ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
177K subscribers
275 photos
1 video
16 files
192 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ወግ
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
🎯መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
☎️• 0922788490

📩@Eyos18
Download Telegram
📕ታምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_አርባ_ስድስት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹የአባትሽ ዘመዶች ነው ያልከው….?››

‹‹አዎ የአባትሽ ወገኖች … ይሄንን ተክል በምድር ላይ  እንዲበቅል አድርገው ሲበትኑት ለመድሀኒትነት እንዲሆን አስበው አይደለም…››

‹‹እና ለምድነው….?››

‹‹አንቺን ለማግኘት….››ብሎ ጭራሽ ግራ አጋባት

‹‹እንዴት አድርገው ነው እኔን የሚያገኑኝ…….?ደግሞ የት ናቸው….?››

‹‹የት እንዳሉማ ታውቂለሽ….››

‹‹እና እንዴት ነው የሚያገኙኝ ….?››

‹‹ልክ  ያቺን ተክል ስትቀነጥሺ ቀጥታ መልእክቱ እነሱ ጋር ይደርሳል››

‹‹እወነትህን ነው….?››ውስጧ ፈነጠዘች..አባቷ የማግኘት ምኞት ሳታስበው አዘለላት..የእናቷን እውነት የማረጋጋጥ ፍላጎት…

‹‹እና አሪፍ ነዋ..ያለሁበትን ካወቁ ይመጣሉ አይደለ..….?አባቴም ይመጣል አይደል….?››ጠየቀችው

‹‹አይ አባትሽ በጥብቅ እስር ላይ ስላላ መምጣት አይችልም.. ወደዚህ ምድር በመጣ ጊዜ ሳይፈቀድለት  ከሰው ጋር በፍቅር በመቆራኘትና አንቺን ስለወለደ ይሄው ባንቺ እድሜ ሙሉ እንደታሰረ ነው››አንጀቷ ተላወሰ..በምድር ላይ ታስሮ ቢሆን ኖሮ  የፈጀውን ያህል   ይፍጅ  እንጂ   መንግስትንም ገልብጣ ቢሆን አባቷን ታስፈታው ነበር

‹‹እና ታዲያ ዘመዶቹም ቢሆን ይምጡ ምን  ችግር አለው….?››

‹‹ሚመጡት  አንቺን ለመውሰድ ነው››

ደስ አለት..ደነገጠችም ‹‹ወዴየት ነው የሚወስድኝ….?››

‹‹ወደራሳቸው አለም….››

‹‹እኔ መሄድ ካልፈለኩስ….?››
‹‹ፈለግሽም አልፈለግሽም ይወስዱሻል …ምንም አይነት ምደራዊ ኃይል አንቺን ከመውሰድ አያግዳቸውም….››

ለአምስት ደቂቃ በትካዜ  ውስጥ ገባች…ሌላ አለም የማየት ፍላጎት… አባቷን እና ዘመዶቹን የማወቅ ፍላጎት..ደግሞ ይህቺን ምድርስ….?

‹‹ቆይ ሄጄ ሁሉን ነገር ካየሁ በኃላ ተመልሼ ወደምድር መምጣት አልችልም….?››

‹‹አይመስለኝም… ብትመለሺም እንደዚህ ሆነሽ አይደለም…ሙሉ በሙሉ ተቀይረሽ.. ሙሉ በሙሉ እነሱን ሆነሽ..የእነሱን ተልዕኮ ለማስፈፀም ነው ሚሆነው.ያ በእነሱ ፍቃድ ላይ የተመሰረተ ነው.ከፈለጉ እስከወዲያኛው ዳግመኛ ምድርን ላትረግጪ ትችያለሽ፡፡››

‹‹በቃ ይሁን.. ለእኛም እዛ መኖር ይሻለናል..የተለየ ዓለም  እኮ አሪፍ ነው..ይቺን ዓለም እንደሆነ በተቻለ መጠን በርብረናታል…ምን ይቀርብናል….?››

‹‹እና ወሰንሽ››

‹‹አዎ ባክህ እንደውም አሪፍ እድል ነው››
እንግዲያው ተዘጋጂ… ከአምስት ደቂቃ በኃላ ሄደሽ መቀንጠስ ትችያለሽ..ከቀነጠስሽ በኃላ ግን አንድ ሳምንት ብቻ ነው በምድር የመቆየት እድል የሚኖርሽ… ልክ የዛሬ ሳምንት በዚህን ሰዓት ካለሽበት ቦታ መጥተው ይዘውሽ ይፈተለካሉ››

‹‹አንድ ሰምንት..አንድ ሳምንት ፈጠነ..ግን ቢሆንም ቀላል ቀን አይደለም….ብዙ ነገር እንሰራበታለን…እናቴን ሄደን እንሰናበታለን..የልጅነት ጎደኞቼን እሰናበታለሁ… አሪፍ ነው..አንድ ሳምንት ይበቃናል..››አለችና ወደተክሏ ተራመደች..
ደረሰችና ልክ ድፍን  6 ሰዓት ሲሆን  ከብሳናው ዛፍ ቅርንጫፎች መካከል  እጇን ዘረጋችውና ጨበጠችው… ቀነጥሰዋለሁ ስትል በእጇ ሟሞና እንደቅባት ተሙለጭልጮ ወደሰውነቷ ሲገባ ታወቀት… ደነገጠች የቀነጠስችው መስሏት ነበር… እጇ ላይ ግን ምንም ነገር የለም… እጇ  የተለየ ቀለም እያመጣ ነው ..ሀመራዊ እሳት መሰል ቀለም… በመላ ሰውነቷ እየተራወጣ ከተዳረሰ በኃላ አንዘርዝሮና አንቀጥቅጦት በአፏ የቴንስ መጫወቻ የምታክል ድብልብል እሳት ብልቅ ብሎ በመውጣት እንደሮኬት ተተኩሶ ወደሰማይ ተምዘገዘገ ..እያየችው  አየሩን ሰንጥቆ ተሰወረ..ግራ ጋባት …እንደምንም ለመረጋጋት እየሞከረች ወደንሰሯ አዕምሮ ተመለስችና ‹‹ምን እየሆነ ነው….?››ጠየቀችው
‹‹በቃ ጨርሰናል እንሄድ››
‹‹እንዴ መቀንጠስ አልቻልኩም እኮ ..እጄ ላይ ምንም የለም….?››
‹‹እጅሽ ላይ ምን ያደርግልሻል …ተክሉ እኮ በመላ ሰውነትሽ ገብቶ ተዋሀደሽ..አሁን መዳኒቱ ተክሉ ሳይሆን አንቺ ራስሽ ነሽ..በዚህ የሳምንት ጊዚ ውስጥ የፈለግሽውን ማዳንም የፈለከግሽውን መግደልም  ትችያለሽ..››

‹‹ደስ ሲል ››

‹‹ደስ አይልም…››አለና ከመጣ ጀምሮ ተዘፍዝፎበት ከነበረው ቋጥኝ ላይ ክንፉን አርገፍግፎ ተነሳን ማጅራቷን ይዞ ወደሰማይ ተምዘገዘገ  ….ወደጀርባዋ ዞረና ተጣበቀባት…  ወደ አዲስአባ ተመልሰው እቤታችን ሲደርሱ ከምሽቱ 8 ሰዓት አልፎ ነበር… …

‹‹ወይኔ ድክም ብሎኛል..ግን መድሀኒቱን ስላገኘን ከአባቴ ወገኖችም ጋር ልንገናኝ ስለሆነ ደስ ብሎኛል…አንተስ ደስ አላላህም….?››ለመተኛት ወደ አልጋዋ እያመራች ነበር ምትናገረው

‹‹በጣም ከፍቶኛል››አላት ንስሯ

ደነገጠች‹‹ለምን….?››

‹‹ከንቺ ጋር የምኖረው ..በህይወትም የምቆየው ለሳምንት ብቻ ስለሆነ››

በህይወቷ እንደዚህ አይነት ድንጋጤ ደንግጣ አታውቅም.‹‹.እንዴ የእኔ ንስር ሟች ፍጡር ነው እንዴ…….?›ብላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰበችብት ጊዜ ነው

‹‹ጥዬህ የምሄድ መስሎህ ነው..አብረን እኮ ነው የምንሄደው››

‹‹ይዘሺኝ መሄድ አትቺይም››

‹‹ለምን….?››

‹‹እኔ መጀመሪያም ከዛ ነው የመጣሁት…ለአባትሽ ብዬ እና አሁን ተመልሼ ለመሄድ ፍፅም አይፈቀድልኝም፡፡››

‹‹በቃ ይቀራላ ..እስከዛሬ ካንተ  ጋር እንጂ ከእነሱ ጋር አልኖርኩ.. ምን  ያደርጉልናል እነሱ መቅረት ይችላሉ››

‹‹እሱማ ጊዜው አለፈ..ቅድም ከአፍሽ የወጣችው እሳት አነሱ ጋር መልዕክት ይዛ የምትሄድ ነች…ወደድሽም ጠላሽም አንቺን ይወስዱሻል..እኔ ደግሞ ካለአንቺ ህይወት የለኝም …ተነጥለሺኝ እንደሄድሽ ወዲያው በዛኑ ሰዓት እሞታለሁ..››

‹‹እንዴ  እሞታለሁ ማለት ምን ማለት ነው….?ይሄንን ታዲያ ተክሉን ከመቀንጠሴ በፊት ለምን አልነገርከኝም….?››

‹‹ውሳኔሽ በእኔ ላይ እንዲመሰረት ስላልፈለኩ ››

‹‹ያምሀል እንዴ . ….?.ካንተ ሚበልጥብኝ ነገር አለ…….?

ህይወቴ እኮ ነህ..››አበደች ጮህች ፕሮፌሰሩ ከእንቅልፋቸው ባነው በራፏን እስኪያንኮኩ ድረስ ግቢውን አተረማመችው …፡፡

     ይቀጥላል

#ክፍል 47,,እንዲለቀቀ (15) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_አርባ_ሰባት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ለሊቱ ያለእንቅልፍ ነው ያለፈው….የጣር ለሊት…የስቃይ ለሊት…፡፡ደግነቱ ፕሮፌሰሩ ለሊቱን ሙሉ አብረዋት ነው ያሳለፍት…..ይሁን እንጂ እሷ ባዘነች መጠን አብረዋት እያዘኑ ነበር ብሎ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም..ግን በታታሪት ሲያዳምጧት እና ደረቅ አልኳል ሲያጣጧት ነበር..  ወፎች የለሊቱን መንጋት የምስራች ሊያበስሩ ሲንጫጩ ድምጻቸው የተሰማው…
ሁለት ጠርሙስ ብላክ ሌብል  ጠርሙስ ጨርሰዋል..እሷ አንድ ጠርሙስ ከግማሹን ሳትጨርስ አልቀርም፡፡በንዴት፤ በስጋትና በብስጭት ያወራችው ወሬ ቢቀረብ እና ወደ መጻሀፍ ቢገለበጥ አንድ ደለብ ያለ መጽሀፍ ይወጣዋል፡፡

‹‹ፕሮፌሰር ምን አቀበጠኝና ተክሉን ቀነጠስኩ..….?ምን ቅብጥ አደረገኝ….?››

‹‹እንደነገርሺኝ እኮ ሙሉ በሙሉ ሚያመጣውን መዘዝ አልተረዳሽም ነበር››

‹‹እኮ ረጋ ብዬ ጊዜ ወስጄ ማሰብ ነበረብኝ…ንስሬ እንኳን ሊነግረኝ ባይፈልግ…ጎትጉቼ ሙሉውን  መዘዝ መረዳት ነበረብኝ፡፡››

‹‹ግን እርግጠኛ ነሽ ..እንደዚህ ያለ ንስርሽ ለመሄድ እንደምትገደጂ ብታውቂ ኖሮ ተክሏን ከመቀንጠስ ትታቀቢ ነበር….?››

‹‹ይቀልዳሉ እንዴ ፕሮፌሰር..ጭርሽ ለማሰብ እንኳን አልሞክርም…እንዴ ንስሬን ጥዬ እንኳን የማላውቃቸው ..ምን አይነት ፍጡር እንደሆኑ እንኳን እርግጠኛ ወዳልሆንኩባቸው..ይመቹኝ አይመቹኝ  መገመት ወደማልችላቸው  የአባቴ ዘመዶች ይቅርና እግዚያብሄርም ቢጠራኝ  ንስሬን ጥዬ በፍቃደኝነት  ለመሄድ አልፈልግም››

‹‹በቃ ተረጋጊ..ያው በሞትም መለየት እኮ አለ››አሏት ፕሮፈሰሩ …በእሳቸው ቤት እሷን የሚያጽናና ቃል መናገራቸው ነው፡፡

‹‹አይ ፕሮፌሰር …ይቀልዱብኛል አይደል?ይሄም እኮ ያው ሞት  ነው…ሞት ማለት የራስ ከሆኑ ሰዎችና ከሚኖሩበት ዓለም ለዘላለም ተለይቶ በስጋ ወደመሬት ውስጥ መግባት በነፍስ ደግሞ ወደማይታወቅ አለም መጓዝ ማለት አይደል…?አሁን እኔም ከሳምንት በኃላ የሚገጥመኝ  ደግሞ በስጋም በነፍስም ከዚህች ምድርም ሆነ  የእኔ ከሆኑት ሰዎች ሁሉ  ተለይቼ ለዘላለም ወደማይታወቅ አለም በስጋም በነፍስም መጓዝ ነው…ታዲያ ይሄ እንደውም ሙሉ ሞት አይደለም..….?ማንም ሰው ስናፍቀው እንኳን መቃብሬ ጋር ሄዶ በማልቀስ ወይም አበባ በማኖር ሊያጽናና ዕድሉ አይኖረውም …. ነፍሴንም ስጋዬንም ይዤ ነው የምሄደው…››

‹‹እሱስ እውነትሽን ነው››

‹‹አዎ ዋናው ችግር  ግን ይሄ አይደለም..ዋናው ንስሬን ጥዬ መሄድ ያለመፈለጌ ነው..እሱን..››ንግግሯን አቋረጧት፡፡  
‹‹እኔ እኮ በህይወት እስካለሁ ድረስ ልንከባከብልሽ እችላለሁ፡፡››

‹‹አይ አይችሉም… እርሶ የሚችሉት በስርዓት የቀብር ሰርዓቱን ማስፈፀም ብቻ ነው››

‹‹አልገባኝም..››አሏት ደንግጠው፡፡
‹‹እኔ  ጥዬው በሄድኩ ቀን እሱም እደሚሞት ነግሮኛል››

‹‹እንዴት ሆኖ ነው የሚሞተው….?››
‹‹እኔ እንጃ ግን  እኔን ከወሰዱኝ በኃላ ለአንድ ቀንም እንኳን በህይወት መኖር እንደማይችል እርግጠኛ ሆኖ ነግሮኛል››

‹‹አይዞሽ ሳምንት እኮ ብዙ ቀን ነው..የሆነ መውጫ መንገድ ልናገኝ እንችላለን..በተለይ ንስርሽ መላ ሚያጣ አይመስለኝም››

‹‹እኔ እንጃ …. እንደዛ ተስፋ አላደርግም …››

‹‹አይዞሽ…ደግሞ ይሄ ጉዳይን እንደመስዋዕትነት ቁጠሪው..ህይወት ለማትረፍ ነው እዚህ ወጥመድ ውስጥ የገባሽው››

‹‹መስዋዕት አሉኝ….መስዋዕትነትማ እንዲህ በቀልድ አይገለጽም..እኔ ከመስዋዕትነት ይልቅ ክስረት ነው የሚሰማኝ…መስዋዕትነት እኮ ለአንድ ክብር አለማ አቅዶና አስቦ ሕይወትንም ጭምር መስጠት ማለት ነው…ህይወትንም ጭምር ቢሆን አጥቶ ሌላውን ለማኖር ቀድሞም አምኖና ወስኖ መተግበር ማለት ነው…

‹‹ልክ እንደ አርበኞቻችን ማለትሽ ነው….?››

‹‹አዎ እንደውም ዛሬ ለሀገር መስዋዕትነት ስለከፈሉ ሰዎች ምስጋና የምናቀርብበት ቀን አይደል…ሀገር ከምትደፈር የእኔ ህይወት ትቀጠፍ ብለው…ለልጆችና ለልጅ ልጆቻችን ባርነትን ከምናወርስ እኛ ዛሬ ደማችንን እረጭተን አጥንታችንን በትነን ነጻነትና ኩራትን እናወርሳቸው ብለው ታሪክ እንደሰሩት አባቶቻችን   ነው መስዋዕትነት….ልክ እንደ በላይ ዘለቀ፡፡ ከገዛ አብራክ ልጅ ይልቅ ሀገርን ወይም ህዝብን ማስቀደም ማለት ነው…ለሀገር ክብር እና ለወገን መድህን ሆኖ መውደቅ ማለት ነው…ከስኬት በኃላም ላደረጉት ነገር የተለየ ክብር እና ሹመት አለመፈለግ ማለት ነው..ለሚወዱት ነገር ያለንን ነገር ሁሉ ህይወትንም ጭምር በነፃ መስጠት ማለት ነው….
እንደዛአይነት መስዋዕትነት ሚስጥሩ ከባድ ነው….ከድል በኃላ የበላይን ይሄንን ለሀገሩ በነፃ የሰጠውን መስዋዕትነት  ሸፍጠኞቹ እና ባንዳዎቹ አልወደዱለትም ነበር..ምክንያም ስለእሱ ዝናና ታሪክ ሲሰሙ የእነሱን ሆዳምነት እና  ትንሽነታቸውን በየጊዜው ስለሚያሳብቅባቸው ከንጉሱ አላትመው በአደባባይ እንዲሰቀል አደረጉት..ከጠላት በክብር የተረፈች ነፍሱ በገዛ ህዝቦቹ ምቀኝነት እና ክፍት ተነጠቀች…ይሄ ነው መስዋዕትነትን መራር የሚያደርገው…ለዚህ ነው መስዋዕትነት የሚለው ቃል ሚያስጠላኝ፡፡

‹‹ትክክል ነሽ ልጄ…ይሄ የበላይ  ታሪክ የእንግሊዞች ቢሆን፤ይሄ የበላይ  ታሪክ የአሜሪካኖች ቢሆን  ኖሮ አንድ ሺ ፊልም እና አስር ሺ መጽሀፍ ተጽፎበት ነበር…?ስንት መንገድ እና ስንት ዩኒቨርሲቲ በስሙ ተሰይሞለት ነበር…?››
እኚህ  ለሊቱን ከፕሮፌሰሩ ጋር በመጠጥ እያወራረድ በእሷ ለቅሷ ታጅበው  ሲያወሩ ከነበሩት ነጥቦች ጥቂቶቹ  ነበሩ..….

አሁን ሰዕቱ ከማለዳ 12፡45 ይላል…ፕሮፈሰሩ በመጠጥ እና በእሷ ወሬ ተዳክመው ይመስላል እዛው የተቀመጡበት ሶፋ ላይ ደገፍ እንደሉ እንቅልፍ ይዞቸው ጭልጥ ብሏል….ንስሯ ያለው መኝታ ቤት ውሰጥ ነው ከእሷ በላይ ትካዜና ቁዘማ ውስጥ ነው…ልትነካካው አልፈለገችም
እየተንገዳገደች እቤቱን ለቃ ወጣችና ወደ መኪና ማቆሚያ አመራች…‹‹ከጠጡ አይንዱ›› የሚለውን የትራፊኮችን ዋና ምክር አዘል መመሪያ ከቁብም ሳትቆጥር መኪናዋን አስነሳችና ግቢው ለቃ ተፈተለከች..ቀጥታ ወደመላኩ ቤት ነው ያመራችው…
እንደደረሰች ወደጊቢው አጥር አስጠጋችና መንገድ እንዳይዘጋ አስተካክላ መኪናዋን ካቆመች በኃላ ሞተሩን በማጥፋት ከመኪናዋ ወረደችና  የግቢውን በራፍ መጥሪያ በሰከንድ ሽርፋራፊ ውስጥ  ደጋግማ አንጣረረችው ፡፡ከጠበቀችው በፈጠነ  ሁኔታ ተከፈተላተት..ከእንቅልፉ የባነነ እና በአንድ እጁ አይኖቹን እያሻሸ በሌላ እጁ የበራፍን እጄታ ይዞ ‹‹ምን ፈለግሽ….? ›› የሚላት ሰው ስትጠብቅ .. ንቁ እንቅልፍ በዓይኑ እንዳልዞረ የሚያስታውቅ..አይ እንደውም እያለቀሰ የነበረ ከዚህ በፊትም ያየችት ዘበኛ ከፈተላትና…ምንም ነገር ሳይጠይቃት እንድትገባ መንገዱን ዞር ብሎ ለቀቀለት …አልፋ ገባችና መንገዷን ቀጠለች ..በፍጥነት ዘግቷ ከኃላዋ ተከተላት፡፡

‹‹ዛሬ ምን አይነት ቀን ነው…….?ሰው ሁሉ ሲያለቅስ እንቅልፍ አጥቶ የሚያድርበት ቀን ነው እንዴ….?››ከዘበኛው ሁኔታ ተነስታ ውስጧን እየጠየቀች ነው…  እራሷን ለመቆጣጠር በዚህ በተወለካከፈ እርምጃ አንድ ነገር አደናቅፏኝ እንዳትደፋ  እየፈራች ስትራመድ ዘበኛው በታፈነ ድምጽ መናገር ጀመረ

‹‹ጋሼ ደውለውልሽ ነው….?››

‹‹አዎ›› አለችው….ምንም ሳታስብበት

‹‹አይ ቢጨንቃቸው እኮ ነው ..በቃ እኮ 10 ደቂቃም ዕድሜ አይራቸውም …አብቅቶላቸዋል…››

‹‹ማን ነው ያበቃለት ….?››ደንግጣ
​​‹‹እትዬ ሰሚራ ናቸዋ… ስንት ነገር ሲታሰብ… ለሰርጋቸው ሲዘጋጁ እንዲህ ባጭር ይቅሩ..….?ውይ ጋሼ በጣም ነው አንጀቴን የበሉት ..ተሳቀቁ፤እትዬስ አንዴ ለይቶላቸው ሊገላገሉ ነው እሷቸው ግን ጤነኛ ሰው የሚሆኑ አይመስለኝም፡፡››

ይህን ሁሉ እያወራ ሳሎኑ በራፍ ድረስ አደረሰታ እና የሳሎኑን በራፍ ከፍቶ አስገብቶ ወደኃላ ተመለሰ….ሳሎኑ ውስጥ በግምት ከ10 ያላነሱ  ፎጣ የለበሱ፤ ጋቢ የደረቡ ፤ የተቀመጡ፤ የሚንጓራደዱ ሰዎች ይታያሉ……

‹‹ዋው !!!ምን አይነት ሰዓት ደረስኩ….?››ስትል እራሷን ጠየቀች…በአይኗ መላኩን ብፈልግ ላየው አልቻልኩም ….እቤቱን ከዚህ በፊት በደንብ እደሚያውቅ ሰው ወደፎቅ የሚወስደውን ደረጃ የመቁጠር ያህል  በዝግታ እየረገጠች  ቀስ እያለች ሀንድሪሉን በአንድ እጇ ተደግፋ ወጣች….፡፡
ተራራ የመውጣት ያህል  ደከማት…. ስትደርስ መኝታ ቤቱ በራፍ ላይ ሁለት ወጣት ሴቶች ወገባቸውን በሻርፕ ጥፍንግ አድርገው አስረው በእንባ በመታጠብ እህህህ…. እያሉ በኮሪደሩ ላይ ይሽከረከራሉ…ዝም ብላ ችላ አለቻቸውና መኝታ ቤቱን ከፍታ ገባች…
ደረቷ ላይ ተደፍቶ ሲንሰቀሰቅ ነበር የደረሰችው…እሷ በቃ የለችም አምልጣቸዋለች….አንጀቴን በላኝ…‹‹አይዞህ›› ስለው ከተደፋበት ቀና ብሎ አየኝና
‹‹አይዞህ?ምን አይዞህ አለው…….?ጥላኝ ሄደች እኮ…ጨከነችብኝ..ብዙ ቃል ገብታልኝ ነበር..በቅርብ ቀን ድል ባለ ሰርግ ልንጋባ ቃል ገብታልኝ ነበር…ልጅ እደምተወልድልኝ ቃል ገብታለኝ ነበር..ቢያንስ 2 ዓመት እንደምትኖር ዓምኜ ነበር..ሀኪሞቹም እንደዛ ብለውኝ ነበር…››

‹‹አይዞህ… በቃ ተረጋጋ››

‹‹ተረጋጋ አትበይኝ…አንቺም እኮ ቃል ገብተሸልኝ ነበር…ግን ይሄው እሬሳዋን ከታቀፍኩ በኃላ ልታፌዥብኝ መጣሽ››

‹‹እስቲ ዞር በልልኝ››አለችው፡፡
የልጅቷን መሞት እና  የእሱን ሀዘን በማየቷ ምክንያት  ስምታ ይዛው የመጣችው ስካር በግማሽ ፐርሰንት በረደላት፡፡ 

‹‹ልነሳ….?ምን …በመገነዝ  ልትተባበሪኝ ነው..….?››ተነሳና ስሯ ቆሞ አፈጠጠባት፡፡

ገፍትራው እሱ በተነሳበት ቦታ ተተካችና ተቀመጠች ..እጇን ጭንቅላቷ ላይ አኖረችና አዕምሮዋን በመክፈት  ትኩረቷን ሰብስባ እጇን ግንባሯ ላይ አድርጋ የሚሆነውን መጠበቅ ጀመረቸ… ከ30 ሰክንድ በኃላ የእጇ ቀለሙ መቀየር እና ለሊት መዳወላቡ ላይ ተክሏን ስትቀነጥስ እዳጋጠማት  ሀመራዊ አይነት  ቀለም  ከውስጧ መፍለቅ ጀመረ ..
ከእሷ እጅ የፈለቀው ወደ ልጅቷ ጭንቅላት ሲገባና የእሷም በተመሳሳይ ሲቀየር ታየ…በዚህ አይነት ሁኔታ ለሁለት  ደቂቃ ያህል  ከቆየ በኃላ ጥቁር ጭስ የመሰለ ትነት ከጭንቅላቷ እየበነነ ወደቤቱ ኮርኒስ በመስገምገም በኖ መጥፋት ጀመር…ከዛ ህይወቷ ያለፈና  በድን የነበረችው ልጅ መንቀጥቀጥና መንዘፍዘፍ ጀመረች…ታአምር ተከሰተ…..
ከደቂቃዎች ቆይታ በኃላ  ልክ ከቀናት እንቅልፍ እንደናቃ ሰው አይኖቾን ገለጠችና አካባቢዋን መቃኘት ጀመረች…ፈገግ አለችና ቀና ብላ እንደሀውልት የተገተረውን መላኩን ተመለከተችው..አፉን እደከፈተና እነዛ ብርሀን የሚረጩ አይኖቾን እንደበለጠጣቸው በገረሜታ እያፈራረቀ ሲመለከታት አየችው…

‹‹የእኔ ፍቅር ምንድነው እየሆነ ያለው….?››አለችና በፍፅም ንቃት ከመኝታዋ ተነስታ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጠች…..ሶፊያ በጥርጣሬ እያየች‹‹አላወቅኩሽም ይቅርታ….?››ስትል ጠየቀቻት፡፡

‹‹አይ አታውቂኝም..ትንሽ አሞሽ ነበር…››

‹‹አረ ምንም የህመም ስሜት አይሰማኝም…እንደውም እንደዚህ ፍጽም ሰላማዊ የሆነ ስሜት ከተሰማኝ ዓመት አልፏታል ››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ..ለማንኛውም እኔ ሀኪምሽ ነኝ..አሁን ስራዬን ስለጨረስኩ ልሂድ››ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ፊት ለፊቱ ተገትራ ቆመች…..ምን እንዳዛ እንዳስቆማት አታውቅም…

‹‹አደረግሺው..እንደፎከርሽው አደረግሽው››ብሎ በመፍለቅለቅ ተጠመጠመባት…እንደዛ ሲያደርግ ፍቅረኛዬ ምን ታስብ ይሆን….? ብሎ እንኳን መጨነቅ አልፈለገም….

እሷም እንዳቀፋት ጆሮው ላይ ተለጠፋችና በማንሾካሾክ‹‹አዎ አድርጌዋለሁ…..ዛሬውኑ ወደሀኪም ቤት ውሰዳትና አስመርምራት…ሙሉ በሙሉ መዳኗን ካረጋገጡልህ ያው በተስማማነው መሰረት በሶስት ቀን ውስጥ ቃልህን እንድትተገብር እፈልጋለሁ..የእቤቴ አድራሻ …››አለችና ከለበሰችው ጂንስ ሱሪዬ ኪስ ውስጥ ቢዝነስ ካርዷን አውጥታ የለበሰው ጃኬት ኪስ ውስጥ ከተተችለት…፡፡
በዝግታ ከእቅፉ አወጣትና በመገረም አፍጥጦ ያየት ጀመር….እሷም አይኖቾን ሳትሰብር አፍጥጣ አየችው …ደስታው  በኖ በአንዴ  አመድ ነፋቶበታል…እንደደነዘዘ ባለበት ቆመ፡፡

..‹‹ሰሚራም ምንድነው እየተካሄደ ያለው ….?››ብላ በጥርጣሬ የተለወሰ ጥያቄዋን ስትደረድር እና  እየተካሄደ ስላላው ነገር ይበልጥ ለማወቅ በጥያቄ ሁለቱንም ስታፋጥጥ… ሶፊያ ከቆመችበት ስፍራ እግሮቾን በማነቃነቅ  የተዘጋውን የመኝታ ቤት በራፍ ከፍታ ወጣች…..
ስትመጣ ከነበራት በተሻለ ፍጥነት   ደረጃውን እየተንደረደረች ወርዳ ሳሎኑን ሰንጥቃ  በመውጣት የግቢው የውጭ በራፍ ጋር ስትደርስ ቅልጥ ያለ የእልልታ ድምጽ እቤቱን ሲያደበላልቀው ሰማች……ፈገግ አለች..
‹‹ይህ  የእነዚህ ሰዎች ደስታ እኔን ምን እንዳስከፈለኝ ቢያውቁ እንዲህ እልል አይሉም ነበር…ግን ምንድነው ለመላኩ ብዬው የመጣሁት?አሁን አስቲ ምን ማድረጌ ነው ….?››ስትል እራሷን ታዘበች፡፡በተስማማነው መሰረት በሶስት ቀን ውስጥ ትከፍለኛለህ ማለቷን ማመን አልቻለችም፡ ..በዛ ላይ እኮ የቤቷን አድርሻ ጭምር  ሰጥታዋለች‹‹..እስቲ ይሄ ደስታው ለዛሬ እንኳን ሙሉ ቢሆንለት ምን ነበረበት..….?ገና ለገና እኔ ስቃይ ውስጥ ነኝ ብዬ ሌላውን ሰውም እንዲሰቃይ ማድረግ ነበረብኝ..….?ደግሞ ለሳምንት ዕድሜዬ እንደዚህ ክፉ መሆን ምን የሚሉት ልበ ጠጣርት ነው ….….?››እራሷን በራሷ ገሰፀች
የመኪናዋን ሞተር በማስነሳት ከአካባቢው በፍጥነት ተፈተለከቸ….

     ይቀጥላል

#ክፍል 48,,እንዲለቀቀ (20) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_አርባ_ስምንት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

የሰው ልጅ ውስጡ ሲጨልምበት እና የመጨረሻ ተስፋው መቁረጥ ላይ ሲደርስ ብስጭቱን የሚያራግፍበት ወይም የሚያላክክበት ሶስት አካላት አሉ…መንግስት፤እግዚያሔር እና እናት ፡፡
የመንግስት እንዝለለው…እግዚያብሄርን ግን ሲከፋን ለምን ፈጠርከኝ….? ብለን እንጠይቀዋለን……መፈጠር ትፈጊያለሽ ወይስ ይቅርብሽ ብለህ ምርጫ ሳትሰጠኝ ለምን ፈጠርከኝ…….?እሺ ይሁን ካለፍላጎቴ ከፈጠርከኝሽ በኋላ ለምን እንደፍላጎቴ ልታኖረኝ አልቻልክም.?  ወይም ብትችል እንኳን ለምን አልፈለክም….? ብለን እንጠይቀዋለን…

እሱ በፍቃዱ እኛን መፍጠሩ እና እንደ እኛ ፍቃድ ሳይሆን እንደእራሱ ፍላጎትም የህይወት ጅረታችን  የሚፈስበትን መስመር ማስመሩ ስህተት አይመስልም...የሰው ልጅም ሲበሳጭ ፤ተስፋ ሲቆርጥና ሲማረር ለምን ….?ብለን እሱን መጠየቃችንም ስህተት አይደለም….የእግዚያብሄር ዋናው ጥቅም የህይወት ሸክማችንን ከብዶን ስንንገዳገድ ከመውደቅ ታድጎ እንዲያግዘን  እና የተሰበረ ተስፋችን እንዲጠግንልን የተንኮታኮተ ሞራላችን እንዲያክምልን ነው….ስለዚህ በከፋን ጊዜ ልንነጫነጭበት የግድ ነው…መነጫነጫችንም ክፋት የለውም፡፡
ከእግዜር ቀጥሎ በዚህ ጉዳይ የፈረደባት እናት ነች …አራት አመት ሆነን አርባ አመት ሁላችንም ውስጣችን ጨልሞ ነጋችንን ማለም ድክም ሲለን ወደ እናታችን ጉያ ሮጠን መሸጎጥ የመጀመሪያ ተግባራችን ነው፡፡ 

…እናታችንን በቅርብ አግኝተን የተመኘነውን ማድረግ ባንችል እንኳን ‹‹….እማዬ ለምን ወለድሺኝ….? ››ብለን ባትሰማንም ማማረራችን አይቀርም….በማማረሩ ውስጥ ምስጋና አለው…ለህልውናችን መሰረቷ ሰው ለመሆናችን ዋናዋ ምክንያቷ  እሷ ለመሆኗ እየተናገርን ለዛም እውቅና እየሰጠናት ነው…
አሁን እነኬድሮን ያሉት ደሎመና ነው…ትውልድ ሀገሯ፡፡ያሉት ሳር ቤት ውስጥ ግድግዳውን ተደግፎ በተሰራ እና ግዙፍ አጎዛ በተነጠፈበት ትልቅ መደብ ላይ ፤ ንስሯን ከጉያዋ አድርጋ እናቷ እግሯ ላይ ተኝታ እንባዋን እያንጠባጠበች ነው….አሁን ካሉበት የሳር ቤት ፊት ለፊት ባለአራት ክፍል ቢላ ቤት ቢኖራትም እናቷ ግን አትወደውም…በቃ አስገዳጅ ሆኖባት እንግዳ ካልመጣባት በስተቀር ውሎዋ እዛች ሳር ቤት ውስጥ ነው…ምግቡ እዛው ይሰራል እዛው ብና ይፈላል….እዛው ጋደም ይባላል…

‹‹ገራኮ ማል ታቴ….?››(ሆዴ ምን ሆንሽ….?)ትጠይቃለች እናቷ
ድምጽ ያላጀበውን እንባዋን ከማፍሰስ ውጭ መልስ ልትሰጣት አልቻለችም….እርግጥ ሊሆን ያለውን ነገር ለእሷ ልትነግራት እና ልትሰናበታት  ነው የመጣችው …ግን እንዲህ በቃላሉ ቃላት ከአንደበቷ ልታወጣ አልተቻላትም፡፡

‹‹ሆማ ኢንታኔ ሀርሜ ኮ..ነገኡማ ›( ….ምንም አልሆንኩ እናቴ…ደህና ነኝ)

‹‹ቀሮ ቲያ .ኢንሶቢን ….? ››(የእኔ ብልጥ አትዋሺኝ….?)

‹‹እማ ጨንቆኛል..በጣም ጨንቆኛል..መልሼ ወደሆድሽ ሁሉ መግባት አምሮኛል››

‹‹እኮ ንገሪኝ …እኔ እናትሽ እያለሁ ለማን ይድላው ብለሽ ትጨነቂያለሽ……?ደግሞ ባንቺ ጭንቀት አያምርም..አንቺ እኮ ለተጨነቀው ሁሉ መፍትሄ ስትሰጪ እንጂ ስትጨነቂ  አያምርብሽም››

‹‹እማ አሁን የገጠመኝ ግን ከባድ ችግር  ነው››

‹‹እኮ ምንድነው….?››

‹‹ልሄድ ነው››

ፈገግ አለች እናቷ‹‹እንቺ እኮ ገና ከልጅነትሽ ጡት ሳትጥይ ጀመሮ እንደሄድሽ ነው….ያንቺ መሄድ ምን አዲስ  ነገር ኖሮት ነው
ሊያስጨንቅሽ የቻለው…….?አይዞሽ ልጄ ንስርሽ ከጎንሽ እስካለ የትም ብትሄጂ ምንም ሀሳብ አይገባኝም..በዛ ላይ የእኔ የእናትሽ ፀሎት እና የአባትሽ መንፈስ በየሄድሽበት ሁሉ ይከተልሻል… ይጠብቅሻል፡፡››

‹‹ሀርሜ…ንስሬ አብሮኝ አይሄድም ….››

ባለማመን አፍጥጣ አየችት..ምክንያቱም ንስሯ ለአንድም ቀን ቢሆን ከእሷ የተለየበትን አጋጣሚ እናቷ አታስታውስም..እንደውም እናቷ ሁለት መንታ ልጇች አሉኝ ብላ ነው የምታወራው…ያው እንደሚታወቀው እናቷ በምትኖርበት አካባቢ በጣም የተከበረችና ሰው ሁሉ የሚፈራት  ነች‹‹….አረ ከዳቢሎስ የተወለደች ልጅ አለቻት …አንድ ነገር ብለን ብናስከፋ በልጇ ታስጠፋናለች….አታዩም እንዴ ልጇ እኮ አቅፋ የምትኖረውን ንስር ዳቢሎሱ አባቷ ነው የላከላት›› እያሉ በማንሾካሾክ እንደሚያሟት ታውቃለች……በዛም ምክንያት ሳይወዱ በግዳቸው ይፈሯታል..ስለሚፈሯትም በጣም ያከብሯታል….ግን ይህን ንስሯን የላከላት አባቷ መሆኑን ትጠራጠራለች እንጂ እርግጠኛ አይደለችም እንዴ….….?

‹‹ለምን ልጄ…?ለምንድነው አብሮሽ የማይሄደው….?››

‹‹የምሄድበት ቦታ እሱን ይዤ መሄድ አይፈቀድልኝም….ቢፈቀድልኝ እሱ አዛ መኖር አይችልም…. አየሩ አይስማማውም…››

ከተጋደመችበት ጭኖ ላይ ገፍትራ አስነሳቻትና እንድትቀመጥ አድርጋ ፊት ለፊት አፍጥጣ እያየቻት‹‹እንዴ ቅሪያ…እንዴት እሱን ጥለሽ መሄድ ታስቢያለሽ…….?የህይወት ጉዳይ  ቢሆን እንኳን ማድረግ የለብሽም..እሱን ጥለሽ ሄድሽ ማለት እኔንም አሳዝነሽ ሄድሽ ማለት ነው…በዕድሜሽ ለመጀመሪያ ጊዜ አዝንብሻለሁ››

‹‹ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው›ይሏችኋል ይሄ ነው..ከእሷ  ባሰች……በጣም ከባዱን ነገር ጭራሽ የበለጠ ጠጣር አደረገችባት፡፡

‹‹ሀርሜ ወዴት እንደምሄድ እኮ አልገባሽም….?››

‹‹ወደ የትም ይሁን አልኩሽ እኮ ..ንስርሽን ጥለሽ የትም መሄድ አትቺይም›› አለችና..ከእቅፌ ንስሬን መንጭቃ ወስዳ ጉያዋ ውስጥ ወሸቀችው…እሱም እጥፍጥፍ ብሎ ተሸጎጠላት፡፡

አፈረጠችው‹‹አባዬ ጋር ነው የምሄደው››
በእድሜዋ ሙሉ እናቷ በዚህ መጠን ስትደነግጥ አጋጥሞት አያውቅም..ሰው እንዴት እየታየ የሰውነት ቀለሙ እየተቀየረ ይሄዳል..?እንዴት እያያችሁት ደም ስሮቹ እየተወጣጠሩ እና ለእይታ ግልጽ እየሆኑ ይታያል….?ሰው እንዴት በሚያግለበልብ ሙቀት ውስጥ ሆኖ የአንታሪቲካ በረዶ ውስጥ እንደጣሉት ጥርሶቹ እርስ በርሳቸው ይንገጫገጫሉ….መልሰው ቃላት ለመለዋወጥ አያሌ ደቂቃዎች ነው ያሳለፈት…..

‹‹እንዴት አድረገሽ ነው የምትሄጂው….?››

‹‹ወገኖቹ ከስድስት ቀን በኃላ መጥተው ይወስዱኝል››

‹‹እሱስ ይመጣል….?››ጉጉት ባሰቃየው እይታ እያየች ጠየቀቻት
‹‹አይ እሱ እንዲመጣ የሚፈቅዱለት አይመስለኝ››

‹‹እሱስ ትክክል ነሽ…ግን እነሱስ እንደሚመጡ በምን አወቅሽ….?››

የሆነውን ሁሉ አስረዳቻት..ቀስ በቀስ በድንጋጤ ወይቦ የነበረው ፊቷ በደስታ እየደመቀ እና እየፈካ መጣ

‹‹እማ እየሳቅሽ እኮ ነው…….?››በገረሜታ ጠየቀቻት ..እያለቀሰችም እየሳቀችም መሆኗ ገርሞት

‹‹አዎ..በጣም ደስ ብሎኝ ነው››

‹‹እንዴ!! እንዴት ደስ ይልሻል..….?ከሄድኩ እኮ አልመለስም››

‹‹አውቃለሁ…ታውቂያለሽ አይደል ትናፍቂኛለሽ …. በጣም ነው የምወድሽ …ግን ወደአባትሽ ነው የምትሄጂው..ደግሞ በአንቺ ዕድሜ ሙሉ ለብቻዬ ተሸክሜው የኖርኩትን እወነቴን ዛሬ አንቺ አረጋገጥሺልኛል… እንዳልተሳሳትኩ አንቺ ልጄ ምስክር ነሽ…እንቡጥ ልጃገረድ ሆኜ ከሌላ አለም የመጣ ሰው መሰል ፍጡር አፍቅሬ እንደነበረ ….ወደእሱ የመኖሬያ አለምም ለአንድ ቀን ወስዶኝ እንደነበረ…የወለድኳት ልጅ አባትም እሱ እንደሆነ ለዘመድም ለጓደኞቼም ሳወራ ነበር የኖርኩት..ግን አውቃለሁ አንድም ሰው አምኖኝ አያውቅም ነበር…እንደውም ነካ እንደሚያደርግኝ ነው የሚስቡት…ዛሬ እወነቴን እንደነበርና ዕድሜዬን ሙሉ ያፈቀርኩት ፍቅር የእውነት እንደነበር አንቺም ተገንዝበኛል…በህይወቴ ሙሉ ከዚህ በላይ ምንም የሚያስደስተኝ ነገር ሊፈጠር
አይችልም››‹‹እማ እኔ እኮ የምታወሪውን ነገር አንድም ቀን ተጠራጥሬሽ አላውቅም…››

‹‹አመሰግናለሁ ልጄ…..….››ጎትታ ግንባሯን ደጋግማ ሳመቻት፡፡

‹‹ልጄ ለአባትሽ መልዕክት ታደርሺልኛለሽ….?››

‹‹አዎ.. ምን ልበልልሽ?››
‹‹ዕድሜዬን ሙሉ እሱን ብቻ ሳፈቅር እንደኖርኩ ንገሪልኝ…አንተ የከፈትከውን ጭኔን ሌላ ሰው እዲከፍተው ፈቅጄ በመሀከላችን የነበረውን ቅዱሱን  ፍቅራችንን ላሳንሰው ስላልፈለኩ እስከዛሬ በስምህ መልኩሼ እየኖርኩ ነው በይልኝ….እንደዛም በማድረጌ ከደስታ ውጭ አንድም ቀን ከፍቶኝ እንደማያውቅ ነግሪልኝ…ደግሞ ቆንጆና ብልህ ልጅ ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ…መልሼ ለአንተ ስልክልህም ደስ እያለኝ ነው በይልኝ፡፡››

የእናትዬው ንግግር አንጀቷን አላወሰው‹‹…እሺ ያልሺኝን ሁሉ እነግረዋለሁ››አለቻት፡፡

መቼስ እሷ ብቻ ሳትሆን እሱም በእሷ እድሜ ሙሉ መስዋዕት እየከፈለ እንደሆነ እና በወገኖቹ እንደጥፋተኛ ተቆጥሮ  እስራት ላይ እንደሚገኝ ባታውቅም ይሄንን ነግራት ደስታዋን ልታደፈርሰው እና እሷ ከሄደችም በኃላ ያለውን ህይወቷን ወደ ትካዜና ሀዘን ልትቀይረው ስላልፈለገች አሳዛኙኝ የታሪክ ክፍል  ደበቀቻት..፡፡

‹‹ልጄ››እናቷ ጠራቻት፡፡

‹‹ወይ ሀርሜ››

‹‹አይዞሽ አታስቢ ንስርሽን እኔ እንከባከበዋለሁ..ማለቴ  በአንቺ ፋንታ እኔን ይንከባከበኛል››

‹‹እስቲ እናያለን››አለቻት ..አዎ እናቷ እንዳለቸው ቢሆን እሷም ደስ ይላት ነበር..ግን እንደዚህ አይነት ተስፋ ከንስሯ አላየችም….እና አሁን በዚህ ሰዓት  እናቷን ይሆናልም አይሆንምም ልተላት አልደፈረችም፡…..

             ይቀጥላል

#ክፍል 49,,እንዲለቀቀ (20) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ቀን ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ

#ተከታታይ ልቦለድ

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ወደሸገር ተመልሰዋል..ማለት እሷ እና ንስሯ ፡፡ለእናቷ በመጨረሻው ቀን ተመልሳ እንደምታያትና ወደአባቷ ዘመዶችም በምትሄድበት ቀን አጠገቧ እንድትሆን እንደምትፈልግ   ነግራትና ቃል ገብታላት ነው የመጣችው፡፡
እስከዛው ያሉትን ቀጣዬቹን በስስት እየተሸራረፉ በመርገፍና በማለቅ ላይ ያሉትን ቀሪ 5  የሰቀቀን ቀናቶችን ሸገር ልታሳልፍ ወስናለች….ምን አልባትም አይታውቅም… በመሀል ሀሳቧን ልትቀይር ትችላለች፡፡
ግን አሁን ተረጋግታ እቤቷ መቀመጥ አልቻለችም … ሰዓቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ቢያልፍም ልትቆጣጠረው የማትችለው ከውስጧ ሚመነጭ ስውር ስሜት ውጪ ውጪ ይላት ጀመር….ልብሷን ቀያየረችና መኪናዋን ወዳለችበት መራመድ ከጀመረች በኃላ ሀሳቧን ቀየረችና ስልኳን አውጥታ ደወለች..አዎ ነፃ መሆን ነው የምትፈልገው….ላዳ ያለው የምታውቀው ልጅ ጋር ነው የደወለችው፡፡

‹‹ሄሎ››

‹‹ሰላም ነው… .ፈልጌህ ነበር…የት ነህ ያለኸው?››

‹‹ይቅርታ ዛሬ ስራ ላይ አይደለሁም መኪናዬ ተበላሽታ ገራዥ ነች››

‹‹በቃ አንተ ናልኛ ..የእኔ መኪና ስላለች ትይዝልኛለህ …ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆንኩ መንዳት አልፈለኩም››

‹‹ደስ ይለኝ ነበር.. ግን ያው ስራ የለኝም ብዬ ከከተማ ወጣ ብያለሁ…..ከፈለግሽ አንድ ጓደኛዬን ልልክልሽ እችላለሁ››

‹‹ደስ ይለኛል››

‹‹በቃ ንገረውና ቁጥርሽን ሰጠዋለሁ…ይደውልልሻል››

‹‹እሺ አመሰግናለሁ››ስልኳን ዘጋችውና ጊቢዋ ውስጥ እየተዘዋወረች እስኪደወልላት መጠበቅ ጀመረች….፡፡
ብዙም ሳይቆይ ስልኳ ላይ የማታውቀው ቁጥር ተንጫረረ …አነሳችው..አናገረችው ….በ15 ደቂቃ እንደሚደርስ ነገራት…..መጠበቅ ጀመረች…..

‹‹አዎ በዚህ ለሊት ምን አልባት ለመጨረሻ ጊዜ ማበድ እፈልጋለሁ..አዎ ብዙ ነገር ማድረግ አምሮኛል…የማሰብ አቅሜን አዳክሞ ጭንቀቴን የሚቀንስልኝን ማንኛውንም ነገር ለማድረግ እፈልጋለሁ…..መጠጣትና መስከር …መቁላላትና መዋሰብ እፈልጋለሁ…መጣላትና መደባደብም ካገኘሁ አልጠላም…››
እግዜር ይስጠው የመኪና ጥሩንባ ድምጽ ሰማች...ጎበዝ ልጅ ነው… በነገረችው ምልክት መሰረት ሳይሳሳት መምጣቱ አስደሰታት… በራፍን ከፈተችና ወጣች…በምልክት ጠራት … የላዳውን በራፍ ከፈተላትና ገባች፡፡

‹‹ወዴት ልውሰድሽ….?››

‹‹መጠጣት ነው የምፈልገው››አለችው፡፡

‹‹መጠጣት›› አላት ግራ ተጋብቶ፡፡

‹‹መጠጣት ስልህ …ብሽቅጥ እስክል መጠጣት ነው የምፈልገው…የፈለከውን ያህል ከፍልሀለሁ እስከንጋትም ቢሆን አብረኸኝ ትቆይና እቤቴ ታስገባኛለህ››

‹‹ይመችሽ ››አላት….

እንዲሁ ወደደችው…አንድን ሰው አይተን በውስጣችን ስለሰውዬው ደስ የሚል ስሜት ሲሰማን ውቃቢዬ ወዶታል  የምንለው ነገር አለ አይደል..….? እሷም ይሄን የላዳ ሹፌር  እንዳየችው  እንደዛ ነው የተሰማት፡፡

‹‹ምርጫሽ የት አካባቢ ነው?››

‹‹የፈለክበት ውሰደኝ ››

‹‹ቺቺኚያ ይመችሻል››

‹‹ይመችህ››

ነዳው….ንስሯ አምኗት እቤት ሊቀር አልቻለም  …ከፊት ለፊታቸው  በላዳዋ   ፍጥነት መጠን  ሲበር በመኪናዋ መስታወት አሻግራ አየችው….

ደረሱና መኪናዋን ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀበት ቦታ ፓርክ አድርገው አንዱ ጭፈራ ቤት ገቡ……እሷ ደረቅ አልኮለሏን ስታዝ እሱ ዉሀ አዘዘ..

‹‹ለምን ትንሽ አትሞከርም….? ››

‹‹አይ …የሞያዬ ስነምግባር አይፈቅድልኝም›› ሲል መለሰላት በቀልድ መልክ

..ዝም አለችው… በላይ በላዩ መለጋቱን ቀጠለች….የሙዚቃው ከጣሪያ በላይ ጩኸት…የለሊት ንገስታቶች በገዢ መሳይ  ወንዶች ዙሪያ መሽከርከር፤  በስካር የሚናውዙና የሚደንሱ ወንዶችና ሴቶች የሆቴሉን ወለል መሙላት…የሆነ ትርምስምስ ያለ ነገር ነው የሚታየው….በዛ ላይ መብራቱ በአምስት አይነት ቀለም በመፈራረቅ ቦግ ብልጭ ሲል  እይታን ብዥ ያደርጋል…….ግን በምትፈልገው መጠን ባይሆንም ተመችቷታል ፡፡ቢሆንም ደስታዋን ሙሉ ማድረግ ፈለገች…

‹‹ሌላ ጓደኛ የለህም….?››ድንገት ከመሬት ተነስታ ጠየቀችው፡፡

‹‹ምን አይነት….?››

‹‹ሹፌር››..

‹‹ምን ያደርግልሻል….?››

‹‹ያንተን መኪና የሚነዳልን››

‹‹እኔስ….?››አላት በጥያቄዋ ግራ ተጋብቶ

‹‹አይ አንተማ እንድታጣጣኝ ፈልጌ ነው..ብቻዬን ደበረኝ››

‹‹እ ..ቆይ እስኪ ደዋውዬ ልሞክር››አለና ስልኩን እየጎረጎረ ከሆቴሉ ወጣ..ሲወጣ ከጀርባው ሳታየው ነበር…ቁመናው መስጧታል..በቃ የተለመደው ችግሯ እያገረሸባት ነው..ጭኗ መካከል አሳከካት…ምን አይነት መጥፎ አመል ነው…እዛም አባቷ  አለም ስትሄድ እንዲህ የሚበላት ነገር ወቅት እየጠበቀ ይፈታተናት  ይሆን እንደዛ ከሆነ ምንድነው የምታደርገው….….?

ሀሳቧን ሳትጨርስ መጣና መቀመጫው ላይ ተመልሶ እየተቀመጠ..‹‹ተሳክቶል…ተቀላቅዬሻለሁ››አላት

በደስታ እየፈገገች‹‹ምን ይምጣልህ..?››ሥትል ምርጫውን ጠየቀችው፡፡

‹‹አንቺ የያዝሺውን…››
ሙሉ ጠርሙስ አዘዙ…መጣላቸው…… ይገለብጡት ጀመረ…እየደነሱ እየተቀመጡ …ደግሞ ተመልሰው በመነሳት እየደነሱ ..ውልቅልቃቸው እስኪወጣ ድረስ አስነኩት‹‹  …አቤት ዳንሱ !!ፕሮፌሽናል ነው ፡፡ልቤን ስልብ ነው ያደረገኝ…›አለች በዳንስ ችሎታው ተመስጣ፡፡ይበልጥ ሰውነቱ ላይ ተለጥፋ በተሸሻችው መጠን የጭኗ መብላላ  አደብ እየነሳት ነው…በትርምሱ መካከል በዳንስ ስልት በማሳበብ እጣቷን  ወደጭኗ በመስደድ   ይሉኝታ እስክታጣ ድረስ እያሻሸች  ነው..ደግነቱ ሁሉም በመጠጥ የደመቀ እና በመብራቱ ቦግ ብልጭ ብዥ ያለበት መሆኑ በጃት …
ከለሊቱ አምስት  ሰዓት አካባቢ ሲሆን ግን ተዳከሙ…

‹‹ቤት እንቀይር ….?››አለችው… ቤት መቀየር የፈለገችው ሙዳችውንም ጭምር መቀየር ስለፈለገች  ነው… ተስማማ ..ሂሳብ ዘግተው ወጡ…

‹‹ጭፈራ ቤት ሳይሆን ዝም ብለን የምንጠጣበት ቦታ ነው የምፈልገው…››

ወደላዳዋ ይዟት ሄደ …ቅድም ተጠርቶ የመጣው ጓዳኛውን ገቢና ቁጭ ብሎ ጫቱን ሲቀመቅም  አገኙት..ሁለቱም ተደጋግፈው ከኃላ ገቡ… ላዳዋ ተንቀሳቀሰች… በመስኮቱ አንጋጣ ሰማዮን ሰታይ ንስሯን ቀድሟት ለመብረር ሲያኮበኩብ አየችው…ሰካራሙ ጓደኛው እይታዋን ተከትሎ ወደውጭ በተመሳሳይ ሁኔታ  ካየ በኃላ‹‹ አይገርምም ይሄ አሞራ ቅድምም ስንመጣ ከፊት ለፊታችን ሲበር  ነበር….እርግጠኛ ነኝ የተለየ ከለር ስላለው አስተውዬው ነበር››አለ

‹‹አሞራ አይደለም..ንስር ነው››አረመችው 

‹‹እንዴ.. አዎ ንስር ነው ትክክል ..አንቺ ግን እንዴት አወቅሽ….?››

‹‹የእኔ ነው››በልበ ሙሉነት መለሰችለት፡፡

‹‹የእኔ ነው ስትይ….?››ያዝ ያዝ በሚያደርገው የስካር አንደበት ጠየቃት 

‹‹ወንድሜ ነው››

ሁለቱም ተንከትክተው ሳቁ

‹‹..ቀልደኛ ነሽ..ይበልጥ ስትጠጪ  ደግሞ ይብልጥ ቀልደኛ የመሆን ተስፋ አለሽ ማለት ነው››አላት፡፡

….አስረድቶ ማሰማንም ሆነ ተከራክሮ ማሸንፈ እንደማትችል ስለተረዳች‹‹ይሁንልህ›› አለችው ፡፡
መገናኛ አካባቢ ደርሱ… ብዙም ትርምስ የሌለበት እሷ የማታውቀው ሁለቱ ግን የሚያውቁት ሆቴል ይዘዋት ገቡ..ሹፌሩ ከላዳዋ አልወረደም…‹‹ጫቴን ብቅም ይሻለኝል›› ብሎ ቀረ …እነሱ ተያይዘው ገቡና የተገነጠለ እና ከታዳሚ የራቀ ወንበር ይዘው ተቀመጡ፡፡
ሙሉ ጠርሙስ ጎርደን ጅን አዘዙ
‹‹አረ ልባችን ትፈነዳለች››አላት
አልመሰለችለትም …መጠጡ መጥቶም ለተወሰኑ ጊዜ ከዲጄው የሚለቀቀውን ለስለስ ያለ ሙዙቃ በተመስጦ እያዳመጡ እና ከራሳቸው ሀሳብ ጋር እየተብሰለሰሉ ቆዩ…. ሰላሳ የሚሆኑ  ደቂቃዎች በየራሳችን ዝምታ ወስጥ ቆይተዋል..ግን ድንገት ስትባንን መጠጡ ግማሽ ጠርሙስ ተጋምሷል..ደነገጠች ….እሷ የተቀዳላት ብርጭቆ ግማሹን እራሱ አላጋመሰችም ..አጅሬ ላካ እየለጋው ነበር..‹‹ወይ ከእኔ የባሰ መጠጥ የራበው ነው እንዴ የገጠመኝ .….?››ስትል አሰበች፡፡ደግሞ ሲያዩት ገና ብዙ የመጠጣት አቅሙ እንዳለው ያስታውቃል….እንግዲህ ምንም ማድረግ አይቻልም አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ናቸው..፡፡ለእሷ እንዲህ መጠጡን መሳቡ ተመችቶታል..ብቻ እራሱን እስከመሳት ደርሶ ሰውነቱን ማዘዝ አያቅተው እንጂ ህሊናው እስኪቆለፍ ድረስ መጠጣቱ አሪፍ ነው ብላ አሰበች…‹‹እበላዋለሁ…ሌላ ተጽዕኖ ወስጥ ሳልከተው  በራሱ ፍላጎት አብሮኝ  እንዲያድር ማደረግ እፈልጋለሁ…እንደማንኛዋም ተራ ሴት ሆኜ ላሸነፈው  ነው የምፈልገው……ሰውኛ ማሸነፍ እንዲሆን …›ስትል እቅድ አወጣች፡

ድንገት ከመሬት ተነስታ‹‹ተጫወት›› አለችው፤

እሱም እንደመባነን አለና ‹‹እሺ …ባይዘወይ ኤርሚያስ እባላለሁ..››አላት

‹‹አሪፍ ስም ነው ..እኔን ሰፊ  በለኝ ››..
‹‹አይገርምም ማን ልበል ሳትይኝ እንዲሁ ከምድር ተነስቼ ኤርሚያስ አባላለሁ በማለት ከበሮ መደለቅ ምን የሚሉት እራስ ወዳድነት ነው..ኤርሚያስ ልባል ሚኪዬስ ለአንቺ ምን ይረባሻል፡፡ግን ያው ትረጂኛላሽ ብዬ አስስባለሁ…በመጀመሪያ እኔ በዚህች አለም ላይ ያለኝን ውክልና ለማሳወቅ ከስሜ መጀመር የግድ ይለኛል..ከስሜ ቀጥሎ ነው  ወደ ሌላ ጫወታ መግባት የምችለው ››

‹‹አረ ትክክል ነህ.. እንደውም እኮ  ገና እንደተገናኘን ነበር ስም መቀያየር የነበረብን ›› 

            ይቀጥላል

#ክፍል 50,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሃምሳ

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹ለማንኛውም ልድገምልሽ ኤርምያስ እባላለሁ…ለ15 ዓመት ያህል በማንዴላ ሀገር በሆነችው ደቡቡ አፍሪካ ጀሆንስበርግ ኖሬያለሁ… ወደሀገሬ ከተመለስኩ  ሁለት ዓመት ከግማሽ ሆኖኛል፡፡የ20ዓመት አፍላ ፍንዳታ ሆኜ ሄጄ የ35 ዓመት ሙሉ  ደንዳና ወጣት ሆኜ ተመለስኩ….››
‹‹አሀ ዲያስፖራ ነሀ….?››
‹‹አይ ዲያስፖራ ..!!! ‹ጽድቁ ቀርቶብኝ  በቅጡ በኮነነኝ ›ትላለች እናቴ… ለማንኛውም  እወነቱን ንገረኝ ካልሺኝ … በእነዛ ዓመታት ውስጥ በሰው ሀገር ላይ  ስዳክር ..ሞራሌን ከማንቆሻቆሽ…ሰው ሆኜ መፈጠሬን ከመጠየፍ እና ወጣትነቴ ላይ ጢቢ ጢቢ ከመጫወት ውጭ ምንም ያተረፍኩት ነገር አልነበረም…ብዙ ህልም በልቤ ብዙ ምኞት በውስጤ አጭቄ ነበር የተጓዘኩት …እርባነቢስ ሆኜ ባዶ እጄን በሀገሬ ለመሞት ብቻ ብዬ  ነበር የተመለስኩት …ይገርማል አይደል?
ሰው እንዴት ለመሞት ብሎ ከደብቡ አፍሪካ ድረስ ኪሎሜትሮችን አቆርጦ ይመጣል ትይኝ  ይሆናል..….?ለእኔ ግን ትርጉም ነበረው..››
‹‹ንገረኝ እስኪ ትርጉሙን…››ከሳዕታት ትርኪ ሚርኪ ወሬ እና መዛለል በኃላ ድንገት ምርር ወዳለ የህይወት ታሪክ ሀተታ መግባቱ አስደምሟታል አስደስቷታልም…አሁን እየነገራት  ያለውን ታሪክ እሱ ሳይነግራት እንደተለመደው  ወጭ እየጠበቀት ያለውን ንስሯን እንዲረዳት አድርጋ በዝርዝር ማወቅ ትችላለች..ግን አልፈለገችም …እንዲሁ እየጓጓችና ቀጥሎ ምን እንደሚናገር እየገመተች ቀጥታ ከራሱ አንደበት መስማቱ የሆነ የተለየ ስሜት ስለፈጠረባት ደስ ብሏታል…
ቀጠለ ‹‹በህይወቴ እያለሁ የመኖር ምኞቴ ሰልበው በድን አድርገውኝ …ወጣትነቴን ከንቱ አስቀርተውብኝ የመጨረሻውን ክስረት ማክሰራቸው ሳይበቃቸው …ከሞቴም በኃላ ክብር ስጋዬን  ለሀገራቸው ምድር  ልገብር …?አላደርገውም ፡፡ለዘላለም የባዕድ ሀገር አፈር ሆኜ መቅረት  አልፈለኩም  ..ይህ  መልካም አይደለም…ቢያንስ አገሬ እትብቴን በክብር በወርቃማ አፈሯ ውስጥ ቀብራ ከማንነቷ ጋር እንዳወሀደችው ሁሉ ስሞትም በድኔን በክብር ልትቀበለኝ እና ለዘላለም በጉያዋ ልትሸሽገኝ ይገባል..አዎ እንደዛ ነው መሆን ያለበት..በዛ ላይ እናቴን ለመጨረሻ ጊዜ ማየት እፈልጋለሁ… አያየኋት መሰናበት፤ስሮ በመኖር  እና እሷን መጦር ችዬ ላስደስታት  ባልታደልም… እጇ ላይ ሞቼ አልቅሳ ልትቀብረኝ እና እርሟን ለማውጣት እንድትችል ግን እድሉን ላመቻችላት ይገባል..አዎ ስመጣ እንደዛ ብዬ  እና እንደዛ ወስኜ ነበር …
‹‹ከዛስ….?››
‹‹ከደረስኩ ኋላማ … ቆይ ዛሬ ስል …ቆይ ትንሽ ልሰንብት ስል ..የመኖር ጉጉቴ ቀስ በቀስ ከሞተበት  እያንሰራራ እና እየተቀሰቀሰ መጣ..ምንም አግኝቼ አልነበረም ..ከእናቴ የማገኘው ተንሰፍሳፊ ፍቅር  እና ከጓደኞቼ የማገኘው ማፃናኛ …››
‹‹በጣም አሪፍ ታሪክ ነው ያለህ››
‹‹አዎ መራር የህይወት ገጠመኞች  ለሰሚው ወይም ለፅሀፊው ሳቢ ታሪክ ይወጣቸዋል…››
‹‹ከዛስ እንዴት ሀሳብህምን ሙሉ በሙሉ ልትቀይር ቻልክ….?››
‹‹አሁንም ሙሉ በሙሉ አልተውኩትም…አሁንም  የመሞት እቅዴ በውስጤ አለ…››
‹‹እሺ እንዴት ልታራዝመው ቻልክ….?››ጥያቄውን አስተካከለችለት፡፡
‹‹እንዴት መሰለሽ….ከዛ ከሰው ሀገር  በገንዘብም በመንፈስም ክስርስር ብዬ የመጣሁ ቢሆንም ብዙም ሳልቆይ ሚስኪን የልጅነት ጓደኞቼ  አዋጥተው አሁን የምጠቀምባትን ላዳ ገዝተው ሰጡኝ..በቃ የመሞት ሀሳቤን አራዘምኩት ..ለራሴ ሁለተኛ እድል ሰጠሁት..ቢያንስ ለጊዜው ሰርቼ ስጋዬን የማኖርበትን  ካገኘሁ አንድ ቀን ምን አልባት ሁለተኛውን የህይወት ምኞቴን በሆነ ተአምር ሊሳካልኝ ይችል ይሆናል…ብዬ ተስፋ አደረኩና መጨረሻውን እስከማይ ሁለት ዓመት ተኩል በሀገሬ ኖርኩ..ዘና ብዬ ለማንም ለምንም ሳልጨነቅ…ባሳኘኝ ሰዓት እየሰራሁ ሲያሰኘኝ ደግሞ እየተኛው..የእናቴን ሽሮ እየበላሁ ተስፋዬን በመጠበቅ እንሆ አለሁልሽ››
‹‹ምንድነው ተስፋህ..ማለቴ ይሳከልኛል ብለህ የምትጠብቀው….?››
‹‹የልጅነት ፍቅሬን… ..አንድ ቀን ቀና ብላ ታየኛለች የሚል ተስፋ..አንድ ቀን ከቄስ ትምህርት ቤት ጀምሮ እንደማፋቅራት እና ዕድሜዬን ሙሉ በልቤ ተሸክሜያት ስዞር እንደኖርኩ  ተረድታ በእቅፎ ታስገባኛለች ብዬ ተስፋ  በማድረግ..አንድ ቀን እጄ ትገባለች በሚል ተስፋ…..››

‹‹ወየው ጉዴ!!›አለኝች በውስጧ፡ በዚህ ቅርብ ጊዜ ውስጥ የምትቀርባቸውና የምትመኛቸው ወንዶች ሁሉ እንዴት እንዴት ሆኖና  ምንስ በሚሉት አጋጣሚ   እንደዚህ በፍቅር ስክር ያሉና የታወሩ ሆነው እንደሚገኙ ግልፅ ሊሆንላት አልቻለም...?‹‹ይሄኛውንስ ዛሬ አልምረውም…በፍጽም፡፡››ስትል ፎከረችው፡፡

‹‹ይቅርታ ሙሉ ታሪኩን እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ….››

‹‹እየነገርኩሽ እኮ ነው …እየተረተርኩልሽ…..ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል አይደል የሚባለው››

‹‹አይ እዚህ አይደለም…እኔ ቤት እንሂድና ተረጋግተን እየጠጣን ታወራልኛለህ….አሁን ሆቴሉም ሊዘጋ መሰለኝ››

‹‹ይቻላል››ይከራከረኛል  ወይም ይቃወመኛል ብላ ነበር የጠበቀችው ..ቀድሟት ተነሳ ..ሂሳብ ከፍላ ተከተለችው …. እየተወለጋገድና እርስ በርስ እየተደጋገፉ ላደው ድረስ ሄድ ..ሹፌሩ ተቀብሏቸው እቤት ድረስ አደረሳቸውና የለሊቱን ግዳጅ ጨረሶ  ተለያቸው.. 
እሷም ዛሬ ለዛውም ከመሸ ያወቀችውን ባለ ላዳ ይዛው  ወደቤቷ ገባች…..

            ይቀጥላል

#ክፍል 51,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሃምሳ_አንድ

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

መኝታ ቤቷ ገብታ ልብሷን ከቀያየረች በኋላ የጀመሩትን አይነት መጠጥ  አምጥታ ለሁለቱም ቀዳችና ወደጫወታቸውን እዲመለሱ ተመቻቸች..

‹‹እሺ አሁን ካቆምክበት ጀምርልኝ››

‹‹ምን….? ››አለት ሁሉን ነገር የረሳው ይመስላል

‹‹ታሪክህን እየነገርከኝ ነበር››

‹‹እ..አዎ…ግን የት ላይ  ነበር ያቆምኩት….?››

‹‹ስለፍቅረኛህ ጀምረህልኝ ነበር..በህይወት የምትኖርበት ምክንያት እሷን አንድ ቀን አገኛት ይሆናል በሚል ጉጉት ምክንያት እንደሆነ ነግረኸኝ ነበር ያቆምከው››

‹‹አዎ….አይገርምሽም …

እስከጥቂት ቀናት ድረስ እኮ ምንም አይነት ተስፋ አልነበረኝም…››
‹‹ቆይ ጠይቀሀት እንቢ ብላህ ነው….?››

‹‹አረ መጠየቅ…ትቀልጂያለሽ እንዴ ….?ቀና ብዬ እንኳን ሰላምታ ልሰጣት ድፍረቱ የለኝም.››

‹‹ግን እኮ እንደዛ አይነት ሰው አትመስልም..በጣም ደፋር ግልጽ እና በራስ መተማመን ያለህ ሰው ነህ››አለችው ከልቧ..

‹‹እኔም እንደዛ ነኝ ብዬ አምናለሁ..ፍቅር የሚባለው ነገር ግን ዋና ባህሪው ያልሆንሺውን ሆነሽ እንድትገኚ ማድረግ ይመስለኛል…እጅግ ክፉ የነበርሽው ሰው በፍቅር ውስጥ ስትሆኚ ስጋዬን ግፈፉት እስከማለት ድርስ የሚደርስ ደግነት ያጓናጽፍሻል….ደንዳናና ኮስታራ የነበርሽው፤አልቃሽና ተርበትባች ሆነሽ ቁጭ….ፍቅር እንደዛ  አይነት በሽታ ነው፡፡››

‹‹ቢሆንም ….ይህን ያህል ካፈቀርካት የሆነ ነገር ማድረግ ነበረብህ ..ለመሆኑ የት ነው የምትኖረው….?››

‹‹የሚገርመው እሱ ነው..በእሷ ቤት እና በእኔ ቤት መካከል ያለሁ እርቀት ግማሽ ኪሎ ሜትር አይሆንም…. ሁለታችንም ሳሪስ  በአንድ ሰፍር ተወልደን እዛው አንድ ሰፈር ያደግን ነን…ቤተሰቦቻን የአንድ እድር አባል ሆነው፤አንድ የጽዋ ማህበር መስርተው ዕድሜያቸውን በጉርብትና  የኖሩ ናቸው….አንድ ቄስ ትምህር ቤትፊደል መቁጠር ጀምረን   .አብረን ኤለመንተር የገባን የእድሜ እኩዬች ነን››

‹‹ይገርማል!!››

‹‹እውነትሽን ነው በጣም ይገርማል…. ከ1ኛ ክፍል አንስቶ እስከ አስረኛ ክፍል አብረን ነበር  የተማርነው…በተለይ ዘጠነኛ ክፍል አንድ ወንበር ላይ ነበር የምንቀመጠው…ግን በወቅቱ እኔ  ግማሽ ልቤ ነበር ክፍል ውስጥ የሚገኘው… እሷ ደግሞ አካሏም ነፍሶም ትምርቱ ላይ የተጣበቀ ነበር፡፡ግን የሚያመሳስለን አንድ ነገር ቢኖር  ሁለታችንም ተአምር ካልተፈጠረ በስተቀር ከትምህርት ቤት አንቀርም ነበር..››

‹‹ለምን ….?››አለችው ገለጻው ገርሞት

‹‹እሷ ለትምህርት ባላት ፍቅር የተነሳ እኔ   ደግሞ ለእሷ ካለኝ ፍቅር  የተነሳ….››

አሳቃት….ብርጭቆውን አንስቶ ከተጎነጨለት በኃላ ቀጠለ

‹‹እሷ እንደማንኛውም የክፍል ጓደኛ ግን ደግሞ ከዛም ትንሽ ከፍ ባለ የሰፈር ልጅነት እና አብሮ አደግነት ነው የምትቀርበኝ…እኔ ደግሞ በዚህ አለም ላይ ሁለት ሴቶች ብቻ ናቸው ያሉኝ.. እናቴ እና እሷ ብቻ..በቃ..ያኔ  አብሬት በምማርበት  በዛ ጊዜ ብቻ አልነበረም እንደዛ የሚሰማኝ.. አገር ለቅቄ  በስደትም እያለው እንደዛ ነበር  እምነቴ…የሆነች ሴት በሆነ ነገሮቾ ትንሽም እንኳን ከእሷ ጋር ካልተመሳሰለችልኝ..የሆነ የእሷን ነገር እንዳስታውስ  ካላደረገችኝ አንድ ደቂቃም ላወራት ወይም አጠገቧ ልቀመጥ አይቻለኝም….ከአስር አመት መለያየት በኃላ ከ10 ዓመት ናፍቆት በኃላ እሷን እና እናቴን አንዴ አይቼ ለመሞት ወስኜ  ወደሀገሩ ስመጣ…እሷን በተመለከተ ጭራሽ ተስፋ የሚያስቋርጥ ነገር ነው ያጋጠመኝ…፡፡አፍላ ልጃገረድ ገና አጎጠጎጤ ሆና ጥያት የሄድኳት  ልጅ አድጋና ፈክታ ሙሉ ሴት ሆና ጠበቀችኝ…፡፡የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሆና የተለየኋት  ልጅ ዶክተር ተብላ ትልቅ ሆስፒታል ውስጥ ትልቅ  ባለሞያ ሆና አገኘኋት..እና የሩቅ ህልሜ የነበረችው ልጅ ጭራሽ መቼም የማትፈታ ቅዠቴ እንደሆነች አሰብኩ…ሳያት በሩቅ መሸሽ ጀመርኩ፡፡ድንገት መንገድ ላይ ስንገጣጠም እንኳን   ቅንድቤን ከፍ ዝቅ በማድረግ አንገቴን አቀርቅሬ  ሰላምታ  ለመስጠት ከመሞከር ውጭ እሷ እንኳን ለሰላምታዬ አፀፋውን መመለሷ እና አለመመለሷን  እርግጠኛ ሆኜ አላውቅም፡፡ይህቺ ልጅ የእኔ ልጅነቴ ነች….የሩቅ እሩቅ ትዝታዬ …ብዙ ብዙ ለሊቶች በህልሜ ያየኋት… ብዙ ብዙ ታሪክ ያጫወተችኝ….ብዙ ብዙ ነገር ያወጋኋት…ያወጋችኝ..፡፡እንደዛ ብቻ ሳይሆን ደጋግሜ ያገባኋት…ብዙ ብዙ ልጆች የወለደችልኝ…ብዙ የሳምኳት፤ ብዙ የሳመችኝ…ብዙ ያፈቀርኳት፤ብዙ የወደደቺኝ…ግን ሁሉም በህልሜ የሆነ ነበር …››

‹‹ምን አይነት ፍቅር ነው..ስል አሰብኩ ደግሞ ከዚህች ልጅ ጋር የሚያመሳስለኝ አንድ ነገር ይኖር  ይሁን .. ….?አዎ መኖርማ አለበት ….እደዛ ቢሆን ነው ይሄን ሁሉ ሰዓት አብሮኝ ያሳለፈው…እቤቴ ድረስ ተከትሎኝ በለሊት የመጣው…አዎ እንደዛ ቢሆን ነው ሚስጥሩን ዘክዝኮ የሚነግረኝ…››ስትል የራሷን ግምት ወሰደች…ግምቷ እውነት ሆኖ  እስከአልጋ መዋደቅና መዋሰብ ድረስ ያደርሷቸው እንደሆነ አሁንም በውስጧ እያሳላሳላች ነው ፡
ቀጠለ እሱ…‹‹እና ይገርምሻል ከሶስት ቀን በፊት  ያልጠበቅኩት አጋጣሚ ተከሰተ…››

‹‹ምን ተከሰተ….?››

‹‹ወደሀገሬ ከተመለስኩ ከሁለት ዓመት ተኩል በኃላ   ትናንት….ድብር እና ጭፍግግ ብሎኝ ሰፈር ላዳዬ  አቁሜ እኔም ላዳዬ  ውስጥ ወንበሬን ወደኃላ ለጥጬ መፅሀፍ በማንበብ በተመስጦ ላይ እያለሁ...በሀይለኛው የላዳው የኃላዋ በራፍ ሲንኳኳ የሆነ  የእብድ ድርጊት መስሎኝ  በርግጌ ተነሳሁና  አንገቴን በመስኮት አስግጌ  ወደ ኃላው ተመለከተኩ…

‹‹እንዴ ሰላም…!!!!!››

‹‹ክፈትልኝ››

‹‹እሺ ››ተረብትብቼ ከፈትኩላት..ተስፈንጥራ ገባች…የሆነ ሰው ከኃላ እያባረራት ይመስላል..ፀጉሯ ሁሉ ጭብርር ብሏል…የአይኖቾ ደም መልበስ ምን አልባት ለቀናት ስታለቅስ እንደቆየች ምስክር ናቸው…..አለባበሶም እንደነገሩ እና ያልታሰበበት ነው….››የአመታት ህልሜ የሆነች ልጅ በእንዲህ አይነት ያልታሰበበት አጋጣሚ ላዳዬ ውስጥ ትገባለች ብዬ እንኳን ማሰብ አልሜ እንኳን አላውቅም…..

‹‹ንዳው ››አለችኝ
ህልም ውስጥ ያለሁ ነበር የመሰለኝ ፡፡ ትዛዞን ተቀብዬ  …ሞተሬን አንቀሳቀስኩ እና  ነደሁት

‹‹-የትኛው ፖሊስ ጣቢያ እንሂድ….?››ጠየቅኳት

‹‹የምን ፖሊስ ጣቢያ….?›› አለችን ግራ በመጋባት

-‹‹አይ እንዲሁ ነገር ስራሽን ስገመግመው  የሆንሽው ነገር ያለ ስለመሰለኝ ነው..››

‹‹ሆኜያለሁ...አዎ የሆነ ነገር ሆኜያለሁ… መች አልሆንኩም አልኩህ …ግን ወደ  ፖሊስ ጣቢያ መሄድ ምን ይፈይድልኛል..….?››አለቺኝ.‹‹ይቅርታ እሺ የት ልወስድሽ..….?››አልኳት
በመለማመጥ..እወነቴን ነው በዛች ላዳ ጆሀንስበርግ  አድርሰኝ ብትለኝ እንኳን እድሜ ልክ ይውሰድብኝ እንጂ እንቢ አልላትም…በምን አቅሜ…በእሷ መታዘዝ እኮ ለእኔ እድል ነው…የአለምን ህዝብ አጥፋልኝ ብትለኝ እንኳን ባልችልም  ከመሞከር ወደኃላ አልልም፡፡ 
‹‹እኔ እንጃ የሆነ ሰው እንደእኔ ሲሆን የት ነው የሚሄደው..….?ወይም የት ነው መሄድ ያለበት..››በቀላሉ ልመልሰው የማልችለውን ውስብስብና  ግራአጋቢ ጥያቄ ጠየቀችኝ ‹‹እኔ እንጃ ምን አልባት ቤተክሪስትያን ልውሰድሽ….?››ይሻል የመሰለኝን አማራጭ አቀረብኩላት ፡
‹‹ቤተክርስትያን….? ጭራሽ ቤተክርስትያን…በፍጽም… የደረሰብኝ መከራ  ሁሉ በእግዚያብሄር ትዕዛዝና ፍላጎት  ነው የሆነው..እንዲህ የቀጣኝ እሱ ነው…..ፍፅሞ ወደቤቱ አልሄድም..››ብላ ተንገሸገሸች
ምርጫውን ወደራሷ መለስኩት‹‹እሺ የት ልውሰድሽ…….?››

‹‹-መጠጥ ቤት…››

‹‹አልተከራከርኳትም..ነዳሁት….እስከለሊቱ 5 ሰዓት ብትን እስክትል ድረስ  እስክትጠጣ ጠበቅኳት …ከዛ አዝዬ ማለት ይቻላል አቤቷ አስገብቼያት ደስ ብሎኝም ከፍቶኝም ወደቤቴ ገባሁ….ደስ ያለኝ ከስንት አመት በኃላ ከእሷ ጋር ማውራት፤ከእሷ ጋር ጊዜ ማሳለፍ በመቻሌ ነው…የከፋኝ በዚያ አይነት በእሷ ባልሆነ ሀዘን፤ በእሷ ባልሆነ ምሬት ውስጥ በተዘፈቀችበት ሰአት ስለገኘኋት ነው …..

‹‹ከዛስ እንዴት ሆነ….?››ስትል ጠየቀችው.. በታሪኩ ከመመሰጧ የተነሳ ምሽቱን  ሙሉ ጭኖን  የሚበላት  የነበረው  ክፉ አመሏ ራሱ ቀንሶላት ነበር።

            ይቀጥላል

#ክፍል 52,,እንዲለቀቀ 👍(5) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