አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
183K subscribers
4.94K photos
156 videos
14 files
750 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
👆👆👆 @coffeefc 👆👆👆

✔️ #ቅድመ_ጨዋታ_ዳሰሳ |

☕️ #ኢትዮጵያ_ቡና#ባህርዳር_ከተማ 🎽

በ21ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች መካከል በአዲስ አበባ ስታድየም የሚደረገውን #የኢትዮጵያ_ቡናን እና #ባህር_ዳር_ከተማን ጨዋታ በቅድመ ዳሰሳችን ተመልክተነዋል።

➡️ ባለፈው ሳምንት መቐለን ድል በማድረግ የፕሪምየር ሊግ ጉዟቸውን እያስተካከሉ ያሉት ባህር ዳሮች ዛሬ ደግሞ ሌላኛውን የአዲስ አበባ ክለብ ኢትዮጵያ ቡናን ከሜዳቸው ውጭ ያስተናግዳሉ።

📜 ዘንድሮ ወደ ሊጉ ከመጡ ሌሎቹ ክለቦች በተሻለ ሁኔታም ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ሳምንት ከወላይታ ዲቻ ጋ ተጫውተው አቻ የነበሩት ቡናዎች የዲቻው ሄኖክ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች በመሸነፋቸው ኢትዮጵያ ቡናዎች ወደ መሪዎቹ የሚጠጉበትን ዕድል መቀጠል ይችሉ የነበሩበትን ዕድል አበላሽተዋል ።

📄 #በመሆኑም እስካሁን ሁለቱ ክለቦች በሚገናኙበት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ሙሉ ነጥብ በማግኘት ከተጋጣሚው ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለመስተካከል ባህርዳር ደግሞ ሦስት ነጥብ ይዞ በመመለስ የሳምንቱን ውጤት ለመድገም እንደሚፋለሙ ይጠበቃል።

📈 #በሌላ_በኩል ጉዳት ላይ ከነበሩት የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋቾች መካከል ግዙፉ አጥቂ #ሱለይማን_ሉኮዋ ፣ ተከላካዩ #ተመስገን_ካስትሮ#ሚኪያስ_መኮንን#ንታምቢ እንዲሁም በረኛው #ዋቴንጋ አሁንም ጉዳት ላይ የሚገኙ በመሆኑ ከዛሬው ጨዋታ ውጪ ሆነዋል።

💧 💧#ባህር_ዳር_ከተማ ከሜዳውም ውጪ በማጥቃት ላይ የተመሰረተ አጨዋወትን የሚተገብር ከመሆኑ አንፃር ሲታይ የዛሬው ጨዋታ ፈጠን ያለ እና በሙከራዎች የታጀበ እንደሚሆን ይገመታል።

💧 #ባህር_ዳሮች ከኋላ ተመስረተው የሚመጡ ኳሶችን በዋነኝነት #በዳንኤል_ኃይሉ እና #ኤልያስ_አህመድ የአማካይ ክፍል ጥምረት ለሦስትዮሹ የፊት መስመር ጥምረታቸው ግብዓት የሚያደርጉ ይሆናል።

🦋 ይህም ሁለቱ የማጥቃት አማካዮች #ከሄኖክ እና #አማኑኤል_ዮሃንስ ጋር የሚገናኙባቸውን ቅፅበቶች እንድንጠብቅ ያደርገናል።

▪️ ከዚህ በተጨማሪም በማጥቃት ላይ አብዝተው የሚሳተፉት የኢትዮጵያ ቡና የመስመር ተከላካዮችም ከባህር ዳር የመስመር አጥቂዎች ከነ #ግርማ_ዲሳሳ ጋር ከባድ ፍልሚያ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

📌 #የእርስ_በርስ_ግንኙነት_እና_እውነታዎች

📍 ክለቦቹ በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ የሚገናኙበት ሁለተኛው ጨዋታ ይሆናል።

🌼 በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ፍጻሜ ጥቅምት ወር ላይ ተገናኝተው ኢትዮጵያ ቡና አሸንፎ ዋንጫ ማንሳቱ የሚታወስ ነው፡፡ ነገር ግን በ ፕሪምየር ሊጉ በመጀመርያው ዙር ባህር ዳር ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን ማሸነፉ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው ።

💧 #ባህርዳር_ከተማ ካደረጋቸው 20 ጨዋታዎች ባለፈው ሳምንት ውጤት በማስመዝገቡ በ 32 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በአንፃሩ #ኢትዮጵያ_ቡና በ 20 ጨዋታ ባለፈው ሳምንት በዲቻ በመሸነፉ በ 29 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ።

🔻 #ግምታዊ_አሰላለፍ 🔻

☕️☕️ #ኢትዮጵያ_ቡና (4-3-3)

#ወንደሰን

👤 #አህመድ_ረሺድ
👤 #ቶማስ_ስምረቱ
👤 #እያሱ_ታምሩ
👤 #ተካልኝ_ደጀኔ

👤 #ሄኖክ_ካሳሁን
👤 #አማኑኤል_ዮሐንስ
👤 #ካሉሻ_አልሀሰን

👤 #ሁሴን_ሻባኒ
👤 #አቡበከር_ነስሩ
👤 #አስራት_ቱንጆ

#ሁሌም_እንደምንለው_መልካም_ዕድል_የሀገሩን_ስም_ከፊት_ላስቀደመው_ኢትዮጵያ_ቡና

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
👆👆👆 @coffeefc 👆👆👆