Intrance result.neaea.gov.et
1.3K subscribers
512 photos
29 videos
299 files
534 links
መረጃዎች ምንጫቸውን ሳንጠቅስ አናጋራም!

ወቅታዊ ፈጣንና ታማኝነት ያላቸውን ት/ተዊ ቴክኖሎጂ፤ ፋሽንን ጨምሮ የመዝናኛ መረጃዎችን በአንድ ቦታ ለማግኘት፤ ዛሬውኑ በመቀላቀል ራሶን ከዘመኑ ጋር ያዘምኑ፤ የአዋቂ ማህበረሰብ አካል ይሁኑ።

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@intrancresult
ሀሳብ @TheRsultBot
Download Telegram
#Update

ትምህርት ሚኒስቴር ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደማይቀላቀሉ የገለፀ ሲሆን ነገር ግን የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት በውጤታቸው መሰረት ተጨማሪ ተማሪዎችን በመቀበል ለቀጣይ ዓመት ዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት እንዲያገኙ ይሰራል መባሉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግባል።


https://t.me/intrancresult2022
https://t.me/intrancresult2022
#Update

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች በመንግስት በሚወሰን ነጥብ "ዕጩ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ" ሆነው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡበት ዕድል እንዳለ ተገለጸ።

መንግስት በዩቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም መሠረት "ዕጩ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች" ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን ነጥብ ከ10 እስከ 15 ቀናት ውስጥ ይፋ እንደሚያደርግ የትምህርት ሚኒስትር ድኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ተናግረዋል፡፡

"ዕጩ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች" ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ተደርጎ ራሳቸውን የሚያበቃቸውን ትምህርት ተከታትለው በሚቀጥለው ዓመት የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በመሆን ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ ሚኒስቴሩ እየሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።

"ዕጩ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች" በዕጩነት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን ነጥብ በጥቂት ቀናት ውስጥ ለማሳወቅ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ሌሎች በራሳቸው ከፍለው በግል ተቋማት የማጠናከሪያ ትምህርት ተከታትለው የሚሰጥ ፈተናን ካለፉ የመጀመሪያ ዓመት የሚሆኑበት ዕድል እንደሚፈጠርላቸውም ሚኒስትር ድኤታው ገልጸዋል፡፡

ለፈጣን መራጀ #shere & #join
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult2022
https://t.me/intrancresult2022
#Update

የዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ይፋ ተደርጓል።


በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በተከታዮቹ አማራጮች ማየት ትችላላች 👉

Website:  https://result.ethernet.edu.et

SMS: 9444

Telegram bot: @moestudentbot

ለፈጣን መረጃ #shere & #join
https://t.me/intrancresult2022
https://t.me/intrancresult2022
#Update

የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና  ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ ጊዜ ብቻ  የሚያገለግል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) እንዲተገበር መወሰኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው በ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን አነስተኛ የመግቢያ ውጤት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ።

1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣  180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ  በመንግስት ተቋማት(ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናል ተብሏል።

(የአቅም ማሻሻያ የመቁረጫ ነጥቡን ከላይ ይመልከቱ)

ትምህርት ሚኒስቴር

ፈጣን መረጃዎች እንዲደርስዎ ሼር ያድርጉ
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
#Update #UAE

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ሙሉ ስኮላርሺፕ መስጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መናገራቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው ከግማሽ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች ውስጥ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች እውቅና በሰጡበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተማሪዎቹ " እንኳን ደስ ያላችሁ " ካሉ በኋላ የተሰጣቸውን ፈተና በአግባቡ መስራት በመቻላቸው " ኢትዮጵያን የሚያግዙ 273 ተማሪዎች ተገኝተዋል በዚህም ደስታ ይሰማናል" ብለዋል፡፡

ተማሪዎቹ እጅግ ዘመናዊ በሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉና ለኢትዮጵያ እና አፍሪካ የሚደርሱ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተማሪዎቹ በርትተው ተምረው ሀገራቸውን ሳይረሱ የሚጠቅሙ እንዲሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ሁሉም ተማሪ ጥበብን እንዲሻ እና ሀገሩን ለመለወጥ እንዲሰራ ጠይቀዋል፤ በተለይ " ለእውነት የቆመ ተማሪ ነገ ሃገሩን ይለውጣል፤ እናንተ የላቀ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎችም እውነትን የምትሹ መሆን አለባችሁ እንደዛ ሲሆን ደግሞ ሀገርን የምትገነቡ ትሆናላችሁ " ብለዋል።

#ኤፍቢሲ

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
#Update

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተከስቶ የነበረዉ የፀጥታ ችግር ተቀርፎ ሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ስራ ተጀመረ

በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠውን የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና አንፈተንም በሚል  በዋናው ግቢ በዉስጥ ተከስቶ የነበረዉ የፀጥታ ችግር ተቀርፎ ሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ስራ መጀመሩ ተገልጿል።

ከዩኒቨሲቲውም ሆነ የሚመለከታቸዉ የፀጥታ ተቋማት  እውቅና ውጪ ባልተፈቀደ ሁኔታ ሰኔ  03 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተደረገውን ሙከራ ተከትሎ በዩኒቨርሲቲዉ ሆነ በሰዉ ላይ ሊደርስ የሚችል ጉዳት ለማስቀረት የፀጥታ ኃይሉ ህግ የማስከበር ተግባሩን ማከናወኑን ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን  በጥቂት የማህበራዊ ሚዲያዎች የፀጥታ ችግር እንዳለና መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ላይ መስተጓጎል እንዳለ በማስመሰል የሚሰራጩ መረጃዎች  ሀሰተኛና ተቀባይነት የሌላቸዉ ናቸው ተብሏል።በመሆኑም የተማሪ ወላጆችና መላው ህብረተሰብ  መረዳት ያለባቸው ከተፈጠረው አነስተኛ ግጭት ውጪ በተማሪዎች ላይ ምንም የደረሰ ጉዳት የሌለ መሆኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ሀላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
📥 📥 📥 📥 📥 📥 📥 📥
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
#Update

የሬሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰኔ 05/2015 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተፈርሞ የተላከ ደብዳቤ እንደሚያሳየው፤ የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የተቀበሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎችን ዝርዝር፣ ፈተናውን የሚወስዱበት ካምፓስ ማዕከልና የከተማ ሙሉ አድራሻ እንዲሁም በማዕከል የተዘጋጀውን ፈተና የሚረክብ የተቋም ኃላፊ ወይም ባለቤት መረጃ እስከ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም ድረስ ለትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን እና በትምህርት ሚኒስቴር ለአካዳሚክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ መላክ እንዳለባቸው ደብዳቤው ያመለክታል፡፡

(የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ከላይ ይመልከቱ፡፡)



            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
↘️ ↘️ ↘️ ↘️ ↘️ ↘️ ↘️ ↘️
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
#Update

የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመውሰድ ከ869 ሺህ በላይ ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

ለ2ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠውን አገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ 869 ሺህ 765 ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን በአገልግሎቱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወንደወሰን ኢየሱስወርቅ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

ከተመዘገቡት ውስጥ 503,812 ተማሪዎች የሶሻል ሳይንስ እና 365,954 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

የፈተና አስፈጻሚዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ምልመላ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30/2015 ዓ.ም በሁለት ዙር እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡


#shere & #join
👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
#ሪሜዲያል #UPDATE

ትምህርት ሚኒስቴር ትላንት ሰኞ ምሽት ከፕሬዚደንቶችና የተቋማት ሃላፊዎች ጋር ከተወያየ በኃላ የሬሜዲያል ፈተና አሰጣጥ በሚከተለው መልኩ እንዲከናወን ወስኗል።

📝 በ26/10/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕርግራም ፈተናዎች #ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ እንዲደረግ ተወስኗል።

📝 ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ #ካምፓስ ያላቸውን #የግል_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማት ፈተና ወደ ፊት ቀርቦ በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም እንዲሰጥ እንዲደረግ።

📝 በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች ፈተና መስጠቱን ወደ መስከረም ወር ማስተላለፉ በተማሪዎችና በተቋማት ላይ የሚያሳድረውን ጫና ከግምት በማስገባት የተዘጋጁትን ፈተናዎች በመለወጥ ፈተናዎች ኢንክሪፕትድ ሆነው ለዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ደርሰው እንዲባዙና ሁሉም ፈተናዎች በተመሳሳይ ጊዜ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ እንዲሰጡ እንዲደረግ።

