እግዚአብሔር ያልከሰሳቸውን መክሰስ ባይገባም ለአብነት ግን እንጠቅሳቸዋለን።

አባታችን ኖኅ ከጥፋት ውኃ በኋላ የወይን ጠጅ ጠጥቶ በመስከሩ ራሱን ስቶ እርቃኑን ተዘርሮ የወደቀበት ጊዜ ነበር። ዘፍ19፥33-35። ይህንንም ይዘን እንኳን እነ እገሌ ሰክረዋል ብሰክር ምን አለበት እያልን እንድንጠቅሳቸው ሳይሆን ከእነርሱ ተምረን አቅማችንን አውቀን ራሳችንን እንድንጠብቅ ነው። ምን አልባት ከመጠኔ አላልፍም፤ በመጠን እጠጣለሁ እንል ይሆናል። ነገር ግን በመጠን እንጠጣ ዘንድ እራሳችንን የገዛን ሰዎች ነን ወይ? ብለን ልንጠይቅ ያስፈልጋል። ምክንያቱም ራሳችንን ካልገዛን መስክራችን ስለማይቀር ነው። ራስን አለመግዛት ደግሞ የሚያጋልጠው ለስካር ብቻ ሳይሆን ለዝሙትና ለተቀሩትም የኃጢአት አይነቶች ነው። "ስለዚህ የልቦናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠኑ ኖራችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ፀጋ ተስፋ አድርጉ። "1ኛ ጴጥ.1፥13 እንደተባለ በመጠን ለመኖር የግድ ራስን መግዛት ያስፈልጋል።ራስን መግዛት የመንፈስ ፍሬ ነው። ገላ 5፥23 ስለዚህ አንተም ሆንክ ጓደኞችህ የመጠጥን ጉዳይ ስታነሱ ከሁለት አንፃር ተመልከቱት።

1. መጠንን ከማወቅ እና ራስን ከመግዛት ፡- መጠጣት ጀምረን በመጠናችን ልክ ስንደርስ ራሳችንን በመግዛት ማቆም አለብን፡፡

2. ከምንሰራው ስራ ለፈቃደ ሥጋ አሳልፎ እንዳይሰጥ እና የድኅነት ጉዟችንንም እንዳያሰናክል ከምናደርገው ጥንቃቄ አንፃር ሊታይ ይገባል። ከነዚህ ጋር የሚጋጭ ከሆነ ግን ኃጢያት ነው ።

በአጠቃላይ መጠጥ በራሱ ኃጢአት አይደለም፡፡ ስለጠጣን አንኮነንም ፤ ስላልጠጣንም አንጸድቅም፡፡ መጠጥን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ በሰርግ ቤት ተገኝቶ ውኃውን ወደወይን ጠጅ በመለወጥ ሰጥቷቸዋል፡፡ መጠጥ በራሱ ኃጢአት ቢሆን ክርስቶስ በሰርግ ቤቱ ያንን ተአምር ባላደረገ ነበር፡፡ ነገር ግን አንድ ሁለት ተብሎ ተጀምሮ ከዚያ ወደሞቅታ ፣ ከዚያ ወደጭፈራ እና መዳራት ፣ ከዚያ ወደስካር ፣ ከዚያ ወደመሳደብ ፣ ከዚያ ወደዝሙት ሲያመራ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ትልቅ ኃጢአት ይሆናል፡፡

• አንዳንድ ሰዎች " ስካር ምን ያደርግ ይሆን? እስቲ ስሜቱን ልየው፡፡ " በሚል ለመስከር ይጠጣሉ፡፡ ይሄ በፍጹም መደረግ የሌለበት ነው፡፡ የሰይጣንን ሥራ አቀለልንለት ማለት ነው፡፡ እኛ ወደን እና ፈቅደን ስንሰክር ከላይ ወደተዘረዘሩት መጥፎ ሥራዎች ይመራናል፡፡ ቤት ውስጥም ሆነን ብንሰክር ቤተ-ሰቦቻችን ላይ የስድብ ቃላትን እንሰነዝራለን ፤ መባልና መደረግ የሌለባቸውን ነገሮች እናደርጋለን፡፡ ስለዚህ እንደእባብ ብልሆች ሆነን ከሰከሩት መማር ነው ያለብን፡፡

