الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
21.8K subscribers
374 photos
17 videos
7 files
913 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
Don't love someone by make the haram relationship. Haram relationship will involved you to Zina In Islam, there are no love between a man and a woman except a love of life partner ... Nikah is the Halal relationship. it is the right way to show your love, if you cant afford to Nikah. Then you should fasting because fasting will curb your passions . Follow the rules of Islam and In shaa Allah your life will be very simple and wonderful as Islam
join the channel

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::እህቴ::::::::☜ ክፍል አምስት/ ⑤ ..አንዱን ዓሊም «እስቲ ስለጀነት ፀጋዎች ንገረንና ጀነትን አስናፍቀን!» አሉት። እሱም በአንዲት ዐ.ነገር ብቻ ልብን ጀነት ላይ እንድትንጠለል ምታደርግን ንግግር ተናገር። መልካም ስራ መስራት ላደከማቸዉ አሪፍ ብርታት ሚሆንን ንግግር ተናገረ። «በዉስጧ ረሱሉ አሉ።» አላቸዉ። አለቀ። አንድ በልቡ ዉስጥ የረሱሉ ሙሃባ ላለበት ሰዉ በቂ ማነቃቂያ ነዉ።…
☞:::::::::እህቴ::::::::::☜

ክፍል ስድስት/⑥

ዛሬ ከሌሎች ጊዜ ለየት ያለ ትንሽ ጠጠር ያለ ሀሳብ ነዉ የማነሳዉ። ርዕሳችን ስለጀነት ነዉና ምናልባትም ይህ ዛሬ የማነሳዉ ጉዳይ በኛና በጀነት መሃል መጋረጃ ሊሆን ስለሚችልም ወቅታዊም ጉዳይ ስለሆነ ማንሳቱን መረጥኩኝ።

ሀገራችን ካፈራቻችዉ ታላላቅ ስብዕናዎች መሃል አንዱ የሆኑት.. ታላቁ ሼይክ ሙሀመድ አሊ ኣደም እንዲህ ይላሉ..

«ወሳኙ ነገር ‛አሉ! አሉ!’ መብዛቱ አይደለም። ወሳኙ ነገር ማስረጃዉ ጠንካራ መሆኑ ነዉ።»

አብዘሀኛዉ ሰዉ የሆነን ነገር ያደርጋል ማለት ያ ነገር ልክ ነዉ ማለትን አያስይዝም። በሆነ መንገድ ላይ ሚሄዱ ሰዎች መበራከታቸዉ ያ መንገድ ልክ ነዉ ማለትን አያስንዝም።

እቺን ወሳኝ ነጥብ ከያዝን ወደ ጉዳያችን እንግባ።

እንበልና ያ ከልበወለድ የማያወራዉ ተወዳጁ ነብይ ሙሀመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከዛሬ 1400 አመታት በፊት አንድን ነገር ከለከሉ። ነገር ግን ከዉዱ ነብይሽ ህልፈት ከ7 እና ከ6 መቶ አመታት ብኋላ አንድ ሰዉ መጣና «ያ ነብያችሁ ሲከለክሉት የነበረዉ ነገር ኮ ስህተት ነዉ። እኔ መልካምን ነገር አዉቅላችኋለሁ። እኔን ብትከተሉ መልካም ነዉ።» ቢል ትከተዪዋለሽ?!

አላህ አይቀድረዉና አንቺ ምናልባት መዉሊድን እያከበርሽ ከሆነ ያን ከ1400 አመታት በፊት «ዲናችሁን ሞላሁላችሁ!» ብሎ ቁርዓንን ያወረደዉን አላህን፣ እንዲሁም ያን «ትዕዛዛችን ያልሆነን አንድን ነገር የፈፀመ በሱ ላይ ተመላሽ ነዉ።» ብሎ የተናገረዉን የረሱሉን ቃል ጥሰሽ.. ከረሱሉ ህልፈት ብኋላ ከ700 አመታት ብኋላ መጥቶ መዉሊድን ያወጀዉን ሙዘፈርን አስበልጠሻል ማለት ነዉ።

አላህ ምስክሬ ነዉ!
እኔ ላንቺ አሳቢና ተቆርቋሪ ብቻ ነኝ።

ያ.. እንዴት መብላት፣ እንዴት መጠጣት፣ እንዴት መልበስ፣ እንዴት መተኛት፣ እንዴት መሄድ፣ እንዴት ማዉራት.. በተጨማሪም ብዙ ቀላል ሚመስሉ ነገሮችን ያስተማሩን ነብይ መዉሊድም ኸይር ቢሆን ኖሮ ባስተማሩንና ባመላከቱን ነበር። ግን በአስተምህሮታቸዉ ዉስጥ አንድንም መዉሊድን ሚደግፍ ነገር አናገኝም።

ሰሀቦችም፣ ታቢዕዮችም፣ አትባዓ ታቢዒንም አንድኛቸዉም አልፈፀሙትም። ታዲያ ዲን በነብያትና ከነሱ ቀጥሎ በመጡት መልካም ዓሊሞች ይመራል እንጂ.. በንጉስና በመጥፎ ዓሊሞች ይመራል እንዴ?!

እህቴ! የዚህ ዘመን ሰዎች ምንስተካከለዉ የበፊቶቹ በተስተካከሉት ነዉ። እነሱ የተስተካከሉት ደግሞ በቁርዓንና በሀዲስ ነዉ። በቁርዓንና በሀዲስ ማስረጃዎች አደራ እልሻለሁ!!

[[አደራ!
ብዙ ሰዉ መዉሊድን ማክበሩ አያታልልሽ!
አብዘሀኛዉ ሰዉ ነፍሱ ምታጌጥለትን እንጂ ቁርዓንና ሀዲስን አይከተልምና።]]
#ይቀጥላል_ኢንሻአላህ

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
☞☞አላህ ሆይ ከጀሀነም እሳትና ወደዛ ከሚወስዱ ስራዎች አንተው ጠብቀን።

☞አቢ ሰኢድ አልኹድርይ رضي الله عنه እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል።

«ከጀሀነም ሰዎች ትንሹ ቅጣት የሚቀጣው ሰው፦ ከእሳት የሆኑ ሁለት ጫማዎች ይደረግለታል። ከጫማው ሙቀት የተነሳ ጭንቅላቱ ይንተከተካል።»
📚 رواه مسلم (211 )

قَالَ رَسُولُ اللهِ ﷺ: «يَا أَيُّهَا النَّاسُ تُوبُوا إلَى اللهِ، فَإِنِّي أتُوبُ إلَيْهِ مِئَةَ مَرَّةٍ»

ነቢዩ ( صلى الله عليه وسلم( እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ ወደ አላህ በፀፀት ተመለሱ፡፡ እኔ በየቀኑ ከመቶ ጊዜ ያላነሰ ተውበት አደርጋለሁ፡፡

☞☞ዉድ የሙስሊም እህትና ወንድሞቼ አላህ ከጀሀነም እሳት ይጠብቀን አሚን←←←←←

       ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::::::::እህቴ::::::::::☜ ክፍል ስድስት/⑥ ዛሬ ከሌሎች ጊዜ ለየት ያለ ትንሽ ጠጠር ያለ ሀሳብ ነዉ የማነሳዉ። ርዕሳችን ስለጀነት ነዉና ምናልባትም ይህ ዛሬ የማነሳዉ ጉዳይ በኛና በጀነት መሃል መጋረጃ ሊሆን ስለሚችልም ወቅታዊም ጉዳይ ስለሆነ ማንሳቱን መረጥኩኝ። ሀገራችን ካፈራቻችዉ ታላላቅ ስብዕናዎች መሃል አንዱ የሆኑት.. ታላቁ ሼይክ ሙሀመድ አሊ ኣደም እንዲህ ይላሉ.. «ወሳኙ ነገር…
☞::::::::::እህቴ! ::::::::::☜

ክፍል ሰባት/⑦

ወሳኝ ጥያቄ!
ዲንን የምትወስጂበት ዋና ቦታ የት ነዉ?!

እስከዛሬ የገባኝ ነገር ቢኖር አብዘሀኛዉ ሰዉ ቀላል የሆነን መንገድ ነዉ ሚከተሉት። ከነፍሳቸዉ ጋር የሚገጥምን ነገር ፈተዋ የሚሰጥን ሰዉ ይወዳሉ። አንዳንዱ እንደዉም ነፍሱ ደስ ያለዉን ነገር ፈተዋ ሚሰጥ ሰዉ ከሰማ በደስታ በሮ.. «ሼይክ ማለትማ ይህ ነዉ፣ ያለንበትን ተጨባጭ የተረዳ ታላቅ ዓሊም ማለት ይህ ነዉ፣ የሙስሊሞችን ቁስል ጠንቅቆ ሚያዉቀዉ እሱ ነዉ።» ይላሉ።

ፈተዋዉ የፈለገዉን ያህል ልክ ባይሆንና በደዒፍ ሀዲሶች ቢሞላ እንኳን የነፍሱን ሙራድ ከገጠመ ፈተዋ ማለት ለሱ ያ ነዉ። ሙፍቲ ማለት ያ ሼይክ ነዉ።

አላህ የቂያማ ቀን እያንዳንዳችንን አንድን ጥያቄ ይጠይቃል..
«..መልዕክተኞችን ምን ብላችሁ መለሳችሁ?!»

አላህ ስለ ሸይክ አገሌ አልያም ስለ ሙፍቲ እገሌ አንጠይቅሽም። ቁርዓንና ሀዲስን ስለመከተልሽ ነዉ የሚጠይቅሽ።

ይበልጥ ግልፅ እንዲሆን ጥያቄዬን ልድገመዉ..

ዲንን የምትወስጂበት ዋና ቦታ የት ነዉ?!

እህቴ! ኮፊያ የለበሰ፣ ጥምጣም የጠመጠመ፣ በአላህ ምስጋና ጀምሮ በ‛ወላሁ አዕለም!’ የዘጋ ሁላ ሙፍቲ ይሆናል እንዴ?!

ዓሊም መስሎ ራሱን ያሳየ ሁሉም ሰዉ ዲን ከሱ ሚያዝ ሰዉ ይሆናል እንዴ?!

እህቴ! ዲንሽን ማንም እንደፈለገዉ የሚቀንሰዉና የሚያበላሸዉ ተራ እቃ አታድርጊዉ! እንደመጣለት የሚፈርድን ተራ ሰዉን እንደሼይክ አድርገሽ አትከተዪዉ! አንቺ ብቻሽን ነዉ ምትመረመሪዉ..

«..መልዕክተኞችን ምን ብላችሁ መለሳችሁ?!» ተብለሽ ብቻሽን ነዉ ምትጠየቂዉ። የጠመሙ ዓሊሞችን እንዳትከተዪ አደራ እልሻለሁ።

እስቲ አንዲት ፈገግ ምታረግን ታሪክ ልንገርሽ!! ላነሳነዉ ርዕስም ምርጥ ምሳሌ ይሆናል።

አንድ ገያስ ኢብኑ ኢብራሂም የሚባል ራሱን ዓሊም ሚያስመስል ዉሸታምና ወራዳ ሰዉ ነበር። ሰዉዬዉ ወሬ ይችላል፣ ሀዲሶችን እንደሀፈዘና ብዙ ዒልም እንዳለዉ ይናገራል። በዚህም ብዙ ሰዎች በዙሪያዉ ይሰባሰባሉ።

አንድ ቀን አንድ ሰዉዬ ገያስን በሚያሳፍር ሁኔታ ላይ ተቀምጦ አየዉና «ከሰዎች አታፍርም?! (ተስተካከል እንጂ!)» አለዉ።

ገያስም «ሰዎች የት አሉ?!» አለዉ። ሰዉዬዉም «እነዚህ በዙሪያህ የተሰበሰቡት ሳ?!» አለዉ። ገያስም «እነዚህማ ሰዎች አይደሉም። እነዚህ ከብቶች ናቸዉ። ከፈለክ ላረጋግጥልህ!» አለዉ።

ከዚያም ገያስ ያለዉን ሊያረጋግጥለት ወደ ሰዎቹ ሄደና ስለጀነትና ፀጋዎቿ ይነግራቸዉ ጀመር። ሁሉም አፉን ከፍቶ ያዳምጣል። ልባቸዉ ወደሱ መንጠልጠላቸዉ ባየ ጊዜ አንድን የዉሸትን ሀዲስ ፈጠረና እንዲህ አላቸዉ.. ረሱል (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል.. በምላሱ የአፍንጫዉን ጫፍ የነካ ሰዉ ጀነት ገባ!

