አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
196K subscribers
5.06K photos
159 videos
14 files
760 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
👆👆👆 @coffeefc 👆👆👆

✔️ #ቅድመ_ጨዋታ_ዳሰሳ |

☕️ #ኢትዮጵያ_ቡና#ባህርዳር_ከተማ 🎽

በ21ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች መካከል በአዲስ አበባ ስታድየም የሚደረገውን #የኢትዮጵያ_ቡናን እና #ባህር_ዳር_ከተማን ጨዋታ በቅድመ ዳሰሳችን ተመልክተነዋል።

➡️ ባለፈው ሳምንት መቐለን ድል በማድረግ የፕሪምየር ሊግ ጉዟቸውን እያስተካከሉ ያሉት ባህር ዳሮች ዛሬ ደግሞ ሌላኛውን የአዲስ አበባ ክለብ ኢትዮጵያ ቡናን ከሜዳቸው ውጭ ያስተናግዳሉ።

📜 ዘንድሮ ወደ ሊጉ ከመጡ ሌሎቹ ክለቦች በተሻለ ሁኔታም ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ሳምንት ከወላይታ ዲቻ ጋ ተጫውተው አቻ የነበሩት ቡናዎች የዲቻው ሄኖክ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች በመሸነፋቸው ኢትዮጵያ ቡናዎች ወደ መሪዎቹ የሚጠጉበትን ዕድል መቀጠል ይችሉ የነበሩበትን ዕድል አበላሽተዋል ።

📄 #በመሆኑም እስካሁን ሁለቱ ክለቦች በሚገናኙበት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ሙሉ ነጥብ በማግኘት ከተጋጣሚው ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለመስተካከል ባህርዳር ደግሞ ሦስት ነጥብ ይዞ በመመለስ የሳምንቱን ውጤት ለመድገም እንደሚፋለሙ ይጠበቃል።

📈 #በሌላ_በኩል ጉዳት ላይ ከነበሩት የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋቾች መካከል ግዙፉ አጥቂ #ሱለይማን_ሉኮዋ ፣ ተከላካዩ #ተመስገን_ካስትሮ#ሚኪያስ_መኮንን#ንታምቢ እንዲሁም በረኛው #ዋቴንጋ አሁንም ጉዳት ላይ የሚገኙ በመሆኑ ከዛሬው ጨዋታ ውጪ ሆነዋል።

💧 💧#ባህር_ዳር_ከተማ ከሜዳውም ውጪ በማጥቃት ላይ የተመሰረተ አጨዋወትን የሚተገብር ከመሆኑ አንፃር ሲታይ የዛሬው ጨዋታ ፈጠን ያለ እና በሙከራዎች የታጀበ እንደሚሆን ይገመታል።

💧 #ባህር_ዳሮች ከኋላ ተመስረተው የሚመጡ ኳሶችን በዋነኝነት #በዳንኤል_ኃይሉ እና #ኤልያስ_አህመድ የአማካይ ክፍል ጥምረት ለሦስትዮሹ የፊት መስመር ጥምረታቸው ግብዓት የሚያደርጉ ይሆናል።

🦋 ይህም ሁለቱ የማጥቃት አማካዮች #ከሄኖክ እና #አማኑኤል_ዮሃንስ ጋር የሚገናኙባቸውን ቅፅበቶች እንድንጠብቅ ያደርገናል።

▪️ ከዚህ በተጨማሪም በማጥቃት ላይ አብዝተው የሚሳተፉት የኢትዮጵያ ቡና የመስመር ተከላካዮችም ከባህር ዳር የመስመር አጥቂዎች ከነ #ግርማ_ዲሳሳ ጋር ከባድ ፍልሚያ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

📌 #የእርስ_በርስ_ግንኙነት_እና_እውነታዎች

📍 ክለቦቹ በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ የሚገናኙበት ሁለተኛው ጨዋታ ይሆናል።

🌼 በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ፍጻሜ ጥቅምት ወር ላይ ተገናኝተው ኢትዮጵያ ቡና አሸንፎ ዋንጫ ማንሳቱ የሚታወስ ነው፡፡ ነገር ግን በ ፕሪምየር ሊጉ በመጀመርያው ዙር ባህር ዳር ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን ማሸነፉ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው ።

💧 #ባህርዳር_ከተማ ካደረጋቸው 20 ጨዋታዎች ባለፈው ሳምንት ውጤት በማስመዝገቡ በ 32 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በአንፃሩ #ኢትዮጵያ_ቡና በ 20 ጨዋታ ባለፈው ሳምንት በዲቻ በመሸነፉ በ 29 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ።

🔻 #ግምታዊ_አሰላለፍ 🔻

☕️☕️ #ኢትዮጵያ_ቡና (4-3-3)

#ወንደሰን

👤 #አህመድ_ረሺድ
👤 #ቶማስ_ስምረቱ
👤 #እያሱ_ታምሩ
👤 #ተካልኝ_ደጀኔ

👤 #ሄኖክ_ካሳሁን
👤 #አማኑኤል_ዮሐንስ
👤 #ካሉሻ_አልሀሰን

👤 #ሁሴን_ሻባኒ
👤 #አቡበከር_ነስሩ
👤 #አስራት_ቱንጆ

#ሁሌም_እንደምንለው_መልካም_ዕድል_የሀገሩን_ስም_ከፊት_ላስቀደመው_ኢትዮጵያ_ቡና

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
👆👆👆 @coffeefc 👆👆👆
አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
👆👆👆 @coffeefc 👆👆👆

​​🔴 #ጅማ_አባ ጅፋርከኢትዮጵያቡና ☕️

▪️ ጅማ አባ ጅፋር ከ27 ቀናት በኋላ ወደ ሜዳ ሲመለስ የደረጃ ለውጥ ባይፈጥርለትም አራተኛ ደረጃ ላይ ወደ ተቀመጠው ቅዱስ ጊዮርጊስ ለመቅረብ የሚረዳውን ጨዋታ በሊጉ አጋማሽ ከሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ጋር ያደርጋል።

▪️ በአንፃሩ ጨዋታው ከረጅም ውዝግብ በኋላ ከመቐለ ጋር ማክሰኞ ዕለት ለተጫወቱት ኢትዮጵያ ቡናዎች ወደ ስድስተኛ ደረጃ ከፍ የማለት ዕድልን ሊያስገኝላቸው ይችላል። ጅማዎች አምበላቸው መስዑድ መሀመድ ከጉዳት የተመለሰላቸው ሲሆን የቀኝ መስመር ተከላካያቸው ዐወት ገብረሚካኤል መሰለፍ ብቻ አጠራጣሪ ሆኗል። በኢትዮጵያ ቡና በኩል ደግሞ ተመስገን ካስትሮ እና ሚኪያስ መኮንን በጉዳት ክሪዚስቶም ንታንቢ እና ሀሰን ሻባኒ ደግሞ በብሔራዊ ቡድን ጥሪ ምክንያት ከቡድኑ ጋር አይኖሩም። 

🔻 #የእርስ\በርስ_ግንኙነት_እና_እውነታዎች🔻

▪️ ጅማ አባ ጅፋር ወደ በሊጉ ከቡና ጋር በተገናኘባቸው ሦስት  ጨዋታዎች አልተሸነፈም ፤ ሁለቱን በ2-0 እና 1-0 ውጤቶች አሸንፎ አንዴ ያለግብ ተለያይቷል።  

▪️ ለ11ኛ ጊዜ ከአዲስ አበባ ስታድየም ውጪ የሚጫወተው  ኢትዮጵያ ቡና ሁለት የድል እና ሦስት የአቻ ውጤቶችን ሲያስመዘግብ ስድስት ጊዜ ተሸንፏል። 

▪️ ጅማዎች በሜዳቸው 13 ተጋጣሚዎችን ያስተናገዱ ሲሆን ሽንፈት ሳይገጥማቸው ስድስቱን በድል ሰባቱን ደግሞ በአቻ ውጤት አጠናቀዋል። 

👨 #ዳኛ

▪️ ጨዋታውን ተፈሪ አለባቸው በመሀል ዳኝነት ይመራዋል። እስካሁን በሰባት ጨዋታዎች በመሀል ዳኝነት የተመደበው ተፈሪ 38 የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመዝ አንድ የሁለተኛ ቢጫ ፣ ሁለት የቀጥታ የቀይ ካርዶች እና አራት የፍፁም ቅጣት ምት ውሳኔዎችንም አሳልፏል። 

#ግምታዊ_አሰላለፍ

☕️ #ኢትዮጵያ_ቡና (4-3-3) ☕️

#ዋቴንጋ_ኢስማ

👤 ኃይሌ ገ/ትንሳይ
👤 ወንድይፍራው ጌታሁን
👤 ቶማስ ስምረቱ
👤 ተካልኝ ደጀኔ

👤 አስራት ቱንጆ
👤 አማኑኤል ዮሀንስ
👤 ዳንኤል ደምሴ

👤 እያሱ ታምሩ
👤 አቡበከር ናስር
👤 አህመድ ረሺድ

🔴 #ጅማ_አባጅፋር (4-4-2) 🔴

                             
#ዳንኤል_አጄይ

👤 ተስፋዬ መላኩ
👤 ከድር ኸይረዲን
👤 አዳማ ሲሶኮ
👤 ኤልያስ አታሮ

👤 ዲዲዬ ለብሪ
👤 መስዑድ መሀመድ
👤 ይሁን እንዳሻው
👤 አስቻለው ግርማ

 👤 ማማዱ ሲዲቤ
👤 ኦኪኪ ኦፎላቢ

© #soccer_ethiopia


ሼር➢ @coffeefc
ሼር➢ @bunnafc
ቅድመ ዳሰሳ | #ድሬዳዋ_ከተማ#ኢትዮጵያ_ቡና


👉 በድሬዳዋ ስታዲየም የሚደረገው የድሬዳዋ ከተማ እና የኢትዮጵያ ቡና ጨዋታን እንደሚከተለው ዳሰነዋል።

የስምዖን ዓባይ ቡድን በ4ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ወደ ባህር ዳር አቅንቶ የደረሰበትን የ4-1 ሽንፈት ለማካካስ አልሞ ነገ ወደ ሜዳ ይገባል። የተደራጀ የተከላካይ መስመር እንደሌለው የታየው ቡድኑ በሊጉ ከሚሳተፉ 16 ክለቦች ከፍተኛ ግብ በማስተናገድ ቀዳሚው ነው(11)። ነገም ቡድኑ በያዘው የተፍረከረከ የተከላካይ ክፍሉ ከሰሞኑ ከፍተኛ መነቃቃት ላይ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቡና ጥቃት ለማቆም ሊቸገር እንደሚችል ተገምቷል። ከዚህ ውጪ ቡድኑ ከማጥቃት ወደ መከላከል በሚያደርጋቸው የዘገዩ ሽግግሮች ክፍተቶችን ለተጋጣሚ ሊሰጥ እንደሚችል ይታሰባል። በተለይ ይህ ጉዳይ ባሳለፍነው ሳምንት በባህር ዳር ሽንፈት ሲያስተናግድ በጉልህ ታይቷል።

➡️ ቡድኑ ካለበት የመከላከል ድክመት እና ከተጋጣሚው የጨዋታ ዘይቤ የተነሳ ከባለፈው ሳምንት የተጨዋች አደራደር ቅርፁ (ፎርሜሽን) ለውጦችን እንደሚያደርግ ይጠበቃል። ምክንያቱም ኢትዮጵያ ቡናዎች በኳስ ቁጥጥር የጨዋታውን ሚዛን ወደ ራሳቸው ለማድረግ ስለሚጥሩ ቡድኑ የመሃል ሜዳ ተጨዋቾችን እንደሚያበዛ ይታመናል። ይህም ሂደት ቡድኑ በጨዋታው ብልጫ እንዳይወሰድበት ያደርጋል ተብሎ ይታሰባል። ቡድኑ የመከላከል ችግሮች ቢኖሩበትም የነገው ጨዋታ በሜዳው እንደመሆኑ ችግሮቹ በመጠኑ ሊሸፈኑ እንደሚችሉ ይታሰባል። ከዚህ በተጨማሪም ቡድኑ ከጨዋታዎች ርቆ የነበረውን አምበሉ ሳምሶን አሰፋ ነገ ሊያገኝ ስለሚችል መነቃቃቶች ሊኖሩ ይችላሉ።

ምንም የተጨዋች ቅጣት የሌለበት ቡድኑ ያሬድ ሃሰን እና ሳምሶን አሰፋን (መሰለፉ ቢያጠራጥርም) ከጉዳት ሲያገኝ ምንያህል ተሾመ እና ረመዳን ናስርን በተቃራኒው ከስብስቡ ውጪ አድርጓል።

🔰 ከጨዋታ ጨዋታ መሻሻል እያሰየ የሚገኘው የካሳዬ አራጌው ኢትዮጵያ ቡና ባሳለፍነው ሳምንት ከፍፁም የጨዋታ ብልጫ ጋር ሃዋሳ ከተማን ማሸነፍ ይታወሳል። ቡድኑ በመጨረሻ ሶስት የሊጉ ጨዋታዎች ከወትሮው በተለየ ወደፊት የሚደረጉ የኳስ ቅብብሎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ለድሬዳዋ ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል ያሳያል። በተለይ በሃዋሳው ጨዋታ ሲጠቀምበት የነበረው የተደራጀ የማጥቃት ሂደት ለቡድኑ ግርማ ሞገስን አጎናፅፎታል። የሜዳውን ስፋት በመስመር አጥቂዎቻቸው የሚጠቀሙት ኢትዮጵያ ቡናዎች የተጋጣሚን (ድሬዳዋ ከተማ) የመከላከል አደረጃጀት ሊረብሽ እንደሚችል ተገምቷል። ከዚህ የመስመር አጨዋወት በዘለለ የፊት መስመር ተጨዋቾቹ ፍጥነት እና ቅልጥፍና ነገም ቡድኑን ሊጠቅም እንደሚችል ይጠበቃል።

✔️ ምንም እንኳን ቡድኑ ከጨዋታ ጨዋታ እየተሻሻለ ቢመጣም ኳስ ከግብ ክልሉ ጀምሮ ለመመስረት የሚያደርገው ጥረት አደጋዎችን ራሱ ላይ ሊጋብዙ በሚችሉ መንገዶች እንደሆነ ታይቷል። ከዚህ የተነሳ የድሬዳዋ ተጨዋቾች ተጭነው የሚጫወቱ ከሆነ በጎ ነገሮችን ለቡድናቸው ሊያመጡ ይችላሉ። ቡድኑ ካለበት የኳስ አመሰራረት ችግር በተጨማሪ የአጨራረስ ብቃቱ ነገ ዋጋ እንዳያስከፍለው ያሰጋል። ምንም እንኳን ቡድኑ ባሳለፍነው ሳምንት ሃዋሳን 4-1 ቢያሸንፍም በእለቱ ሲገኙ የነበሩ ጥሩ ጥሩ አጋጣሚዎችን ሲያመክን ታይቷል። እንደ ባለሜዳዎቹ ሁሉ ምንም የቅጣት ዜና የሌለባቸው ቡናማዎቹ በነገው ጨዋታ የታፈሰ ሰለሞን እና የአቡበከር ናስርን ግልጋሎት ያገኛሉ።

#እርስ_በርስ_ግንኙነት

☑️ ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ለ16 ጊዜያት ያህል ተገናኝው ኢትዮጵያ ቡና ገሚሱን (8) በማሸነፍ የበላይ ሲሆን 5 ጊዜ አቻ ተለያይተው በ3 አጋጣሚዎች ድሬዳዋ ከተማ አሸንፏል።

በ16ቱ ግንኙነቶች 39 ጎሎች ሲቆጠሩ 25 ጎሎች ቡናማዎቹ ያስቆጠሯቸው ናቸው። ቀሪዎቹ 14 ጎሎችን ብርቱካናማዎቹ አስቆጥረዋል።

#ግምታዊ_አሰላለፍ

#ድሬዳዋ_ከተማ (4-2-3-1)

ፍሬው ጌታሁን

ያሬድ ዘውድነህ – በረከት ሳሙኤል – ዘሪሁን አንሼቦ – አማረ በቀለ

አማኑኤል ተሾመ – ዋለልኝ ገብሬ

ያሬድ ታደሰ – ኤልያስ ማሞ – ሳሙኤል ዘሪሁን

ሪችሞንድ ኦዶንጎ

#ኢትዮጵያ_ቡና (4-3-3)

ተ/ማርያም ሻንቆ

አህመድ ረሺድ – ፈቱዲን ጀማል – ወንድሜነህ ደረጀ – አስራት ቱንጆ

ታፈሰ ሰለሞን – ዓለምአንተ ካሣ – አማኑኤል ዮሐንስ

አቤል ከበደ – እንዳለ ደባልቄ – አቡበከር ናስር

© ሶከርኢትዮጵያ

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