📝 የፈተና ጥያቄዎች ለዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ከመድሳቸው በፊት ተማሪዎች #ከቀኑ_6 ሰዓት ላይ ተፈትሸው ወደ መፈተኛ አዳራሽ ገብተው ፈተናውን እንዲጠባበቁ በማድረግ እንዲፈፀም ውሳኔ ተላልፏል።

📝 ተቋማት ከትምህርት ሚኒስቴር በተላከላቸው ውሳኔ መሰረት ተማሪዎቻቸው #ከቀኑ_6 ሰዓት ተፈትሸው ወደመፈተኛ ክፍል ገብተው ፈተናውን እንዲጠባበቁ።

#shere & #join
👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
#Update የ8ኛ ክፍል ውጤት ( አዲስ አበባ ) ይፋ ሆኗል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በዛሬው እለት የ2015 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ማለፊያ ውጤትን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን በመግለጫቸውም በዘንድሮው ማለፊያ ውጤት 50% እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዘጠነኛ ክፍል እንደሚዘዋወሩ ጠቁመው የተለያየ የአካል ጉዳት  ላለባቸው ተማሪዎች  የማለፊያ ነጥቡ 45% መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘንድሮ 73,385 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደው 70.6% ያህሉ 50 ፐርሰንትና ከዛ በላይ በማምጣት ማለፋቸውን ዶክተር ዘላለም ገልጸው 61,840 ከሚሆኑ የቀን ተማሪዎች መካከል 50,812 የሚሆኑት ማለትም 82.16 % ያህሉ የማለፊያ ውጤቱን በማስመዝገብ ወደቀጣዩ የትምህርት እርከን መዘዋወራቸውን አስረድተዋል፡፡

የፈተናውን ውጤት በአስቸኳይ ይፋ ለማድረግ ቢሮው ባለሙያዎችን መድቦ ቀን ከሌት ሲሰራ መቆየቱን ኃላፊው በመግለጫችው በመጥቀስ በመጪው ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት ደግሞ የ6ኛ ክፍል ውጤት ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል፡፡ 

ተማሪዎች ውጤታችሁን ለማየት ሊንኩን በመጫን https://aa.ministry.et/#/result

Registration number ና first name በማስገባት መመልከት ትችላላችሁ።

⚠️ VPN ማጥፋት ይኖርባችኋል ⚠️

የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ ‼️

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
#Share  #share🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
#Update

12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የነበሩና ወደየመጡበት መመለስ ያልቻሉ መምህራንን በቻርተርድ አውሮፕላን ከክልሉ ለማስወጣት ፈቃድ እየተጠበቀ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

የመልቀቂያ ፈተና ለመስጠት በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የነበሩ መምህራን ወደየመጡበት መመለስ ባለመቻላቸው ችግር ላይ እንደሚገኙ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በጎንደር እና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸውን የተናገሩት መምህራኑ፤ የተሰጣቸውን አበል እንደጨረሱና የዕለት ምግብና መጠጥ ለማግኘት እንዳልቻሉም ገልጸዋል፡፡

የሚመለከታቸው አካላት ይታደጉን ሲሉ የተማፀኑት መምህራኑ፤ መንግሥት በአፋጣኝ ካሉበት የፀጥታ ስጋት አውጥቶ ወደየመጡበት እንዲመልሳቸውም ጠይቀዋል፡፡

መምህራኑን ካሉበት አውጥቶ ወደየመጡበት ለመመለስ እየሠራ እንደሚገኝ የትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡

መምህራኑ የደህንነት ችግር እነዳይደርስባቸው ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት መደረጉን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

"በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ላሉ መምህራን ህብረተሰቡ ምግብ እያቀረበ ነው" ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ መምህራኑ ከክልሉ በአፋጣኝ የሚወጡበት መንገድ እየተመቻቸ ነው ብለዋል፡፡

መምህራኑን በቅርብ ጊዜ ውስጥ በቻርተርድ አውሮፕላን ለማስወጣት የሚመለከተው አካል ፈቃድ እየተጠበቀ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ውጪ መመህራኑ ካሉበት ለመውጣት ሲሉ የደህንነት ዋስትና የሌለው አማራጭ እንዳይጠቀሙ ዋና ዳይሬክተሩ አሳስብዋል፡፡


➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
#Update

በፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተናቸውን ያላጠናቀቁ ተማሪዎች ፈተናቸውን መውሰድ ጀምረዋል።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናቸውን ያላጠናቀቁ 11,581 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ዛሬ ማስፈተን መጀመሩን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አሳውል።

ተማሪዎቹ ጠዋት የኬሚስትሪ ትምህርት ፈተና የወሰዱ ሲሆን ከሰዓት ደግሞ የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና እየወሰዱ እንደሚገኙ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ካሳሁን ተገኘ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

➢➢➢
#Share  #join 🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
#Update

"አምስት ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸው ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ አሳልፈዋል፡፡"

"ሌሎች አምስት ትምህርት ቤቶች ድግሞ ካስፈተኗቸው ውስጥ 95 ከመቶ ተማሪዎቻቸውን አሳልፈዋል፡፡"

ከፍተኛ አፈጻጻም ያሳዩ አስር ትምህርት ቤቶች (በደረጃ)፦

1. አዲስ አለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት
2. ደሴ አዳሪ ትምህርት ቤት
3. ባህርዳር ስቴም ትምህርት ት
4. ሀይራንዚ አዳሪ ትምህርት ቤት (ስልጤ ዞን)
5. ልጅ ጎጎ አዳሪ ትምህርት ቤት (ሀድያ)
6. ኦዳ አዳሪ ትምህርት ቤት (አዳማ)
7. ኮተቤ ሼርድ ካምፓስ
8. የኔታ አካዳሚ
9. ወላይታሊቃ አዳሪ ትምህርት ቤት
10. ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት

ላልሰሙ JOIN እና ሼር ያድርጉ! 👇👇

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!👇👇👇

https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
@TheRsultBot
#Update

በትግራይ ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ተጠናቀቀ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል አገራዊ ፈተና በተረጋጋ እና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ተጠናቋል ሲል አሳውቋል።

በተመሳሳይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮው ፈተናው በተረጋጋ ሁኔታ መጠናቀቁ አሳውቋን።

የቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ ፤ዥ አገር አቀፍ ፈተናው በተያዘለት ዕቅድ እንዲጠናቀቅ ያደረጋችሁ ከፌደራል እስከ ትምህርት ቤቶች እና ዩንቨርሲቲዎች ያላችሁ ተቋሞች፣ የትምህርት ኣመራሮች እና መምህራን፤ ከፌደራል እስከ ወረዳ ያላችሁ የፀጥታ እና ደህንንት ተቋሞች እና ኣመራሮች፤ ከተለያዩ ኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲዎች የተውጣጣችሁ ፈታኞች የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን "  ብለዋል።

ሃላፊው " ፈተናው በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ  ተፈታኝ  ተማሪዎቻችን ከናንተ የሚጠበቀው ሁሉ ስለደረጋችሁ ለናንተም የላቀ ምስጋና ይገባቹሃል " ሲሉ አክለዋል። 

ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ/ም  ለአራት ተከታታይ ቀናት በትግራይ ክልል ሲሰጥ የቆየውን የ12 ክፍል አገራዊ ፈተና ከ9,000 በላይ ተማሪዎች መፈተናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያሳያል።

ብሔራዊ ፈተናው የተሰጠው በመቐላ፣ አዲግራት፣ አክሱምና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ነው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና ውጤቱን ባጠረ ጊዜ ለማሳወቅ እንደሚሰራ ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መስከረም 28 /2016 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የትግራይ ተፈታኞቹን ውጤት በአንድ ሳምንት ውስጥ ለማሳወቅ ይሰራል።

የሚያልፉ ተማሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ውጤታቸው ከተገለጸ ተማሪዎች ጋር አብረው ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግ መግለፃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#Update

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 66.96 በመቶዎቹ 50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸው ተገለፀ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ በማኅበራዊ ገፁ ባወጣው መልዕክት እንደገፀው ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች 73.09% በተፈጥሮ ሳይንስ እና 51.38% በማኅበራዊ ሳይንስ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ማግኘታቸውን አሳውቋል።

በክልሉ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን በድረ-ገጽ eaes.et ወይም በቴሌግራም ቦት @eaesbot ላይ መመልከት ይችላሉ ተብሏል።

ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች በአገልግሎቱ ድረ-ገጽ ላይ እንዲሁም በትግራይ ትምህርት ቢሮ በአካል በመቅረብ እስከ ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም ድረስ ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑ ተመላክቷል።

በተያያዘ በክልሉ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 657 ከፍተኛው ውጤት ሆኖ መመዝገቡ ታውቋል።

ሙሴ ኪዳነ የተባለ የቀላሚኖ ትምህርት ቤት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ከፍተኛውን ውጤት ያመጣው ተማሪ መሆኑን ለመመልከት ችለናል።



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
Shere 👇🙏🙏🙏
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
Forwarded from ዩኒቨርስት info
#Update

ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና የወሰዱ #የግል እና #የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ውጤት ይፋ አድርጓል፡፡

በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ ውጤታቸውን ሲመለከቱ ቆይተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ የግል እና የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ጀምሮ መመልከት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ከደቂቃዎች በፊት አሳውቋል፡፡

ውጤት ለማየት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ 👉

https://result.ethernet.edu.et



ለፈጣን መረጃ 👇👇👇
https://t.me/unv_info
#Update

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ ማድረጋቸውን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በቅርቡ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው የአገሪቱ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ መጠናቀቁም ተገልጿል።

የፈተናው ሕትመት በቀጣይ ቀናት እንደሚጀመር ለኢሳት የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥም አረጋግጠዋል፡፡

ለ3ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ! 👇 👇 👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
T.me/unv_info
#Update

የመውጫ ፈተና ከ ሰኔ 14-25

ትምህርት ሚኒስቴር ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ፤ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎችን መረጃ በማሰባሰብ በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በኩል አረጋግጠው ባሳለፍነው ሳምንት ለትምህርት ሚኒስቴር መላካቸውን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
#shere & #join
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/unv_info
https://t.me/unv_info
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ይፋ አድርጓል።

በንቅናቄው ተፈታኝ ተማሪዎችን ለፈተና ለማዘጋጀት ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት መርሐግብር በትምህርት ቤቶች ይሰጣል።

በማጠናከሪያ ትምህርቱ የተማሪዎችን የመማር ብቃትና የሥነ-ልቦና ዝግጅት ለማሳደግ እንደሚሠራ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገልፀዋል።

ይህን ሥራ አንዳንድ ክልሎች ቀደም ብለው መጀመራቸው የሚያበረታታ ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል።

ንቅናቄው ውጤታማ እንዲሆን የክልል ትምህርት ቢሮዎች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በጎ ፈቃደኞች፣ የተቋማት ባለሙያዎች፣ ወዘተ በማሳተፉ እንዲሠሩ ጥሪ አድርገዋል።
#ኢትዮጵያ
#join
#ኢትዮጵያዊ
#shere
#MoE
#ተከፍሏቸው
#update
ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
👇 👇 👇🙏🙏🙏☘️☘️
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
#Update

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኦንላይን ተፈታኞች መፈተኛ ይፋ ሆኗል፡፡


የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እና በበይነ መረብ የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚህም በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ብቻ ፈተናውን እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

ስለሆነም ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ሁሉም ተፈታኞች በቂ ልምምድ ማድርግ አስፈላጊ

በመሆኑም ከዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 10/2016 ዓ.ም ጀምሮ የበይነ መረብ ተፈታኞች ባሉበት ሆነው ልምምድ ማድረግ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ተፈታኞች ልምምድ ለማድረግ ከዚህ በፊት ለክልል/ከተማ አስተዳደር የተላከውን የይለፍ ቃል እና ስም (User Name and Password) ከየትምህርት ቤቶቻቸው ማግኘት ይችላሉ፡፡

በዚሁ መሠረት መጀመሪያ ወደ መፈተኛ ሲሰተሙ እንደገቡ የማይረሱትን የግላቸውን የይለፍ ቃል የሚቀይሩ ይሆናል፡፡

ተፈታኞች ከተደለደሉበት ክለስተር ውጪ ሲሰትሙን መጠቀም #እንደማይችሉ አገልግሎቱ አሳስቧል።

(ፈተናው የሚሰጥበት አድራሻ እና ተፈታኞቹ የሚገኙበት ክልል/ከተማ አስተዳደር ከላይ ተያይዟል።)


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግ
ኘት
ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
👇 👇 👇🙏🙏🙏☘️☘️
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor