TIKVAH-ETHIOPIA
1.38M subscribers
54.6K photos
1.35K videos
197 files
3.61K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#AmharaRegion #Gojjam ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላና ኧሌ ዞኖች ተነስተው ለደን ምንጣሮ ስራ ወደ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እያመሩ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ጎዛምን አካባቢ በ " ፋኖ ታጣቂዎች " የተያዙ የቀን ሰራተኞችን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረገ መሆኑን የምልመላና የቅጥር ሂደቱን የፈፀመው " ኒኮቲካ ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር አሳውቋል። የታገቱት ሰራተኞች ብዛታ 272…
#Update

" 4 ሚሊዮን ብር ለማስለቀቂያ ከፍለናል ሰነዱ በእጄ አለ፤ ከለቀቋቸው በኃላ ድጋሜ በመያዝ 6 ሚሊዮን ብር ጠይቀዋል " - ቀጣሪ ድርጅቱ

ወደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለደን ምንጣሮ ስራ በግል ድርጅት ተመልምለው ወደ ስፍራው በአማራ ክልል፣ በምስቅው ጎጃም ፣ ጎዛመን በኩል አቋርጠው ሲጓዙ የካቲት 18/2016 ዓ/ም " በፋኖ ታጣቂዎች " ታገቱ የተባሉ ሠራተኞች እስካሁን ከእገታ አልተለቀቁም ሲል ቀጣሪው ድርጅት ገለጸ።

የቀጣሪው ድርጅት ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ሙልጌታ አለነ ፤ ላለፉት 24 ቀናት ታግተው የሚገኙትን 272 #የቀን_ሰራተኞች ጉዳት ሳያገኛቸው ለማስለቀቅ መጋቢት 1 ቀን 2016 ዓ/ም 4 ሚሊዮን ብር በተለያዩ 3 ሰዎች አማካኝነት ክፍያ ፈፅመናል ብለዋል።

አቶ ሙልጌታ ፤ " ገንዘቡን #ተቀበሉን ከዛም ለቀቋቸው ከለቀቋቸው በኃላ እንደገና ጎዛመን የሚባል ቦታ ላይ ለዋናው አስፓልት 5 ኪ/ሜ ሲቀር እንደገና ሌላ ኃይል መልሶ ያዛቸው። ... የውሸት የውሸት ፖለቲካ የእውነት አምላክ ይፍረድልን ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረድልን " ሲሉ ተናግረዋል።

" 4,000,000 ብር (4 ሚሊዮን) ነው #የከፈልናቸው " ያሉት አቶ ሙልጌታ ፤ " የከፈልኩበት ሰነድ በእጄ አለ ፤ በ3 ሰው ስም ነው የገባው። ' አስገባ ' ተባልኩኝ አስገባሁ ተለቀቁ እንደገና ከተለቀቁ በኃላ ሌላ ቡድን ያዛቸውና ለእያንዳንዱ መኪና አሁን 1,500,000 ብር ተጠይቋል ፤ ልጆቹን ለቀይ መስቀል ነው አሳልፈን የምንሰጠው ብለውን እየጠበቅን ነው " ብለዋል።

መጋቢት 1 ተለቀው እና ድጋሚ ተይዘው ከሆነ ከቀናት በፊት ቃለ ምልልስ በሰጡበት ወቅት ይህን ገንዘብ ለአጋቾቹ #መክፈላቸውንና ተለቀው መያዛቸውን ለምን እንዳልተናገሩ ተጠየቀው ፤ " አንደኛ የነበርኩት እዛው አካባቢ ነው ለደህንነቴ አስቸጋሪ ነበር። ሁለተኛ ደግሞ ልጆቹን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረኩ ነበር በዛ የተነሳ ነው " ሲሉ መልሰዋል።

ስራ አስኪያጁ ፤ ሰራተኞቹ #ከእገታው_ተለቀው መሄድ ከጀመሩ በኃላ በድጋሚ በቡድኑ ሌላ ክንፍ የተያዙት እዛው በምስራቅ ጎጃም ፣ ማቻከል ወረዳ አማኑኤል አካባቢ መሆኑን ተናግረዋል።

