አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
183K subscribers
4.94K photos
156 videos
14 files
750 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
‍ ‍አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
👆👆👆 @coffeefc 👆👆👆

#የሻማ_ማብራት_ስነስርዓት

ስታድየም ውስጥ #ከማን_አንሼ በወንበር የሚያስተባብር እንዲሁም የኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊ የሆነው #ግሩም_ያሲን ህይወቱ ማለፉ ይታወቃል በመሆኑም ነገ 11:30 ጀምሮ #የሻማ_ማብራት ስነስርአት ስለሚካሄድ
#የቡና_ደጋፊ የሆናችሁ ወንድማችንን ቤታቸው ሄደን ቤተሰቦቹን እንድናፅናና እናሳስባለን ።

ለቤተሰቦቹ ፣ ለቡና ደጋፊዎች ፣ ለጔደኞቹ እና ዘመዶቹ እንዲሁም ለእግር ኳስ አፍቃሪዎች በሙሉ በ (#አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጲያ ቡና አደገኞቹ)ስም መፅናናትን እንመኛለን የወንድማችንንም ነፍስ ይማርልን ። 😢
ማልያ መልበስ እንዳይረሳ
@coffeefc @bunnafc @coffeefc
👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ👆

#አረንጓዴ_አሻራ_በቡናማዎቹ
@coffeefc @bunnafc @coffeefc
👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ👆

#አረንጓዴ_አሻራ_በቡናማዎቹ
@coffeefc @bunnafc @coffeefc
👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ👆

#አረንጓዴ_አሻራ_በቡናማዎቹ
@coffeefc @bunnafc @coffeefc
👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ👆

#አረንጓዴ_አሻራ_በቡናማዎቹ
#ደስ የሚል ድባብ ነበር ተጋበዙልን

@coffeefc @bunnafc @coffeefc


❗️ #የኢትዮጵያ_የወንዶች የእግር ኳስ ተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ሐምሌ 25/2011 ዓ·ም መከፈቱ ይታወቃል። በተጨማሪም #የኢትዮጵያ_እግር_ኳስ_ፌደሬሽን የዝውውር መስኮቱ ከሐምሌ 25/2011 እስከ 2012 የኢትዮጵያ #ፕሪሚየር_ሊግ እስከሚጀምርበት ቀን እንደሚቆይ ማስታወቁ ይታወሳል።

❗️ #የኛ_ኢትዮጵያ_ቡና የ2011 ክፍተቶችን ሞልቶ በ ጥሩ ተጨዋቾች ጠንካራ ቡድን ይዞ ይመጣ ይሆን የሚለው የብዙዎቻችን ጥያቄ እና ጉጉት እንዳለ ነው።


❗️እንደ አምናው ስህተቶችን ሳይፈፅም ክለባችን በጥሩ ስኳድ ለ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ይቀርባል እናም በክለባችን የተወሰኑ ልጆችን ክለቡ ያናገረ በመሆኑ እና በ ቢሮ #ፊርማቸውን ያሰፈሩ ተጨዋቾች አሉ።

ከእነሱ መካከል #የሜዲካል_ምርመራውን ጨርሶ ለ ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ተጨዋች ዛሬ እንደፈረመ ለማወቅ ችለናል ።

⚽️ #በረከት_አማረ ይባላል #ወልዋሎ አ ይጫወት የነበረ ነው

#ስም :– በረከት አማረ
#የተወለደበት ቀን: –1999
#ክብደት: - 65KG
#ቁመት: - 1.77
#የሚሰለፍበት ቦታ : - በረኛ
#የተወለደበት ቦታ : - አዲግራት
#አሁን ያለበት ክለብ : - ኢትዮጵያ ቡና