ሰዎቹም ይህን በሰሙ ጊዜ ወዲያዉ ምላሳቸዉን እያወጡ አፍንጫቸዉን ለመንካት መሞከር ጀመሩ።

ገያስም ወደሰዉዬዉ ዞረና «ከብት ናቸዉ አላልኩህም ነበር።» አለዉ።

እህቴ! አላህ የጠበቀዉ ሰዉ ሲቀር አብዘሀኛዉ የኛ ዘመን ሰዉ ቁርዓንና ሀዲስን ሳይሆን እንዲህ አይነት ዓሊሞችን በጭፍን ሚከተሉ «ከብቶች» ሆነዋል።

እህቴ መላልሼ አደራ የምልሽ ነገር..
ዲንሽን ማንም ‛ዓሊም ነኝ!’ ባይ ከመሬት ተነስቶ የሚመራዉ ተራ ነገር አድርገሽ አትያዢዉ።

[[አንድ ሰዉ ዓሊም ሚባለዉ ሁለትን ነገር አንድ ላይ ሲይዝ ነዉ። ዒልምና ተቅዋን።

ዒልም ከቁርዓንና ከትክክለኛ ሀዲሶች ማስረጃ የሚያረግበት መሳሪያዉ ሲሆን.. ተቅዋው ደግሞ በፈተዋዉ ዉስጥ አላህን እንዲፈራ፣ በሀብትና በክብር እንዳይታለልና ሀቅን ለመናገር የወቃሽን ወቀሳ እንዳይፈራ ያደርገዋል።

ትክክለኛ ምርጥ የአላህ ዑለሞች በኛ ዘመን አቤት ማነሳቸዉ።
#ይቀጥላል_ኢንሻአላህ

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
☞ሱብሀን አላህ ልብ የሚነካ ነገር ነው

#ሼኽ_ናይፍ_እንዲህ_ይለናል

አላህ( سبحانه وتعالى) ሁላችንንም  ይጣራል ማረኝ በሉኝ ምህረትን  ጠይቁኝ ይላል

ከአንድ ወር ግማሽ በፊት እኔና ሸኽ ወሊድ  ሌሎችም ሼኾች  ከጅዳ ወደ ጣኢፍ  ለሙሃደራ  ለመሄድ አስበን መንገድ ላይ ሸኽ ወዲድ እንዲህ አለኝ የናይፍ አንድ እናት አለች ከጣኢፍ  አንድ ሳምንት ሆናት ስታናግረኝ ። እርሱም  አንድ ወንድ ልጅ አላት ። የልጁ እናትም እንዲህ አለችኝ የሸኽ ልጄን መታችሁ ብታውልኝ ዝያራ ብታደርጉለት አለች
። አመኛለሁ አላህ ብታስታውሱን  ከእናንተ ጋር ዳዕዋው ቦታ ብትወስዱልኝ እናንተ አላህን የምትዘክሩበት ቦታ አላህን ከምታስታውሱበት ቦታ  ውሰዱት ልጄ እንዲሰግድ እፈልጋለሁ ልጄ ወደ ጌታው እንዲመለስ እፈልጋለሁ  ልጄ  እደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ ሆኖ ቢሞትብኝ አልፈልግም ጌታውን ያውቅ ዘንድ እርዱኝ አለች ።
#ሼኽ_ወሊድም አለኝ የናይፍ ምን ይመስልሃል የዚህችን እናት ቃል ሰምተን ወደ ልጁ ብንሄድ አለኝ ። እኔም አልኩኝ መርሀባ የሼኽ ። ከዛም  ለልጁ  እናት ስልክ ወደልን  ። ልጁን ማናገር እንፈልጋለን አልናት  አናገርነውም ። አልነው ስማ  ወንድሜ  እኛ ከቤታችሁ ቅርብ ነን ። ከጂዳ ወደ ጣኢፍ የዳዕዋ የመጣን ሼኾች ነን  አልነው ። ቦታ ተቀጣጠርን እና ተገናኘን ።
ተሰላለምን ።ካላሰብነው በላይ መልካም ልጅ ሆኖም አገኘነው ። ከጌታው የራቀ ቢሆንም ግን አላህ ሙሉ አካል የሰጠው ሁሉ ነገሩ የተሟላ ነበር ። ከተሰላለምን በኃላም እንዲህ አልነው
። የምንልህ ነገር አለ ። እርሱም እሺ ምንድን ነው አለ ። እኛም አልነው ።

ዛሬ ጣኢፍ  ሙሀደራ አለ እናም ከእኛ ጋር እንድትሄድ እንፈልጋለን አልነው ።እርሱም አለ ስሙኝ መምጣታችሁ ለእኔ ወድጄዋለሁ ። ወላሂ እመጣለሁ ። የእህቴን ልጅ ይዤ አብረን እንመጣለን ሙሀደራውን አብረን እንከታተላለን አለን ።
ወላሂ በሙሀደራው ውስጥ ከ2000 በላይ ህዝብ ነበርና ሙሀደራ በምናደርግ ሰአት ልጁን እረሳነው ። ከሙሀደራው መጨረሻ ላይም ያ ልጅ ቀስ እያለ ወደ እኛ መጣ  አቀፈኝ እና ያለቅስ ጀመር ።ለጌታው  ስጁድም ወረደ ።

ጌታዬን አመሰግነዋለሁ እያለ ስጁድ ላይ ተደፋ ። ወላሂ ከ4 ቀን በፊትም መሞቱን ሰማን እናቱንም አላህ ያፅናሽ አልናት ። ሰው ሁሉ ይሞታል ። ግን ይሄ ልጅ እንዴት ሞተ የሚለው ነገር ። እናቱም አለች ወላሂ ከሙሀደራው  ወዲህ  የእናቱን ሀቅ ሲወጣ ነበር  አለች ።

ኡምራም አድርጎ መጣ አለች ። ከዛም የሱቢህ ሰላትን ሰገደ  ከመካ ወደ ጣኢፍ እየመጣ ከቤቱ ሲደርስ ሞተ ። አላህ  አዛኝ ነው አላህ መሀሪ ነው አላህ የባሮቹን መክፈር አይወድም ።
አላህ ምህረትን ይሻልናል አላህ ጀነትን ይወፍቀናል ። አላህ ለምንድን ነው ጥሩኝ ምህረትን ጠይቁኝ ያለው እኛ ምህረትን እናገኝ ዘንድ ነው ""!
የረብ የአላህ አንተ ተገዢዎች ሆነን እንጂ አትግደለን ። አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን አሚን ።

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
በጁሙዓ ለሊት እና ቀን ላይ ሰለዋት አብዝታችሁ አውርዱብኝ ፣በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ካወረዳችሁ አላህ በእናንተ ላይ አስር ጊዜ ያወርዳል ረሱል ﷺ
      اللهُمّ صَلِّ وسَلّم على نبيّنا محمد ﷺ

ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
በሱና ያጌጠች በኢማን ያበበች
ከሽርክ ከቢድአ ፈፅሞ የራቀች
በተውሂድ ታንፃ ጌታዋን ያጠራች
ሀያዕን ተላብሳ በሂጃብ ያማረች
በኒቃቧ ደምቃ የተዋበች

ለባሏ መከታ ለወንድሟ አለኝታ
ለአባቷ ክብር ለእናቷ ምስክር
ለልጇ ተምሳሌት ፈርጥ የአማኝ ሴት
የዚች አይነት እንስት የእንቁዎች እንቁ የውዶች ውድ ናት
ሙስሊሟ እህቴ እዎድሻለዉ🌷

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
🌷አል ሂጃብ🌹
"ሒጃብ" ማለት ትርጉሙ የቅርብ ዘመዶቿ ካልሆኑ ወንዶች ሰውነቷን መሸፈን ማለት ነው።አሏህ እንዲህ ይላል፦
ولا ييدين زينتهن إلا ما ظهر منها وليضربن بخمرهن على جيوبهن ولا يبدين زينتهن إلا لبعولتهن أو ءابائهن أو ءاباء بعولتهن أو أبناء بعولتهن أو إخوانهن))النور ٣١
"...ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልፅ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ።ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው  ላይ ያጣፉ።(የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው።"(አን-ኑር:31)

በሌላ የቁርኣን አንቀፅ አሏህ እንዲህ ይላል፦
((وإذاسألتموهن متعا فسآلوهن من وراء حجاب))الأحزاب:٥٣
"ዕቃንም (ለመዋስ) በጠየቃችኋቸው ጊዜ ከመጋረጃ ኋላ ኾናችሁ ጨይቋቸው።"(አል-አህዛብ:53)
ሂጃብ የሚለው ፅንሰ ሃሳብ የሚፈለግበት ሴትን ልጅ የሚሸፍን እንደ አጥር ወይም መዝጊያ ወይም ልብስ ማለት ነው።የቁርኣን አንቀፁ የወረደው በነብዩ ዓለይሂ ሰላቱ ወሰላም ባለቤቶች ቢሆንም መመሪያነቱ ግን ለአጠቃላይ አማኝ ሴቶች ነው።ለምን ቢባል?አሏህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ምክንያቱን እንዲህ ሲል ይገልፃል፦
((ذالكم آطهر لقولبكم وقولبهن))الأحزاب:٥٣
"ይህ ለልቦቻችሁ፤ለልቦቻቸውም የበለጠ ንጽሕና ነው።"(አል-አሕዛብ:53)

ምክንያቱ ሁሉንም ሴቶች የሚያካትት መሆኑ መመሪያነቱ(ህጉ) ለሁሉም ለመሆኑ ማስረጃ ነው።አሏህ እንዲህ ይላል፦
((يأيها النبي قل لأزاجك وبناتك ونساء المؤمنين يدنين عليهن من جلابيبهن))الأحزاب:٥٩
"አንተ ነቢዩ ሆይ!ለሚስቶችህ፤ለሴት ልጆችህም፣ለምእመናን ሚስቶችም መከናነቢያዎቻቸውን በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው።"(አል አህዛብ:59)

💥ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ መጅሙዑል ፈታዋ 22ኛው ጥራዝ ገፅ 110-111 ላይ እንዲህ ይላሉ፦"ጅልባብ ማለት መከናነቢያ ሲሆን ዐብደሏህ ኢብኑ መስዑድ እና ሌሎችም ኩታ እያሉ ሲጠሩት ተራው ሰው ሽርጥ ይለዋል።ይህም እራስን እና ሌላውን ሰውነት የሚሸፍን ትልቅ ሽርጥ ነው።ከአቡ ኡበይዳ እና ከሌሎችም እንደተወራው ከራሷ በላይ ወደ ታች የምትለቀው ሆኖ ሁለት አንኖቿን ብቻ ግልፅ የምሸታደርግበት ነው፤ኒቃብም የእሱው አካል ነው።"
💥ሴት ልጅ የቅርብ ዘመዶች ካልሆኑ ወንዶች ፊቷን መሸፈኗ እና ዋጂብ ስለመሆኑ ከሃዲስ ካሉት ማስረጃዎች ውስጥ አንዱ የአዒሻ ሐዲሥ ነው። ኣዒሻ አሏህ ስራዋን ይውደድላትና እንዲህ ትላለች፦

وكان الركبان يمرون بنا ونحن مع رسول الله صلى الله عليه وسلم محرمات،فإذا حاذوا بنا سدلت إحدانا جلبها من رأسها على وجهها،فإذا جاوزنا كشفناة>>
"ከአሏህ መልዕክተኛ ጋር ሐጅ ላይ ሁነን ሳለን ጋላቢዎች ባጠገባችን ሲያልፉ ከመካከላችን አንዷ ጅልባቧን ከራሷ በፊቷ ላይ ትለቃለች፤ሲያልፉን እንገልጸዋለን።(አቡዳዉድ:አሕመድ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል።)
💥ሴት ልጅ የቅርብ ዘመዶቿ ካልሆኑ ወንዶች ፊቷን መሸፈን ግዴታ መሆኑን የሚያመላክቱ ከቁርኣን እና ከሱና ብዙ ነው።በዚህ ዙሪያ ላይ የሚከተሉትን ኪታቦች እጠቁምሻለሁ፦
☀️"ሪሳለት አል-ሒጃብ ወሊባስ ፊ ሰላህ" የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ
☀️"ሪሳለቱል- ሒጃብ"የሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ዐብደሏህ ኢብኑ ባዝ
☀️"ሪሳለቱ አሷሪም አል መሽሁር ዐለል መፍቱኒነ ቢሱፉር"የሸይኽ ሐሙድ ኢብኑ ዐብደሏህ አት-ቱወይጅሪ
☀️"ሪሳለቱል-ሒጃብ" የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል ዑሰይሚን
እነዚህ መጣጥፎች በቂ የሆነ ማስረጃ ይዘዋሉ።
💥አንቺ ሙስሊሟ እህቴ ሆይ!ያንቺን ፊት መግለጥ የፈቀዱልሽ ዑለሞች አባባላቸው ሚዛን የተደፋበት ከመሆኑም ጋር እነሱም ቢሆን ፈተና አለመኖሩ የሚታመንበት ከሆነ ይላሉ።ፈተና ደግሞ የሚታመን አይደለም በተለይ በዚህ ዘመን የዲን መካሪ የሆኑ ወንዶች  እና ሴቶች ባሉበት፣ሃያዕ (እፍረት) ባነሰበት፣ወደ ፊትና የሚጣሩ በበዙበት፣ሴቶችም የተለያዩ የመዋቢያ አይነቶችን ፊቶቻቸው ላይ መጠቀም የተካኑ መሆናቸው ወደ ፊትና ከሚጣሩ ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው።
💥አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ!ከመገላለጥ ተጠንቀቂ! (በአሏህ ፍቃድ) ከፈተና ጠባቂሽ የሆነውን ሂጃብሽን ያዥ።በንግግራቸው ግምት ከሚሰጣቸው የጥንትም ይሁን የአሁን ዐሊሞች ለእነዚህ ተፈታኝ ለሆኑ ሴቶች የወደቁበትን የፈቀደ የለም።
💥አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ! ሂጃብ የሰው ውሻ ከሆኑ እና የልብ በሽታ ካለባቸው ሰዎች ከሚያመነጩት መርዛማ እይታ ይጠብቅሻል ሒጃብሽን በፅናት ከያዝሽው የተቃጠለ ስሜትን ካንቺ ይነቅልልሻል።ሂጃብን ለምትዋጋ ወይም የሂጃብን ጉዳይ ቀለል አድርጋ ለምታይ ዓላማ አዘል ተጣሪ ቦታ አትስጪ።እሷ ላንቺ የምትመኝልሽ ሸር ነው።አሏህም እንዲህ ይላል፦
((ويريد الذين يتلعون الشهوات أن تميلو ميلا عظيما))النساء:٣٧
"እነዚያም ፍላጎታቸውን የሚከተሉት ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ።"(አን-ኒሳእ:27)

ወሏሁ አዕለም
አይሰል....
ቴሌግራማችን

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
🌸ትዳር ማለት ምን ማለት ነው??? ዓላማውስ ምንድነው?? የሚለውን ነገር ቀድሞ ማወቅና መማር ይባጀል🌸

📌ብቻ ትዳር ነው ስለ ታበለ ጆይን ብሎ መውጣት ከዛ ቡሀላ ትንሽ ነገር ኮሽ ሲል ሌፍት ብሎ የሚወጣበት ቻናል ወይም ጉሩፕ አይደለም ።

