Intrance result.neaea.gov.et
1.35K subscribers
545 photos
29 videos
301 files
551 links
መረጃዎች ምንጫቸውን ሳንጠቅስ አናጋራም!

ወቅታዊ ፈጣንና ታማኝነት ያላቸውን ት/ተዊ ቴክኖሎጂ፤ ፋሽንን ጨምሮ የመዝናኛ መረጃዎችን በአንድ ቦታ ለማግኘት፤ ዛሬውኑ በመቀላቀል ራሶን ከዘመኑ ጋር ያዘምኑ፤ የአዋቂ ማህበረሰብ አካል ይሁኑ።

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@intrancresult
ሀሳብ @TheRsultBot
Download Telegram
የ 12ኛ ክፍል ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ‼️

በ 2015 የ 12ኛ ክፍል ፈተና በ ሁለት ዙር ከ ሐምሌ 19-30 መሰጠቱ ይታወሳል ። በዚህም መሰረት የተማሪዎችን ውጤት ቶሎ ለማሳወቅ ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

የፈተናው እርማት በቶሎ ለመጨረስ እና የተማሪዎችን ውጤ ይፋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

መቼ ይገለጻል ??

የፈተናው ውጤት ከመስከረም መጀመሪያዎቹ አከባቢ ልገለፅ ይችላል ተብሏል። በ 2016 የትምህርት ከለንደሩን ለማስተካከል እየተሰራ ነው። ስለዚህ በመስከረም ወር ተማሪዎች ውጤታቸውን አውቆ ማለፊያ ያመጡ ተማሪዎች ወደ ተቋም እንድገቡ ይደረጋል ተብሏል።


የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ



➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
#Share  #join 🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
የ Remedial ተማሪዎች ፈተና ተራዝሟል‼️

የግል ከፈተኛ ተቋማት ላይ ሬሜዲያል ፕሮግራም ስከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ከነሐሴ 23-26 አጠቃላይ ፈተና ይሰጣል ተብሎ ነበር።

ነገር ግን አሁንም ባልታወቀ ምክንያት መራዘሙን ዩኒቲ ዩንቨርስቲ አሳውቋል ።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
#Share  #join 🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
#MoE

የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን ከአሁን በኋላ በካድሬነት ሳይሆን በብቃታቸው ብቻ እንደሚመረጡ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን ያለው ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 30ኛውን ዓለም አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ምን አሉ ?

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" የትምህርት ቤቶች አስተዳዳሪዎች ከአሁን በኋላ የሚመረጡት በካድሬነት ሳይሆን፣ ባላቸው ብቃትና ችሎታቸው ላይ መሠረት ተደርጎ ይሆናል።

በዚህ መሠረት በአገር አቀፍ ደረጃ በብቃታቸውና በችሎታቸው የተመዘኑ 1,600 የትምህርት አስተዳዳሪዎች ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል። ይህ ዓይነቱ አሠራር ቀጣይነት ይኖረዋል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሳደግ ሥራ በተጨማሪ የመምህራንና ርዕሳነ መምህራን ብቃትና ችሎታ ማጎልበት ትኩረት ተሰጥቶበታል፡፡

ትኩረት ካገኙ መሠረታዊ ጉዳዮች ትምህርት ቤቶችን በግብዓትና በጥራት ከማሻሻል ባሻገር ክህሎት፣ ብቃትና ችሎታ ባላቸው ርዕሳነ መምህራን እንዲተዳደሩ ማድረግ ትልቁን ድርሻ ይይዛል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል በተጨማሪ በዕውቀት ተማሪዎቻቸውን ተወዳዳሪ ማድረግ የሚችሉ መምህራንን ማብቃት ከተያዙ ግቦች መካከል አንዱ ነው።

ባለፉት 30 ዓመታት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ጥራት ወርዷል ፤ በኑሮ ለተሻሉ ደግሞ የግል ትምህርት ቤቶች የሚማሩበት ሥርዓት ተዘርግቷል።

ይህ ዓይነት አካሄድ በዜጎች መካከል በኑሮ ደረጃ ከተፈጠሩ ልዩነቶች አልፎ በትምህርት ዘርፍ ላይ መታየቱ ትልቅ ክስረት ነው። ይህ አካሄድ በአገር አቀፍ ደረጃ አደገኛ ሁኔታዎች የሚፈጥር ነው ፤ በየትኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በገንዘብ ዕጦት ሳቢያ የትምህርት ጥራት ሊጓደልባቸው አይገባም።