#ከዚህ_በፊት_የተጫወተባቸው_ክለቦች

#2005 ሁመራ
#2006-2007 አማራ ውሃ ስራ (ኣውስኮድ)
#2008-2011 ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ የተጫወተ ሲሆን
ከ 2012–2013 መጨረሻ ድረስ ሁለት አመት የሚያቆየውን የውል ስምምነት ዛሬ ተፈራርሟል

❤️ #በረከት አማረ እንኳን ፍቅር ወደ ሆነው ክለባችን #ኢትዮጵያ_ቡና በሰላም መጣህ መልካም የውድድር ጊዜ እንዲገጥምህ ምኞታችን ነው ።

ሁሉም መረጃ በክለቡ ፔጅ ወይም በ #አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ እስኪፖሰት ድረስ ምንም አይነት መረጃዎች እንዳይረብሻቹ ለማለት ነው

#መልካም_የዝውውር_ግዜን_እንመኛለን

ድል ለኢትዮጵያ ቡና

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉 @coffeefc 👈
👉 @bunnafc👈
#አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
የኛ ፔጅ ከተከፈተ 6 አመት አካባቢ ይሆነዋል ማለትም በሁለት አመት ከ5ሺ ተከታይ ከደረስን በኋላ ፔጁ ቢደለትብንም ሰለቸኝ ሳንል ድጋሚ በመክፈት በ4 አመት ውስጥ 28ሺ በላይ ተከታይ አፍርተናል በአጠቃላይ 6 አመት ሞልቶናል በቻልነው አቅም ለደጋፊዎቻችን መረጃ ለማድረስ እየጣርን ነው በዚ መሀል ግን ባልገመትነው ሁኔታ በስማችን ሌላ ገፆችና ማህበሮች እየተከፈቱ ነው እና ብዙ ሰው ግራ እየተጋባ ነው ስሙ እንደተያዘ እያወቁ ሌላ ስም ቢጠቀሙ ጥሩ ነበር ከቻሉ አሁንም ቢቀይሩት ደስተኞች ነን ፍቃደኛ ከሆናችው ስማችሁን እንድትቀይሩ በፔጃችን ስም በትህትና እንተይቃለን🙏🙏🙏እውነተኛው እና የመጀመሪያው 'አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ' ከ 28ሺ በላይ ላይክ ያለው ፔጅ ይሄ ነው በአዲሱ የውድድር አመት ለየት ባሉ አቀራረቦች የመረጃ ፍላጎትዎን ለማርካት በርትተን እንሰራለን እናመሰግናለን!!!
#Share #Share #Share

#የፌስቡክ ፔጃችንን ይቀላቀሉ
https://m.facebook.com/etbunna/?ref_component=mbasic_bookmark&ref_page=%2Fwap%2Fhome.php&refid=8&ref=opera_speed_dial


👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
ኢትዮጵያ ቡና ባህር ዳር ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

ባህደር በሚገኙ የኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊዎች በስፖንሰሮቻችንን ቡና ባንክ እና ሀበሻ ቢራ እንዲሁም በጨዋው የባህርዳር ደጋፊ ኢትዮጵያ ቡና ደማቅና አስደሳች አቀባበል ተደርጎለታል በ #አረንጓዴ #ወርቅ #ኢትዮጵያ ቡና - #አደገኞቹ ፔጅ ና ቻናል ስም ሁላችሁንም ከልብ እናመሰግናለን !

በድል ተመለሱልን አደገኞቹ👆👆👆

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @coffeefc 👈👈
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ለ2016 ዓ.ም የውድድር ዓመት የሚጠቀምባቸውን ማሊያዎች እርክክብ አድርጓል። እነዚህ አራት አይነት ቀለማት የያዙ ማሊያዎ ከክለባችን ጋር ያላቸውን ቁርኝት ምን ይመስላል የሚለውን በቀጣይነት እናያለን
#የኢትዮጵያ_ቡና_በታሪኩ_ያደረጋቸው_ማሊያዎች

