አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
201K subscribers
5.15K photos
168 videos
14 files
772 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ለ2016 ዓ.ም የውድድር ዓመት የሚጠቀምባቸውን ማሊያዎች እርክክብ አድርጓል። እነዚህ አራት አይነት ቀለማት የያዙ ማሊያዎ ከክለባችን ጋር ያላቸውን ቁርኝት ምን ይመስላል የሚለውን በቀጣይነት እናያለን
#የኢትዮጵያ_ቡና_በታሪኩ_ያደረጋቸው_ማሊያዎች

🔥 #ቡኒ (በርገንዲ) ማሊያ
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ 'የንጋት ኮከብ' ተብሎ ከተመሰረተ ጀምሮ በተለያየ ጊዜ የለበሰው እና እስካሁንም ድረስ የመጀመሪያ መለያ ማሊያው ሆኖ እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን፤ 56ኛ ቡድን ሆኖ በፌዴሬሽን ተመዝግቦ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ሻምፒዮን አደይ አበባን 3-0 በሆነ ውጤት ድል ሲያደርግ ለብሶት የገባው ማሊያ ነበር።

🔥 #ቢጫ_ማሊያ
ከንጋት ኮከብ እስከ ኢትዮጵያ ቡና በተለያየ ጊዜ ይህንን መለያ ያደረገ ሲሆን እስካሁንም ጊዜ የክለቡ ሁለተኛ መለያ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ2003 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቡና ሻምፒዮን ሲሆን ይህንን መለያ አድርጎ ነበር።

🔥 #ነጭ_ማሊያ
ይህ ማሊያ በሦሥት የተለያዩ ጊዜያት የተደረገ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በ1972 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ 3ኛ ዲቪዚዮን በሚጫወትበት ጊዜ ያደረግው መለያ ሲሆን በድጋሚ በ1985 ዓ.ም ለአንድ ዓመት እንዲሁም በ2014 የውድድር ዓመት የክለባችን ሦሥተኛ ማሊያ እንደነበር የሚታወስ ነው።

🔥 #አረንጓዴ_ማሊያ
የኢትዮጵያ ቡና በ1989 የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ሐዋሳ ዱቄትን 1-0 በተሸነፈበት ወቅት የተለበሰ መለያ ነው።
ይህ መለያ የተደረገው ለአንድ ጊዜ ሲሆን ከዚህ ጨዋታ በኋላ ለሴቶች መረብ ኳስ ቡድን ተሰጥቶ ለሁለት ተከታታይ ዓመት ሴት የመረብ ኳስ ቡድናችን አድርጎት ተጫውቷል።

➲ ከላይ በታሪኩ ለማየት እንደተሞከረው የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እነኚህን ቀለማት የያዙ ማሊያዎች ከትጥቅ አቅራቢው #ብርሃኑ_እና_ጥሩነህ_የማስታወቂያ_ድርጅት (ከሀ-ፐ) የተረከበ ሲሆን ለ2016 ዓ.ም የውድድር ዓመት ለብሷቸው የሚቀርብ ይሆናል።

በቅርቡም እነዚህን ቀለማት የያዙ መለያዎች በብራንድ ሾፑ ውስጥ ለደጋፊዎች ለሽያጭ የሚቀርቡ ይሆናል።

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛🤎 
@coffeefc 💛🤎
💛🤎 
@coffeefc  💛🤎