ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
197K subscribers
281 photos
1 video
16 files
209 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ወግ
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
🎯መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
☎️• 0922788490

📩@Eyos18
Download Telegram
😭ያልታጠበ እንባ😘

#የመጨረሻው ክፍል 3⃣6⃣

#ተከታታይ ልቦለድ

...ህይወቴ መስመር ያዘ ብዬ ማዉራት ስጀምር ግን ዝብርቅርቁ ወጣ! ቆይ እኔ መቼ ነዉ ችግር ማያጣኝ? አሁን እንኳን ከመጠን በላይ ሆነብኝ ነገር ሁሉ ከልኩ አያልፍም እየተባልኩ ነዉ ያደኩት ግን ታዲያ የኔ ሲሆን ነዉ ልኩ ሚያልፈዉ።

" ናቲ ከዳኒ ጋር ስትሳሳሙ በገዛ አይኖቼ አይቻለዉ ብሎ ምክንያት ፈጥሮ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ተለየኝ ። ፂሆንም በማላቀዉ ምክንያት ተጣላችኝ ሂወት ዉጥን ቅጦ ወጣችብኝ አቅጣጫዋን ቀየረች።

" ለሁሉም ወንድ አንድ አይነት አመለካከት ነዉ ያለኝ ሁሉም ጊዜ ለማሳለፊያዉ ብቻ ነዉ ሚፈልገኝ ብዬ እራሴን ወንድ ከተባለ ፍጡር ደብቄ ማኖር ጀመርኩ ።
"ለነገሩ ሴትም አልቀርብም.... ሰዉን እንደ አዉሬ ፈራዉ ሁሉም ሰዉ እኔን ለመጉዳት የተፈጠረ ይመስለኛል ወንድ በወንድ ይተካል ብለን ብናስብም የልብ ጓደኛ ግን በምን....?"

"እና ከናቲ በሗላ ወንድ እርሜ ብይ ተዉኩ ዳኒም ይሄን አጋጣሚ ተጠቅሞ እኔን ማገዝ ከጎኔ መሆን ሲገባዉ ግን እሱ ማንም የላትም ብሎ የፍቅር ጓደኛዉ እንድሆን ጠየቀኝ አይሆንም ስለዉ እሱም ድጋሚ ከጠገቤ እንደማይደርስ ነግሮ ተወኝ ።የእዉነት ዳኒ ወንድሜም እራቀኝ ?! "
"የሆነ ቀን ከመጠን በላይ ከፋኝ ሰዉ በሞላበት ሀገር ግን እኔ ሰዉ ራበኝ ብቸኝነቴ ኦና የሆነዉ ልቤ ሰዉ ናፈቀ የሆነ ማወራዉ ሰዉ ፈለኩ ብቻ ማንም ቢሆን ግድ አልነበረኝም ብቻ ሚያዳምጠኝ ይሁን! እና በሀሳቤ ዳኒ መጣ ምንም ሳላንገራግር ቶሎ ብዬ ደወልኩለት አያነሳም ብዙ ሞከርኩ በመጨረሻም አነሳልኝ ግን እኳ ያለጥፋቴ እሱም ጠልቶኛል ።
"ግን እኔ ሁሉን ረስቼ እንገናኝ አልኩት እንቢ አለኝ እንደህፃን እያለቀስኩ ለምኜዉ በስንተ መከራ ተስማምቶ ተገናኘን ግን እሱ በምላሹ ወንድነቱ ሊፈትንብኝም ፈለገ ያን ሁሉ ሚስጥሬን ነግሬዉ ስለሱ የቱን ነግሬ የቱን ልተዉ እእእ አንድ ሰሞን እነደዛ ሲሆንልኝ እሱን ማምለክ ነበር እኳ የቀረኝ እሺ የትኛዉ ወንድ ነዉ ለኔ ሚበጀኝ ለነገሩ የገዛ አጎቴ ልጅ ለኔ ያልተመለሰ ታዲያ ማነዉ ለኔ ...........?" ኧረ ማይሆነዉን በቃ ባጠቃላይ ወንድ የተባለ ፍጡር ጠላዉ ጠላዉ "
"ወንድ ልጅ አንዴ ተሳስቶ ካየኝ ሁሉ የተመኘኝ እየመሰለኝ ያ ቀኔ ይበላሻል ያየኝን ልጅ ስረግመዉ እዉላለዉ። ሁሌም ቢሆን የበፊት ሂወቴን እያስታወስኩ ማታ ማታ ማልቀስ ለኔ ኖርማል ሆኖ ቀጠለ ሳላለቅስ የተኛሁበት ቀን ትዝ አይለኝም ተሳስቼ እንኳን ከተኛዉ በማግስቱ ማታ ሁለት ድርብ ለቅሶ ይሆንብኛል ። "ታዲያ ማነዉ የኔን እንባ ሚያብሰዉ ያጓቴ ልጅ ተግባር ባረሳዉም ግን ላለማስታወስ እየሞከርኩ ነበር !" "ግን በዛ ህመሜ ላዬ ፂሆን ናቲ እና ዳኒን ማጣቴ በንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆነብኝ እነሱስ እሺ ግን ፂሆን እኔን መራቆ ሁሌም ማላምነዉ ነገር ነዉ ያዉም በማላቀዉ ጉዳይ ብዙ ጊዜ ላወራት ሞከርኩ ግን እድሉን ነፈገችኝ!
ከስንት አመታት በሗላ ወሬ ደረሰኝ ለካ አጅሬሆዬ ከፂሆን ጋር ከገዛ ጓደኛዬ ፍቅር ጀምሮ ነዉ ከኔ የራቀዉ ምን እሱ ብቻ እሷም ያለምክንያት የራቀችኝ ለዚሁ ነበር እኔም እስከ ዛሬ ያላወኩት ምንም ጓደኛ ስለሌለኝ ነበር በርግጥ እኳ የማስተዋል ችግር ነዉ እንጂ ብዙ ጊዜ አብረዉ መንገድ ላይ አይቻቸዋለዉ ግን እኔ በዚ መልኩ አላሰብኩም እንዴትስ የገዛ ፍቅረኛይ ከጎደኛዬ ኧረ ለማሰብም ሁሉ ይከብዳል
"ከዳኒ ጋር ምን አምን ያለኝ መራቂያ ሙዱ ነበር " እሷስ ብቶን እንደዛ እንደማፈቅረዉ እያወቀች እንዴት እንዲ ታደርጋለች ለካ ሰዉ በጥርሱ እየሳቀ በሆዱ ይቀብራል
"ማንም ማያዉቀዉ እዉነታዬ እሷን ናቲን እና ዳኒን ላለማስታወስ ብዙ ጣርኩኝ በብዙ ነገሮች ራሴን ደበኩ ግን ለካ አባባሉ እዉነት ነዉ የማይረሱትን ሰዉ ለመርሳት መሞከር ይበልጡን ማስታወስ ነዉ በማስታወስ ዉስጥ ትዝታ አለ በትዝታ ዉስጥ ብዙ ናፍቆቶች አሉ ግን ግን ናቲ በጓደኛዬ ቀየረኝ ያዉም ባመንኳት በገዛ ጓደኛዬ።
"ህይወት ሠንሰለት ናት አንዱ አንዱን ሲፈልግ ሚፈልገዉ ደሞ ሌላ ይፈልጋል ህይወት የማትፈታ ቅኔ ናት አንዱን ስንቀንስ ሌላዉ ምንተካበት ግን ከምንም በላይ ሀያል የሆነዉ ፍቅር ህይወት ነዉ ይሄን ሁሉ ነገር አንድ ላይ አቀናጅቶ የያዘ ሁሉም ሠዉ ልብ ዉስጥ ያለ ግን አዉቆ ለተጠቀመበት ብቻ ደስታን ምታጎናፅፍ።

#"ከአራት አመታትም በሗላ ሂወት ተለወጠች መልኳን ቀየረች ከብዙ ትግል በሗላ ሁሉንም በልቤ ይቅር ብያቸዉ ኑሮዬን ቀጥያለዉ "የጊቢ መግቢያ ፈተናን በጥሩ ዉጤት አጠናቀኩ "ግን እኔ ጊቢ መግባት አልፈለኩ ማሰብም አልፈልግም "እንደኔ በትላንት ሂወታቸዉ ታምቀዉ እና ታስረዉ ላሉ ሴት ወገን እህቶቼ መድረስ ስላለብኝ የ Psychology ( ስነ ልቦና ) ትምህርት መማር ስለፈለኩ ቤተሰቤም ተስማምተዉ በግል ትምርቴን መማር ጀመርኩ አላማዬ እኔ ላይ የደረሰዉ በሌላ ሴት ላይ እንዳይደረስ ብቻ አይደለም ሂወቴን ይፋ እያወጣዉ ከኔ ሂወት የትኛዉም ሰዉ ተምሮ አሁን ያለበት ማንነቱ ላይ ቆሞ ራሱን እንዲፈትሽ ነዉ እና psychologist መሆኔ የማይቀር ነዉ ይቅናሽ ይሳካልሽ በሉኝ በፊት እናት እና አባቴ በልጃቹ በቤኑ ድረሱ እያሉ ሲመርቁ ምፈራ የነበርኩ ልጅ ግን ዛሬ ላይ የምርቃቱ ተቆዳሽ አሚን ባይ የመጀመሪያዋ ሆኛለዉ አሁን ላይ I'm 2nd year psychology student

"የባለታሪኮ መልክት" 👇

#ወንድ ልጅ እንደ #ጭቃ ሴት ልጅ ደሞ #እንደ መስታወት ናት። መስታወት አንዴ ከተሰበረ ለመጠገን ቢሞከር እንኳን የቀድሞዉን ይዞታና መልክ ሊይዝ አይችልም #ጭቃ ግን አሁን ያለበትን ቅርፅ እና መልክ መያዝ ይችላል !!!። ሴቶች ዛሬ ላይ #እንደቀልድ ወይ # ለሙድ በሚል የጓደኛ ግፊት የምናደርጋቸዉ ልክ ያልሆኑ ነገሮች የነገ ሂወታችን ላይ ከባድ የሚባል ችግር ሲፈጥርብን አስተዉያለዉ የሚገርመዉ ነገር ልክ እንደተሰበረዉ መስታወት ያሳለፍናቸዉ ጥሩ የማይባሉ ነገሮች ሙሉ በሙሉ አድሰዉ በአዲስ ማንነት ለመኖር ብናስብም ቀድም ብለን ይዘነዉ የነበረዉ ጥሩ ያልሆኑ ማንነት እና ስም በማህበረሰቡ እይታ ዉስጥ አሻራ ጥሎ ስላለፈ ያሁኑን አዲስ ማንነት አሚን ብሎ ለመቀበል ይቸግራል
ወንድ ጋር ስንመጣ ደሞ እንደሴቶ አልያም ከሴቶ በላይ ጥሩ የማይባሉ ነገሮች ሰርቶ የሆነ ሰአት ላይ ያን ማንነት መቀየር ቢፈልግ አንደጭቃዉ እንደገና ፈርሶ ወደሚፈልገዉ አይነት ማንነት እና ስም ቅርፁን መቀየር (መለወጥ)ይችላል በተጨማሪም
#ማህበረሰቡ ከወንድ ይልቅ ሴት ላይ ነገር ማጥበቅ ስለሚወድ በወንድ የሚደረጉ ነገሮችን ያን ያህል ትኩረት ሰቶት አያያቸዉም ሴት ስታደርገዉ ግን ወደቀ ሲባል ተሰበረ ነዉና ነገሩ
ሴቶችዬ ዛሬ ላይ እንደቀልድ ባለማስተዋል የምታደርጎቸዉ ነገሮች የነገዉ #የትዳር _ሂወታችሁ ላይ እንቅፋት ሆኖ መንገድ እንዳያበላሽባቹ ዛሬ ላይ በቆማችሁበት ማንነት #ነጋችሁን ፈትሹት !🙏🙏🙏። ብልህ የሆነ ሰዉ ከኔ ህይወት ይማር🙏


#


ስለድርሰቱ ያላቹ ወይ ደግሞ የተሰማቹ አስተያየት ሁሉ በዚ አድርሱኝ👇

🎙ግሩፑን ለማግኘት

@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha

❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
#የአና ማስታወሻ የመጨረሻው ክፍል
Join on telegram @Eyosc1
👩‍🦰የአና ማስታወሻ

#የመጨረሻው ክፍል 1⃣6⃣
ተርጓሚ አዶኒስ,
🎙ተራኪ ዩሐንስ የዝና

👩‍🦰የ15 ዓመት ልጃገረድ የሆነችው የአና ፍራንክ ዲያሪ

🎙ግሩፑን ለማግኘት👇

@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
📝ያልፋል

#የመጨረሻው ክፍል

#ክፍል፡-2⃣4⃣

#ፀሀፊ፡- ሂራ

አቡኪ ሽማግሌ ልኮ ኒካህ ካሰርን ሁለት ሳምንት ሆነን፣ የአቡኪ እናት ስለሁሉም ነገር አፉታን ጠይቃኛለች፣ ትምህርቴንም እንደምቀጥል ተነጋግረናል፣ እነ እማማ ደግሞ የተሻለ ቤት ባዶ ግቢ ተከራይቶላቸው እዛ ውስጥ ይኖራሉ፣ እኔም እየኖርኩበት ነው ግን ከሳምንት ቡሀላ እቀይራለው ከኸውሊ ጋር ቬሎ በስንት መከራ መርጠን ቀብድ ሰጥተን መጣን፣ ሲትሩዬም ሚዜዬ ሁና ልታጅበኝ ነው አልሀምዱሊላህ የሚዜም ልብስ መረጣ መከራ ነው፣ ከወንዶች ጋር ማች መግጠም አለበት በሚል መከራችንን በላን፣ ደግሞ ሂና የሚባልም ታሪክ አለ፣ የሰርግ ሽርጉድ በጣም ነው የሚያደክመው፣ ብቻ አልሀምዱሊላህ ከዛ አጣብቂኝ ህይወት አውጥቶ ለዚህ ያደረሰኝ ጌታ ምን ይሳነዋል፣ ሳሚ ጋርም አውርተን ነበር እኔ በማላውቀው መንገድ ሌባ ተብዬ ለካ ሌባዋ የበፊት ፍቅረኛው ናት መቼም ይህን ወሬ የሰማችሁት ይመስለኛል፣ ያም ሆኖ ይህ ሁሌም እኔ አጣራልሀለው የምትለው አልዋጥ ብሎት ለማጣራት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሲሄድ የገጠመው ነገር ሌላ ነበር ፖሊሶቹን በብር አፍ አዘግታቸው እንጂ ስራው የራሷ ነበር
ይህን ለማወቅ ረዥም ግዜ ቢወስድበትም ግን አውነቱን ለማወቅ ችሏል፣
<<አንቺ ኢሉ አትመርጪም እየጠበቅንሽ እኮ ነው>> ኸውሊ ኡዱ ላድርግ ብያት ወጥቼ ነው ከናንተ ጋር የማወራው ዛሬ ቅዳሜ የሂና ቀኔ ነው ሰዎች እየጠበቁኝ ነው፣ ቻው ደግሞ ለሰርጌ ሁላችሁንም ጠርቻቹሀለው መቅረት የተከለከለ ነው ቻው በቃ መቼም ማውራት ከጀመርኩ አላቆምም ኧረ በቃ ቻው፡፡
*
<<ምን ያክል ደስታ እንደሚሰማኝ አታውቅም፣ በደስታህ ተደስቻለው ትዳራችሁን የአብረሀም እና የሳራ ያድርግላችሁ>>
<< አሚን ሳሚ እና ለምን አታድርም>>
<< አላድርም ባይሆን ነገ በጠዋት ካሜራ ማኖችን ይዤ እመጣለው>>
<<እሺ ሳሚዬ ሹክረን በጣም>>
<< ወንድም ወንድሙን አያመሰግንም ግዴታዬን ነው የተወጣሁት>>
<<እሺ እና ልሸኝህ>>
<< እንዴ ሙሽራው አርፈህ ተቀመጥ እንጂ ሙሽራ እኮ አርፎ ሲቀመጥ ነው የሚያምርበት>>
ሳሚ በጣም ጥሩ ሰው ነው፣ እኔ በጣም ብዙ ጓደኞች አሉኝ የሳሚን የሚደርስ ግን አላየሁም አላህ ሂዳያ ሰጥቶት ይህ ጓደኝነታችን ጀነት ቢዘልቅ ደስታዬ ነው፣ እናንተም ዱዓ አድርጉለት
ነገ እሁድ የልቤን ንግስት ወደ ቤቴ አመጣታለሁ፣
ስሙኝማ አንድ ሚስጥር ልንገራችሁ ኢሉን አሁን ሳይሆን ገና ድሮ ከማገገሚያ ሳትወጣ ነበር በልቤ የፈለኳት ግን መናገር ማውጣት አልቻልኩም ምክንያቱም የምረዳት የራሴን ጥቅም ለማስበለጥ ይመስልብኛል ብዬ ነው፣ሆነም ቀረ ግን አሁንም አልቀረችብኝም ሁል ግዜ የምጨቀጭቀው ኢላሂ ግዜው ሲደርስ መልስ ሰቶኛል፡፡አልሀምዱሊላህ
<<አንበሳው ውጪ ላይ ብቻህን ምን ትሰራለህ>> አባዬ ነበር
<<አይ ምንም ሳሚን ሸኝቼው እየተመለስኩ ነው>>
<<በል ግባ ደግሞ ብርድ መቶህ ነገ በሰርግህ ቀን እንዳትታመም ጓደኞችህም ውስጥ እየጠበቀህ ነው>>
<<እሺ አባ መጣሁ ግባ>>
መቼም ሴቶችን ኢሉ ጠርታለች ወንዶች ደግሞ እንዳትቀሩ ሁላችሁም ተጠርታቹኋል፣ምን ምን "የቤትህ አድራሻ"ነው ብላችሁ ስትንሾካሾኩ የሰማሁት፣ #ጥበብ_ኢስላም ወይም @tibebislam_nw ብላችሁ ሰርች አድርጉና ግቡ አድራሻዬን ታገኛላችሁ ለማንኛውም ነገ መቅረት የተከለከለ ነው ቻው ሰዎች እየጠበቁኝ ነው፣ መቼም ከናንተ ጋር ውዬ ወረኛ ሁኛለው ቻው "መልካም ጋብቻ" ነው ያላችሁኝ ኸረ በእስልምናው ባረከላህ በሉኝ
*
ኢሉና አቡኪ ባረከላህ ለኩማ ወባሪክ አለይኩማ ወጀመዓ በይነኩማ ፊል ኸይር ብለናል ያማረ የተዋበ ኢማን የሞላው መተሳሰብ እርስ በእርስ መደጋገፍ አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ ተባብላችሁ የምትኖርበት ትዳር ያርግላችሁ፡፡
*
ህይወት ብዙ አይነት መንገድ ነው ያላት ፣ ሁሉም ሰው በመረጠው የህይወት መንገድ ለመጓዝ ይጥራል ግን ሁሉም ሰው እራሱ ባሰበውና በመረጠው ሳይሆን አላህ በፃፈለት መንገድ ይሄዳል ህይወት ብዙ መሰናክሎች አሏት ያንን መሰናክል ያለፈ አማረለት የወደቀ ግን በዛው የህይወት መሰናክል ህይወትን ይጨርሳል፣ ኢሉም ሆነች አቡኪ የህይወት መሰናክሎቻቸውን ለማለፍ ቢቸገሩም የማያልፍ ቢመስላቸውም ግን በራህማኑ እዝነት መከራዎችን አልፈው የደስታን ህይወት ለመኖር 1 ብለው ጀመሩ፡፡
አላህ ለሁላችንም የተስተካከለ ያማረ ህይወት ይስጠን
አሚን ያረበል አለሚን!!


~~~~~~~ተፈፀመ~~~~~!!!

#አስተያየታችሁን comment ላይ አስቀምጡልን በሌላ ታሪክ እስክንገናኝ ሰላም ቆዩልኝ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
❇️ኢማን

#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሠረተ

#ክፍል_9

ወደ 7 ሰአት ገደማ ሰርገኛ መጣ በእልልታም ተቀበሉት። ምሳ ተበላ ተጨፈረ ኒካም ታሰረ ብናይ አይወጡም ብናይ አይወጡም። የሆነ የሰፈር ህፃን ልጅ መጣና በጆሮዬ " ልክ ቀለበቱን እጅሽ ላይ ሲያጠልቅ እኔን ከልብሽ አውጥተሽ አትጣይኝ ሁሌም አኑሪኝ" የሚል ከ ሀምዛ የተላከ መልእክት ነበር ውስጤ ተረበሸ ግራ ገባኝ እያለቀስኩ ሳለ የ አባ ወንድም አጎቴ መጣ
"እ ኢሙ ተበላ ተጠጣ መዝናኛ እንሂድ እየተባለ ነው ፎቶ ተነስታቹ አመሻሽ ላይ ትመለሳላቹ" ምን ትዝ አለኝ አንዷን ጓደኛችን እንዲህ ብለው ማይሆን ነገር ሰርተዋታል ማለት ወሰዷት እቤታቸው የሷ በቤተሰብ ቢሆንም ወዳዋለች ግን እኔስ?? ሃሃሃሃ በጣም ትሸውዱ የለም እንዴ በል ንገራቸው እንዳልተስማማው
"አረ እንደሱ አያደርጉም ካደረጉማ 20,000 አስይዘናል ይቀጣሉ" ታድያ ለኔ ምን ያደርግልኛል ከሄድኩ በኋላ እናንተ ትበሉበታላቹ ትጠጡበታላቹ በቃ🤷‍♀ ሲያቅተው አብዱን ጠራው ያው ቀረቤታዬም ከሱ ጋር ስለሆነ ምንም ቢለኝም አምነዋለዋ።
እ አብዱ የሚለው እውነቱን ነው?
"አዎ እውነቱን ነው" አለኝ አይ እንደሱ ከሆነማ እሺ ብዬ ስነሳ ዘወር ብሎ በምልክት እንቢ በይ አለኝ አረ አልፈልግም አልሄድም አልኩ ድጋሜ አጎት ተብዬው ተናዶብኛል ከፈለጋቹ እነሱ ከሄዱ በኋላ እኛ ሄደን እንዝናናለን አልኩት።

እንደዚህ እየተከራከርን 12 ሰአት ሆነ እነ ሀምዛ ቤት ተረብሸዋል ይሄ ነገር የምር እዚህ የሚደርስ አልመሰላቸውም ነበር ማዘርየው አልመጡም መረጃ የሚያመላልስ አለ ከኔ ወደነሱ ከነሱ ወደ እኔ መጨረሻ ላይ ጀማልን ጥሩልኝ ብዬ መጣ።
ቆይ ግን ያምሀል ምን ብላቹ ነበር መጀመሪያ እእእእ
"አንቺ ራሱ ምንድነው የምትይው እኔ ትምህርትሽን ስትጨርሺ እና የማስተካክላቸው ነገሮች አሉ ስጨርስ ብዬሽ አልነበር በአንዴው ምን ተለውጦ ነው ካልወሰድከኝ የምትይው"??
በጣም ደነገጥኩ ምን እንደሚያወራ ራሱ ግራ ገብቶኛል በሰአቱ ለካ ይሄን ሁሉ የሚጠነስሱት የኔ አጎት እና የሱ አባት ነበሩ። አባ እና እማ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም የሱ አባት ልጅቷን ይዘን ካልሄድን ከዚህ ንቅንቅ አንልም አሉ አማም አባም ግራ ተጋብተዋል እኔን ተነሽ ሂጂ እንዳይሉ እጎዳባቸዋለው የመጣውንስ ሽማግሌ እንግዳውን ምን ብለው ተነስታቹ ውጡ ይላሉ? ተያይዘው ወጥተው መስጊድ ሄደው ማልቀስ ጀመሩ። ህዝብም ደሞ መጨረሻውን ሳናይ ንቅንቅ አንልም ብለዋል መሰለኝ የሚወጣም የለም በቆሙበት እርስ በእርሳቸው ይንሾካሸካሉ ትወጣለች አትወጣም የሚለውን በመሀል አባን ጥሩልኝ ስል ነው እንደሌሉ ያስተዋልኩት
ቆይ በአላህ ከኔ ከልጃቸው ሽማግሌ በልጦባቸው ነው የሸሹት? እ ለምንድነው መተው ማያባርሩልኝ ሁሉም እኔን እያየ የሚያለቅስ እንጂ ምንም የሚለኝ ጠፋ።

ማንም ከጎኔ ሊቆም አልቻለም ነበር መጨረሻ ላይ ተሸነፍኩ የተሸነፍኩትም አብዱ መጣና ይዞኝ ባዶ ክፍል ገብተን እንዲህ አለኝ
"በቃ ኢሙ አልቻልኩም ወላሂ ብዙ ጣርኩ አቃተኝ ከዚህ በላይ ምን ላርግልሽ እእ "ስቅስቅ እያለ ነበር የሚያለቅሰው
በቃ አብዱ አንተም ተሸነፍክ ምንም ተስፋ የለኝም ማለት ነው ከጎቴ በሩን እየቀጠቀጠ አንተ ነህ ልጅቷን የምትመክራት ተዋት ትሂድበት ይለዋል
"ኢሙ ሰማሽ አይደል ሁሉም እኔን እየወቀሱኝ ነው ኢሙዬ ከዚህ በላይ መታገል አልችልም ይቅርታ"እያለ እግሬ ስር ወደቀ
የኔ የ ኢማን ህይወት እዚህ ጋር አበቃ ማለት ነው እንጫወታለን ብለን ተጫወቱብን አይደል? አቅፌው መንሰቅሰቅ ጀመርን።


#የመጨረሻው_ክፍል10_.........
#የሚለቀቀው ከታች ባለው ግሩፓችን አድ ስታደርጉ ነው (Add Member) ሁላችሁም የተቻላችሁን Add Member አድርጉ🙏

#Add_Member_ለማድረግ👇
@Mtshaf_bicha

🎙ግሩፑን ለማግኘት
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha

❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉
┉┄
🔊ዴንግ ሻኦፒንግ #ክፍል 4
Join @Eyosc1 on telegram
ዴንግ ሻኦፒንግ

#የመጨረሻው ክፍል

#የሀገርና የልጅ ዋጋ ስንት ነው?»

#ክፍል 4⃣

🎙ግሩፑን ለማግኘት
👇👇👇
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሃምሳ_አንድ

#የመጨረሻው ክፍል

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ጎረምሳውና ጆ ውሃ ውስጥ እየሰጠሙ ስታይ ጮኸች፡፡
ወጣቱ ልጅ ወደ ላይ ለመውጣት ሲሞክር ጆ ደግሞ ህይወቱን ለማትረፍ ወጣቱን ወደ ታች ይጎትታል፡፡ በጣም አስፈሪ ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡
ማርጋሬት መጮኋን ሰምቶ ሉተር በመስኮት ተመለከተና ‹‹ባህሩ ውስጥ ወድቀዋል››› ሲል ጮኸ በጭንቀት፡፡

‹‹እነማ ናቸው?›› አለ ቪንቺኒ፡፡

‹‹ጎረምሳውና ጆ›› አለ ሉተር፡

የጀልባው ነጂ ገመድ ቢወረውርላቸውም ሁለቱ ሰዎች አላዩትም፡፡ እነሱ
የሚይዙትን አጥተው በፍርሃት ውሃ ውስጥ እየተንቦራጨቁ ሲሆን ጆ
ጎረምሳውን ልጅ ወደ ባህሩ ውስጥ እየደፈቀው ነው፡፡

‹‹እባክህ እርዳቸው›› አለ ሉተር እሱም በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ፡፡

‹‹ምን?›› አለቪንቺኒ ‹‹ምንም ልንረዳቸው የምንችለው ነገር ያለ
አይመስለኝም፡ እነሱም ራሳቸውን ለማዳን አቅም የላቸውም፡፡›› በመጨረሻም
ሁለቱን ሰዎች ጨካኙ ባህር ሰለቀጣቸው፡

‹‹እንዴት ሊሆን ቻለ?›› ሲል ጠየቀ ሉተር ‹‹በመጀመሪያ ውሃ ውስጥዐእንዴት ሊወድቁ ቻሉ?››

‹‹ምናልባት የሆነ ሰው ገፍቷቸው ይሆናል›› አለ ቪንቺኒ፡

‹‹ማን?››

‹‹እዚህ አይሮፕላን ውስጥ የሆነ ሌላ ሰው ይሆናል፡›› ማርጋሬት የሁለቱን ሰዎች ንግግር ስትሰማ ስለነበር ሄሪ ሊሆን ይችላል› ስትል
ገመተች፡ ሄሪ ጀልባው ውስጥ ይኖር ይሆን?
ፖሊሶቹ አይሮፕላኑን
ሲፈትሹ እሱ የሆነ ቦታ ተደብቆ አይሮፕላኑ ባህሩ ላይ ሲያርፍ ከተደበቀበት
ወጥቶ ይሆን? ሁለቱን ወሮበሎች ውሃ ውስጥ ገፍቶ የጨመራቸው እሱ
ይሆን? እያለች መልስ የሌለው ጥያቄ በአዕምሮዋ ተጉላላ፡፡

በኋላ ደግሞ ወንድሟ ትዝ አላት ፔርሲ የወሮበሎቹ ጀልባ ከአይሮፕላኑ ጋር በሚታሰርበት ጊዜ ነው የጠፋው፡፡ ‹ምናልባትም መጸዳጃ ቤት ሄዶ ግርግሩ እስኪያልቅ እዚያው ሊቆይ አስቦ ይሆናል› አለች በሆዷ፡
እሱ ደግሞ እንዲህ አይነት ባህሪ የለውም፡፡ እሱ እንደውም ሁሉን ነገር
ለማወቅ ስለሚፈልግ ችግር አይፈራም፡፡

ሉተር ‹‹ሁሉ ነገር ከእጃችን እየወጣ ነው ምን ብናደርግ ይሻላል?›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹አሁን በመጣችው አይሮፕላን እንሄዳለን እንዳቀድነው፡፡ አንተ፣ እኔና
ሳይንቲስቱ›› አለ ቪንቺኒ፡ ‹‹መንገዳችንን ሊያሰናክል የሚሞክር ሰው ካለ
በሆዱ ጥይት ልቀቅበት፡ አሁን ረጋ ብለን እንውጣ፡፡››
ማርጋሬት ወሮበሎቹ ፔርሲን ደረጃው ላይ ያገኙትና በሆዱ ጥይት
ይለቁበታል ብላ ሰጋች፡
ሶስቱ ሰዎች ከምግብ ቤቱ ሲወጡ የፔርሲ ድምጽ ከበስተኋላቸው
ተሰማ፡፡ ድምጹንም ከፍ አድርጎ ‹‹እንዳትነቃነቁ!›› አለ፡፡
ፔርሲ ቪንቺኒ ላይ ሽጉጡን መደገኑን ስታይ ማርጋሬት ዓይኗን ማመን አቃታት፡፡ የሽጉጡን አፈሙዝ አይታ ካፒቴኑ ከኤፍ.ቢ.አዩ ሰውዬ
ላይ የነጠቀው መሆኑን ገመተች፡

ቪንቺኒ ቀስ ብሎ ወደ ፔርሲ ዞረ፡፡

ማርጋሬት የወንድሟ ህይወት አደጋ ላይ ቢሆንም በፔርሲ ኮራች፡፡

የመብል ክፍሉ በሰው
ተሞልቷል፡፡ ከቪንቺኒ ኋላ ማርጋሬት ከተቀመጠችበት አጠገብ ሉተር በሃርትማን ላይ ሽጉጡን ደግኗል፡ በሌላኛው በኩል ናንሲ፣ መርቪን፣ ዳያና፣ ኤዲ እና ካፒቴኑ ቆመዋል ቪንቺኒ ፔርሲን ዘለግ ላለ ጊዜ አየውና ‹‹ልጅ ከዚህ ጥፋ›› አለው፡፡

‹‹ሽጉጥህን ጣል!›› ሲል ፔርሲ አዘዘ፡፡

በመሃል አንድ ጥይት ጮኸች፡፡ የጥይቱ ድምጽ ጆሮ ያደነቁራል፡
ማርጋሬት ጩኸቷን አቀለጠችው: ማን ማን ላይ እንደተኮሰ አላወቀችም:: ፔርሲ ምንም አልሆነም፡፡ ትንሽ ቆይቶ ቪንቺኒ ከደረቱ ላይ ደም እየተንፎለፎለ ተንገዳገደና መሬት ዘፍ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ቦርሳው
ሲወድቅ ተበረገደና ብሮቹ በደም ታጠቡ፡

ፔርሲ ቪንቺኒን ሲያይ ሽጉጡን ጣለ፡፡ ደንግጧል፡
ሁሉም ሰው ሽጉጥ የያዘው የመጨረሻው ወሮበላ ላይ አፍጧል፡

ካርል ሃርትማን በተፈጠረው
ሁኔታ ከተዘናጋው ሉተር መንጭቀው ራሳቸውን ነጻ አደረጉና መሬት ያዙ ማርጋሬት ሳይንቲስቱን ይገድላቸዋል ብላ ሰግታለች ፔርሲንም እንዲሁ፡ ነገር ግን ወዲያው የሆነው ግን
አስደንግጧታል፡፡

ሉተር አፈፍ አድርጎ ያዛት፡ ከወንበሯ ጎትቶ አነሳትና ጭንቅላቷ ላይ ሽጉጡን ደገነባት፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉም በድንጋጤ በድን ሆኑ።

ማርጋሬት ፍርሃት ስለገባት መንቀሳቀስ መጮህ አልቻለችም፡ የሉተር
ሽጉጭ ጭንቅላቷን እየወጋት ነው፡ ሉተር ራሱ ይንቀጠቀጣል፡፡ ከዚያም
ሳይንቲስቱን ‹‹ውጣና ጀልባ ውስጥ ግባ፡፡ ትዕዛዜን ካልፈጸምክ ልጅቷ
ጭንቅላት ላይ ጥይት እቀረቅርበታለሁ›› አለ፡፡
ወዲያው ፍርሃቷ ሲለቃት ታወቃት፡፡ ሉተር  ብልህ መሆኑን ተገንዝባለች፡፡ ሽጉጡን ሃርትማን ላይ ደግኖ ቢሆን ኖሮ ሃርትማን ግደለኝ ጀርመን አገር ከምመለስ ሞቴን እመርጣለሁ› እንደሚሉ እርግጠኛ ሆኗል፡ አሁን ግን የእሷ ህይወት አደጋ ላይ ነው፡ ሃርትማን ምናልባት
ህይወታቸውን ለመስጠት ዝግጁ ይሆኑ
ይሆናል፡፡

ሃርትማን ቀስ ብለው ተነስተው ቆሙ፡፡

ሁሉም ነገር በማርጋሬት ላይ የተጣለ ነበር፡ ራሷን ሰውታ ማዳን ትችላለች፡ ሆኖም ይህ አድራጎት ጥሩ አይደለም፡፡ እሷም ይህን አደርጋለሁ ብላ አልጠበቀችም፡፡ ለዚህ ራሴን አላዘጋጀሁም፡፡ ማድረግ አልችልም› አለች
በሆዷ፡
ከአባቷ ጋር ዓይን ላይን ግጥም አሉ፡፡ አባቷ በጣም ደንግጠዋል ሲያበሻቅጧት እንደኖሩ ምን ያህል
አቅመቢስ እንደሆነች ጦሩንም ተቀላቅላ አንድ ቀን እንኳን እንደማትቆይ
የነገሯት ሁሉ ትዝ አላት፡፡
አባቴ ያለው እውነት ይሆን?› አለች ለራሷ፡
ስለዚህ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባት ወሰነች፡፡ ሉተር ሊገላት ይችላል ነገር ግን አንድ ነገር ከማድረጉ በፊት ሌሎች ሰዎች ዘለው ይረባረቡበታል ጊዜው እየሄደ ነው፤ አንድ ነገር ማድረግ አያቅተኝም, አለች በሆዷ፡

ከዚያም ‹‹ሁላችሁም ደህና ሁኑ›› አለች፡፡ አፍታም ሳይቆይ የሄሪን ድምጽ ከኋላዋ ሰማች፡፡

‹‹ሚስተር ሉተር ጠላቂው መርከብህ ደርሷል›› አለ፡፡

ሁሉም ሰው በአይሮፕላኑ መስኮት ተመለከተ፡፡ ማርጋሬት ሄሪ በተናገረው ነገር ሉተር ልቡ መወሰዱን አወቀች፡፡ ከዚያ አንድ ጥይት ጮኸች፤ እሷ ግን ምንም አልሆነችም፡፡ ሁሉም አንድ ጊዜ ተንቀሳቀሰ፡፡ ኤዲ ዘለለና እንደ ተቆረጠ ዛፍ ሉተር ላይ ወደቀበት፡፡ ሄሪ የሉተርን ሽጉጥ
መንጭቆ ወሰደ፡፡

ፔርሲ ወደ ማርጋሬት ሄደና አቀፈችው፡፡ ‹‹አንተ ግን ደህና ነህ?››ቸ ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ ይመስለኛል››
‹‹በጣም ጎበዝ ነህ››
‹‹አንቺም እንዲሁ››
‹አዎ እኔ ጎበዝ ነኝ አለች ለራሷ፡
ፀጥ ብሎ የቆየው ተሳፋሪ ሁሉ በአንድ ጊዜ ተንጫጫ፡፡ በዚህ ጊዜ
ካፒቴኑ ‹‹ፀጥታ እባካችሁ ዝም በሉ›› አለ፡፡
ማርጋሬት ዙሪያውን ቃኘች፡፡
ሉተር ኤዲ እና ሄሪ ላዩ ላይ ወጥተውበት ከመሬቱ ላይ እንደተደፋ ነው፡፡ አይሮፕላኑ ውስጥ ያንዣበበው አደጋ ተወግዷል፡ ሃርትማንና
ሉተርን ሊወስድ የመጣው ጠላቂ መርከብ ተንሳፎ ይታያል፡

ካፒቴኑም የባህር ኃይል መርከብ በቅርብ ርቀት ይታያል፡ ‹‹ጠላቂ
መርከብ እዚህ እንዳለ የሬዲዮ መልእክት እናስተላልፋለን፡፡››
‹‹ቤን›› ሲል ተጣራ፡
‹‹አቤት ጌታዬ›› አለ የሬዲዮ ኦፕሬተሩ ‹‹የጠላቂው መርከብ አዛዥ
ሬዲዮ መልእክት ማስተላለፋችንን ካወቀ ወደ እኛ ሊተኩስ እንደሚችል
ተገንዝበኸዋል?›› አለ ቤን፡፡

‹‹ደህና ይቅር›› አለ ካፒቴኑ ‹‹ተሳፋሪዎቻችን እስካሁን የደረሰባቸው መከራ
ይበቃል፡››
ጠላቂው መርከብ መግቢያው እንደተዘጋ ነው አዛዡ  አንድ ነገር
ይሆናል ብሎ እየጠበቀ ነው፡፡

‹‹ቤከር አንድ ያልተያዘ ወሮበላ  ይቀረናል፡ እዚህ እንዲመጣ እፈልጋለሁ፡፡ የጀልባዋ ነጂ፡ ኤዲ ሂድና ቪንቺኒ እንደሚፈልገው ንገረው አለው
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት እኔ የቀጠልኩት (ክፍል 17)
Join @Eyosc1 የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉን
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት እኔ የቀጠልኩት

#የመጨረሻው ክፍል 17 - የፍቅር ታሪክ

ከሜሪ ፈለቀ
ትረካ በ ረድኤት ኃይሌ እና አማኑኤል አሻግሬ


ተፈፀመ              

#መልካም ምሽት ተመኘሁ!!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት
     
@Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ @Eyos18 አድርሱን
   
    📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
🔊ሪቻርድ ሶርጌ - #የመጨረሻው #ከፍል 4
Join @Eyosc1 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን
📕የመፃህፍት ትረካ   

😎ሪ ቻ ር ድ  ሶ ር ጌ

#ጀርመናዊው ጥልማሞት»

#የመጨረሻው ክፍል 4⃣
       
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽̶»̶̥🎶••✿••🎶»̶̥✽̶┉┉┄
 ባለ አራት እግሮቹ ከንቲቦች #ክፍል 2
Join @Eyosc1የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
 📕የመፃህፍት ትረካ     

 ባለ አራት እግሮቹ ከንቲቦች

  
#የመጨረሻው ክፍል ሁለት

🎙ግሩፑን ለማግኘት

              👇👇👇
        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽̶»̶̥🎶••✿••🎶»̶̥✽̶┉┉┄
🔥የእናቴ ልጅ

#የመጨረሻው ክፍል

#ክፍል ሠላሳ ሁለት

#ተከታታይ ልቦለድ

ቀን ቀንን እየተካ በሄደ ቁጥር በወንድሜ ላይ የነበረኝ የመረረ ጥላቻ እና ቂም እየደበዘዘ ሲመጣ ይታወቀኛል  ይህን ስሜት ወደድኩት ምክንያቱም እኔ ቂመኝነት በውስጤ ሰርፆ ቤቱን እንዲሰራብኝ የምፈልግ ሰው አይደለውም ። መጥፎ እና ልክ ያልሆኑ ጉዳዮች ጭንቅላቴ ውስጥ ጊዜ ወስደው በቁዩ ቁጥር እታመማለው ፡መረጋጋት አልችልም ። ያንን ስሜት ለማስታገስ ስል ነውጠኛ ነው የምሆነው ፡ከዚበፊት የእናቴን ጥላቻ እና የሰፈሬን ሰው ግልምጫ ለመወጣት ስል ንዴቴን ካገኘውት ሰው ጋር ሁሉ ነገር ፈልጌ እጣላ ነበር ። አሁን ላይ ከጉርምስናውም እየወጣው ነው እና ያ ስሜት እንዲቆጣጠረኝ አልፈልግም ። ስለዚ በወንድሜላይ ያለኝ ብስጭት እየቀነሰልኝ ሲመጣ ተጠቃሚ ነኝና ደስታ እየተሰማኝ ነው ። እሱ በሰው አገር ላይ ምን እያሳለፈ እንዳለ የምናውቀው ነገር የለም ። ሲዊዲን መድረሱን ከተቀባዮቹ ጋር ሆኖ ለእናቴ ደውሎ ከነገራት በዋላ ።ድጋሚ ደውሎም አያውቅም ። እናቴም ብትሆን ጨከን ብላበታለች ። 'ከአሁን በዋላ ቤተሰብ አለኝ ብለህ ወደእኛ እንዳታስብ 'ብላ እንደተናገረቸው አባቴ ነግሮኛል ። በእርግጥ ምንእንደሚሰማት  እሷው ነው የምታውቀው ።የእናት አንጀት እንዲ በቀላሉ ይቆርጣል ማለት ዘበት ነው ። አባታችንም ቢሆን ስሙን ለማንሳት ድፍረቱ ባይኖረውም አንዳንዴ በጨዋታችን መሃል ተክዞ ተክዞ በረጅሙ ሲተነፍስ አጋጥሞኛል ።ምን አልባት ስለ አቤል እያሰበ ይሆናል ብዬ እጠረጥራለው  ።
እኔ እራሱ ሳስበው ለአቤል እንዲመሆን ጥፋተኛው ማነው ? ብዬ አስባለው ። ያለ አባት አድገናል ፣እናታችን የሌለ አቅርባው አቅብጣውም ነበር ። የራሱስ አስተዋፆ ? እኔስ ብሆን ጥፋቶቹን በኔ ሲያላክክ የረዘመ ዝምታ አሳይቼስ አልነበረ ? ብቻ አንዳንዴ ሳስበው አቤል እንዲ እንዲሆን ትንሽ አስተዋፅዖ ሳይኖረን አይቀርም እላለው !!!!
🍑እሁድ ቀን  ተሰብስበን እንደተለመደው እየተጨዋወትን ፡ ቤቱን ሞቅ ደመቅ አድርገነዋል ፣ አባታችን እናቴን እየቀለደባት ያስቀናል ማማ በእናቴ ዙሪያ እየዞረች ባልገባት ነገር ትፈነድቃለች የኛ ሳቅ ሳይጋባባት አይቀርም ፣ እናቴ  ስለተሳቀባት አልከፋትም በጣም ደስተኛ ትመስላለች በባሏ ጎኗ መሆን ሙሉነት ሳይሰማት አይቀርም ልዩ ሆናለች ፡ በዛላይ ትላንትና የማማን እናት በማግኘቷ እፎይታ ተሰምቷታል ፡ የአቤልን ትልቅ ስህተት እንዳረመች ሳይሰማት አይቀርም ፡ የማማን እናት ይዛት መጥታ በማንኛውም ሰአት ልጇን የማየት መብት እንዳላት ነግራ ፡ ነገር ግን እፃኗ ከኛጋር መኖር እንዳለባት አስረግጣ አስረድታታለች እሷም ብትሆን ለልጇ ያን ያክል የምትጓጓ መስላ አልታየችም ።እንዲ መሆኑን የፈለገች ነው የምትመስለው ይሄ በራሱ ለኔም እንደ ግልግል ነው ።በአራስነቷ የተረከብኳትን ስንት ነገር ያየውባትን ልጅ ልውሰድ ብትል ምን እንደሚሰማኝ አላውቅም ።  ማማ ለኔ ትምህርት ቤቴ ናት በሷ የተነሳ እራሴን ገዝቻለው  ስለ ዓለም ክፋት ደግነት አይቻለው  ማጣት ምን ያክል እንደሚፈትን ገብቶኛል ። ብቻ ብዙ ብዙ ,,,,,
ዛሬ ላይ ግን በዛ ሂደት ውስጥ ስንት የምወዳቸውን ሰው አውቄ አለው ።ለየት ባለ መልኩ ባዩሽን የክፉ ቀኔ ። ብሌኔን ፍቅሬን የወደፊት ሚስቴ የአይኔን ማረፊያ ፡የልብ ምቴ የሕይወቴ ቅመም ማጣፈጫዬን ፡ ብሌኔ ውዴን ብሌኔ ብሌኔ ፡ስሟን እንኳ ስጠራው የሆነ መሃዛ ከአፌ ወጥቶ አብሮ ያውደኛል  ብሌኔ ብሌኔ ......
እረፋዱ ላይ አንዳችን በአንዳች እየሳቅን ጨወታችን ደርቶ ፡  ሳለ የእናቴ ስልክ ጮኽች ።እናቴ እንደሌላው ጊዜ አልፈጠነችም ታነሳዋለች ብለን ስንጠብቅ ፡ወደኛ ማየት ሆነ ። ስትዘገይብኝ ስልኳን አንስቼ ቁጥሩን አየውት የውጪ ለጠ ር ነው ደንገጥ አልኩ ። እናቴ በፍርሃት ስታየኝ
"የውጪ ስልክ ነው አንሺው አልኳት "
"አንተአንሳው "አለች እንደፈራች ስለገባኝ ፡ እኔው አነሳሁት
"ሄሎ "
"ሄሎ የወይዘሮ ዘውድነሽ ስልክ አይደለም "አለኝ የሴት ድምፅ ድንጋጤዬ ጨመረ አቤል ምን ሆኖ ነው
"ነው ማን ልበል አንቺን"አልኳት
"ዲና እባላለው እእ ከሲዊዲን ነው የምደውለው "አለች
"እሺ ምምን የየተፈጠረ ችግር አለ ወንድሜ ምን ሆኖ ነው "አልኳት እየተርበተበትኩ ።እናቴ ስታቃስት ሰማው ዞሬ ሳይ ዕንባዋ ቀድሟል ።
"ኧረ ተረጋጋ እሱ ምንም አልሆነም እኔ ፍቅረኛው ነኝ ያው ብቻ ስለ እናንተ ብዙጊዜ ያወራኛል እና ዛሬ አበረታትቼው አብረን እናወራቸዋለን ብዬ ነው በስንት መከራ የደወልኩት "አለች ፈጠን ፈጠን ብላ
"ድምፁን መስማት እንችላለን "አልኳት
"አዎ እባክህ አንተ ወንድሙ ከሆንክ በጣም ተፀፅቷል እና ይቅር በለው  "አለች
"ችግር የለም ይቅር ብዬዋለው አጠገብሽ ካለ ስልኩን ለሱ ስጪው እናቱን ያናግራት "አልኳት
"እሺ "ብላ ስታስተላልፍ እኔም ስልኩን ለእናቴ ሰጠዋት ።እናቴ ልትደብቀው የማትችለው የልጇ ፍቅር ገንፍሎ ወጣ ፡ በቃ ከአቤል ጋር በናፍቆት አወሩ በተደጋጋሚ ይቅር በይኝ ሲላት ይሰማል ልቡ የተሰበረ ይመስላል ፡ ከአባታችንም ጋር አወራ ፡አባታችንም አለቀሰ ፡ብዙ ነገር ተናገረው እንደዚ አይነት ክፋት ከገዛ ልጁ ስላልጠበቀ እስካሁንም ድረስ እየተሰቃየ እንደሆነ ነገረው አቤል ስቅስቅ ብሎ ሲያለቅስ ይሰማል ፡ጓደኛው ነኝ ያለችው ሴት ታባብለዋለች ፡ላውድ አድርገነው ስለሆነ የምናዳምጠው ፡አክስቴ ደግነሽም ባዩሽም ማልቀሳቸው አልቀረም ፡ አክስቴ ደግነሽ ወደኔ እያየች "ይቅር በለው ልጅነት ነው አውሬ ያደረገው "አለችኝ ሆደባሻነቷ አይሎ ፡  እኔ ውስጤ ተረጋግቷል ሞተ የምባል መስሎኝ ስለነበር ክፉ ነገር ስላልሰማው ሰላም ሰፍኖብኛል ። ዓለም እንግዴ እንደዚ ናት እንደ ዥዋዥዌ ነው ነገሯ ወደዚ ወደዚያ ፣ እንደ ፈለገች አንተ ጠንክረ ገመዷን ይዘህ እየተቆጣጠርክ ካልተጫወጥክ ፈንግላ ልትጥልህ ትችላለች ፡ እራስህን ከማንም ጋር ሳታወዳድር የማንንም ንዋይ ሳትመኝ የሕይወት መንገድህን በራስህ በንፁ ሕሊናህ ታግዘህ አስምር መስመሩ ሲበላሽ በትህግስት እያስተካከልክ  ወደፊት ቀጥል ። ለሌሎች የደስታ የሰላም ምንጭ እንጂ ፣የስቃይ የመከራ ምንጭ አትሁን ፣ አንተ ደስተኛ የምትሆነው በዙሪያህ ደስተኞች ሲኖሩነው ፡ 'ብቻህን በሚያለቅሱ ሰዎች መሃል ብትስቅ እብድ ነው የምትባለው'
             ,
   🔅🔅🔅ተፈፀመ🔅🔅🔅

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