🔥 #ቡኒ (በርገንዲ) ማሊያ
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ 'የንጋት ኮከብ' ተብሎ ከተመሰረተ ጀምሮ በተለያየ ጊዜ የለበሰው እና እስካሁንም ድረስ የመጀመሪያ መለያ ማሊያው ሆኖ እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን፤ 56ኛ ቡድን ሆኖ በፌዴሬሽን ተመዝግቦ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ሻምፒዮን አደይ አበባን 3-0 በሆነ ውጤት ድል ሲያደርግ ለብሶት የገባው ማሊያ ነበር።

🔥 #ቢጫ_ማሊያ
ከንጋት ኮከብ እስከ ኢትዮጵያ ቡና በተለያየ ጊዜ ይህንን መለያ ያደረገ ሲሆን እስካሁንም ጊዜ የክለቡ ሁለተኛ መለያ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ2003 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቡና ሻምፒዮን ሲሆን ይህንን መለያ አድርጎ ነበር።

🔥 #ነጭ_ማሊያ
ይህ ማሊያ በሦሥት የተለያዩ ጊዜያት የተደረገ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በ1972 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ 3ኛ ዲቪዚዮን በሚጫወትበት ጊዜ ያደረግው መለያ ሲሆን በድጋሚ በ1985 ዓ.ም ለአንድ ዓመት እንዲሁም በ2014 የውድድር ዓመት የክለባችን ሦሥተኛ ማሊያ እንደነበር የሚታወስ ነው።

🔥 #አረንጓዴ_ማሊያ
የኢትዮጵያ ቡና በ1989 የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ሐዋሳ ዱቄትን 1-0 በተሸነፈበት ወቅት የተለበሰ መለያ ነው።
ይህ መለያ የተደረገው ለአንድ ጊዜ ሲሆን ከዚህ ጨዋታ በኋላ ለሴቶች መረብ ኳስ ቡድን ተሰጥቶ ለሁለት ተከታታይ ዓመት ሴት የመረብ ኳስ ቡድናችን አድርጎት ተጫውቷል።

➲ ከላይ በታሪኩ ለማየት እንደተሞከረው የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እነኚህን ቀለማት የያዙ ማሊያዎች ከትጥቅ አቅራቢው #ብርሃኑ_እና_ጥሩነህ_የማስታወቂያ_ድርጅት (ከሀ-ፐ) የተረከበ ሲሆን ለ2016 ዓ.ም የውድድር ዓመት ለብሷቸው የሚቀርብ ይሆናል።

በቅርቡም እነዚህን ቀለማት የያዙ መለያዎች በብራንድ ሾፑ ውስጥ ለደጋፊዎች ለሽያጭ የሚቀርቡ ይሆናል።

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛🤎 
@coffeefc 💛🤎
💛🤎 
@coffeefc  💛🤎
ቡናችን 🤝 አረንጓዴ ውርቅ ኢትዮጵያ ቡና

👉በኢትዮጵያ ቡና ስም ከተከፈቱ የቴሌግራም ገፆች ፈርቀዳጅ በመሆን የሚታወቁት #አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ እና #ቡናችን ቻናሎች በአንድነት ሰለክለባችን ኢትዮጵያ ቡና መግለጫ እያዘጋጀን ሲሆን.....

ለክለባችን ደጋፊዎች ይበጃል ይጠቅመናል ያልነውን ሀሳብ ነገ በጋራ ይፉ የምናደርግ ሲሆን ከአሁኑኑ ግን የምንንግራቹ ነገር በክለባችን ኢትዮጵያ ቡና እኛም ቀልድ እንደማናቅ ነው!

እኛ አንድ ሆነናል ነገ ይፋዊ መግለጫችንን እናሳውቃቹኋለን!!

👉ቡናችን የቴሌግራም ቻናል ገፃቸው የሌላችሁ መቀላቀል ትችላላችሁ!
https://t.me/+TJSH9renuITUpJiy

ኑ በጋራ ከለባችንን እንታደግ!