ትምህርት የአገር የሉዓላዊነት እሴት መለኪያ ነው ፤ በዚህ ጉዳይ ለዓመታት የተቀለደበት ዘርፍ ነው አሁን እርስ በርስ መነጋገር የማይቻልበት ሁኔታ ላይ መደረሱ የችግሩ ማሳያ ነው።

የትምህርት ዘርፍ መሠረታዊ መርሆዎች ሁለት ናቸው ፤ ዜጎች በብሔራቸውና በሃይማኖታቸው ሳይታዩ እኩል ጥራት ያለው ትምህርት የማግኘት መብታቸውን ማረጋገጥ አንደኛው ነው።

የትኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች ከሁሉም እኩል ተወዳዳሪና ተፎካካሪ የሚሆኑበትን የትምህርት ሥርዓት በመዘርጋት፣ አሁን ያለውን የኢፍትሐዊነት ችግር በዘላቂነት መፍታት ይቻላል።

በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉ ከአሥር ዓመታት በኋላ ትምህርት ቤቶች እንደ አሁኑ የፀብ (የረብሻ) መፍለቂያ ሳይሆኑ የመወዳደሪያና የብቃት ማጎልበቻ ይሆናሉ፡፡

ከዚህ በኋላ እንደ ከዚህ ቀደሙ ዲግሪ እንደ ከረሜላ የሚታደልበትን አሠራር አስቀርቶ፣ በብቃት እና በችሎታ ብቻ ዜጎች ማዕረግ የሚያገኙበት ሥርዓት በዘላቂነት ይዘረጋል። "

Via Reporter Newspaper

የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
#Share  #join 🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
የ 12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ከሁለተኛው ዙር ፈተና በፊት አይገልጽም !

በመጀመሪያው ዙር ፈተና ከሐምሌ 19-28 የተሰጠ ሲሆን ውጤቱ ከሁለተኛው ዙር ፈተና ጋር ተጠቃሎ ሚገለጽ ይሆናል

የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤታችሁን በትዕግስት እንድትጠብቁ እያሳሰብን ውጤት ሲለቀቅ በዚሁ ቻነል የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
#Share  #join 🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
በጸጥታ ችግር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያቋረጡ ተማሪዎችን ለመፈተን ዝግጁት መጨረሱን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር: ነሐሴ 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ባገጠመው የጸጥታ ችግር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያቋረጡ ተማሪዎችን ለመፈተን ዝግጅት መጨረሱን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ ከሐምሌ 19 እስከ 30/2015 ዓ.ም ድረስ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት በአማራ ክልል በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናቸውን ሳይጨርሱ ከዩኒቨርሲቲ ወጥተዋል፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነትና የጽሕፈት ቤት ኀላፊ ጌታቸው ቢያዝን የሀገር አቀፍ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት በተፈጠረው የጸጥታ ችግር በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች የመጨረሻ ፈተናዎችን ሳይወስዱ መቅረታቸውን ተናግረዋል፡፡ በሰላም እጦት ምክንያት ፈተናቸውን ያልወሰዱ ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲፈተኑ እየተሠራ መኾኑን ነው ያመላከቱት፡፡ የሰላም ኹኔታው ባለበት መሻሻል ከቀጠለ በመስከረም ሁለተኛው ሳምንት ገደማ ፈተናውን ለመስጠት ማቀዳቸውንም ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎች ከሰላም እጦቱ ድባብ ወጥተው አስፈላጊውን የሥነ ልቦና ዝግጅት አድርገው እንዲፈተኑ መምህራን፣ ወላጆች እና መላው የትምህርት ማኅበረሰብ ድጋፍ ማድረግ አለባቸውም ብለዋል፡፡ ተማሪዎችን ለማስፈተን ከትምህርት የሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገሩ መኾናቸውንም አመላክተዋል፡፡

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ማንጠግቦሽ አዳምጤ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሁልጊዜ በተሻለ መልኩ ስኬታማ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን በአማራ ክልል በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት በጎንደር ዪኒቨርሲቲ ሲፈተኑ የነበሩ ተማሪዎች ፈተናቸውን ሳይጨርሱ መውጣታቸውን ነው የገለጹት፡፡

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመጨረሻዎቹን ፈተናዎች ሳይፈተኑ መቋረጡንም አስታውቀዋል፡፡ ተቋማቸው ፈተናዎችን በማዘጋጀት ፈተናውን ያልጨረሱ ተማሪዎች ፈተና እንዲወስዱ ዝግጅት መጨረሱንም ተናግረዋል፡፡ ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል አስተማማኝ ደኅንነት እንደሚያስፈልጋቸውም ገልጸዋል፡፡

አስተማማኝ ደኅንነት እና መረጋጋት እንዲኖር የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ጥረትና ርብርብ እንደሚፈልግም ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎች ፈተናቸውን እንዲወስዱ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት መሥራት እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎችም ፈተናቸውን ለመውሰድ ዝግጁ መኾን እንደሚጠበቅባቸውም ገልጸዋል፡፡ በክልሉ አስተማማኝ ሰላም በተፈጠረበት ጊዜ ሁሉ መስጠት እንደሚችሉም ተናግረዋል፡፡

Share share

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
#Share  #join 🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
የ 2016 የ 12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ  ፈተና በምን መልኩ ይሰጣል


ትምሀርት  ሚንስትር  ሶስት አማራጮችን አስቀምጦ  ውሳን ላይ እዳልተደረስ ገለጹ

1,ከ 9-11 በቀድሞ ስርአት ትምህርት  የተማሩትና በ2016 የሚማሩት በአንድ ላይ ለመፈተን የተያዘ እቅድ

2,12ኛ ክፍሎች ብቻ በ 2016 በቀድሞ የትምህርት  ስርአት   ተምረው ከ9-12 እዲፈተኑ

3,በአዲሱ የትምህርት  ስርአት የ 12 ኛ ክፍል ትምህርት  ብቻውን ፈተና ለመስጠት  የተያዘ እቅድ ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
#Share  #join 🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተማሪዎች ተጠቀሙበት 👌


ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
#Share  #join 🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
" የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን ይሰጣል (ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ) " - የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን #በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በ #ኦንላይን እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ይህን ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው።

ሚኒስትሩ ፤ በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚሆን አሳውቀዋል።

ለዚህም ተግባራዊነት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ፤ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመው የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን እንደሚሰጥም ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከአዲሱ የትምህርት ስርዓት ጋር በተያያዘ በመጽሐፍት ሕትመትና ስርጭት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ ነው በዋል።

በመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የመጽሐፍት እጥረት ማጋጠሙን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ፤ ችግሩ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ እንዳያጋጥም ቀደም ብሎ ጨረታ በማውጣት መጽሐፍትን በወቅቱ ለማድረስ እየተሠራ ነው ብለዋል።

መጽሐፍት እስከ መስከረም ወር መጨረሻ ድረስ እንደሚቀርቡ የትምህርት ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡


ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
#Share  #join 🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
#MoE

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም አጋማሽ ድረስ ይፋ ይደረጋል።

የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም 2016 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ ይፋ እንደሚደረግ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።

በጥቅምት 2016 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመጀመር ዕቅድ መያዙንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በፀጥታ ችግር ምክንያት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሦስት ፈተናዎች ያልወሰዱ ተማሪዎች በቅርቡ ፈተናቸውን ይወስዳሉም ብለዋል።

በ2015 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን ሲወስዱ የነበሩት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች፣ የመጨረሻዎቹን ሦስት ፈተናዎች አለመፈተናቸው ይታወቃል።

እነዚህ ተማሪዎች በዚህ ዓመት መጨረሻ ድረስ ፈተናቸውን እንዲያሚያጠናቅቁ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በኦንላይን እንደሚሰጥም ጠቁመዋል።



ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
#Share  #join 🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
የ12ኛ ክፍል ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናው መቼ ይሰጣል?

ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለጹ ይታወቃል።

ተማሪዎቹ ፈተናውን እንዲወስዱ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ተናግረዋል።

ለዚህም የፈተና ህትመት፣ የሰው ኃይል እና የበጀት ዝግጅት እየደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ተማሪዎቹ በስነ-ልቦና ለፈተና ዝግጁ ሲሆኑ እንዲሁም ፈተናው በሚሰጥባቸው አካባቢዎች አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ መኖሩ ሲረጋገጥ "በአጭር ጊዜ ውስጥ" ፈተናው እንዲሰጥ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁመዋል።

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለፈተና ተቀምጠው የመጨረሻ ቀናት ሦስት ፈተናዎችን ያልወሰዱ ተማሪዎች በዚህ ዓመት መጨረሻ ፈተናቸውን እንዲያሚያጠናቅቁ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) መናገራቸው ይታወሳል፡፡


ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
#Share  #join 🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ይሰጣል።

በፀጥታና በሌሎች ምክንያቶች ፈተና ላልወሰዱ ከ18 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በጎንደር፣ በጋምቤላ፣ በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች 17,753 ተማሪዎች እንዲሁም 300 በውጭ ሀገራት ለሚገኙ ተማሪዎች ፈተናው እንደሚሰጥ የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ለኢዜአ ተናግረዋል።

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሦስት መፈተኛ ጣቢያዎች ሲፈተኑ ከነበሩ ተማሪዎች መካከል ከ16 ሺህ በላይ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሁለት እስከ ሦስት የትምህርት ዓይነቶች ሳይፈተኑ መቅረታቸውን አስታውሰዋል።

በጋምቤላ ደግሞ ከ100 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን በከፊል እና ሙሉ ለሙሉ አልወሰዱም ብለዋል።

በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ 982 ተማሪዎችን ጨምሮ በድምሩ ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናው ይሰጣል ብለዋል።

በውጭ ሀገራት በኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርት የሚማሩ 300 ተማሪዎች ከዛሬ ነሐሴ 28/2015 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 02/2015 ዓ.ም ፈተናው ይሰጣል።

ለዚህም የፈተና ጣቢያ አስተባባሪዎች ከኢትዮጵያ ፈተናው ወደሚሰጥባቸው ሀገራት መጓዛቸውን ም/ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። #ENA

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
#Share  #join 🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
በፀጥታ ችግር ፈተና ያልወሰዱ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ከመስከረም 8 ቀን ጀምሮ ይፈተናሉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፀጥታ ችግርና በሌሎች ምክንያቶች ፈተና ያልወሰዱ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ለመፈተን መዘጋጀቱን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት (12ኛ ክፍል) ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በሁለት ዙር መሰጠቱን አገልግሎቱ አስታውሷል፡፡

ይሁንና በጎንደርና በጋምቤላ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ሙሉ በሙሉ እና በከፊል 14 ሺህ 891 ተማሪዎች እንዲሁም በሕህ ግ ጥላ ስር በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ 419 ተፈታኛ ተማሪዎች ፈተናውን ሳይወስዱ መቅረታቸው ተጠቅሷል፡፡

እነዚህን ተፈታኞች ከመጪው መስከረም 8 እስከ መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ውጤታቸውም ከመጀመሪያው ዙር ጋር እንደሚገለጽም የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
#Share  #join 🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተማሪዎች ተጠቀሙበት 👌 👌 👌 👌
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️👆👆

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
#Share  #join 🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት መቼ ይገለጻል?

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤትን ቶሎ ለማድረስ በሙሉ አቅም እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል፡፡

ፈተናውን የማረም ሥራ በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ ማንጠግቦሽ አዳምጤ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

ከመስከረም 07 እስከ 11/2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን ጨምሮ ውጤት ለመግለፅ መታሰቡን ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡

"ምናልባትም እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ውጤቱ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል" ተናግረዋል፡፡

በነሐሴ መጨረሻ በሰጡት መግለጫ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር) የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም አጋማሽ ድረስ ይፋ ይደረጋል ብለው እንደነበር አይዘነጋም።

በትግራይ ክልል በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ለነበሩ ተማሪዎች ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ.ም የመልቀቂያ ፈተናው ይሰጣል መባሉ ይታወቃል።

➢➢➢
#Share  #join 🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
#Update

በፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተናቸውን ያላጠናቀቁ ተማሪዎች ፈተናቸውን መውሰድ ጀምረዋል።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናቸውን ያላጠናቀቁ 11,581 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ዛሬ ማስፈተን መጀመሩን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አሳውል።

ተማሪዎቹ ጠዋት የኬሚስትሪ ትምህርት ፈተና የወሰዱ ሲሆን ከሰዓት ደግሞ የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና እየወሰዱ እንደሚገኙ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ካሳሁን ተገኘ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

➢➢➢
#Share  #join 🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎉🎉🎉 #share #share
ይሄ channel ከ ቀን ወደ ቀን member እየዳጋ 1k ደርሰናል🎉🎉🎉 ::እንኳን ደስ አላችሁ 🌹🌹🌹🌹 እርስዎም ቢያንስ ለ 10 ሰው share  ያድርጉልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን:: እኛም ደከመን ሰለቸን ሳንል እርሶን ለማገልገል ዝግጁ ነን በቀጣይም ብዙ ነገሮችን ለማሻሻል ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረግን እንገኛለን::ስለ ትብብርዎ እናመሰግናለን🙏🙏
Share #share 🙏

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ይቀላቀሉ ፤
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
🔰ትንሽ ጠብቁን🙏

"School Code " System ማስገባት አስቸጋሪ ስለነበር ለመቀነር ስባል ነው የዘገየው ።

Registration number እና የመጀመሪያ ስም ብቻ ተጠቀሙ።

1. eaes.edu.et 👉(Reg.no & First name )
2. eaes.et 👉 (Reg.no & First name )
3. eaes.gov.et 👉 (Reg.no & First Name )

SMS :6284

Bot :@EAESbot

በተባለው ሰዓት ባለመለቀቁ ይቅርታ እንጠይቃለን።

ለተማሪዎች ሼር አድርጉ🙏
#Share #share 🙏

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ይቀላቀሉ
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
በ12ኛ ክፍል ውጤት “ራቁታችንን ምን እንደምንመስል አይተነዋል” - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ የመስሪያ ቤታቸውን የዘንድሮ እቅድ እና የበጀት ዓመቱን የሩብ ዓመት አፈጻጸም ለማቅረብ ዛሬ ረቡዕ በፓርላማ ተገኝተው ነበር። የዛሬውን ስብሰባ በጠራው የተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለሚኒስትሩ ካቀረባቸው ጥያቄዎች መካከል የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን የሚመለከተው ይገኝበታል።

የቋሚ ኮሚቴውን ጥያቄዎች በንባብ ያሰሙት የፓርላማ አባል “በተከታታይ ለሁለት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት በጣም ዝቅተኛ የሆነበት ምክንያት ምንድነው? ትምህርት ሚኒስቴር የፈተናውን ውጤት እንዴት ያየዋል?” ሲሉ ጠይቀዋል። ፕ/ር ብርሃኑ ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ “የ12ኛ ክፍል ውጤት እንደዚህ መሆን፤ ምንምን እንኳ really መጠበቅ የነበረን ነገር ቢሆንም ሁላችንንም አስገርሞናል” ብለዋል።

“የፈተናውን አሰጣጥ መቀየር ብቻ ይሄን ካሳየ፤ ከዚህ ተነስተን ብቸኛ ነገር ልንል የምንችለው፤ ከዚያ በፊት ስንሰጣቸው የነበሩ ፈተናዎች በሙሉ የተማሪን እውነተኛ ችሎታ የሚያሳዩ አይደሉም ማለት ነው” ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ይሰጡ በነበሩ ሀገር አቀፍ ፈተናዎች በትምህርት ቤቶች እና በክልል ደረጃ ሳይቀር በተደራጀ መልኩ “ፈተናዎች የሚሰረቁበት” እንደነበር የጠቀሱት ፕ/ር ብርሃኑ፤ በዚያን ጊዜ የነበሩ ውጤቶች የተማሪዎችን ችሎታ የሚያንጸባርቁ እንዳልነበር አስረድተዋል።

“አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ refelect አድርጎልናል። አሁን የምንደበቅበት ቦታ የለም። ሰርቀን የምናሳይበት ቦታ የለም። ራቁታችንን ምን እንደምንመስል አይተነዋል” ሲሉም የትምህርት ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ለተማሪዎች ሼር አድርጉ🙏
#Share #share 🙏

shere Shere 👇🙏🙏🙏
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor