ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
197K subscribers
282 photos
1 video
16 files
210 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ወግ
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
🎯መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
☎️• 0922788490

📩@Eyos18
Download Telegram
😭ያልታጠበ እንባ😘

#የመጨረሻው ክፍል 3⃣6⃣

#ተከታታይ ልቦለድ

...ህይወቴ መስመር ያዘ ብዬ ማዉራት ስጀምር ግን ዝብርቅርቁ ወጣ! ቆይ እኔ መቼ ነዉ ችግር ማያጣኝ? አሁን እንኳን ከመጠን በላይ ሆነብኝ ነገር ሁሉ ከልኩ አያልፍም እየተባልኩ ነዉ ያደኩት ግን ታዲያ የኔ ሲሆን ነዉ ልኩ ሚያልፈዉ።

" ናቲ ከዳኒ ጋር ስትሳሳሙ በገዛ አይኖቼ አይቻለዉ ብሎ ምክንያት ፈጥሮ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ተለየኝ ። ፂሆንም በማላቀዉ ምክንያት ተጣላችኝ ሂወት ዉጥን ቅጦ ወጣችብኝ አቅጣጫዋን ቀየረች።

" ለሁሉም ወንድ አንድ አይነት አመለካከት ነዉ ያለኝ ሁሉም ጊዜ ለማሳለፊያዉ ብቻ ነዉ ሚፈልገኝ ብዬ እራሴን ወንድ ከተባለ ፍጡር ደብቄ ማኖር ጀመርኩ ።
"ለነገሩ ሴትም አልቀርብም.... ሰዉን እንደ አዉሬ ፈራዉ ሁሉም ሰዉ እኔን ለመጉዳት የተፈጠረ ይመስለኛል ወንድ በወንድ ይተካል ብለን ብናስብም የልብ ጓደኛ ግን በምን....?"

"እና ከናቲ በሗላ ወንድ እርሜ ብይ ተዉኩ ዳኒም ይሄን አጋጣሚ ተጠቅሞ እኔን ማገዝ ከጎኔ መሆን ሲገባዉ ግን እሱ ማንም የላትም ብሎ የፍቅር ጓደኛዉ እንድሆን ጠየቀኝ አይሆንም ስለዉ እሱም ድጋሚ ከጠገቤ እንደማይደርስ ነግሮ ተወኝ ።የእዉነት ዳኒ ወንድሜም እራቀኝ ?! "
"የሆነ ቀን ከመጠን በላይ ከፋኝ ሰዉ በሞላበት ሀገር ግን እኔ ሰዉ ራበኝ ብቸኝነቴ ኦና የሆነዉ ልቤ ሰዉ ናፈቀ የሆነ ማወራዉ ሰዉ ፈለኩ ብቻ ማንም ቢሆን ግድ አልነበረኝም ብቻ ሚያዳምጠኝ ይሁን! እና በሀሳቤ ዳኒ መጣ ምንም ሳላንገራግር ቶሎ ብዬ ደወልኩለት አያነሳም ብዙ ሞከርኩ በመጨረሻም አነሳልኝ ግን እኳ ያለጥፋቴ እሱም ጠልቶኛል ።
"ግን እኔ ሁሉን ረስቼ እንገናኝ አልኩት እንቢ አለኝ እንደህፃን እያለቀስኩ ለምኜዉ በስንተ መከራ ተስማምቶ ተገናኘን ግን እሱ በምላሹ ወንድነቱ ሊፈትንብኝም ፈለገ ያን ሁሉ ሚስጥሬን ነግሬዉ ስለሱ የቱን ነግሬ የቱን ልተዉ እእእ አንድ ሰሞን እነደዛ ሲሆንልኝ እሱን ማምለክ ነበር እኳ የቀረኝ እሺ የትኛዉ ወንድ ነዉ ለኔ ሚበጀኝ ለነገሩ የገዛ አጎቴ ልጅ ለኔ ያልተመለሰ ታዲያ ማነዉ ለኔ ...........?" ኧረ ማይሆነዉን በቃ ባጠቃላይ ወንድ የተባለ ፍጡር ጠላዉ ጠላዉ "
"ወንድ ልጅ አንዴ ተሳስቶ ካየኝ ሁሉ የተመኘኝ እየመሰለኝ ያ ቀኔ ይበላሻል ያየኝን ልጅ ስረግመዉ እዉላለዉ። ሁሌም ቢሆን የበፊት ሂወቴን እያስታወስኩ ማታ ማታ ማልቀስ ለኔ ኖርማል ሆኖ ቀጠለ ሳላለቅስ የተኛሁበት ቀን ትዝ አይለኝም ተሳስቼ እንኳን ከተኛዉ በማግስቱ ማታ ሁለት ድርብ ለቅሶ ይሆንብኛል ። "ታዲያ ማነዉ የኔን እንባ ሚያብሰዉ ያጓቴ ልጅ ተግባር ባረሳዉም ግን ላለማስታወስ እየሞከርኩ ነበር !" "ግን በዛ ህመሜ ላዬ ፂሆን ናቲ እና ዳኒን ማጣቴ በንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆነብኝ እነሱስ እሺ ግን ፂሆን እኔን መራቆ ሁሌም ማላምነዉ ነገር ነዉ ያዉም በማላቀዉ ጉዳይ ብዙ ጊዜ ላወራት ሞከርኩ ግን እድሉን ነፈገችኝ!
ከስንት አመታት በሗላ ወሬ ደረሰኝ ለካ አጅሬሆዬ ከፂሆን ጋር ከገዛ ጓደኛዬ ፍቅር ጀምሮ ነዉ ከኔ የራቀዉ ምን እሱ ብቻ እሷም ያለምክንያት የራቀችኝ ለዚሁ ነበር እኔም እስከ ዛሬ ያላወኩት ምንም ጓደኛ ስለሌለኝ ነበር በርግጥ እኳ የማስተዋል ችግር ነዉ እንጂ ብዙ ጊዜ አብረዉ መንገድ ላይ አይቻቸዋለዉ ግን እኔ በዚ መልኩ አላሰብኩም እንዴትስ የገዛ ፍቅረኛይ ከጎደኛዬ ኧረ ለማሰብም ሁሉ ይከብዳል
"ከዳኒ ጋር ምን አምን ያለኝ መራቂያ ሙዱ ነበር " እሷስ ብቶን እንደዛ እንደማፈቅረዉ እያወቀች እንዴት እንዲ ታደርጋለች ለካ ሰዉ በጥርሱ እየሳቀ በሆዱ ይቀብራል
"ማንም ማያዉቀዉ እዉነታዬ እሷን ናቲን እና ዳኒን ላለማስታወስ ብዙ ጣርኩኝ በብዙ ነገሮች ራሴን ደበኩ ግን ለካ አባባሉ እዉነት ነዉ የማይረሱትን ሰዉ ለመርሳት መሞከር ይበልጡን ማስታወስ ነዉ በማስታወስ ዉስጥ ትዝታ አለ በትዝታ ዉስጥ ብዙ ናፍቆቶች አሉ ግን ግን ናቲ በጓደኛዬ ቀየረኝ ያዉም ባመንኳት በገዛ ጓደኛዬ።
"ህይወት ሠንሰለት ናት አንዱ አንዱን ሲፈልግ ሚፈልገዉ ደሞ ሌላ ይፈልጋል ህይወት የማትፈታ ቅኔ ናት አንዱን ስንቀንስ ሌላዉ ምንተካበት ግን ከምንም በላይ ሀያል የሆነዉ ፍቅር ህይወት ነዉ ይሄን ሁሉ ነገር አንድ ላይ አቀናጅቶ የያዘ ሁሉም ሠዉ ልብ ዉስጥ ያለ ግን አዉቆ ለተጠቀመበት ብቻ ደስታን ምታጎናፅፍ።

#"ከአራት አመታትም በሗላ ሂወት ተለወጠች መልኳን ቀየረች ከብዙ ትግል በሗላ ሁሉንም በልቤ ይቅር ብያቸዉ ኑሮዬን ቀጥያለዉ "የጊቢ መግቢያ ፈተናን በጥሩ ዉጤት አጠናቀኩ "ግን እኔ ጊቢ መግባት አልፈለኩ ማሰብም አልፈልግም "እንደኔ በትላንት ሂወታቸዉ ታምቀዉ እና ታስረዉ ላሉ ሴት ወገን እህቶቼ መድረስ ስላለብኝ የ Psychology ( ስነ ልቦና ) ትምህርት መማር ስለፈለኩ ቤተሰቤም ተስማምተዉ በግል ትምርቴን መማር ጀመርኩ አላማዬ እኔ ላይ የደረሰዉ በሌላ ሴት ላይ እንዳይደረስ ብቻ አይደለም ሂወቴን ይፋ እያወጣዉ ከኔ ሂወት የትኛዉም ሰዉ ተምሮ አሁን ያለበት ማንነቱ ላይ ቆሞ ራሱን እንዲፈትሽ ነዉ እና psychologist መሆኔ የማይቀር ነዉ ይቅናሽ ይሳካልሽ በሉኝ በፊት እናት እና አባቴ በልጃቹ በቤኑ ድረሱ እያሉ ሲመርቁ ምፈራ የነበርኩ ልጅ ግን ዛሬ ላይ የምርቃቱ ተቆዳሽ አሚን ባይ የመጀመሪያዋ ሆኛለዉ አሁን ላይ I'm 2nd year psychology student

"የባለታሪኮ መልክት" 👇

#ወንድ ልጅ እንደ #ጭቃ ሴት ልጅ ደሞ #እንደ መስታወት ናት። መስታወት አንዴ ከተሰበረ ለመጠገን ቢሞከር እንኳን የቀድሞዉን ይዞታና መልክ ሊይዝ አይችልም #ጭቃ ግን አሁን ያለበትን ቅርፅ እና መልክ መያዝ ይችላል !!!። ሴቶች ዛሬ ላይ #እንደቀልድ ወይ # ለሙድ በሚል የጓደኛ ግፊት የምናደርጋቸዉ ልክ ያልሆኑ ነገሮች የነገ ሂወታችን ላይ ከባድ የሚባል ችግር ሲፈጥርብን አስተዉያለዉ የሚገርመዉ ነገር ልክ እንደተሰበረዉ መስታወት ያሳለፍናቸዉ ጥሩ የማይባሉ ነገሮች ሙሉ በሙሉ አድሰዉ በአዲስ ማንነት ለመኖር ብናስብም ቀድም ብለን ይዘነዉ የነበረዉ ጥሩ ያልሆኑ ማንነት እና ስም በማህበረሰቡ እይታ ዉስጥ አሻራ ጥሎ ስላለፈ ያሁኑን አዲስ ማንነት አሚን ብሎ ለመቀበል ይቸግራል
ወንድ ጋር ስንመጣ ደሞ እንደሴቶ አልያም ከሴቶ በላይ ጥሩ የማይባሉ ነገሮች ሰርቶ የሆነ ሰአት ላይ ያን ማንነት መቀየር ቢፈልግ አንደጭቃዉ እንደገና ፈርሶ ወደሚፈልገዉ አይነት ማንነት እና ስም ቅርፁን መቀየር (መለወጥ)ይችላል በተጨማሪም
#ማህበረሰቡ ከወንድ ይልቅ ሴት ላይ ነገር ማጥበቅ ስለሚወድ በወንድ የሚደረጉ ነገሮችን ያን ያህል ትኩረት ሰቶት አያያቸዉም ሴት ስታደርገዉ ግን ወደቀ ሲባል ተሰበረ ነዉና ነገሩ
ሴቶችዬ ዛሬ ላይ እንደቀልድ ባለማስተዋል የምታደርጎቸዉ ነገሮች የነገዉ #የትዳር _ሂወታችሁ ላይ እንቅፋት ሆኖ መንገድ እንዳያበላሽባቹ ዛሬ ላይ በቆማችሁበት ማንነት #ነጋችሁን ፈትሹት !🙏🙏🙏። ብልህ የሆነ ሰዉ ከኔ ህይወት ይማር🙏


#


ስለድርሰቱ ያላቹ ወይ ደግሞ የተሰማቹ አስተያየት ሁሉ በዚ አድርሱኝ👇

🎙ግሩፑን ለማግኘት

@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha

❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