✂️ሴቶች እድሜያችሁ ሂድዋል ትዳር ያዙ ወንድ የለም እያተባሉ ለዚህ ብቻ ብለው ዘው ብለው ይገባሉ ከዛ ቡሀላ ምንንነቱን ሳያውቁ ስለገቡበት ትዕግስት ማድረግ እነሱ ዘንድ ውርደት ነው ህዕ❗️

👉እንዴትስ ትታጋሽያለሽ ዓላማው ሳይገባሽ ገብተሽባት ⁉️

ኡኽቲልጋሊያህ አደራሽን ግዜያዊ ስሜትሽ ገፋፍቶሽ በገዛ እጅሽ ጣፋጭ ህይወትሽን አታበላሺ ጀግናና ብልህ ሴት ሁኚ 👌

ህይወትሽን  ለፉላንና ለዒላን እንዲፈላሰፉበት አትፍቀጂ ❗️

ስለ የትኛውም ጉዳይ ከማድረግሽና ከመግባትሽ በፊት ጥቅሙና ጉዳቱን ለይተሽ መወቅ አለብሽ ❗️

👉በታላይ ስለ ትዳር ስታስቢ ግዜያዊ ስሜትሽን ብቻ አይደለም ማሰብ ያለብሽ  ትዳር ውስጥ ብዙ መማርና ማወቅ ያለብሽ ነገሮች አሉ እንዲሁም ደሞ ብዙ ሀላፍትና ያለው የሆነ ትልቅ ተቋም ነው ይህንን ለመገንባትና ግምባታውም እንዳይፈርስ የምታደርሽያቸውን አስባቦችን መወቅና ለዛ ነገር ራስሽን ማዘገጀት እንዳለብሽ ጠንቅቀሽ ልታውቂ ይገባሻል 👌

↪️የትዳር ዓላማው ምንድነው የሚለውንም ቀድመሽ ማወቅ አለብሽ


👉ደሞ  ውዷዬ ትዳርን የመሰላ ህይወት ልሞክረውና ካልሆነ ላሽ እላላሁ የምትይዋ እህቴ አደራሽን ትዳር የሙከራ ህይወት አይደለም ሰምታሽኛል ኣ⁉️

ልሞክረው ከልሽ ሞክረሽው ላሽ እንዳምትይም እወቂ የኒያሽን ነው የምታገኚው ዋ 👌

ምንድነው ሩጫው ገብተሽ ልትወጪበት ለምን ትነካክያልሽ ⁉️

ለምን በጌታሽ ጠንካር ያለ የቂን የለሽም ⁉️

ለምን ስለ ትዳር ህይወት ና ዓላማ ሶብር አድርገሽ አትማሪም ⁉️


ይቀጥላል ኢንሻ አሏህ 
ቴሌግራማችን

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::::::እህቴ! ::::::::::☜ ክፍል ሰባት/⑦ ወሳኝ ጥያቄ! ዲንን የምትወስጂበት ዋና ቦታ የት ነዉ?! እስከዛሬ የገባኝ ነገር ቢኖር አብዘሀኛዉ ሰዉ ቀላል የሆነን መንገድ ነዉ ሚከተሉት። ከነፍሳቸዉ ጋር የሚገጥምን ነገር ፈተዋ የሚሰጥን ሰዉ ይወዳሉ። አንዳንዱ እንደዉም ነፍሱ ደስ ያለዉን ነገር ፈተዋ ሚሰጥ ሰዉ ከሰማ በደስታ በሮ.. «ሼይክ ማለትማ ይህ ነዉ፣ ያለንበትን ተጨባጭ የተረዳ…
☞::::::::እህቴ::::::::::☜

ክፍል ስምንት/⑧

የጀነት ሰዎች ነፍሳቸዉ ከፍጥረቱ ዉዴታ ተሳንፋ ወደ ፍጥረቱ ፈጣሪ የተጠናከረች ናት። ጌታቸዉ ከንብረታቸዉ፣ ከቤተሰባቸዉ፣ ከነፍሳቸዉ በላይ እነሱ ዘንድ ተወዳጅ ነዉ።

ምናልባትም በሌሊት ተነስተዉ ለሱ አንሾካሽከዋል፣ ቀንም በሱ ፍራቻ አንብተዋል፣ ