ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
7.08K subscribers
1.29K photos
8 videos
37 files
262 links
የዲ.ን ዮርዳኖስ አበበ ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
በዚያ ወራትም የግብጽ ንጉሥ አብዶ አልዓዚዝ ወደ እስክንድርያ ከተማ መጣ ይህ አባት ሊቀ ጳጳሳት ስምዖንም ሊቀበለው ወጣ ንጉሡም በሊቀ ጳጳሳቱ ፊት ላይ የደዌ ምልክት አይቶ መሳፍንቶቹን መልኩ እንዲህ እስኪለወጥ ድረስ ሊቀ ጳጳሳቱ ምን ደረሰበት ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም ክፉዎች ካህናት በእርሱ ላይ እንዳደረጉበት መርዝንም እንዳበሉት ነገሩት ንጉሡም ተቆጣ ካህናቱንና መሠርያኑንም በእሳት እንዲአቃጥሏቸው አዘዘ ያን ጊዜም ይህ አባት ከንጉሡ እግር በታች ወድቆ ይምራቸው ዘንድ እያለቀሰ ለመነው ንጉሡም አይደለም እንደሚገባቸው ያቃጥሏቸው እንጂ አለው። ይህም አባት ስለእኔ አንተ ከአቃጠልካቸው ለእኔ ክህነትና ሊቀ ጵጵስና አይገባኝም አለው። ንጉሡም ሰምቶ ከየዋህነቱና ከርኅራኄው የተነሣ አደነቀ እነዚያን ካህናትና መሠርዮች ከእስክንድርያ እንዲያሳድዷቸው አዘዘ።

ንጉሡም ይህን አባት እጅግ ወደደው አከበረውም እንደወደደም አብያተ ክርስቲያናትን ገዳማትን ይሠራ ዘንድ ፈቀደለት። እርሱም በምስር ሰሜን አልዋህ በሚባል አገር አብያተ ክርስቲያን ሠራ በሹመቱም ዘመን ሌሎች ብዙዎችን ሠራ።

ካደረጋቸው ተአምራቶቹ ሌላው ይህ ነው ሚናስ የሚባል አንድ ቄስ ነበረ ሙቶ ከተገነዘ በኋላ በዚህ አባት ጸሎት ተነሣ። የመነሣቱ ምክንያትም እንዲህ ነበር ይህ አባት ስምዖን በመላው አብያተ ክርስቲያናት ንብረት ንዋየ ቅድሳትና አልባሳት ላይ መጋቢ አድርጎ ይጠብቅ ዘንድ ቄሱን ሾመው። ሁልጊዜም የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ በቤትህ ውስጥ አታኑር እያለ ያዝዘው ነበር።

ከዚህም በኋላ ድንገተኛ ደዌ አገኘውና አንደበቱና ጒረሮው ተጣጋ። ሊቀ ጳጳሳቱም ሰምቶ እጅግ አዘነ ስለ አቢያተ ክርስቲያናትም ንብረት ያንን ቄስ ከሞት ያድነው ዘንድ በዚያች ሌሊት እግዚአብሔርን እየለመነ መላዋን ሌሊት ለጸሎት ተጋ።

መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ያ ቄስ ለመሞት እንደተቃረበ ይህ አባት ሰምዖን ሰማ ስለ አቢያተ ክርስቲያናት ነብረት ይጠይቃት ዘንድ አዝዞ ወደ ቄሱ ሚስት ረዳቱን ላከ።

ወደ ቄሱ ቤትም በቀረበ ጊዜ ሰዎች እያለቀሱለት ጩኸታቸውን ሰማ በገባ ጊዜም ሙቶ ልብሰ ተክህኖ መጐናጸፊያ ሲያለብሱት በዐልጋ ላይም ሲያስተኙት ብዙዎችም በዙሪያው ሲያለቅሱ አገኛቸው ያም ረዳቱ የቄሱን በድን ሊሳለም ዘንበል አለ። ያን ጊዜም ያ የሞተው ቄስ ተነሥቶ አቀፈውና የክቡር አባ ስምዖን ፈጣሪ እግዚአብሔር ሕያው ነው አለው። ረዳቱም በርታ አትፍራ አለው። ቄሱም በጌታው በአባ ስምዖን ጸሎት አዎ በእውነት ጸናሁ እግዚአብሔር ሕይወትን ሰጥቶ ከሞት አስነሥቶኛልና አለ።

ያን ጊዜም ያ ረዳት ስለ መሞቱ ደንግጠው የነበሩትን ካህናት እነሆ ቄሱ ከሞት ተነሥቷል ብሎ ጠራቸው። ካህናቱና ሕዝቡም ወደርሱ በቀረቡ ጊዜ ቄሱ እንዲህ አላቸው እኔ ሙቼ እንደነበረ ዕወቁ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ዙፋን ፊት አቆሙኝ ከአባት ሐዋርያ ማርቆስ እስከ አባ ይስሐቅ ያሉትን ሁሉንም የጳጳሳት አለቆች ክብር ይግባውና በክርስቶስ ዙፋን ፊት ቁመው አየኋቸው እኔንም ከወንድማችን ከሊቀ ጳጳሳት ስምዖን የአብያተ ክርስቲያናትን ንብረት ለምን ሸሸግህ ብለው ገሠጹኝ። ያን ጊዜም ጌታ ክርስቶስ ይቺን ነፍስ በውጭ ወዳለ ጨለማ ውሰዱአት ብሎ አዘዘ።

ሊወስዱኝም በጐተቱኝ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ዙፋን ፊት የጳጳሳት አለቆች ሰገዱ እንዲህ እያሉም ማለዱ ይህን ሰው አንድ ጊዜ ማረው ንብረታቸውን ስለሚጠብቅላቸው አብያተ ክርስቲያናት ብሎ ወንድማችን ስምዖን ስለ እርሱ እነሆ ቁሞ ይጸልያልና። ጌታችንም ልመናቸውን ተቀብሎ ነፍሴን ወደ ሥጋዬ መለሰ እንዲህም አለኝ እነሆ ስለ ምርጦቼና ስለ ወንድማቸው ስለ ሊቀ ጳጳሳት ስምዖን ማርኩህ አንተም የአብያተ ክርስቲያናትንም ንብረት ግለጥለት። አለዚያ ግን ወደዚህ እመልስሃለሁ የእነዚህንም ልመናቸውን ስለአንተ ሁለተኛ አልቀበልም።

በዚያ የነበሩም ሰዎች ይህን በሰሙ ጊዜ እጅግ አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ኀዘናቸውም ወደ ደስታ ተለወጠ ይህም ቄስ ይህን ተአምር ለሁሉ እየተናገረ ብዙ ዘመናት ኖረ።

ይህም አባት ስምዖን በበዐቱ ውስጥ በገድል የተጸመደ ሁኖ ኖረ መንጋዎቹንም ያስተምራቸው፣ ይገሥጻቸውና በቀናች ሃይማኖትም ያጸናቸው ነበር። ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ዘዮሐንስ_ጻድቅ_ዘክብራን_ገብርኤል (ኢትዮዽያዊ)

ዳግመኛም በዚህች ቀን ጣና ክብራን ገብርኤል ገዳምን የመሠረቱት አቡነ ዘዮሐንስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ይኸውም አባቱ ዘካርያስና እናቱ ሶፍያ #እግዚአብሔርን በማመን የተመሰገኑ ምግባር ሃይማኖታቸው የቀና ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ የሀገር ሰዎችም መክረው ዘካርያስን በእነርሱ ላይ ጌታና ገዥ አደረጉት፡፡ እርሱም በጥሩ አገዛዝ በፍቅር ገዛቸው፡፡ እነርሱም እንደ አሽከሮች ሆኑት፣ እርሱም እስከ አማራ ጠረፍ ድረስ ለሸዋ ሰዎች እንደ ቸር እረኛ ሆናቸው፡፡ ዘካርያስና ሚስቱ ሶፍያም በጎ ሥራን ሁሉ አላቋጡም፡፡ ምጽዋትን መስጠትን፣ ከገንዘባቸውም ከፍለው ለ #እግዚአብሔር አሥራት መስጠትን አላቋረጡም፡፡ የተቸገሩትን፣ የተራቡትንና የተጠሙትን ሁሉ ያበላሉ፣ ያጠጣሉ፡፡ ይህንንም ሲሄዱም ሲመለሱም ሁልጊዜ ያደርጋሉ፡፡

#ጌታችንን_የኢየሱስ_ክርስቶስንና የቅድስት #ድንግል_ማርያምን፣ የ #ጻድቃንና#ሰማዕታን መታሰቢያም ያድርጋሉ፡፡ ልጅም አልነበራቸውምና ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ይማፀኑ ነበር፡፡ ሶፍያም ጠዋት ማታ እንዲህ እያለች ትጸልይ ነበር፡- ‹መካን ለነበረች ለሐና ልጅ እንደሰጠኻት፣ ለአብርሃም ሚስት ለሣራም፣ ለጸጋ ዘአብ ሚስት እግዚእ ኀረያም እንደሰጠኻቸው አቤቱ እንደ እነርሱ አንተን ደስ የሚያሰኝህን ልጅ ስጠኝ› እያለች #እመቤታችንንም እየተማፀነች ታለቅስ ነበር፡፡ #እግዚአብሔርም መጥምቁ ዮሐንስን የመሰለ ልጅ ‹አባ ዘዮሐንስ› የተባለ ቅዱስ ልጅ ሰጣቸው፡፡ እሱም በሸዋ፣ በመራቤቴ እስከ አማራ ጠረፍ ድረስ የሚያበራ መብራት ሆነ፡፡››

በኋላም በጣና ሐይቅ ላይ የሚገኘውን ‹‹ክብራን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን›› የመሠረቱት እኚህ አባ ዘዮሐንስ የተባሉ ጻዲቅ ናቸው፡፡

ለአባ ዘዮሐንስ በጌታ ዘንድ ታዘው ነቢዩ ኤልያስና ዮሐንስ በእኩለ ሌሊት ተገልጠውላቸው አስኬማና ቆብ ሰጥተዋቸዋል፡፡ #እመቤታችንም ተገልጣላቸው ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደው እንዲመነኩሱ ነግራቸው ኤልያስና ዮሐንስ እየመሩ ከቦታው አድርሰዋቸዋል፡፡ ሰባት ዓመትም በዚያ ሲያገለግሉ ኖሩ፡፡ ስግደታቸውም ሁልጊዜ ስምንት ሺህ ነበር፡፡ ጌታም በደብሊባኖስ ሲያጥኑ ተገልጦላቸው ስምህ ‹‹ዘዮሐንስ ይሁን›› ብሎ ትልቅ ቃልኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ ደመናም ተሸክማ ወስዳ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም አድርሳቸው በዚያም ከቆዩ በኋላ ደመናዋ መልሳ ወደ ሸዋ አምጥታቸዋለች፡፡ በትግራይ ለራሳቸው መጠለያ ሲሠሩ የ #ጌታ ፈቃድ አልነበረምና ከባድ የሆድ ሕመም መጣባቸው፡፡ ደመናዋም ደራ ሮቢት አደረሰቻቸው፡፡ በዚያም እንደደረሱ ገብርኤልና መስቀል ክብራ በሚባሉ #እግዚአብሔርን በሚወዱ ደጋግ ባለትዳሮች ቤት ዕረፍት አደረጉ፤ ለሰባት ቀናትም በዚያ ቆዩ፡፡ ከዚያም መልአኩ ተገልጦ ወደ ደሴቷ እንዲሄዱና እርሷም ዕጣ ክፍላቸው እንደሆነች ነገራቸው፡፡
#መስከረም_6

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም ስድስት በዚች ቀን ታላቅ ነቢይ የአሞጽ ልጅ #ቅዱስ_ኢሳይያስ አረፈ፣ #የአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ዐፅማቸው ከዋልድባ አብረንታንት ወደ ደብረ ዓባይ የፈለሰበት ዕለት ነው፣ #ቅድስት_ሰብልትንያ በዲዮቀልጥያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ሞተች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ነቢዩ_ኢሳይያስ

መስከረም ስድስት በዚች ቀን ታላቅ ነቢይ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ አረፈ። ይህም ነቢይ ለይሁዳ በነገሡ በአምስቱ ነገሥታት ዘመን አስተማረ ትንቢትም ተናገረ እሊህም አዝያን ኢዮአታም አካዝ ሕዝቅያስና ምናሴ ናቸው።

በአካዝ ዘመንም እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ። እነሆ ስለዚህ #እግዚአብሔር ምልክትን ይሰጣችኋል። እነሆ ድንግል ፀንሳ ወንድ ልጅን ትወልዳለች ስሙንም #አማኑኤል ትለዋለች። ትርጓሜውም #እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ አንድ ሆነ ማለት ነው።

እርሱም በኃጢአታቸው ከሚመጣባቸው ፍዳ ወገኖቹን የሚያድናቸው ወደ ሃይማኖቱም የሚአስገባቸው እንደሆነ የእስራኤልንም ልጆች መሥዋዕታቸውንና ክህነታቸውን እንደሚሽር ከሐዲስ ወገኖችም የሚያመሰግኑት ካህናትን እንደሚሾም ተናገረ።

የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬምም ኢየሩሳሌምን ከቦ የስድብ ቃልን በክብር ባለቤት በ #እግዚአብሔር ላይ በተናገረ ጊዜ የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬምን ያጠፋው ዘንድ #እግዚአብሔር እንዳለው ለሕዝቅያስ ትንቢትን ተናገረ።

በዚያች ሌሊትም #እግዚአብሔር የላከው የመላእክት አለቃ #ቅዱስ_ሚካኤል ወደ ሠናክሬም ሰፈር መጥቶ ከፋርስ ሠራዊት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ አርበኞችን ገደለ። የለኪሶ ሰዎች ሲነጋ በተነሡ ጊዜ የሞቱትን ሰዎች ሬሳ ሁሉ አዩ።

ሕዝቅያስም ታሞ ለሞት በተቃረበ ጊዜ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደርሱ መጥቶ #እግዚአብሔር ትሞታለህ እንጂ አትድንም ብሏልና ቤትህን አዘጋጅ አለው። ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ ወደ #እግዚአብሔር ለመነ ፈጽሞ ጽኑ ልቅሶንም አለቀሰ።

ይህን ከነገረው በኋላ የ #እግዚአብሔር ቃል ወደ ነቢዩ ወደ ኢሳይያስ መጣ ሒደህ ለሕዝቅያስ የአባትህ የዳዊት ፈጣሪ #እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰማሁ ዕንባህንም አየሁ። እነሆ በዘመንህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት ጨመርኩልህ አለ በለው።

ዳግመኛም ስለ እስራኤል መማረክና ከምርኮ ስለ መመለሳቸው ትንቢት ተናገረ የፈሳሽ ውኃን ምንጭ በማፍሰስ በእጆቹ ላይ #እግዚአብሔር ምልክትን ገለጠ።

ክብር ይግባውና ስለ #መድኃኒታችን_ክርስቶስ መከራ ትንቢት ተናገረ እንዲህም አለ። እርሱም በመከራው ጊዜ ነገርን አልተናገረም እንደ በግ ይታረድ ዘንድ መጣ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንደ ማይናገር እንዲሁ በመከራው ጊዜ አልተናገረም።

ከዚህም በኋላ ደግሞ በሕዝቅያስ ልጅ በንጉሥ ምናሴ ላይ ትንቢት ተናገር ጣዖትን ስለማቆሙና ስለማምለኩ ገሠጸው። ስለዚህም ንጉሥ ምናሴ ተቆጥቶ በዕንጨት መሰንጠቂያ መጋዝ በራሱና በእግሮቹ መካከል ሠነጠቀው ምስክርነቱንም በዚህ ፈጸመ።

ትንቢት እየተናገረ የኖረበትም ዘመን ሰብዓ ዓመት ከዚያም በላይ ይሆናል። እርሱም ያስተማረው ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት በዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሦስት ዓመት ነው።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ነብይ ኢሳይያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ

ዳግመኛም በዚህች ቀን የዋልድባው የአቡነ ሳሙኤል ዐፅማቸው ከዋልድባ አብረንታንት ወደ ደብረ ዓባይ የፈለሰበት ዕለት ነው፡፡ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ትውልዳቸው ከካህናቱ ወገን አክሱም ነው አባታቸው እስጢፋኖስ እናታቸው አመተ ማርያም ይባላሉ። ለመምህር ሰጥተዋቸው ሲማሩ አድገው በኋላም ወላጆቻቸው በሞት ሲለዩአቸው ደብረ በንኰል ገዳም ገብተው ሥርዓተ ምንኩስናን ከአበው እያጠኑ ለትልቁም ለትንሹም በትሕትና እየታዘዙ ውሃ እየቀዱ እንጨት እየሰበሩ በትኅርምት በጽሞና በጸሎት ይኖሩ ነበር።

ሰይጣን በውዳሴ ከንቱ ጾር ቢመጣባቸው ከማሕበረ መነኮሳቱ ተለይተው በተባሕትዎ ለመኖር ሽተው ወጥተው ሲሔዱ ተከዜ ደረሱ። ወንዙ ሞልቶ የማያሻግራቸው ቢሆን ውሃውን በትምህርተ #መስቀል ባርከው በአንድ እጃቸው መጽሐፍ በአንድ እጃቸው መብራት እንደያዙ ገብተው መብራቱ ሳይጠፋ መጽሐፉ ሳይበላሽ ተሻግረዋል። ዋልድባ ሲደርሱ #ጌታ እዚህ ተቀመጥ ስላላቸው ገዳም መሥርተው ሥርዓተ ምንኩስናን እያስተማሩ ተቀመጡ። ዛሬ በዋልድባ የሚያመሰግኑበት #ውዳሴ_ማርያም #ቅዳሴ_ማርያምን ከተከዜ ወዲህ ያመጡ እሳቸው ናቸው። ይህንን እየጸለዩ ሲሔዱ ክንድ ከስንዝር መሬት ለቀው ይታዩ ነበር። አንድ ቀንም ይህንን ጸሎት ደግመው ውኃውን ቢባርኩት ኅብስተ ሕይወት ሆነላቸው ከነደቀ መዛሙርቶቻቸው ተመግበውታል።

#እመቤታችንም የፍቅር መግለጫ ዕጣን፣ ወርቅ፣ እንቁ ሰጥታቸዋለች። ውዳሴዬን ከቅዳሴዬ አንድ አድርጎ የደገመውን አንተ ከገባህበት መካነ ሕይወት አስገባዋለሁ ብላ ቃልኪዳን ሰጥታቸዋለች። ጊዜ እረፍታቸው ሲደርስ #ጌታን በስብሐተ መላእክት ተገልጦ በስምህ የተማጸነውን በጎ የሰራውን፣ ዜና ገድልህን የጻፈውን፣ ያስጻፈውን፣ ያነበበ፣ የተማረ፣ ያስተማረ፣ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ምሬልሃለሁ። በዚህ ቦታ በዋልድባ የሚሰበሰቡ ልጆችህን ከእዳ ከፍዳ እሰውርልሃለሁ አላቸው። እንኪያስ ቦታዋን ባርክልኝ ብለው እንደ መሶብ አንስተው አስባርከዋታል #ጌታችንም እህል አይብቀልብሽ ኃጢአት አይሻገርብሽ ብሎ ቃል ኪዳን ገባላት ለገዳመ ዋሊ። አባታችን አቡነ ሳሙኤል በበዓታቸው ውስጥ ጸንተው ሲኖሩ ታህሣሥ 12 ቀን ያረፉ ሲሆን ዛሬ መስከረም 6 ግን ፍልሰተ አጽማቸው የተከናወነበት እለት ነው።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ሰብልትንያ

በዚህችም ቀን ቅድስት ሰብልትንያ በከ*ሀዲ ንጉሥ ዲዮቀልጥያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ሞተች። ይችንም ቅድስት ዕድሜዋ ዘጠኝ ዓመት ሲሆን ከሀ*ድያን ያዙዋት እጆቿንና እግሮቿንም አሥረው ከሚነድ እሳት ውስጥ ጣሏት የክብር ንጉሥ በሆነ በ #እግዚአብሔርም ኃይል ከእሳት ዳነች።

ውኃን በተጠማች ጊዜ #እግዚአብሔርን ለምናው ውኃን አፈለቀላትና ጠጣች ክብር ምስጉን የሆነ #ጌታችንንም አመሰገነችው። ከዚህም በኋላ ነፍሷን በ #እግዚአብሔር እጅ አደራ ሰጥታ ራሷን ከእሳት ውስጥ ወረወረች ምስክርነቷንም ፈጸመች።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም_6 እና #ከገድላት_አንደበት)
#እመቤታችን ልጇን ይዛ ወደ ግብጽ ከዚያም ወደ አገራችን ኢትዮጵያ ስትሰደድ በእግሯ እየሄደች በሞረት ዋሻ በአቡነ ዜና ማርቆስ ቦታ ግራርያ ከሚባል ቦታ ተቀምጣ እንደነበር የሐምሌው ድርሳነ ቅዱስ ዑራኤል ይናገራል፡፡ በኋላም ተጭነው ከእነ ልጇ በዚህ በአቡነ ገብረ ማርያም ገዳም በሆነ ቦታ ስታልፍ #ጌታችን ለቅድስት እናቱ ‹‹ይህች ቦታ ሐንታ ትባላለች፣ በኋለኛው ዘመን በስምሽ የሚጠራ የእኔ ወዳጅና ታዛዥ የሆነ የታላቅ ጻድቅ ቦታ ትሆናለች›› ብሎ ስለነገራት በኋላም ትንቢቱ ደርሶ ጻድቁ ገዳማቸውን በዚሁ ቦታ ስለገደሙት ገዳሙ ‹‹አማን ደብረ ሐንታ›› ይባላል፡፡ ጻድቁ በመንዝና በመርሐ ቤቴ ከ1245-1268 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከ19 በላይ የተላያዩ አብያተ ክርስቲያናትን ተክለዋል፡፡ ጾም ጸሎተኛ ባሕታዊ ከመሆናቸው በተጨማሪ የወንጌል ገበሬ፣ ጻድቅና ደራሲም ናቸው፡፡

አቡነ ገብረ ማርያም በጣም ከሚታወቁበት ድርሰታቸው አንዱ የማኅሌተ ጽጌን ድርሰት ከታላቁ ሊቅ ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ድርሰቱን በመዝሙረ ዳዊት መጠን 150 አድገው ደርሰዋል፡፡ አቡነ ገብረ ማርያምና አቡነ ጽጌ ድንግል ማኅሌተ ጽጌን በጥምረት ሊደርሱት የቻሉት አቡነ ገብረ ማርያም በወሎ ክፍለ ሀገር በወረኢሉ አውራጃ ልዩ ስሙ ደብረ ሐንታ በሚባለው ገዳም የሕግ መምሕር ሆነው በተሾሙበት ወቅት ነው፡፡ እነዚህም ሁለት ቅዱሳን የዘመነ ጽጌ የማኅሌት አገልግሎትን ሳይለያዩ በሰላምና በፍቅር በአንድነት አግልግለዋል፡፡ ይኸውም የሆነው እንዲህ ነው፡- አንድ ዓመት አቡነ ገብረ ማርያም የክረምት መውጫና የዘመነ ጽጌ ዋዜማ በሆነው መስከረም 25 ቀን ከደብረ ሐንታ መጥቶ ደብረ ብሥራት አቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም ገብተው ከመስከረም 25 ቀን እስከ ኅዳር 5 ቀን ያለውን የዘመነ ጽጌ የ40 ቀን አገልግሎት ከአቡነ ጽጌ ድንግል ጋር ፈጽመው ኅዳር 8 ቀን ወደ ደብራቸው ደብረ ሐንታ ይመለሳሉ፡፡

በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ አቡነ ጽጌ ድንግል ከገዳማቸው ከደብረ ብሥራት ተነሥተው ወደ ደብረ ሐንታ ሄደው እንዲሁ እንደ አቡነ ገብረ ማርያም 40ውን ቀን አግልግሎ ይመለሳል፡፡ እነዚህ ሁለት ቅዱሳን እንደዚህ እያደረጉ በየተራ አንደኛው ወደ ሌላኛው ገዳም እየሄዱ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ በፍጹም ፍቅርና በትሕትና አብረው ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡

ይኸውም በራሳቸው በአቡነ ገብረ ማርያም ገድል ላይ እና በአቡነ ዜና ማርቆስ ገድል ገጽ 72-73 ላይ በሰፊው ተጠቅሶ ይገኛል፡፡ የሁለቱ ድርሰታቸው የሆነው ‹‹ማኅሌተ ጽጌ›› ድርሰት የ #እመቤታችንንና የልጇን የ #ጌታችንን ሥጋዊ ስደት የሚገልጽ ሲሆን በተጨማሪም ስደት የማይገባው #አምላካችን_ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ አህጉራችን አፍሪካ ተሰዶ የሠራቸውን ድንቅ ድንቅ ተአምራትና የ #እመቤታችንን ንጽሕናዋን ቅድስናዋን አማላጅነቷን የሚያስረዳ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡

አቡነ ገብረ ማርያም አዲስ አፍልሰው በሠሯት ቤተ ክርስያን ውስጥ ልጆቻቸው ተሰበሰቡና ‹‹አባታችን ሆይ የት እናድራለን? ማረፊያን ያዘጋጅልን ዘንድ #እግዚብሔርን ለምነው›› አሉት፡፡ አባታችንም ‹‹ይህ ሥራ ለእኔ አይቻለኝምና እናንተ ለምኑት›› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹አባታችን ሆይ አትበትነን›› ብለው ግድ አሉት፡፡ ልጆቹም ግድ ባሉት ጊዜ አባታችን ተነሥቶ ጸለየ፡፡ ስለዚህም ነገር ሲናገር አባታችን እንዲህ አለ፡- ‹‹ከዚህ ነገር አስቀድሞ በቁርባን ጊዜ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ይመጣና ይባርከኝ ነበር፣ እናቱ #ድንግል_ማርያምም ትባርከኝ ነበር፡፡ ስለዚህ ነገር ግን #ጌታችን ተቆጣ፣ እምቢ አለኝ፡፡ ከእኔም ፊቱን መለሰ፡፡ እኔም ብዙ አለቀስኹ የእጁን ቡራኬ አጥቻለሁና፡፡ እናቱ #ድንግል_ማርያምም ፈጽሜ ሳለቅስ ባየችኝ ጊዜ ‹ወዳጄ ገብረ ማርያም ሆይ ለምን ታለቅሳለህ?› አለችኝ፡፡ እኔም #እመቤቴ_ሆይ #ጌታዬና_አምላኬ ፊቱን ከእኔ መልሷልና ስለዚህ አለቅሳለሁ አልኳት፡፡ #እመቤታችን_ማርያምም የተወደደ ልጇን ‹ልጄ ሆይ ወዳጅህ ገብረ ማርያምን በምን ሥራ አሳዘነህ?› አለችው፡፡ #ጌታችንም#ድንግል እናቱ ‹እርሱ አሳዝኖኛል፣ የዮሴፍ ልጅ ያዕቆብ ‹ይህን ዓለም የሚወድ የ #እግዚአብሔር ጠላት ይሆናል› (ያዕ 4፡4) እንዳለ ከእኔ ፍቅር ይልቅ የዓለምን ፍቅር ወዷልና› አላት፡፡› እናቱ #እመቤታችንም የተወደደ ልጇን ‹ልጄ ሆይ ወዳጅህ ገብረ ማርያምን አታሳዝነው ይቅር በለው ባጠባሁህ ጡቶቼ አምልሃለሁ› አለችው፡፡ #ጌታችንም ይህን ጊዜ ቅድስት እናቱን ‹የላይኛውን ወይም የታችኛውን ይወድ እንደሆነ ጠይቂው› አላት፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም ከዚያ ቆሞ ነበርና ወዲያው ለእኔ ‹የላይኛው ያለህ መንግሥተ ሰማያትን ነው፣ የታችኛው ያለህ ይህች ዓለም ናት› አለኝ፡፡ እኔም ያንጊዜ ይህችን ዓለም አልፈልጋትም ነገር ግን ማረፊያ እንዲሰጠን በጸሎቴ የጠየቁት ልጆቼ ከሞቴ በኋላ ተስፋ እንዳይቆርጡ እንዳይበተኑም ብዬ ነው አለኩት፡፡ #ጌታችንም ‹‹ገብረ ማርያም ሆይ ለምን ይህንን ታስባለህ? ለልጆችህ እኔ አስብላቸዋለሁና፡፡ ወዳጄ ዳዊት ‹የጻድቃን ልጆች ይባረካሉ፣ ክብርና ባለጠግነት በቤቱ ነው፣ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል› (መዝ 111፡33) ብሎ እንደተናገረ እኔ ለፍጥረት ወገን ሁሉ አስባለሁ› አለኝ፡፡ ይህንንም ብሎኝ ሰላሙን ሰጥቶኝ ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡››

አቡነ ገብረ ማርያም ያደረጓቸው ተአምራት ተነግረው የሚያልቁ አይደሉም፡፡ በብቸኝነት ሳለ በአንዲት አገር የሚኖር ልጁ የሞተበት ሰው የልጁን አስክሬን ወደ አባታችን አምጥቶ በፊታቸው አስቀመጠውና ‹‹አባታችን ሆይ ልጄ እንደሞተ ተስፋዬ ሁሉ ጠፍቷልና አሁን ብትወድ ከሞት አንሣው ባትወድ ግን እዚሁ ቅበረው›› እያለ አለቀሰባቸው፡፡ አባታችንም የሰውየውን ሁኔታውን አይተው ፈጽመው አለቀሱ፡፡ ልቡናቸውም ታወከባቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ይጸልዩ ዘንድ ተነሡና ‹‹…በተቀበረ በ4ኛው ቀን አልዓዘርን ያስነሣኸው አሁንም ይህን ሕፃን አስነሣው…›› ብለው ከጸለዩ በኋላ የልጁን እጅ ይዘው ‹‹በ #ጌታችን_በአምላካችን_በመድኃኒታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ ኃይል ተነሥ›› ብለው እፍ አሉበት፡፡ ያንጊዜም ሕፃኑ ከእንቅልፉ እንደሚነቃ አፈፍ ብሎ ተነሣ፡፡ ለአባቱም ‹‹ልጅህን ውሰድ ፈጣሪዬ አስነሣልህ›› ብለው ሰጡት፡፡ ሰውዬውም ከእግራቸው ሥር ሰግዶ የእግራቸውን ትቢያና ሰውነታቸውን ሁሉ ሳመው፡፡ ልጁንም ይዞ ፈጽሞ ደስ እያለው ወደ ቤቱ ሄደ፡፡

በአንዲት ሀገርም አንድ ልጅ ብቻ ያላት አንዲት ሴት ነበረች፡፡ ልጁም ወደ አባታችን እየመጣ ‹‹አመንኩሱኝ›› እያለ ሁልጊዜ ይጠቃቸው ነበር፡፡ አንድ ቀንም እንዲሁ መጣና ‹‹አባት ሆይ ካላመነኮሱኝ ወደሌላ ሰው ዘንድ ሄጄ እመነኩሳለሁ›› አላቸው፡፡ በዚህም ጊዜ አባታችን ፈቃደ #እግዚአብሔርን ጠይቀው የፍላጎቱን ፈጸሙለትና አመነኮሱት፡፡ ወላጅ እናቱም መጥታ ልጇ የምንኩስናን ልብስ እንደለበሰ ባየች ጊዜ እያለቀሰች ሄደችና ራሷን ወደ ገደል ውስጥ ጨመረች፣ ሞተችም፡፡ ሰዎችም ተሰብስበው አለቀሱላትና አስክሬኗን ተሸከመው ይቀብሯት ዘንድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ወሰዷት፡፡ ሰዎችም ወደ አባታችን መጥተው ‹‹ሴትዮዋ ከመቀበሯ በፊት መጥተው ይዩዋት›› አሏቸው፡፡ አባታችንም ወደ አስክሬኗ አልመለከትም›› አሉ፡፡ እነርሱም በ #እግዚአብሔር ስም ባማሏቸው ጊዜ አባታችን አስክሬኗ ወዳለበት መጡና አዩዋት፡፡ በማግሥቱም ከገነዟት በኋላ አባታችን ከመዝገበ ጸበላቸው
#ማኅሌተ_ጽጌ፤ ምንጩ ትርጉሙና መልእክቱ (ክፍል ሁለት)

በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

የቀጠለ…

2, #ታሪክ

በብሉይና በሐዲስ ኪዳን በተለያዩ ጊዜያት የተፈጸሙትን ድርጊቶች እያነሣ የሚሔድና በዚያውም ከታሪኩ ጋር አብሮ ጸሎትና ምሥጢር የያዘ ነው፡፡ ታሪክን ከሚያነሡት መካከል የሚከተሉትን ለአብነት መመልከት ይቻላል፡፡

2.1. «እስከ መነነቶ ሜልኮል ቅድመ ታቦተ ሕግ ከመ ዘፈነ፣
ንጉሠ እስራኤል ኪያኪ ዘጸገየ ስነ፣
ቅድመ ገጸ ሥዕልኪ ድንግል እዘፍን አነ
ዘይሜንን ተአምረኪ ወስብሐተኪ ቁርባነ፣
በአፈ መላእክት ወሰብእ ለይኩን ምኑነ፡፡

ዳዊት ታቦተ ጽዮንን ከአቢዳራ ቤት ወደ ከተማው ባስመጣ ጊዜ በሙሉ ኃይሉ በ #እግዚአብሔር ታቦት ፊት ሲዘምር ሜልኮል ተመልክታ በልብዋ ናቀችው፡፡ በዚህም ምክንያት #እግዚአብሔር ስላዘነባት ልጅ ሳትወልድ ሞታለች፡፡ ሳሙ.6፡12-23፡፡ ደራሲውም ይህንን ታሪክ ካስታወሰ በኋላ «ቅድመ ገጸ ሥዕልኪ ድንግል እዘፍን አነ - ዳዊት ለ #እመቤታችን ምሳሌ በሆነች በታቦተ ጽዮን ፊት እንደዘመረ እኔም በሥዕልሽ ፊት ላንቺ እዘምራለሁ»፤ «ዘይሜንን ተአምረኪ ወስብሐትኪ ቁርባነ በአፈ መላእክት ወሰብእ ለይኩን ምኑነ ሜልኮል፡- በዳዊት ይቀርብ የነበረውን የታቦተ ጽዮንን ምስጋና በመናቋ እንደተረገመች ያንቺንም ተአምርሽንና ምስጋናሽን የሚንቅ ሁሉ በሰውና በመላእክት አፍ የተረገመ ይሁን» የሚል ነው፡፡ ሜልኮል የምሳሌዋን የታቦተ ጽዮንን ምሥጋና በመናቋ ከተረገመች ዛሬ የአማናዊቷን ታቦተ ጽዮን የ #እመቤታችንን ምሥጋና የሚንቁና ምሥጋና የሚያቀርቡትን የሚነቅፉ ሰዎች ምን ያኽል የተረገሙ ይሆኑ? እነዚህም «በድፍረትና በመናቅም በጻድቅ ላይ የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ» /መዝ.3ዐ÷18/ ባለው ርግማን የተረገሙ ናቸው፡፡

2.2. እንበይነ አውሎጊስ ለዳንኤል አመ አርአዮ ስቅለተ፣
ከመ እገሪሁ ሰዓምኪ ወሰአልኪዮ ምሕረተ፣
ለተአምረ ሣህል ወልድኪ በእንተ ፍቅረ ሰብእ ዘሞተ፣
እንዘ ታዘክሪዮ ድንግል ይምሐረኒ ሊተ፣
ከናፍሪሁ ጽጌ አንኂ ስዕመተ፡፡

አውሎጊስ የሚባል የወፍጮ ድንጋይ እየጠረበ በመሸጥ ከዚያ በሚያገኘው ትንሽ ገቢ የሚተዳደር ደኃ ሰው ነበር፡፡ የሚያገኘውንም ገንዘብ ለራሱ ትንሽ ለዕለት ኑሮው ካስቀረበ በኋላ ከርሱ የባሰባቸው ችግረኞችን እየረዳ ይኖር ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን በዚህ ግብር ሳለ አባ ዳንኤል የሚባል ባሕታዊ ያየዋል፡፡ ይህም ባሕታዊ አውሎጊስ በዚህ በድህነት ኑሮው እንደዚህ ድሆችን የሚረዳ ከሆነ ብዙ ገንዘብማ ቢያገኝ ምን ያክል ብዙ ሰው በረዳና መልካም ሥራ በሠራ ነበር» ብሎ #እግዚአብሔር ለዚህ ሰው ብዙ ሀብት እንዲሰጠው ሱባኤ ያዘ፡፡ #እግዚአብሔርም ሀብት ለዚህ ሰው /ለአውሎጊስ/ እንደማይጠቅመው ቢነግረውም አባ ዳንኤል በራሱ ሀሳብ ብቻ በመጓዝ ሀብቱን እንዲሰጠው አጥብቆ ስለተማፀነ እንደለመነው ሊያደርግለት ጸሎቱን ተቀበለ፡፡ ከዚህ በኋላ አውሎጊስ እንደልማዱ ድንጋይ ሲቆፍር በማሰሮ የተቀበረ ወርቅ አገኘ፡፡ ወርቁን ወስዶ ለንጉሡ ሰጠ፡፡ ንጉሡ ወርቅ ሲያገኝ ለራሱ ሳያደርግ ለንጉሥ የሚያመጣ ሰው ምን ያክል ታማኝ ቢሆን ነው ብሎ በዚያው በቤተ መንግሥቱ እንደራሴ አድርጎ ሾመው፡፡ አውሎጊስ ከተሾመ በኋላ አጃቢው ክብሩና ሀብቱ ሲበዛ ትሩፋት መጨመሩ ቀርቶ የቀደመ ሥራውንም ተወ፡፡ ለተበደለ የማይፈርድ ባለጉዳይ የሚያጉላላ ሆነ፡፡ በዚህ ጊዜ አባ ዳንኤል በሕልም #እግዚአብሔር ሲቆጣውና ሲፈርድበት አየ፡፡ የማይገባ ልመና ለምኖ አውሎጊስን የቀደመ ትሩፋቱን እንዲተውና አሁን እንዲበድል ምክንያት ሆኗልና፡፡ አባ ዳንኤል በደሉ ገብቶት ከ #ሥዕለ_ማርያም ሥር ወድቆ ተማፅኖ #እመቤታችን ልጇን ተማጽና ይቅር አስባለችው፡፡
አባ ዳንኤል በሕልም ያየው ነገር ስለከበደው ምናልባት አውሎጊስ ድሀ በድሎ ፍርድ አጓድሎ እንደሆነ ብሎ ሊያየው ቢሄድ እርሱንም የማያናግረው ሆነ፡፡ «ስለ ሰው ፍቅር የሞተ ልጅሽን ስለ አባ ዳንኤል ለምነሽ እንዳስማርሽው እኔንም ይቅር እንዲለኝ የጽጌ ልጅሽን ምሕረት ለምኝልኝ» በማለት እኛንም ባላወቅነው እየገባንና እየፈረድን ለሚመጣብን ቅጣት እንድታስምረን የሚያመለክት ነው፡፡

2.3. ኦ ረዳኢተ ድኩማን ዘይረድአኪ ኢትኃሥሢ፣
እምንበረ ላዕክኪ በምዕር ከመ ገፍታዕኪዮ ለወራሲ፣
ለገፍትዖ ፀርየ ድንግል ኃይለ ጽጌኪ ልበሲ፣
እንዘ ይሣለቅ ተአምረኪ ወሐሰተ ይሬሲ፣
መፍትውኑ ከመ ይህየው ከይሲ፡፡

#እመቤታችንን ተአምር አሰባስቦ የጻፈው ቅዱስ ደቅስዮስ ነው፡፡ #እመቤታችንም ለዚህ ውለታው ሌላ ሰው የማይቀመጥበት ሰማያዊ ወንበር እና ሌላ ሰው የማይለብሰው አጽፍ ሰጥታዋለች፡፡ ከደቅስዮስ ዕረፍት በኋላ በእርሱ ቦታ የተሾመው ኤጲስ ቆጶስ በዚህ መንበር ለመቀመጥና አጽፉን ለመልበስ ሲል «ተው ይህ ለደቅስዮስ ብቻ የተሰጠ ነው» ቢሉት «እኔም እንደርሱ ኤጲስ ቆጶስ ነኝ ከእርሱ በምን አንሳለሁ?» በማለት ከወንበሩ ሲቀመጥ ወዲያው ሞቷል፡፡ ከላይ የተጻፈው ድርሰትም የሚያስረዳው ይህንን ነው፡፡ «ድኩማንን፣ ችግረኞችን የምትረጅ አንቺ ግን ረዳት የማትሽ ሆይ ከወዳጅሽ ከደቅስዮስ ወንበር ላይ በትዕቢትና በድፍረት የተቀመጠውን እንደተቀበልሽው የእኔንም ጠላቶች አጋንንትን እኩያት ኃጣውእን ለማስወገድ የጽጌሽን ማለት የልጅሽን ኃይል ይዘሽ ተነሽ» በማለት ለወዳጆቿ የምትቆም #እመቤታችን ከጠላታችን እንድትታደገን ከታሪኩ አንጻር የቀረበ ጸሎት ነው፡፡

2.4. «በጌጋየ አዳም ወሔዋን ሱራፌል ዘአጸዋ፣
እንበለ ጽጌኪ መኑ ለአንቀጸ ገነት ዘአርኃዋ፣
ተፈሥሒ ድንግል መያጢተ አዳም እምጼዋ፣
በተአምርኪ ውስተ ምድረ ጽጌ አቲዋ
ከመ ጣዕዋ አንፈርዓፀት ጼዋ፡፡

አዳምና ሔዋን ባጠፉት ጥፋት ከገነት ተባረው ወደ ምድረ ፋይድ እንዲወርዱ ተፈርዶባቸው ገነትን ሱራፌል መልአክ በምትገለባበጥ የእሳት ሰይፍ ይጠብቅ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ የተዘጋጀት ገነትን «እንበለ ጽጌከ መኑ ለአንቀጸ ገነት ዘአርኃዋ፤ ያለ አንቺ ጽጌ ያለ #ክርስቶስ በሱራፌል ስትጠበቅ የነበረችውን ገነት ሊከፍታት የቻለ ማንም ፍጥረት የለም» ዘፍ.3፡24፡፡ ካንቺ በተገኘ በ #ክርስቶስ ወደ ቀደመ ክብሯና ቦታዋ የተመለሰች ሔዋን የእናቱን ጡት ጠብቶ ደስ እንደሚሰኝ እንደሚዘል እንቦሳ ደስ ተሰኘች፡፡ በአጠቃላይ ይህ የሚያስረዳው ያለ #ክርስቶስ ሰው መሆንና በ #መስቀል ተሰቅሎ ቤዛ መሆን ማንም የገነትን በር ሊከፍት እንደማይችል ሲሆን የተዘጋውን የገነት በር የከፈተና የሰው ልጅ ያጣውን የልጅነት ጸጋ የመለሰ #ክርስቶስ ደግሞ ከ #እመቤታችን የተገኘ መሆኑን ነው፡፡ #እግዚአብሔር በኢሳይያስ አንደበት «መድኃኒቴም አይዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኃኒትን ለእስራኤል ሰጥቻለሁ» ኢሳ.46÷13፡፡ እንዳለ የተዋረደው የሰው ልጅ የከበረበትና የዳነበት መድኃኒት #ኢየሱስ_ክርስቶስ የተገኘው ጽዮን ከተባለች ከእመቤታችን ከቅድስት #ድንግል_ማርያም ነው፡፡ ይህንን መድኃኒት ለዓለሙ ያበረከተች እርሷ ናት፡፡

3. #ተግሣጽ

አባ ጽጌ ድንግል ይህንን ማኅሌተ ጽጌ ሲደርስ ለ #መስቀልና#እመቤታችን ክብርና ስግደት አይገባም የሚሉ ደቂቀ እስጢፋ የሚባሉ መናፍቃን ተነሥተው ነበር፡፡ በዘመኑ የነበሩት ንጉሥ አፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጉባኤ አሠርተው አከራክረው መናፍቃኑ ተረትተዋል፡፡ አባ ጽጌ ድንግልም በማኅሌተ ጽጌ ውስጥ እነዚህን የ #እመቤታችንን ተአምርና ክብር በመግለጽ መናፍቃንን በመገሰጽ በዚህ የተግሣጽ ድርሰታቸው አስተምረዋል፡፡ ለምሳሌ የተወሰኑትን እንመልከት፦
ንጉሡም ቅዱስ እስጢፋኖስን ይህ የምትሠራው ምንድር ነው ለራስህ ጥፋትን አምጥተሃልና አለው ከዚህም በኋላ ሰይፉን መዝዞ መታውና ከሁለት ከፈለው የቅዱስ እስጢፍኖስም ራስ ለረጅም ጊዜ በንጉሥ ፊት ሁና በክርስቲያን ወገኞች ላይ የሚደረገውን ሁሉ ግፍ ዳግመኛም በስተኋላ በንጉሡ ላይ የሚመጠበትን ዐይኖቹ እንደሚታወሩ ምጽዋትንም እንደሚመጸወት ከዚያም በኋላ እንደሚጠፋ ተናገረች።

ከዳተኛ ንጉሥ ሄሮድስን የምጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራስ እንደ ዘለፈችው የቅድስ እስጢፋኖስም ራስ ዲዮቅልጥያኖስን ስትዘልፈው ያዩዋት ዘንድ ብዙ ሕዝቦች የሚመጡ ሆኑ ሄሮድስና ዲዮቅልጥያኖስ አንድ ጠባይ ናቸውና በከፋች ሥራቸውም አይለያዩም።

ሴቶች ከወለዱአቸው የሚመስለው የሌለ የልዑል ነቢይ የሆነ ጻድቅ ሰውን ሄሮድስ በገደለው ጊዜ ዝሙቱ እንዳይገለጽ ሽቶ ነበር ስለዚህም ተልቶ ተበላሽቶ እስኪሞት ሚስቱንም ምድር እስከ ዋጠቻት ልጅዋም እስከ አበደች ድረስ ጉስቍልና አገኘው የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራስም ዝሙቱን ግልጽ አድርጋ ዘለፈችው።

ይህም ጐስቋላ ዲዮቅልጥያኖስ የረከሱ የጣዖታትን አምልኮ ሊገልጥ የማይደበቅ የሕያው #እግዚአብሔርን አምልኮ ሊደብቅ ወዶ የቅዱስ እስጢፍኖስን ራስ ቆረጠ የቅዱስ እስጢፍኖስ ራስ ግን ዘለፈችው አማልክቶቹም የርኩሳን አጋንንት ማደሪያዎች እንደ ሆኑ ገለጠች አሳፈረችውም ።

በምድርም ውስጥ እንዲደፍኑዋት አዘዘ ። እርሷም በምድር ውስጥ ተደፍና ሳለች ዝም አላለችም ሦስት ቀን ያህል አብዝታ እየተናገረች ትዘልፈው ነበር ሕዝቡም ሁሉ ይሰሟታል እጅግም አፈረ ከእርሳስም ሣጥን ውስጥ እንዲጨምሯትና ሣጥኑን አሽገው ከጥልቅ ባሕር ውስጥ እንዲጥሉት አዘዘ በዚያንም ጊዜ የ #እግዚአብሔር መልአክ ወረደ ሣጥኑንም ከባሕር አውጥቶ በባሕሩ ዳር አኖረው ።

እናቱም ሥጋውን እየፈለገች በ #እግዚአብሔር ፈቃድ ከዚያ ደረሰች አግኝታውም ዘመን እስቲያልፍ በሥውር ቦታ አኖረችው በፊቱም መብራት አኖረች የመከራውም ወራት ከአለፈ በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ተሠራችለት ከእርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቶማስ_ሐዋርያ

በዚችም ቀን በሕንድ አገር ቅዱስ ሐዋርያ ቶማስ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ ።

ይህም እንዲህ ነው ሐዋርያ ቶማስ እንደ ባሪያ ተሽጦ ወደ ሕንድ አገር ከአበኒስ ጋር በገባ ጊዜ አበኒስ ወደ ንጉሥ ጎንዶፎር አቀረበውና ሐናፂ እንደሆነም ለንጉሡ ነገረው ንጉሡም ስለሚችለው ሙያው ሐዋርያውን ጠየቀው ቅዱስ ሐዋርያ ቶማስም እንዲህ ብሎ ለንጉሥ መለሰለት እኔ የጥርብ ሥራን ሁሉ ቀንበሮችን ሚዛኖችን ሠረገላዎችን መርከቦችን በግንብ ሥራም ቤተ መንግሥትን እሠራለሁ ንጉሡም እጅግ ደስ አለው ።

ቤተ መንግሥቱንም እንዲሠራለት ከሚሻው ቦታ ወሰደውና በምን ወር ትሠራለህ አለው ሐዋርያውም ከኅዳር መባቻ ጀምሬ በሚያዝያ ወር እጨርሳለሁ አለው ። ንጉሡም አድንቆ ሕንፃ ሁሉ በበጋ ይታነፃል አንተ ግን እንዴት በክረምት ወር ታንፃለህ አለ ሐዋርያም ስለዚህ ነገር ችግር የለም አለ ።

ከዚህም በኋላ ንጉሡ ለራሱና ከእርሱ ጋር ለሚሠሩ ሠራተኞች የሚሆን ብዙ ገንዘብን ሰጠው ቅዱስ ሐዋርያ ቶማስም ተቀብሎ ሔደ ። የንጉሥን ለንጉሥ እሰጣለሁ እያለ ለድኆችና ለምስኪኖች መጸወተው ዳግመኛም የቤተ መንግሥቱ ግድግዳው ተፈጽሞ ጣሪያው ቀርቷል ብሎ ወደ ንጉሡ ላከ ። ያን ጊዜም ንጉሥ ብዙ ገንዘብ ላከለት ሐዋርያውም ተቀብሎ እንደ ልማዱ መጸወተው ።

ከዚህም በኋላ ንጉሡ በመጣ ጊዜ ስለ ቤተ መንግሥቱ ሕንፃ ጠየቀ ምንም የተሠራ ነገር አላገኘም ነገር ግን ገንዘቡ ለድኆች ምጽዋት ሁኖ እንደተበተነ ሰማ ። እጅግም ተቆጣ በሚገለውም ነገር እስቲመክር ድረስ ሐዋርያ ቶማስን ከአመጣው ከአበኒስ ጋር አሠረው ።

በዚያችም ሌሊት የንጉሡ ወንድም ጋዶን በደንገት ታመመና ሞተ መላእክትም ነፍሱን ወስደው ተመሳሳይ የሌለው በወርቅና በዕንቍ የተሠራ ቤተ መንግሥትን አሳዩዋት ። ጋዶንም መላእክትን ይህ ቤተ መንግሥት የማነው አላቸው መላእክትም ለጋዶን ሐዋርያ ቶማስ ለንጉሥ ጎልዶፎር የሠራለት ነው አሉት ከዚህም በኋላ ጋዶን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ያየውንም ሁሉ ለወንድሙ ለንጉሥ ጎልዶፎር ነገረው ። በዚያንም ጊዜ ወደ እሥር ቤት ሮጡ ቅዱስ ሐዋርያ ቶማስንም አበኒስንም ከወህኒ ቤት አወጡአቸው ። ለሐዋርያውም ሰገዱለት የሀገር ሰዎችም ሁሉ ከንጉሥ ጎልዶፎር ጋር አመኑ በ #አብ#ወልድ#መንፈስ_ቅዱስ ስም ተጠመቁ የ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስንም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን አቀበላቸው ። ከዚህም በኋላ ባረካቸውና ከእርሳቸው ዘንድ ወጥቶ ወደ ሌላ ቦታ ሔደ ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_መዝገበ_ሥላሴ_ጻድቅ

አቡነ መዝገበ ሥላሴ በታሪካዊነቱና በያዛቸው ድንቅ ድንቅ ቅርሶች ከሚታወቀውና ኢትዮጵያዊውን ሀሳበ ዘመን በመቀመር ከሚታወቀው ከእውነተኛው የብህትውና ቦታ ከደብረ ገሪዛን ቅድስት ማርያም ጉንዳጉንዶ ገዳም የተገኙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ እነ አቡነ አበከረዙንን ጨምሮ የባሕረ ሐሳብ ፍልስፍናና የሥነ ጽሑፍ ማዕከል ከሆነው ከዚህ ገዳም የወጡ ገድል ተጽፎላቸው፣ ታቦት በስማቸው የተቀረጸላቸው ከ17 በላይ ታላላቅ ቅዱሳን አሉ፡፡ አቡነ መዝገበ ሥላሴም ከእነዚህ የበቁ ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ አባታቸው ሀብተ ጽዮን እናታቸው ማርያም ሞገሳ ሲባሉ እነርሱም በ #እግዚአብሔር ፊት ቅኖች ነበሩ፡፡

ማርያም ሞገሳ ዕለት ዕለት አምሃ(ስጦታ) እየያዘች ወደ ቤተ ክርስቲያን እየሄደች ስትጸልይ በአንደኛው ዕለት የታዘዘ መልአክ መጥቶ ‹‹በ #እግዚአብሔር ፊት ሞገስ ያገኘና የተባረከ ልጅ ትወልጃለሽ›› ብሎ አበሰራት፡፡እርሷም ‹‹ከማኅፀኔ እንደፀሐይ የሚያበራ ልጅ ሲወጣ አየሁ›› አለች፡፡ በዚህም መሠረት አቡነ መዝገበ ሥላሴ በምሥራቃዊ ትግራይ ዞን በገላውዴዎስ ዘመነ መንግሥት በ1532 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ በ40ኛ ቀናቸውም ሲጠመቁ ሰጊድለአብ ተባሉ፡፡ ሰጊድለአብ ከዕለታት በአንደኛው ቀን የ #እግዚአብሔር መልአክ ከእናታቸው እቅፍ ውስጥ ነጥቆ ወስዶ ደብረ ከስዋ (ደብረ ገሪዛን) ጉንዳጉንዶ ቅድስት ማርያም ገዳም አደረሳቸው፡፡ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑም ካስገባቸው በኋላ በውስጥ የነበሩትን ንዋያት ሁሉ እያሳየ ‹‹አንተ ሕፃን ሆይ! ዕወቅ ይህ የምታየው ሁሉ የአንተ ነው፣ ትጠብቀውም ዘንድ #እግዚአብሔር ሰጥቶሃል፡፡ ደግሞም የ #ክርስቶስን በጎች ትጠብቅ ዘንድ ተሰጥቶሃልና ፈጽሞ ደስ ይበልህ›› አላቸውና ፈጥኖ ወደ እናታቸው እቅፍ መለሳቸው፡፡ ዕድሜአቸውም ለትምህርት ሲደርስ ወደ ጉንዳጉንዶ ተመልሰው የሁሉንም መጻሕፍትን ምሥጢር ጠንቅቀው ተማሩ፡፡ በገዳሙም የምንኩስናን ሥራ እየሠሩ በተጋድሎ ኖሩ፡፡ ክብርት #እመቤታችንም ተገልጻላቸው ‹‹ልጄ በተፈቀደልህ ተጋድሎ አሰልጥኖሃልና ጨክን፣ በርታ እኔም ከአንተ አልለይም›› አለቻው፡፡ ከመነኮሱም በኋላ ስማቸው ‹‹አቡነ መዝገበ ሥላሴ›› ተባሉ፡፡

አቡነ መዝገበ ሥላሴ ስብከተ ወንጌልን በመላ ሀገራችን በማስፋፋት ብዙ የደከሙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ‹‹የሐዋርያት አምሳል›› ተብለዋል፡፡ የገዳሙ አበምኔት ሲያርፉ መነኮሳቱ በፈቃደ #እግዚአብሔር አቡነ መዝገበ ሥላሴን ይዘው በግድ አበምኔትነት ሾሟቸው፡፡ እሳቸውም ከተሾሙ በኋላ በመላ ሀገራችን ተዘዋውረው ወንጌልን ሰብከዋል፡፡ ብዙ ድውያንን ፈውሰዋል፣ ሙታንን አንሥተዋል፡፡ በዓታቸውንም በማጽናት በጸሎት ተወስነው የዐይኖቻቸው ቅንድቦች እስኪላጡ ድረስ ጉንጮቻቸውም እስኪቀሉ ድረስ በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ 40
ቀንና 40 ሌሊትም ይጾማሉ፡፡ ስግደታቸውም በቀንና በሌሊት ያለ እረፍት እንደመንኮራኩር ፈጣን ሆነ፡፡ ወዛቸውና ዕንባቸው አንድ ላይ ተቀላቅሎ እንደጅረት እስኪፈስ ድረስ በጭንቅ ተጋድሎ እንደኖሩ ገድላቸው ይናገራል፡፡ #እመቤታችንም ብዙ ጊዜ እየተገለጠችላቸው ከህመማቸው እየፈወሰች ታበረታቸው ነበር፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አቡነ መዝገበ ሥላሴ ራእይ ተመለከቱ፡፡ እነሆም ውበታቸው የሚያስገርም፣ መልካቸውም የሚያስደንቅ፣ የምስጋና ነፀብራቅ የከበባቸው፣ የራሳቸው ፀጉር ነጭ የሆነ ሦስት ወፎችን ተመለከቱ፡፡ አባታችንም አንድ ጊዜ ሦስት ሌላ ጊዜ ደግሞ አንድ ሲሆኑ ተመልክተው ፈጽሞ አደነቁ፡፡ እንዲህ እያደነቁ ሳለ #እግዚአብሔር በቃሉ ጠርቶ ካነጋገራቸው በኋላ ብዙ ምሥጢራትን ነገራቸው፡፡ ለመረጣቸው ቅዱሳን እንዲህ መገለጥ ለ #እግዚአብሔር ልማዱ ነውና ለአባታችን ለአዳም፣ ለሄኖክ፣ ለኖኅ፣ ለአብርሃም በልዩ ልዩ ህብር ተገልጧል፡፡ ኦ.ዘፍ 3፡10፣ 5፡24፣ 6፡13፣ 18፡1 ፡፡ ለሕዝቅኤልም በኮበር ወንዝ፣ ለዳንኤል በሱሳ ግንብ፣ ለኢሳይያስ ሱራፌል እያመሰገኑት ተገልጦላቸዋል፡፡ ሕዝ 1፡1፣ ዳን 8፡1-3፣ ኢሳ 6፡1-3፡፡

አቡነ መዝገበ ሥላሴ በዘመን ደረጃ በኋለኛው ዘመን የተነሡ አባት ይሁኑ እንጂ በሰጡት ሐዋርያዊ አገልግሎትና ገንዘብ ባደረጉት የተጋድሎ ጽናት የከበሩ ቅዱሳን ሐዋርያትን መስለዋቸዋል፡፡ የታዘዘ መልአክ ወደ መንግሥተ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ማደሪያቸውን አሳይቷቸው መልሶ ወደ ምድር ካመጣቸው በኋላ የዕረፍታቸው ጊዜ እንደደረሰ ነገራቸው፡፡ ‹‹በሰኔ ወር ታርፋለህ›› ቢላቸው ‹‹በሰኔማ ልጆቼ ተዝካሬን ማድረግ አይችሉም›› አሉት፡፡ መልአኩም መልሶ ‹‹ዕረፍትህ በሐምሌ ይሁን›› ቢላቸው ጻድቁ አሁንም ‹‹አይሆንም›› ብለው ተከራከሩ፡፡ በነሐሴም እንደዚያው ሆነ፡፡ መልአኩም መስከረምን አሳልፎ በጥቅምት እንደሚያርፉ ነግሯቸው ዐረገ፡፡ ከዚህም በኋላ ለስም አጠራሩ ምስጋና ይግባውና #ጌታችን ቅድስት እናቱን፣ መላእክትን፣ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታትን ሁሉ አስከትሎ መጥቶ ‹‹አንተ የዓሥራ አንደኛው ሰዓት ቅጥረኛ ወዳጄ ሆይ! (ከቅዱሳን ሁሉ በኋላ የተነሣህ-ማቴ 20፡1-5) የምስራች እነግርህ ዘንድ የድካምህም ዋጋ እሰጥህ ዘንድ መጥቻለሁ፡፡ እነሆ ከጠዋት ጀምሮ ከደከሙት ጋር አንድ አድርጌሃለሁ፡፡ ከአንተም ጋር ቃልኪዳን ገብቻለሁ፣ ስምህን በእምነት የጠራ፣ መታሰቢያህን ያደረገ፣ በጸሎትህም የታመነ እስከ ሰማንያ ሺህ ስድስት መቶ (80,600) ነፍሳት ዓሥራት ይሁኑህ…›› በማለት ቃልኪዳን ከገባላቸው በኋላ ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡ በዚያን ጊዜም አቡነ መዝገበ ሥላሴ ፊታቸው እንደፀሐይ አበራና ጥቅምት 9 ቀን ከሌሊቱ በ6 ሰዓት እንደመልካም እንቅልፍ ዐረፉ፡፡ መላ ዘመናቸው 115 ሲሆን የደብረ ገሪዛን ጉንዳጉንዶ ቅድስት ማርያም ገዳም አበምኔት ሆነው ከመሾማቸው በፊት 62 ዓመት፣ ከተሾሙበት ጊዜ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ 53 ዓመት ነው፡፡ መካነ መቃብራቸው እዚያው የደብረ ገሪዛን ጉንዳጉንዶ ቅድስት ማርያም ገዳም ይገኛል፡፡

በጉንዳጉንዶና አዲግራት በሚገኘው ገዳማቸው ውስጥ በስማቸው የፈለቁ ብዙ ፈዋሽ ጠበሎች አሉ፡፡ አዲግራት የሚገኘው ገዳማቸው ውስጥ ያለው ጠበል የትኛውንም በሽታ በአስቸኳይ ፈውስ በመስጠት ይታወቃል፡፡ ተጠማቂው ሰው የማይድንም ከሆነ ቶሎ ይሞታል እንጂ ከ7 ቀን በላይ አይቆይም፡፡ ጻድቁ ብዙ የተጋደሉበት ይህ ገዳም በግራኝ አህመድ ዘመን 44 ጽላቶች ተሰውረውበታል፡፡ ዮዲት ጉዲትም ልታገኘው ያልቻለችው ታላቅ ገዳም ነው፡፡ በአንድ ወቅት ከሃዲያን አሕዛብ ጦረኞች ወደ ገዳሙ ሲወጡ በተአምራት ወደ ፅድ ዛፍነት ተለውጠዋል፡፡ ፅዶቹ አሁንም ድረስ በገዳሙ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ፅዶቹን በእሳት አቃጥለው ከሰል ቢያደርጓቸው ደም ሆነው ይፈሳሉ እንጂ ፈጽሞ ከሰል መሆን አይችሉም።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት_9 #ከገድላት_አንደበት)
#ጥቅምት_14

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ዐሥራ አራት በዚች ቀን ታላቁና የከበረው አባታችን #አቡነ_አረጋዊ ተሰወሩ፣ የቊስጥንጥንያ ንጉሥ የቴዎዶስዮስ ልጅ #ቅዱስ_ገብረ_ክርስቶስ አረፈ፣ ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የሆነ አንዱ #ቅዱስ_ሐዋርያ_ፊልጶስ አረፈ፣ ከሮሜ ሀገር የሆነ የከበረ የእግዚአብሔር ሰው #ሙሽራው_ቅዱስ_ሙሴ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ጻድቁ_አቡነ_አረጋዊ

ጥቅምት ዐሥራ አራት በዚህች ቀን ታላቁና የከበረው አባታችን አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) የተሰወሩበት ነው።

እኚህ አባት ከ9 ቅዱሳን አባቶች አንዱ ሲሆኑ
አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉስ ነበሩ፡፡ እናታቸው ንግስት እደና ይባሉ ነበር፡፡ የመጀመሪያ ስማቸው ዘሚካኤል ነው፡፡ ጥበብ መንፈሳ ሲማሩ አድገው ወደ እስክንድርያ ገዳም ገቡ፡፡ አበምኔቱ አባ ጳኩሚስ በፈቃደ #እግዚአብሔር የመጡ መሆናቸውን አውቀው መዓረገ ምንኩስና ሰጥተዋቸዋል፡፡

የንጉሳዊ የቅንጦት ኑሮ ንቀው ትተው ገዳም ገብተው በምንኩስና ተወስነዋል፡፡ አባታችን በተጋድሏቸውም ከአባ እንጦንስ፣ ከአባ ጳውሊ እና ከአባ መቃርስ ቀጥሎ በአራተኛ ማዕረግ አበ መነኮሳት ሆነው ተመርጠዋል።

በገዳመ ዳውናስ 7 ዓመት ከቆዩ በኋላ ወደ ሮም ተመልሰው ሲያስተምሩ የሀገራችን ኢትዮጵያን ዜና ሰምተው ለመምጣት በ480 ዓ.ም ከአባ ፍሬምናጦስ በኋላ መንገድ ጀመሩ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም በክንፉ ተሸክሞ አክሱም አድርሷቸዋል፡፡

ተመልሰውም ሄደው ስለ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መስክረዋል፡፡ ሐዋርያ ሳይላክላት በሃይማኖት በምግባር ጸንታ ትኖራለች ብለው ለሰባቱ ዘመዶቻቸው አበው መነኮሳት ነገሯቸው፡፡ ስምንቱም ጓዛቸውን ጠቅልለው በሮም ነግሶ የነበሩ ይስሐቅን (አባ ገሪማን) ጨምረው ንጉስ አልአሜዳ በነገሰ በአምስተኛ ዓመት ማለትም በ480 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ዘጠኝ ሆነው መጥተዋል፡፡

አባ አረጋዊ እናታቸው ቅድስት እድናን ደቀ መዝሙራቸውን ማትያስን አስከትለው እግረ መንገዳቸውን እያስተማሩና ድውያንን እየፈወሱ ደብረ ዳሞ ደረሰዋል፡፡

ከእግረ ደብር ሆነው አሁን ይህን ተራራ በምን ልወጣው እችላለሁ እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግሩ ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነቢዩ ዳዊት ላይ አድሮ በመዝሙር 90/91፥11-16 ላይ “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። እንዳለው የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስደሳ ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ ቅዱስ ሚካኤል ሰይፈ እሳት ይዞ እየጠበቃቸው ከተራራው አናት አድርሷቸዋል፡፡

ወዲያው ሃሌ ሉያ ለ #አብ ሃሌ ሉያ ለ #ወልድ ሃሌ ሉያ ለ #መንፈስ_ቅዱስ ብለው አመስግነዋል፡፡ ቦታውም ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሏል፡፡ በዚያ ዕለት ግማሽ ህብስት በልተው ጠገቡ፤ ከዚያ በኋላ ግን ምድራዊ ሕብስት አልተመገቡም፡፡ በሰንበተ ክርስታያን ከቅዳሴ በኋላ ሕብስተ ሰማያዊ እያመጡላቸው ይመገቡ ነበር እንጂ፡፡ ኋላም ዜና ጽድቃቸውን ሰምተው ከስድስት ሺህ ያላነሱ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበውላቸዋል፡፡

ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታ በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ መንግስቴን አወርሰሃለሁ ብሎ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ በስምህ የተማጸነውን እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ ብሎ ተስፋቸውን ነገራቸው፡፡ እሳቸው መነኮሳቱን ሰብስበው ከእንግዲህ በሥጋ አታዩኝም ብለው ነግረዋቸው አበምኔት ሾመውላቸው በዚህች ዕለት በዚያው በደብረ ዳሞ ተራራ በስተምስራቅ አቅጣጫ ተሰውረዋል፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ገብረ_ክርስቶስ

በዚህችም ቀን ዳግመኛ የቊስጥንጥንያ ንጉሥ የቴዎዶስዮስ ልጅ የቅዱስ ገብረ ክርስቶስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ይህም ቴዎዶስዮስ #እግዚአብሔርን የሚፈራ ነው ሚስቱም በጎ የምትሠራ #እግዚአብሔርንም የምትፈራ ናት ስሟም መርኬዛ ነው። እነርሱም ልጅ ስለሌላቸው ያዝኑ ነበር ወደ ኢየሩሳሌምም ሒደው ስእለትን ተሳሉ ቸር መሐሪ ወደሆነ #እግዚአብሔርም ለመኑ እርሱም ልመናቸውን ተቀበሎ ይህን ያማረ ልጅ ሰጣቸው ስሙንም አብደልመሲህ ብለው ሰየሙት ትርጓሜውም ገብረ ክርስቶስ ማለት ነው ። የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ የሥጋዊንም ትምህርት አስተማሩት ።

አድጎ በጕለመሰም ጊዜ የሮሜውን ንጉሥ ልጅ አጭተው እንደ ሥርዓቱ አጋቡት ከሌሊቱ እኩሌታም በሆነ ጊዜ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ ተነሥቶ ወደሙሽራዪቱ ገባ እጅዋንም ይዞ ከእርስዋ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ ። ከዚያም የሃይማኖት ጸሎት በአንድ አምላክ እናምናለን የሚለውን እስከ መጨረሻ ጸለየ የተሞሸረበትንም ልብስ ከላዩ አውልቆ የግምጃ ልብስን ለበሰ ወደ ሙሽሪቷም ሒዶ ራስዋን ሳማት እንዲህም እያለ ተሰናበታት #እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይኑር ከሰይጣን ሥራ ሁሉ ያድንሽ ። እርሷም አልቅሳ ጌታዬ ወዴት ትሔዳለህ ለማንስ ትተወኛለህ አለችው እርሱም በ #እግዚአብሔር ዘንድ እተውሻለሁ እኔም #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስን ልከተለው እሔዳለሁ የአባቴ መንግሥት አላፊ ነውና አንቺም መሐላሽን አስቢ አላት ያን ጊዜ መሐላዋን አስባ ዝም አለች ።

ለሠርጉም የታደሙት ሁሉ እንደተኙ በሌሊት ወጥቶ ሔደ ወደ ባሕርም ዳርቻ ደርሶ በመርከብ የሚጓዙ መንገደኞችን አገኘ የዓመት መንገድ ወደሚሆን አርማንያም እስከሚደርስ ከእነርሱ ጋር ተጓዘ ።

ነግቶ ወደ ሠርጉ አዳራሽ አባትና እናቱ በገቡ ጊዜ ሙሽራውን ልጃቸውን አላገኙትም ሙሽሪትንም ልጃችን ወዴት አለ ብለው ጠየቋት እርሷም እንዲህ አለቻቸው ። በሌሊት ወደ እኔ ገባ መሐላን አማለኝ ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ ራሴንም ስሞኝ ከእኔ ዘንድ ወጣ እኔም እያለቀስኩ ብቻዬን አደርኩ ነገርዋንም ሰምተው ወድቀው በመጮህ ታላቅ ልቅሶን አለቀሱ ።

በዚያችም ጊዜ በሀገሮች ውስጥ ሁሉ ልጁን ገብረ ክርስቶስን ይፈልጉት ዘንድ ንጉሡ አምስት መቶ አገልጋዮቹን ላከ ለድኆችና ለምስኪኖችም ምጽዋት አድርገው የሚሰጥዋቸውን ብዙ ገንዘብን ሰጣቸው ።

ገብረ ክርስቶስ ግን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል #ማርያም ስም በአርማንም አገር በተሠራች በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ደጅ የሚኖር ሆነ ። አባቱ የላካቸውም ሁለቱ አገልጋዮች ከዚያ ደርሰው ስለርሱ መረመሩ ግን ወሬውን ማግኘት ተሳናቸው ለድኆችም ምጽዋትን ሰጡ እርሱም ከድኆችም ጋር ምጽዋትን ተቀበለ ።

በዚያም ዐሥራ አምስት ዓመት ከኖረ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያም ለአንድ ቄስ ተገለጸችለት ቦታውንም አመልክታ እንዲህ አለችው ። የ #እግዚአብሔር ሰው ገብረ ክርስቶስን ይዘህ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ አስገባው ከውጭ አትተወው ቄሱም #እመቤታችን እዳዘዘችው አደረገ ።

ከዚህም በኋላ የተመሰገነ ገብረ ክርስቶስ በሌሊት ተነሣ ከ #እመቤታችንም ሥዕል ፊት ቁም ጸለየ እንዲህም አላት እመቤቴ ሆይ የተሠወረ ሥራዬን አንቺ ለምን ገለጥሽ አሁንም ወደሚሻለኝ ምሪኝ ይህንንም ብሎ የ #እመቤታችንን ሥዕሏን ተሳልሞ በሌሊት ወጥቶ ወደ ባሕሩ ወደብ ደረሰ ወደሌላ ሀገርም ሊሔድ ወዶ በመርከብ ተሳፈረ። ግን በ #እግዚአብሔር ፈቃድ ከአባቱ አገር ደረሰ የአባቱና የእናቱም ባሮች እየናቁትና እየሰደቡት በአባቱ ደጅ ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ ።
እነርሱም ታዛዦች ሁነው ወደ ኢትዮጵያ መጡ የኢትዮጵያ ንጉሥም መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ አለው እሊህንም ቅዱሳን አባቶች ይቀበሏቸው ዘንድ አሽከሮቹን በቅሎዎችን አስይዞ ላከ በመጡም ጊዜ በታላቅ ደስታ ሰላምታ አቀረበላቸው ከእርሳቸውም ቡራኬን ተቀበለ ታላቅ ክብርንም አከበራቸው ። እነርሱም የሊቀ ጳጳሳት አባ ማርቆስን ደብዳቤ ሰጡት እርሱም ተቀብሎ አንብቦ ለሊቀ ጳጳሳቱ ቃል ታዛዥ መሆኑን ገለጠላቸው።

ከዚህም በኋላ ወደ ሀገረ ስብከታቸውና ወደ ሕዝባቸው መመለስን በአሰቡ ጊዜ ስለ ቅድስናቸውና ስለ ትምህርታቸው ጣዕም ስለ ወደዳቸው የተከበረው ንጉሥ መመለስን ከለከላቸው በእርሱ ዘንድ እነርሱ እንደ #እግዚአብሔር መላእክት ሁነዋልና ፊታቸውም እንደ ፀሐይ ያበራል።

ከጥቂት ወራትም በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው #እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ በላዩ ደዌ ላከበት በዚያውም ደዌ በሰላም አረፈ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_አላኒቆስ

ዳግመኛም በዚህች ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ አላኒቆስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ አቡነ አላኒቆስ የትውልድ ቦታቸው ሸዋ አንኮበር ሲሆን አባታቸው ንጉሡ ዐፄ ይኩኖ አምላክ ነው፡፡ ንጉሡ አባታቸው ‹‹አግባና መንግሥቴን ይዘህ ተቀመጥ›› ቢላቸው እርሳቸው ግን ንግሥናን በመናቅ እምቢ ብለው ሄደው ከ#እመቤታችን ሥዕል ሥር ወድቀው ቢለምኗት #እመቤታችን ተገልጣላቸው ‹‹ክፍልህ ምናኔ ነው፣ የአባትህ መንግሥት ያልፋል የልጄ መንግሥት ግን ዘላለማዊ ነው›› አለቻቸው፡፡ ጻድቁም ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሄደው በዚያው መንኩሰው ገዳሙን እያገለገሉ ተቀመጡ፡፡ ከጸሎታቸው በኋላ ራሳቸውን ወደ ባሕሩ ይጥሉ ነበርና አንድ ቀን እንዲሁ ራሳቸውን ወደ ባሕሩ ሲጥሉ መላእክት አውጥተዋቸዋል፡፡ አቡነ አላኒቆስ ወደ አክሱም እንዲሄዱ ታዘው ከሄዱ በኋላ በዚያም የጽላተ ሙሴ የታቦተ ጽዮን አጣኝ ሆነው 40 ዓመት ተቀምጠዋል፡፡ #እመቤታችንም ተገልጣላቸው በዓታቸውን እንዲያጸኑ ከነገረቻቸው በኋላ ከአክሱም ወጣ ብሎ የሚገኘውን ማይበራዝዮ ገዳምን መሠረቱ፡፡ በዚያም እጅግ አስገራሚ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እያስተማሩ አገልግለዋል፡፡

አንድ ቀን መኰንኑ ወደ ሩቅ ቦታ ሲሄድ ቤተሰባቸውን ለንስሓ አባታቸው አደራ ሰጥተው ሄዱ፡፡ የንስሓ አባታቸውም የአቡነ አላኒቆስ ጓደኛ ነበሩ፡፡ መኰንኑም ከሄዱበት ሲመለሱ ሚስታቸው ከአሽከሯ አርግዛ ጠበቀቻቸው፡፡ ‹‹ከማን አረገዝሽ?›› ብለው ጽኑ ግርፋት ቢገርፏት ዋሽታ ‹‹ያረገዝኩት ከንስሓ አባቴ ነው›› አለች፡፡ መኰንኑም መነኩሴውን እገላለሁ ብሎ ሲነሣ መነኩሴውም ወደ አቡነ አላኒቆስ ሄደው አለቀሱ፡፡ አቡነ አላኒቆስም የመኰንኑን ሚስት ቢጠይቋት ባሏን ፈርታ ‹‹አዎ ከመነኩሴው አባት ነው ያረገዝኩት›› አለች፡፡ እሳቸውም ‹‹የተረገዘው ከዚህ መነኩሴ ከሆነ በሰላም ይወለድ፣ ካልሆነ ግን አይወለድ›› ብለው በቃላቸው አስረውና ገዝተው ሸኟቸው፡፡

በግዝታቸው መሠረት ሴቲቱ ድፍን 22 ዓመት ሙሉ ሳትወልድ በጭንቅና በጣር ኖረች፡፡ በአልጋ ላይ ሆና ተጨንቃ ስትኖር በመጨረሻ ለቤተሰቦቿ ተናግራ ወደ አቡነ አላኒቆስ ዘንድ በቃሬዛ ወሰዷትና ይቅርታ ጠይቃ እውነቱን ተናገረች፡፡ እሳቸውም ‹‹#እግዚአብሔር ይፍታሽ›› ቢሏት 22 ዓመት ሙሉ ተረግዞ የነበረው ልጅ ትልቅ ሰው ሆኖ ጥርስ አውጥቶ፣ ፂም አብቅሎ በሰላም ተወለደ፡፡ እርሱም ከተወለደ በኋላ አባቱ ማን እንደሆነ ተናገረ፡፡ ጻድቁ አባታችንም ልጁን አሳድገውት አስተምረው አመንኩሰውታል፡፡ ስሙንም ተወልደ መድኅን አሉት፡፡ በስሙ የተሠሰራ ቤተ ክርስቲያን በትግራይ ጽንብላ ወረዳ ይገኛል፡፡

ጻድቁ አቡነ አላኒቆስ ሌላም የሚታወቁበት አንድ ግብር አላቸው፡፡ የማይበራዝዮ ገዳማቸው አገልጋይ የሆነው መነኩሴ በሬ ጠምዶ ሲያርሱ አንበሳ ከጫካው ወጥቶ አንዱን በሬ በላው፡፡ መነኩሴውም መጥተው ለአቡነ አላኒቆስ ነገሯቸው፡፡ እሳቸውም ‹‹ጸሎቴን እስክጨርስ ድረስ ወደ ጫካው ሂድና አንበሳውን ‹አላኒቆስ ባለህበት ጠብቀኝ እንዳትንቀሳቀስ ብሎሃል› ብለህ ተናገር›› ብለው ለመነኩሴው ነገሯቸው፡፡

መነኩሴውም እንደታዘዙት ወደ ጫካው ሄደው ጮኸው በሉ የተባሉትን ተናገሩ፡፡ አቡነ አላኒቆስም ጸሎታቸውን ሲጨርሱ ወደ ጫካው ሄደው አንበሳውን የበላውን በሬ አስተፍተውት በሬውን ነፍስ ዘርተውበት ከሞት አስነሥተው ዕለቱን እንዲታረስ አድርገውታል፡፡ አንበሳውንም ገዝተው ወደ ገዳማቸው ወስደው ሰባት ዓመት ውኃ እያስቀዱት እንዲያገለግላቸው አድርገውታል፡፡

አቡነ አላኒቆስ አንበሳውን አስረው ያሳድሩበት የነበረው ዛፍና ውኃ ያጠጡበት የነበረው ትልቅ የድንጋይ ገበታ ዛሬም ድረስ በገዳሙ ይገኛል፡፡ ከ22 ዓመት እርግዝና በኋላ ሴቲቱ ጥርስና ፂም ያለው ልጅ እንድትወልድ ያደረጉበት ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይም ከነቅርጹ በገዳሙ በግልጽ ይታያል፡፡ ጻድቁ ጥቅምት 21 ቀን ዐርፈው በዚያው በማይባራዝዮ ገዳማቸው ተቀብረዋል፡፡ ጸበላቸው እጅግ ልዩ ነው፣ ያላመነውን ሰው አስፈንጥሮና ገፍትሮ ይጥለዋል እንጂ አያስቀርበውም፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶች ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት_21 እና #ከገድላት_አንደበት)
🌹 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹

                          
🌹 ጻድቃን ሲባል በስንክሳር ላይ የተጻፉ ከመቶ ዓመታት በፊት የነበሩ በትረካ እና ገድል መልክ ብቻ እንጂ እውነት ዛሬ የሚፈጠሩ የማይመስሉን ስንቶቻችችን ነን? ዛሬ ዕረፍቷ የሚታሰበው ጻድቋ ሴት ሔራኒ ግን እንደኛ በመኪና እየተጓዘች በአውሮፕላን እየተመላለሰች በዘመናዊ አለም ኑራ በተአምሯ ብዛት አለምን አስደንቃለች እናም ዛሬ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከተነሱት ተአምር ሰሪ ጻድቃን አንዷ የሆነችው በተአምራቷ ብዛት የምታተወቀው የድሮ ካይሮ የአቡሰይፊን ወይም ቅዱስ መርቆሬዎስ የሴቶች ገዳም የበላይ ጠባቂ እና እመምኔት እማሆይ ጣማፍ ኡምና ኤሬን በ1999 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በክብር ያረፈችበት ቀን ነው። (ጥቅምት 21) በጣም በብዙ መጽሀፍ ከሚታተመው ተአምራዊ ህይወቷ በጥቂቱ እነሆ።

                         ✝️ ✝️ ✝️
🌹 #እመምኔት_ታማቭ_ሔራኒ(ሂራኒ)፦ በግብፅ አገር ልዩ ስሙ ጊርጋ በተባለ ስፍራ በየካቲት 2 ቀን 1929ዓ.ም በዘመነ ሰማዕታት ከአባቷ ያሳኼላ እና እናቷ ጄኔየፍ ማታ አል-ፌዚ  ተወለደች። የልደት ስሟ ፋውዚያ ይባላል፡፡ ይህች ቅድስት እንደ ሌላዉ ቅዱሳን በሰላም አልተወለደችም ማለትም እናቷ ከመጠን በላይ ነበር የታመመችዉ (እርሷን በምወትልድበት ጊዜ) በዚያ በጭንቅ ሰዓት አባቷ እና አያቷ ይፀልዮ ነበር አባቷ አምላክን ለወለደቸች ለክብርት እመቤታችን አያቷ ደግሞ ለሰማዕታት አለቃ ለቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲያማልዷቸዉ አጥቀብዉ ይጸልዮ ነበር ከዚያም አምላክን የወለደች ክብርት #እመቤታችን ቅዱስ ጊዮርጊስን አስከትላ መጥታ ለእናትዋ ተገለጸችላት ቅዱስ ጊዮርጊስንም "ጀርባዋን ዳስሰዉ" አለችዉ እርሱም እጅ ነስቶ ጀርባዋን ዳሰሰዉ በሰላምም ተገላገለች #እመቤታችንም ህጻኗን ታቅፋ "ይህች ልጅ የእኛ ናት" ብላ ህጻኗን ባርካ ወደ ሰማይ አረገች።

ከዚያም እያደገች በሄደች ቁጥር ለክርስቶስ ያላት ፍቅር እየጨመረ መጣ ሳታውቀውም ወደ ገዳም ለመሔድ ትናፍቅ ጀመረ እንደዚህ አይነት ፍላጎት የነበራት ገና የ8 ዓመት ልጅ በነበረችበት ጊዜ ነዉ፡፡የምትማረዉ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ነበረ በዚያም ደናግላን (ሴት መነኰሳይያት) ነበሩ እንደ እድሜ ጓደኞቿ መጫዎትን ትታ እነርሱን ታይ ነበረ እንድ ቀን በትምህርት ቤታቸዉ በሚገኝ የደናግላኑ ጸሎት ቤት ሔደች ከዚያም አንዷ የካቶሊክ ደናግል ስትጸልይ አገኘቻት ጸሎቷን እስክትጨርስ ቁጭ ብላ መጠበቅ ጀመረች ያቺ መነኩሲት ጸሎቷን ፈጽማ ወደ ተቀመጠቸዉ ቅድስት ሄዳ "ልጄ ምን ሆንሽ" አለቻት ቅድስቲቱም "እኔ እንደ እናንተ መነኩሴ መሆን እችላሁ?" ብላ ጠየቀቻት መነኩሲቷም "አዎን ትችያለሽ" አለቻት በመቀጠልም በመጀመሪያ "እኔ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ስለሆንኩ በራሴ ቤተክርስትያን ልቁረብና ከዚያም ልቀላቀላችሁ" አለቻት መነኩሲቷም መነኩሴ "መሆን ከፈለግሽ ትችያለሽ ግን መቁረብ የምትችይዉ በእኛ ቤተክርስትያን ነዉ ምክንያቱም የእኛ እምነት ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ይለያልና" አለቻት ቅድስቲቱም ታዲያ "የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ገዳማትን አላውቃቸውም" አለቻት መነኩሲቷም "እኔ እነገርሻለሁ ለምንኩስና የመሚያስፈልጉትን ነገሮች ምን ምን እንደሆኑ አስተምርሻሁ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትሽን እንድትለቂ አልፈልግም" አለቻት፡፡ መነኩሲቷም እንደነገረቻት በቤቷም ሆነ በቤክርስትያን ትጸልይ ነበረ በተለይም ጠዋት ጠዋት ደስ የሚል የቤተክርስትያን ዕጣን ይሸታት ነበረ ግን ይህ የሚሆነዉ ከቅዳሴ በፊት ነበረ፡፡ ይህ ነገር ያሳሰባት እናቷ ወደ ቤተክርስትያን ሄዳ ለካህኑ ነገረችዉ እርሱምም "ልጅሽ የተባረች ናት ያ የዕጣን ሽታ ሥውራን ባህታውያን በሚጸልዩት ሰዓት የሚሸት ነዉ" አላት፡፡

ከጥቂት ጊዜያት በኋላ እናቷ ታመመች ህመሙም የሚያነቃንቅ አልነበረም ይህንን የምታውቀዉ ቅድስቲቱ እናቷን አጽናንታ ወደ ቤተ-ክርስትያን ሄዳ አምላክን በወለደች በእመቤታችን ስዕል ፊት ቆማ መጸለይ ጀመረች " #እመቤቴ ሆይ እባክሽ እናቴን ፈውሻት እኛ ልጆችሽ ነን አምንሻሁ" ብላ ጸለየች። አምላክን የወለደች ክብርት #እመቤታችን ለእናቷ ተገለጻ እንዲህ አለቻት "ለምን ታቅሻለሽ" እናትየዋም "ልጆቼ ህጻናት ናቸዉ እኔ ከሞትኩ እግዚአብሔር እንደሚፈልገዉ ላያድጉ ይችላሉ
እባክሽን ከጌታ ፊት አማልጂኝ ታላቅ እህታቸዉ እስክታድግና ኀላፊነትን እስክትረከብ ድረስ" አለቻት አምላክን የወለደች ክብርት #እመቤታችን መልሳ "ከእኔ ጋር ነይ" አለቻት ከዚያም እናትየዋ ወዴት "እኔ ለባለቤቴ ሳልናር አልወጣም" አለቻት አምላክን የወለደች ክብርት #እመቤታችን መልሳ "አንቺ በባልሽ ቦታ ብትሆኚ ከ #ጌታ እናት ጋር ለመሄድ ደስ ይልሽ ነበረ" ብላ ወደ ሰማይ ይዛት ሄደች ከዚያም በመልካም መኝታ አስተኛቻት ከዚያም #እመቤታችን ቅዱስ ጊዮርጊስን "ጊዮርጊስ
እስኪ እያት መርምራት" አለችዉ እርሱም " #እናቴ_እመቤቴ_ሆይ እንደምታውቂዉ የእርሷ ጉዳይ አብቅቷል ድናለች" አላት ክብርት #እመቤታችንም "እኔ እንዳማልዳት ጠይቃኝ ነበረ እኔም ልመናዋን ተቀብዬ ለልጄ ለወዳጄ ነግሬዋለሁ አሁን ያለባትን ችግር ነቅለህ ጣልላት" አለችዉ ቅዱስ ጊዮርጊስም "እናቴ ያንቺ እጅ ይዳሳትና ከዚያ አወጣዋለሁ" አላት #እመቤታችንም ዳሰሰቻት ቅዱስ ጊዮርጊስም አውጥተቶ ለእናትየዋ "ይህንን ይዘሽ ወደ ቤትሽ ሂጂ" አላት፡፡

ቅድስት ኄራኒ ገዳም የመግባት ፍላጎቷ እየጨመረ መጣ ከዚያም ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተገለጸላት ስለእርሱም ሰምታ አታውቅም ነበረ እርሱም ራሱን ካስተዋቃት በኋላ ወደ ገዳሙ ወሰዳት ከወሰዳትም በኋላ ገዳሙን ሁሉ ካስጎበኛት በኋላ ወደ ቤቷ በደቂቃ መለሳት ገዳሙ ርቀት ነበረዉ የወሰዳትም በሕልም ሳይሆን በውን በፈረሱ ነዉ፡፡ #እመቤታችን ለእናትየዋ ተገልጻላት "ያኔ ስትወልጂ የኛ ነች ብየሽ አልነበረ አሁንም ወደ ገዳም ውሰጃት አለቻት" (ምክንያቱም አባቷ አትሄጂም ብሎ ስለከለከላት)፡፡


ገዳምም ገብታ የገዳም ኑሮ ጀመረች በዚያ ገዳም እማሆይ አፍሮዚና የምትባል ኢትዮጵያዊት ቅድስት መናኝ ነበረች እርሷም እንዳየቻት "ኢንቲ አልደብራ ረይሳ ደብራ አቡ ሰይፈን" አለቻት ትርጓሜውም "አንቺ የደብረ አቡ ሰይፈን ገዳም እመምኔት (አለቃ) ትሆኛለሽ" አለቻት (ግብፆች ቅዱስ መርቆሬዎስን አቡ ሰይፈን ብለዉ ይጠሩታል አቡ ሰይፈን ማለት የሁለት ሰይፎች አባት ማለት ነዉ፡፡) የበጎ ነገር ጠላት የሆነዉ ሰይጣን ቅድስቲቱን ይፈትናት ነበር እርሷም በ #ጌታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ ስም ታባርዉ ነበር #እመቤታችንም በየጊዜዉ ትጎበኛት ነበር፡፡ የተተነበየላት ነገር ደረሰ እመምኔት እንድትሆን በቅዱስ ቄርሎስ ስድስተኛ ተመረጠች እርሱም ፕትርክና ከመሾሙ በፊት አንድ ጊዜ አግኝቷት እመምኔት እንደምትሆን ነግሯት ነበር፡፡

ከዚያም ቅድስት ታማቭ ኢሪኒ "እኔ እመምኔት መሆን አልፈልግም" አለች በግድ ጎትተዉ ወደ ጳጳሱ ወስደዋት ተባርካ አስኬማ ለብሳ እመምኔት ሆነች እመምኔት ከሆነች በኋላ በግል ፀባዩዋ ላይ የታየ ለውጥ አልነበረም እንደድሮ ትሕትናዋን ለብሳ እናቶችን ታገለግል ነበር። የቅዱስ ፓኩሚየስን ( ጳኵሚስ) የገዳማዊ ኑሮ ሥርዓት እንደገና በሥራ ላይ እንዲውል ያደረገች ቅድስት ናት፡፡ ካለችበት ቦታ ወደ ፈለገችው ቦታ ልክ እንደቀደሙት ቅዱሳን ወዲያውኑ ሰከንድ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ትደርስ ነበር ገነት እና የተሰወሩ የቅዱሳን ያሉበትን ቦታ በየጊዜው ትጎበኝ ነበር። #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ቅድስት
#ውራ_ኢየሱስ ገዳምን የመሠረቱትና #ጌታችን ከገነት ዕንጨቶች የተሠሩ ታቦታት አምጥቶ የሰጣቸው ታላቁ ጻድቅ #አቡነ_ዮሐንስ ዘውራ #ኢየሱስ ጥቅምት 22 ቀን ዕረፍታቸው ነው።
+ + + + +
#አቡነ_ዮሐንስ_ዘውራ_ኢየሱስ፦ የአባታቸው ስም የማነ ብርሃን የእናታቸው ስም ሐመረ ወርቅ ይባላል።በመጀመሪያ እናታቸው ሐመረ ወርቅን ወላጆቿ ያለ ፈቃዷ ሊድሯት ሲሉ እርሷ ግን “ደብረ ሊባኖስ ሔጄ ከአባታችን ተክለ ሃይማኖትና ከሌሎቹም ቅዱሳን መቃብር ሳልባረክ አላገባም በማለት ነሐሴ 16 ቀን ወደ ደብረ ሊባኖስ ሔደች። በዚያም ሳለች አቡነ ተክለ ሃይማኖት በራእይ ተገለጡላትና የብርሃን ምሰሶ አሳይተዋት ይኸ ለአንቺና ለባልሽ ለየማነ ብርሃን ነው› አሏት። ይኽንንም ራእይ ለሰባት ቀን የገዳሙ አባቶችና አበ ምኔቱ አባ ዳንኤል አዩት። ከዚኸም በኋላ ባለጸጋውና ሃይማኖትን ከምግባር አስተባብሮ የያዘው የማነ ብርሃን ከዘርዐ ያዕቆብ ሀገር በ #እመቤታችን ትእዛዝ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሲመጣ አበ ምኔቱ አባ ዳንኤል የማነ ብርሃንን እና ሐመረ ወርቅን ኹለቱ ተጋብተው የተባረከ ልጅ እንደሚወልዱ በራእይ ያዩትን ነገሯቸው፤ ከዚኽም በኋላ በአባታችን በተክለ ሃይማኖት የዕረፍታቸው በዓል ዕለት ነሐሴ 24 ቀን ተጋቡ። እነርሱም በሃይማኖት በምግባር #እግዚአብሔርን ደስ አሰኝተው ሲኖሩ #እግዚአብሔር ልጅ ሰጣቸውና አቡነ ዮሓንስ ነሐሴ 24 ቀን ተፀንሰው ግንቦት 24 ቀን ተወለዱ።

የፈለገ ብርሃን ናዳ #ማርያም እና የክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም አበምኔት፣ የቅኔ፣ የትርጓሜ መጻሕፍት፤ የፍትሐ ነገሥት እና የባሕረ ሐሳብ መምህር የሆኑት ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ ይባቤ በላይ ከግእዝ ወደ አማርኛ የተረገሙት የአቡነ ዮሐንስ ዘውራ ኢየሱስ ገድል እንደሚናገረው ጻድቁ በሰባት ዓመታቸው ይኸችን ዓለም ንቀው የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ኹለተኛ ልጅ ወደሆነው አባ ጸጋ ኢየሱስ ዘንድ ሔደው 5 ዓመት እየተማሩ ተቀምጠው በ12 ዓመታቸው መነኰሱ። ከዚኽም በኋላ አቡነ ዮሐንስ ወደ ዋልድባ በመሔድ አባቶችን ማገልገል ጀመሩ። መነኰሳቱም ሌሊትና ቀን እንዲገለግሏቸው በሥጋ ቍስል ሁለንተናው
ለተላና ለሸተተ ግብሩ ለከፋ ለአንድ መነኵሴ ሰጧቸው። በሽተኛውም መነኵሴ አቡነ ዮሐንስን ይረግማቸው አንዳንድ ጊዜም ይደበድባቸው ነበር፣ ነገር ግን አቡነ ዮሐንስ በዚህ ከማዘን ይልቅ ደስ እያላቸው ያንን ሊቀርቡት የሚያሰቅቅ በሽተኛ በማገልገል ለዓመታት አስታመመ።

እንዲሁም የዋልድባ መነኰሳትን መኮሪታ በማብሰል፣ ቋርፍ በመጫር እና ዕንጨት በመልቀም፣ ውኃ በመቅዳት ገዳማውያንን ያገለግሉ ነበር። ከዕለታትም በአንደኛው ቀን በዋልድባ የሚኖር በክፉ በሽታ ተይዞ የሞተ አንድ መነኩሴ ሞቶ ሣለ ሽታውን ፈርተው መነኰሳቱ ለመገነዝ ፈሩ፡ ነገር ግን አበ ምኔቱ ለመገነዝ ወደ ውስጥ ሲገባ አቡነ ዮሐንስ አብረው ገቡ። አቡነ ዮሐንስም ወደሞተው መነኵሲ ቀርበው አቀፉት፣ በዚኸም ጊዜ ጥላቸው ቢያርፍበት ያ የሞተው መነኵሴ አፈፍ ብሎ ከሞት ተነሣና ከሞትሁ 3ኛ ቀኔ ነው አይቶ የጎበኘኝ የለም፣ ዛሬ ግን የ #እግዚአብሔር ሰው የገዳማት ኮከብ የቅድስት ውራ ገዳም መነኰሳት አባት፣ የማይጠልቅ ፀሓይ፣ የማይጠፋ ፋና ወደ ሰባቱ ሰማያት ወጥቶ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የ #ሥላሴን ዙፋን የሚያጥን አባታችን ዮሐንስ ባቀፈኝ ጊዜ ነፍሴ ከሥጋዬ ጋር ፈጽማ ተዋሐደች፤ አምላክን የወለደች #እመቤታችን_ማርያምም ንዑድ ክቡር ቅዱስ በሆነ በዮሐንስ ጸሎት ከሞት አስነሥቶ ሕያው አደረገህ አለችኝ› ብሎ ተናገረ። ዳግመኛም #እመቤታችን አባ ዮሐንስን ወደ ኢየሩሳሌም ሔደው እርሳቸውን ሲጠብቁ የኖሩትን ሦስት ታቦታት ያመጡ ዘንድ አቡነ ዮሐንስን እንዳዘዘቻቸው ተናገረ። በዚኽም ጊዜ የዋልድባ መነኰሳትና የገዳሙ አለቃ ለፍላጎታችን አገልጋይና ታዛዥ አደረግንህ ይቅር በለን ብለው ከእግራቸው ሥር ወድቀው ለመኗቸው። አባታችንም ‹‹አባቶቼ ሆይ! እናንተ ይቅር በሉኝ፡ ይህ የሆነው ስለ እኔ አይደለም፡ ስለ ክብራችሁ ነው እንጂ አሏቸው። መነኰሳቱም በትሕትናቸው ተገርመው እያለቀሱ ወደ ኢየሩሳሌም ሸኟቸው። በዚኸም ጊዜ አባታችን ዕድያቸው ገና 19 ነበር።

አባታችን ዮሐንስም ጎልጎታ ደርሰው ከቅዱሳት ቦታዎች ተባርከው ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔዱ። በዚያም 500 ዓመት የኖረ ኹለተኛ እንጦንስ የተባለ አንድ ባሕታዊ ኣገኙ። #እመቤታችንም አባ እንጦንስን ታቦተ ኢየሱስን፣ ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን እና ታቦተ ጽዮንን እያስጠበቀችው ይኖር ነበር። አባ እንጦንስም ኣቡነ ዮሐንስን ባገኛቸው ጊዜ በልቡ ተደስቶ በመንፈሱ ረክቶ በዐይኖቼ አንተን ያሳየኝ በጆሮዎቹም ቃልህን ያሰማኝ የአባቶቻችን አምላክ #እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፤ እመቤታችን #ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ጋር በእጇ የሰጠችኝን ያስጠበቀችኝን እነዚኽን ታቦታት ተቀበለኝ›› ብለው ሦስቱን ጽላት ‹‹ወደ ሀገርህ ይዘህ ሒድ›› ብለው ሰጧቸው። አባታችን ዮሐንስም ‹‹…እኔ እርሱ አይደለሁም እንዴት አወከኝ?› ሲሏቸው አባ እንጦንስም ፈገግ ብለው ከሞተ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት የሆነውን ሰው በጸሎትህ ከሞት ካስነሣኸው በኋላ ከሀገርሀ ከኢትዮጵያ ከዋልድባ ገዳም ከተነሣኽ ዘጠኝ ወር ነው፤ ይኸንንም የ #እግዚአብሔር መላእክት ነገሩኝ መምጣቱን ተስፋ የምታደርገው ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ከሀገሩ ዛሬ ተነሣ አሉኝ አሏቸው። አባታችን ዮሐንስም እመቤታችን #ማርያምን እንዴት አገኘሃት? አሏቸው። አባ እንጦንስም ከልጇ ከወዳጇ ጋር በብርሃን መርከብ ላይ ተቀምጣ መላእክት፣ ነቢያት፣ ሐዋርያት ጻድቃን፣ ሰማዕታት ሲከቧትና በክብር በምስጋና ሲሰግዱላት ግንቦት 21 ቀን በደብረ ምጥማቅ አገኘኋት አሏቸው። #እመቤታችንም ልጇን #ኢየሱስ_ክርስቶስን ፈቃድህን ለሚያደርጉ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለዓለሙ ሁሉ የመዳን ተስፋ ስጠኝ አለችው። #ጌታችንም ያንጊዜ መላእክትን ከገነት ዕንጨትና ዕብነ በረድ፡ ከጎልጎታ መቃብሩና ከጌቴሴማኒ አፈር እንዲያመጡ አዘዛቸው። መላእክትም የታዘዙትን አምጥተው በሰጡት ጊዜ #ጌታችን ከገነት የመጡትን ዕንጨትና ዕብነ በረድ ሦስቱን ታቦታት አድረጋቸው በማለት አባ እንጦንስ ለአባ ዮሐንስ ነገሯቸው።

አቡነ ዮሐንስም ሦስቱን ጽላት ይዘው አንዲት እንደፀሓይ የምታበራ ድንጋይ እየመራቻቸው ሰኔ 12 ቀን ጎጃም ደረሱ። ድንጋዩዋንም መንገድ እንድትመራቸው የሰጣቸው #ጌታችን ነው። ከዚያም ውሮ ተብሎ የሚጠራ አንድ ባላባት ቤት ገብተው አድረው በሚገባ ተስተናግደው በቀጣዩ ቀን ድንጋዩዋ እየመራቻቸው ቅዱሳን ከነበሩበት ጫካ ወስዳ አገናኘቻቸው። ቅዱሳኑም ለአቡነ ዮሐንስ የጠበቅንልህን ይኸችን ቦታ ተረከበን የዘለዓለም ማረፊያህ ናትና› ብለው እነርሱ ወደ ኢየሩሳሌም ሔዱ። አባታችንም ታቦተ #ኢየሱስን በዚኽች ገዳም ተክለው ቦታዋን መጀመሪያ በተቀበላቸው ሰው በውሮ ስም "ውራ #ኢየሱስ ብለው ሰየሟት።

ከዘጠኝ ዓመትም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል እየመራቸው ወደ ጣና ወስዶ ዘጌ አደረሳቸውና ታላቋን ዑራ #ኪዳነ_ምሕረትን ተከለ።