✝️ይቆየን ✝️

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
🌺 @zekidanemeheret🌺
🌺 @zekidanemeheret 🌺
🌺 @Zekidanemeheret🌺
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
ኢዮአታም፡
ስለ #አዳምና_ሄዋን_ጥያቄ_ከነ_መልሱ
1/ እግዚአብሔር አዳምን ከፍጥረታት መጨረሻ ለምን ፈጠረው?
2/ እግዚአብሔር ሌሎችን ፍጥረታት አስጎንብሶ ሲፈጥራቸው አዳምን አቅንቶ ለምን ፈጠረው?
3/ እግዚአብሔር አዳምን የሚቆም ፣የሚተኛ አድርጎ ለምን ፈጠረው?
4/ እግዚአብሔር ለአዳም ስንት ሀብታትን ሰጠው?ምንምን ናቸው?
5/ እግዚአብሔር ሄዋንን ከአዳም ከጎኑ አጥንት ለምን ፈጠራት ?ከግንባር ወይም ከ እግር ለምን አልፈጠራትም?
6/ በገነት ውስጥ ስንት አይነት ዛፎች ነበሩ?
7/አዳምና ሄዋን የእግዚአብሔርን ህግ በማክበር በገነት ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ቆዩ?
8/ አዳምና ሄዋን በእባቢቱ ላይ አድሮ ያሳታቸው ሰይጣን ስም ማን ይባላል?
9/አዳምና ሄዋን ስንት ልጆች ነበራቸው ?
10/ አዳም በተፈጠረ በስንት ዓመቱ አረፈ?
#አዳም ማለት ከመሬት የተፈጠረ ያማረ መልከ መልካም ማለት ሲሆን የተፈጠረው ከአራቱ ባህርያተ ስጋ ማለትም ከነፋስ፣ከእሳት ፣ከውሀ፣ከመሬት እንዲሁም ከሶስቱ ባህርያተ ነፍስ ማለትም ከልብ ፣ከቃል፣ከእስትፋስ
የስነ ፍጥረት መካተቻ በሆነች በእለተ አርብ በ3 ሰዓት ከብህቱም ምድር ሚያዝያ 4 ቀን በምድር መካከል በምትገኘው <ኤልዳ> በተባለች ስፍራ የ30 ዓመት ጎልማሳ ሁኖ በእግዚአብሔር አርአያነት መልክ ተፈጠረ፡፡
ኦሪት ዘፍጥረት 1÷27 ፣ኩፉሌ 5÷6
#መልስ ፡-
1/አዳም ከፍጥረታት መጨረሻ ለምን ተፈጠረ?
☞መጨረሻ የተፈጠረበት ምክንያት እግዚአብሔር አምላካችን "በጎ አምላክ" ስለሆነ በጎ አባት ለልጁ አብሮት ከብት ያረባለታል ፣ጥማጅ ያጠምድለታል፣ የኑሮ ጓደኛ ያመጣለታል አስቀድሞየሚበላው፣የሚጠጣ
ው፣የሚገዛውና የሚነዳውን ፈጥሮለት በመጨረሻም በሁሉ ላይ ሊያሰለጥነው አዳምን ፈጠረው፡፡
2/ ሌሎችን ፍጥረታት አስጎንብሶ ሲፈጥራቸው አዳምን ለምን አቅንቶ ፈጠረው?
☞ እሱ ገዥ እናንተ ተገዥ ናችሁ ሲል ነወ፣እንዲሁም እናንተ ፈርሳችሁ በስብሳችሁ ትቀራላችሁ እሱ ግን" ትንሳኤ ሙታን " አለው ሲል አቅንቶ ፈጠረው፡፡
3/ አዳምን የሚቆም የሚተኛ አድርጎ ለምን ፈጠረው?
☞ መቆሙ- ሰማያዊ ፣
☞መቀመጡ- ምድራዊ ነህ ሲለው ነው፣
☞የሚተኛ ፣ የሚነሳ አድርጎ መፍጠሩ ደግሞ
☞መተኛቱ ሞቱን
☞መነሳቱ - ትንሳኤውን ሲነግረው ነው፡፡
4/ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም ስንት ሀብታት ሰጠው?ምን ምን?
☞ሰባት ሀብታትን የሰጠው ሲሆን እነሱም፡-
➊ሀብተ መንግስት (የማስተዳደር ሀብት
➋ሀብተ ክህነት ( የመቀደስ፣የመባረክ፣መስዋዕት የማቅረብ
➌ ሀብተ ትንቢት (የመጣውን የመናገር
➍ሀብተ መዋኢ (የማሸነፍ
➎ሀብተ ሀይል (የጥንካሬ
➏ሀብተ ፈውስ ( የማዳን ፣የመፈወስ
➐ሀብተ ዝማሬ (የመዝሙር
5/ ሄዋን ከአዳም ከጎኑ አጥንት ተወስዳ ለምን ተሰራች?ከግንባር ወይም ከእግር ለምን አልሰራትም?
☞ አዳም ለእንሰሳት፣ለሰማይ ወፎች ና ለምድር አራዊቶች ሁሉ ተባእትና እንስት ሁነው ሲመጡ ስም ያወጣላቸው ነበር፡፡ነገር ግን ለአዳም እንደ ራሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር ፡፡
"እግዚአብሔርም " ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት አለ ፡፡ኦዘፍ 2÷18
ከዚያም በአዳም ላይ እንቅልፍ አመጣበትና ፈፅሞ ሳይተኛ ፣ፈፅሞ ሳይነቃ ከጎኑ አጥንት አንስቶ ያችን ስጋ አልብሶ የ15 ዓመት ቆንጆ አድርጎ ፈጠራት ፣ኦዘፍ 2÷18
አዳምም ስሟንም "ሄዋን" አላት ፣ሄዋን ማለት "ሀይው" ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም" የህያዋን ሁሉ እናት "ማለት ነው፡፡
ፈፅሞ ሳይተኛ ፣ፈፅሞ ሳይነቃ ሄዋንን መፍጠሩ
☞ፈፅሞ ተኝቶ ቢሆን ኑሮ ምትሀት መስሎት ከየት መጣች ብሎ ይፈራታል
☞ፈፅሞ ነቅቶ ቢሆን ኑሮ ከአካሉ አጥንት ሲነሳለት ያመው ነበርና ይጠላት ነበር ፡፡
☞ከፍ አድርጎ ከግምባር ዝቅ አድርጎ ከእግር ያልሰራት ግምባርና እግር በልብስ አይሸፈንም ጎኑ ግን በልብስ ይሸፈናልና ተሰውራ ወይም ተሸፍና መኖር ይገባታል ሲል ነው፡፡
በሌላ በኩል ግንባር የባለቤት እግር፣ የቤተሰብ ምሳሌ ነው ፡እሷም ከባለቤቷ በስተ ታች ከቤተሰብ በላይ ሁና ትኑር ሲል ነው ፡፡1ኛ ቆሮ 12÷19-22
እንዲህ አድርጎ አዳምና ሄዋንን እስከ 40 ቀን ድረስ በተፈጠሩበት በማዕከለ ምድር በቀራንዮ አሰነበታቸው
ጌታችን አምላካችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰቀልበት ቦታ ነውና ከዛም በ40ኛው ቀን አዳምን ብርሃን አልብሰው ፣ብርሀን አጎናፅፈው፣የብርሀን ዘውድ አቀናጅተው በብርሃን ሰረገላ አስቀምጠው ወደ ገነት አስገቡት፡፡
ሄዋንንም በ80 ቀኗ እንደ አዳም ባለ ክብር ወደ ገነት አስገቧት ፡፡ኩፉሌ 4÷12-15
አዳምና ሄዋን ከእግዚአብሔር የባህሪ ደግነት የተነሳ እርሱን ለማመስገንና ክብሩን ለመውረስ ተፈጠሩ፡፡ኩፋሌ 4 ÷3-5
እግዚአብሔር ለአዳም ረዳት የፈጠረለት ስለ ሶስት ነገሮች ሲል ነው፡፡
➊ዘርን ለማብዛት
➋ ከዝሙት እንዲፀዳና
➌ረዳት እንድትሆነው ነው
6/ በገነት ውስጥ 3 አይነት ዛፎች ነበሩ
➊ ዕፀ መብል -እንዲበሉት የተፈቀደላቸው ምግብ ነው
➋ዕፀ በለስ-እንዳይበሉ የታዘዙት ነው
➌ዕፀ ህይወት - እንደ <እግዚአብሔር > ፈቃድ የሚመገቡት የዘለዓለም ህይወት የሚሰጥ ምግብ ነው፡፡
ህግን ጠብቀው በገነት ውስጥ 1000 ዓመት ከኖሩ ብኀላ እፀ ህይወት በልተው ከገነት ወደ ሰማያዊ ኢየሩሳሌም (መንግስተ ሰማይ ) እንዲገቡ ለበለጠ ክብርና ፀጋ ሽልማት እንዲሆናቸው ነበር፡፡ነገር ግን ያለ ጊዜው ሳቱ እንጅ
'እፀ በለስ ' እንዳይበሉ የታዘዙበት ህግ አዳም ፈጣሪ እንዳለው ፣ለፈጣሪው ያለውን ፍቅር የሚገልፅበትና ተገዥነቱን የሚያሳይበት ነው፡፡
7/ አዳምና ሄዋን የእግዚአብሔርን ህግ በማክበር በገነት ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ቆዩ?
☞አዳምና ሄዋን ይህን ህግ በማክበር በገነት ውስጥ ለ7 ዓመት ከ 2ወር ከ 17 ቀን ኖሩ፡፡
8/ አዳምና ሄዋንን በእባብ ላይ አድሮ ያሳታቸው ሰይጣን ስም ማን ይባላል ?
☞አዳም በሳጥናኤል ተተክቶ መቶኛ ሁኖ ከመላእክት ጋር ተቆጥሮ ነበር ሰይጣንም በእባብ አድሮ አሳታቸው ጽድቃቸውም ተገፈፈ አዳምና ሄዋንን በእባብ ላይ አድሮ ያሳታቸው ሰይጣን ስም ' ጋርድኤል ይባላል፡፡
9/ አዳምና ሄዋን ስንት ልጆች ነበሯቸው?
☞ ከገነት ከተባረሩ ብኀላ በደብረ ቅድስት ይኖሩ ነበር፡
አዳምና ሄዋን በሰሩት ሀጢያት በመፀፀታቸውና በንሰሀ በመመለሳቸው "እግዚአብሔር" መሀሪ ነውና 5 ቀን ተኩል ወይም 5500 ዘመን ሲፈፀም ሰው ሁኖ በመወለድ እንደሚያድናቸው ቃል ኪዳን ገባላቻው ፡፡ኦዘፍ 3÷15-22
አዳም ግን የራሱን ደም በስንዴ ለውሶ ሲሰዋ ጌታችን በአንተ ደም አይደለም ዓለም የሚድነው በእኔ ነው ብሎ ተስፋ ሰጠው፡፡
አዳምና ሄዋንም በምድር ላይ ዘርን ተክተዋል ገብርኤል ፣ሚካኤል ፣ሩፋኤል ወርቅ ,እጣን,ከርቤ አምጥተው ለአዳም ሲሰጡት ወርቁን ማጫ ይሁንሽ ብሎ ሰጣት ከዛም አዳምና ሄዋን በ 30 ሩካቤ 60 ልጆችን ወልደዋል
10/ አዳም በተፈጠረ በስንት ዓመቱ አረፈ?
☞ አዳም በተፈጠረ በ930 ዓመቱ አረፈ ፡አዳም ለሄዋን የሰጣት ወርቅ ለሴት ሰጠችው ሴትም ለኖህ አስተላለፈው እጣኑንም ኖህ አፅመ አዳም እያጠነ ድኖበታል ፡፡
በአዳም ስም በሀገራችን የተሰሩ ቤተክርስቲያኖች ብዛታቸው 5 ናቸው
በአዳም ስም የተቀረፀው ታቦት ከሶሪያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ያመጣው ፃድቅ አባት 'መልከአ እግዚአብሔር ' ይባላል፡፡
----------ምንጭ----------
መፅሀፈ ኩፋሌ
በቅንነት ሼር አድርጉት!!!! 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉@zekidanemeheret👈
👉👉@zekidanemeheret👈
👉👉@zekidanemeheret👈
🌅🌅🌅🌄🌅🌅🌅🌄🌅🌅🌅🌄🌅
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

#ጥያቄ
የሞተ ሰው የፍርድ ቀን እስኪመጣ ነፍሱ እዛው የተቀበረበት ነዉ ሆኖ ነው ሚጠብቀዉ ወይስ ወዲያዉ ይፈረድለታል??

#መልስ ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

ሰው ሰጋና ነፍስ አሉት፡፡ ስጋ ግዙፍ የሚዳሰስ ነፍስ ደግሞ ረቂቅ ናት፡፡ ሰው ሲሞት ወደ መቃብር ይሄዳል፡፡ ነፍስ የተለየው ነውና ሬሳ ይባላል፡፡ ጠቢቡ ሰለሞን በመጽሐፈ መክብብ"የሰው ልጅ ነፍስ ወደ ላይ እንደምትወጣ የእንስሳም ነፍስ ወደ ታች ወደ ምድር እንደምትወርድ የሚያውቅ ማነው?" መክ 3:21 በማለት የሰው ነፍስ ወደ ላይ እንደምትወጣ ነግሮናል፡፡

የሙታን ነፍሳት ከስጋ እንደተለዩ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ በማረፍያ ቦታ ይቆያሉ እንጂ በቀጥታ ወደ መንግሰተ ሰማያት ወይም ወደ ገሃነመ እሳት እንደማይላኩ ቤተ ክርስቲያን የምታምነውና የምታስተምረው ትምህርት ነው፡፡ እስከ ፍርድ ጊዜ የሚቆዩበትም ቦታ ለጻድቃን ገነት ሲሆን ለኃጢአተኞች ደግሞ ሲዖል ነው፡፡ የፃድቃን ማረፍያ ቦታቸው ገነት መሆኑን ለማመልከት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቀሎ በነበረ ጊዜ ንስሐ ለገባው በቀኝ ለተሰቀለው ወንበዴ "እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከኔ ጋር ትኖራለህ ፡፡ ሉቃ 23:43 ብሏል፡፡ የኃጢአተኞች መቆያ ደግሞ ሲዖል መሆኑን ሲያመለክት ሐብታሙ በሲዖል ይሰቃይ እንደነበር በባለጠጋውና በአልዓዛር ታሪክ ላይ ይመለከቷል፡፡ ሉቃ 16:23

የፃድቃንም ሆነ የኃጥአን ነፍሳት ወዲያው ከስጋ እንደተለዩ የመጨረሻ ዘላለማዊ መኖርያቸው ወደ ሆነው መንግስተ ሰማያት ወይም ገሃነመ እሳት የማይወሰዱበት ምክንያት ነፍስና ስጋ ሆነው በአንድነት ሆነው ለፈጸሙት በጎም ሆነ ክፉ ተግባር ዋጋቸውንም አብረው ሆነው ማግኘት ስላለባቸው ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

#ጥያቄ 👇👇👇👇👇👇👇👇
#ፈጣሪ_ለሰው_ልጅ_የታዘለለትን_እንዲያገኝ_አስቀድሞ_ይወስናል?
#በኅጢአት_ስንወድቅ_ለምን_ዝም_ይላል?

#መልስ👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇

#እግዚአብሔር_የተወሰኑ_ሰዎችን_ለመንግሥቱ_ሌሎችን_ደግሞ_ለገሃነም_ወስኗልን? ✞

"...አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኗልና፡፡" ሮሜ. 8:29 የሚለውና ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ገጸ ንባቦችን በመያዝ የቅድመ ውሳኔ (Predestination) ትምህርትን የሚያስተምሩ ካልቪኒስቶች አሉ፡፡ እኚህ ወገኖች “የሰው ዕድል ፈንታው ጽዋዕ ተርታው ከጻድቃን ወይም ከኩንኖች መሆን አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተወሰነ ነው” በማለት ይናገራሉ፡፡ በዚህም የሰው ነፃ ፈቃድንም ገደል የሚከት ትምህርት ያስተምራሉ፡፡ ይህ የቅድመ ውሳኔ (Predestination) ትምህርት ከመጽሐፍ ቅዱስ አላማ ጋር የሚጋጭ ስህተቶችን የያዘ ነው፡፡

#1_አስቀድሞ_ሁሉን_ማወቅ_ወይስ_አስቀድሞ_መወሰን?

እግዚአብሔር ዓለምን ከመፍጠሩ በፊት እስከ ዓለም ፍጻሜ ሊሆን ያለውን ነገር ምንም ሳይሰወርበት ሁሉን ያውቃል፡፡ አንድ ሰው ከቅዱሳን ወገን አልያም ከኃጥአን ወገን እንደሚሆን አስቀድሞ ያውቃል /ሮሜ.8፡28-30/፡፡ ሆኖም ግን የተወሰኑትን ለመንግሥተ ሰማያት የተወሰኑትን ደግሞ ለገሃነም ለኩነኔ አልፈጠራቸውም፡፡ #እንዲህ_ቢሆንስ_ኖሮ_እግዚአብሔር_አንድስ_እንኳ_ይጠፋ_ዘንድ_እንደማይፈልግ_ባልተናገረ_ነበር /2ጴጥ.3፡9/፤ የዓለም ሕዝብ በሙሉ ለድኅነት መጥራት ባላስፈለገ ነበር /ማቴ.28፡19፣ ሮሜ.8፡19/፤ ሰዎች ሁሉ ይድኑ እውነትንም ያውቋት ዘንድ ባልወደደ ነበር /1ጢሞ.2፡4/፡፡ በመሆኑም ሰው ከእግዚአብሔር በተቀበለው ነጻ ፈቃዱ ተጠቅሞ ወይ ርትዕት በሆነች የሕይወት መንገድ ይጓዛል አሊያም የሞት መንገድ በምትሆን በኃጢአት መንገድ ይሄዳል፡፡ ድኅነት ለሁሉም የተሰጠ ቢሆንም የሰው ድኅነቱ በራሱ መሻትና የነጻ ፈቃድ ምርጫ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ሄሬኔዎስ የተባለ አባትም፡- “ጥቂቶች በተፈጥሮ ክፉ ቢሆኑ ሌሎችም መልካም ቢሆኑ መልካሞቹ ስለ መልካምነታቸው መልካም ሠሩ ተብለው ምስጋና የተገባቸው አይሆኑም፡፡ ሲፈጠሩ እንዲህ ሆነው ነውና፡፡ ክፉዎቹም ስለ ክፋታቸው ነቀፌታን ባላገኛቸው ነበር፡፡ ጥንቱንም ሲፈጠሩ እንዲህ ሆነዋልና” ብሏል /Iraneus, Book IV, Chap.37/፡፡

#2ኛ.#እግዚአብሔር_አያዳላም_ፍርዱ_ርቱዕ_ነው!

እግዚአብሔር የተወሰኑ ሰዎችን ለመንግሥተ ሰማያት ሌሎችን ደግሞ ለገሃነም አስቀድሞ ወስኗል ማለት ክብር ምስጋና ለስም አጠራሩ ይሁንና እግዚአብሔር ያዳላል እንደማለት ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ግን “#አምላካችሁ_እግዚአብሔር_የአማልክት_አምላክ_የጌቶች_ጌታ_ታላቅ_አምላክ_ኃያልም_የሚያስፈራም_በፍርዱም_የማያዳላ_መማለጃም_የማይቀበል_ነው” /ዘዳ.10፡17/፤
“እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንደማያዳላ በእውነት አየሁ” /ሐዋ.10፡34/ ፤ “ከእግዚአብሔር ዋጋችሁን እንደምትቀበሉ ታውቃላችሁ ለክርስቶስ ትገዛላችሁና የሚበድል ግን ፍዳውን ያገኛል እርሱም አያደላለትም” ይላል /ቈላ.3፡23/፡፡

#3_አስቀድሞ_መወሰን_አለ_ከተባለ_ትእዛዛት_ለምን_ተሰጡ?

እግዚአብሔር የተወሰኑትን ሰዎች ለመንግሥተ ሰማያት የተወሰኑትን ደግሞ ለገሃነም ፈጠረ ከተባለ ሰዎች በአእምሮ ጠባይ መሪነት፣ በሥነ ፍጥረት አስተማሪነት፣ በሕገ ልቡና አዋቂነት መልካም ሥራ መሥራት ሲያቅታቸው በየዘመናቱ ነቢያትን፣ ነገሥታትን፣ ካህናትን እያስነሣ መላኩ (ሎቱ ስብሐትና) ለከንቱ ነውን? ሐዋርያትና ሊቃውንት እንዲሁም ሰባክያን ለትምህርት ለተግሳጽ መላካቸው ምን ፋይዳ አለው /ማቴ.28፡19፣ 2ቆሮ.5፡8/?

#ይቀጥላል

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

🕊👉 @zekidanemeheret