በዚያ ወራትም የግብጽ ንጉሥ አብዶ አልዓዚዝ ወደ እስክንድርያ ከተማ መጣ ይህ አባት ሊቀ ጳጳሳት ስምዖንም ሊቀበለው ወጣ ንጉሡም በሊቀ ጳጳሳቱ ፊት ላይ የደዌ ምልክት አይቶ መሳፍንቶቹን መልኩ እንዲህ እስኪለወጥ ድረስ ሊቀ ጳጳሳቱ ምን ደረሰበት ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም ክፉዎች ካህናት በእርሱ ላይ እንዳደረጉበት መርዝንም እንዳበሉት ነገሩት ንጉሡም ተቆጣ ካህናቱንና መሠርያኑንም በእሳት እንዲአቃጥሏቸው አዘዘ ያን ጊዜም ይህ አባት ከንጉሡ እግር በታች ወድቆ ይምራቸው ዘንድ እያለቀሰ ለመነው ንጉሡም አይደለም እንደሚገባቸው ያቃጥሏቸው እንጂ አለው። ይህም አባት ስለእኔ አንተ ከአቃጠልካቸው ለእኔ ክህነትና ሊቀ ጵጵስና አይገባኝም አለው። ንጉሡም ሰምቶ ከየዋህነቱና ከርኅራኄው የተነሣ አደነቀ እነዚያን ካህናትና መሠርዮች ከእስክንድርያ እንዲያሳድዷቸው አዘዘ።
ንጉሡም ይህን አባት እጅግ ወደደው አከበረውም እንደወደደም አብያተ ክርስቲያናትን ገዳማትን ይሠራ ዘንድ ፈቀደለት። እርሱም በምስር ሰሜን አልዋህ በሚባል አገር አብያተ ክርስቲያን ሠራ በሹመቱም ዘመን ሌሎች ብዙዎችን ሠራ።
ካደረጋቸው ተአምራቶቹ ሌላው ይህ ነው ሚናስ የሚባል አንድ ቄስ ነበረ ሙቶ ከተገነዘ በኋላ በዚህ አባት ጸሎት ተነሣ። የመነሣቱ ምክንያትም እንዲህ ነበር ይህ አባት ስምዖን በመላው አብያተ ክርስቲያናት ንብረት ንዋየ ቅድሳትና አልባሳት ላይ መጋቢ አድርጎ ይጠብቅ ዘንድ ቄሱን ሾመው። ሁልጊዜም የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ በቤትህ ውስጥ አታኑር እያለ ያዝዘው ነበር።
ከዚህም በኋላ ድንገተኛ ደዌ አገኘውና አንደበቱና ጒረሮው ተጣጋ። ሊቀ ጳጳሳቱም ሰምቶ እጅግ አዘነ ስለ አቢያተ ክርስቲያናትም ንብረት ያንን ቄስ ከሞት ያድነው ዘንድ በዚያች ሌሊት እግዚአብሔርን እየለመነ መላዋን ሌሊት ለጸሎት ተጋ።
መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ያ ቄስ ለመሞት እንደተቃረበ ይህ አባት ሰምዖን ሰማ ስለ አቢያተ ክርስቲያናት ነብረት ይጠይቃት ዘንድ አዝዞ ወደ ቄሱ ሚስት ረዳቱን ላከ።
ወደ ቄሱ ቤትም በቀረበ ጊዜ ሰዎች እያለቀሱለት ጩኸታቸውን ሰማ በገባ ጊዜም ሙቶ ልብሰ ተክህኖ መጐናጸፊያ ሲያለብሱት በዐልጋ ላይም ሲያስተኙት ብዙዎችም በዙሪያው ሲያለቅሱ አገኛቸው ያም ረዳቱ የቄሱን በድን ሊሳለም ዘንበል አለ። ያን ጊዜም ያ የሞተው ቄስ ተነሥቶ አቀፈውና የክቡር አባ ስምዖን ፈጣሪ እግዚአብሔር ሕያው ነው አለው። ረዳቱም በርታ አትፍራ አለው። ቄሱም በጌታው በአባ ስምዖን ጸሎት አዎ በእውነት ጸናሁ እግዚአብሔር ሕይወትን ሰጥቶ ከሞት አስነሥቶኛልና አለ።
ያን ጊዜም ያ ረዳት ስለ መሞቱ ደንግጠው የነበሩትን ካህናት እነሆ ቄሱ ከሞት ተነሥቷል ብሎ ጠራቸው። ካህናቱና ሕዝቡም ወደርሱ በቀረቡ ጊዜ ቄሱ እንዲህ አላቸው እኔ ሙቼ እንደነበረ ዕወቁ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ዙፋን ፊት አቆሙኝ ከአባት ሐዋርያ ማርቆስ እስከ አባ ይስሐቅ ያሉትን ሁሉንም የጳጳሳት አለቆች ክብር ይግባውና በክርስቶስ ዙፋን ፊት ቁመው አየኋቸው እኔንም ከወንድማችን ከሊቀ ጳጳሳት ስምዖን የአብያተ ክርስቲያናትን ንብረት ለምን ሸሸግህ ብለው ገሠጹኝ። ያን ጊዜም ጌታ ክርስቶስ ይቺን ነፍስ በውጭ ወዳለ ጨለማ ውሰዱአት ብሎ አዘዘ።
ሊወስዱኝም በጐተቱኝ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ዙፋን ፊት የጳጳሳት አለቆች ሰገዱ እንዲህ እያሉም ማለዱ ይህን ሰው አንድ ጊዜ ማረው ንብረታቸውን ስለሚጠብቅላቸው አብያተ ክርስቲያናት ብሎ ወንድማችን ስምዖን ስለ እርሱ እነሆ ቁሞ ይጸልያልና። ጌታችንም ልመናቸውን ተቀብሎ ነፍሴን ወደ ሥጋዬ መለሰ እንዲህም አለኝ እነሆ ስለ ምርጦቼና ስለ ወንድማቸው ስለ ሊቀ ጳጳሳት ስምዖን ማርኩህ አንተም የአብያተ ክርስቲያናትንም ንብረት ግለጥለት። አለዚያ ግን ወደዚህ እመልስሃለሁ የእነዚህንም ልመናቸውን ስለአንተ ሁለተኛ አልቀበልም።
በዚያ የነበሩም ሰዎች ይህን በሰሙ ጊዜ እጅግ አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ኀዘናቸውም ወደ ደስታ ተለወጠ ይህም ቄስ ይህን ተአምር ለሁሉ እየተናገረ ብዙ ዘመናት ኖረ።
ይህም አባት ስምዖን በበዐቱ ውስጥ በገድል የተጸመደ ሁኖ ኖረ መንጋዎቹንም ያስተምራቸው፣ ይገሥጻቸውና በቀናች ሃይማኖትም ያጸናቸው ነበር። ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ዘዮሐንስ_ጻድቅ_ዘክብራን_ገብርኤል (ኢትዮዽያዊ)
ዳግመኛም በዚህች ቀን ጣና ክብራን ገብርኤል ገዳምን የመሠረቱት አቡነ ዘዮሐንስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ይኸውም አባቱ ዘካርያስና እናቱ ሶፍያ #እግዚአብሔርን በማመን የተመሰገኑ ምግባር ሃይማኖታቸው የቀና ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ የሀገር ሰዎችም መክረው ዘካርያስን በእነርሱ ላይ ጌታና ገዥ አደረጉት፡፡ እርሱም በጥሩ አገዛዝ በፍቅር ገዛቸው፡፡ እነርሱም እንደ አሽከሮች ሆኑት፣ እርሱም እስከ አማራ ጠረፍ ድረስ ለሸዋ ሰዎች እንደ ቸር እረኛ ሆናቸው፡፡ ዘካርያስና ሚስቱ ሶፍያም በጎ ሥራን ሁሉ አላቋጡም፡፡ ምጽዋትን መስጠትን፣ ከገንዘባቸውም ከፍለው ለ #እግዚአብሔር አሥራት መስጠትን አላቋረጡም፡፡ የተቸገሩትን፣ የተራቡትንና የተጠሙትን ሁሉ ያበላሉ፣ ያጠጣሉ፡፡ ይህንንም ሲሄዱም ሲመለሱም ሁልጊዜ ያደርጋሉ፡፡
የ #ጌታችንን_የኢየሱስ_ክርስቶስንና የቅድስት #ድንግል_ማርያምን፣ የ #ጻድቃንና የ #ሰማዕታን መታሰቢያም ያድርጋሉ፡፡ ልጅም አልነበራቸውምና ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ይማፀኑ ነበር፡፡ ሶፍያም ጠዋት ማታ እንዲህ እያለች ትጸልይ ነበር፡- ‹መካን ለነበረች ለሐና ልጅ እንደሰጠኻት፣ ለአብርሃም ሚስት ለሣራም፣ ለጸጋ ዘአብ ሚስት እግዚእ ኀረያም እንደሰጠኻቸው አቤቱ እንደ እነርሱ አንተን ደስ የሚያሰኝህን ልጅ ስጠኝ› እያለች #እመቤታችንንም እየተማፀነች ታለቅስ ነበር፡፡ #እግዚአብሔርም መጥምቁ ዮሐንስን የመሰለ ልጅ ‹አባ ዘዮሐንስ› የተባለ ቅዱስ ልጅ ሰጣቸው፡፡ እሱም በሸዋ፣ በመራቤቴ እስከ አማራ ጠረፍ ድረስ የሚያበራ መብራት ሆነ፡፡››
በኋላም በጣና ሐይቅ ላይ የሚገኘውን ‹‹ክብራን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን›› የመሠረቱት እኚህ አባ ዘዮሐንስ የተባሉ ጻዲቅ ናቸው፡፡
ለአባ ዘዮሐንስ በጌታ ዘንድ ታዘው ነቢዩ ኤልያስና ዮሐንስ በእኩለ ሌሊት ተገልጠውላቸው አስኬማና ቆብ ሰጥተዋቸዋል፡፡ #እመቤታችንም ተገልጣላቸው ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደው እንዲመነኩሱ ነግራቸው ኤልያስና ዮሐንስ እየመሩ ከቦታው አድርሰዋቸዋል፡፡ ሰባት ዓመትም በዚያ ሲያገለግሉ ኖሩ፡፡ ስግደታቸውም ሁልጊዜ ስምንት ሺህ ነበር፡፡ ጌታም በደብሊባኖስ ሲያጥኑ ተገልጦላቸው ስምህ ‹‹ዘዮሐንስ ይሁን›› ብሎ ትልቅ ቃልኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ ደመናም ተሸክማ ወስዳ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም አድርሳቸው በዚያም ከቆዩ በኋላ ደመናዋ መልሳ ወደ ሸዋ አምጥታቸዋለች፡፡ በትግራይ ለራሳቸው መጠለያ ሲሠሩ የ #ጌታ ፈቃድ አልነበረምና ከባድ የሆድ ሕመም መጣባቸው፡፡ ደመናዋም ደራ ሮቢት አደረሰቻቸው፡፡ በዚያም እንደደረሱ ገብርኤልና መስቀል ክብራ በሚባሉ #እግዚአብሔርን በሚወዱ ደጋግ ባለትዳሮች ቤት ዕረፍት አደረጉ፤ ለሰባት ቀናትም በዚያ ቆዩ፡፡ ከዚያም መልአኩ ተገልጦ ወደ ደሴቷ እንዲሄዱና እርሷም ዕጣ ክፍላቸው እንደሆነች ነገራቸው፡፡