ሲጓዙበት የነበረ 4 ተሽከርካሪ ቁልፍም በታጣቂዎች መወሰዱን ገልጸዋል።

6 ሚሊዮን ብር ማስለቀቂያ መጠየቁን አመልክተዋል።

' የአማራ ፋኖ የጎጃም ቃል አቀባይ ' እንደሆኑ የገለጹት ፋኖ ማርሸት ፀሀይ ግን ምንም አይነት የገንዘብ ጥያቄ አላቀረብንም ፤ ገንዘብም አልተቀበልንም ፣ ድርጅቱ ስም ማጥፋት ነው የያዘው ብለዋል።

ፋኖ ማርሸት " ይሄ ኒኮቲካ የሚባለው የኮንስትራክሽን ድርጅት የፋኖን ስም በዓላማ እያጠፋ ያለ ተቋም ነው። ምርኮኞች የተያዙት በ4ኛው ክ/ጦር በሚያስተዳድረው ቀጠና ነው። ክፍለ ጦራችን #አማኑኤል / ማቸከል፣ ጎዛመን እስከ ደ/ማርቆስ እና ልጆቹ አሁን ያሉበትን በረሃ ያጠቃልላል። ስለዚህ በዚህ ቀጠና እስካሉ የኛ ሙርከኞች ናቸው " ብለዋል።

" #ገንዘብ_የጠየቀ_አካል_የለም። ተጭነውባቸው ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም የመጡባቸው የአውቶብሶቹ ባለቤቶች (4 አውቶብሶች) ' አውቶብሶቻችን ስጡን ' ሲሉ  አንሰጥም የሚል መልስ ሲሰጣቸው ' ለፋኖ ገንዘብ እንስጥና ድጋፍ አድርገን አውቶብሶቻችን ይመለሱ ' አሉ እኛ የገንዘብ ችግር የለብንም ፤ ገንዘብ አንጠይቅም አውቶብሶቹ ግን ቀይ መስቀል መጥቶ ልጆቹን ሲረከብ ተጭነው የሚሄዱባቸው ናቸው ብለን አቆይተናል " ብለዋል።

ልጆቹ ከነበሩበትም #እንዳልተንቀሳቀሱ ፣ ኒኮቲካም ሊቀበል እንዳልመጣ ገልጸው ድርጅቱ " የፋኖን ስም እያጠፋነው " ሲሉ ከሰዋል።

" እነዚህ ልጆች ታጋቾች ሳይሆኑ #ምርኮኞች ናቸው። ምርኮኞቹን ደግሞ ለቀይ መስቀል የምናስተላልፍበት ምክንያት ፦
1. እኛ ተንቀሳቃሽ ኃይል ስለሆንን፣
2. ለነሱ የምንመግበውን ምግብ ለወታደራችን ማዋል ስላለብን ፣
3. ዓለም አቀፍ የጦርነት ህግን አክብረን የምንዋጋ የነፃነት ታዋጊዎች / ኃይሎች መሆናቸውን ለማረጋገጥ ነው " ብለዋል።

እስካሁን ቀይ መስቀል እንዳልመጣ በአካል ከመጡ እናስረክባለን ሲሉ ተናግረዋል።

የተያዙት ደግሞ ድርጅቱ እንዳለው " 272 " ሳይሆኑን 246 ብቻ ናቸው ብለዋል።

ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን አሁን ጉዳዩ ከእኛ ከአቅማችን በላይ ነው ሲል አሳውቋል።

አቶ ሙልጌታ አለነ ፤ " ለሚመለከተው ሁሉ ስራውን ለሚያሰራን ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም በፅሁፍ አሳውቀናል ምንም መፍትሄ የለም #የድሃ_ልጅ ነው እየተሰቃየ የሚገኘው " ሲሉ ተናግረዋል።

" የአማራ ህዝብ እውነቱን ብቻ አይቶ ይዳኘን ፣ እነዚህ ወንድም ህዝቦች ናቸው የመጡት ለስራ ነው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰራተኞቹን ጉዳይ እንደሚያውቅ ፣ ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ጋር በመሆን እየሰራበት እንደሆነ ገልጾ ለጊዜው ለታጋቾች ደህንነት ሲባል ከዚህ በላይ አስተያየት እንደማይሰጥ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከቪኦኤ ሬድዮ /ጋዜጠኛ ዮናታን ዘብዲዮስ ማግኘቱን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia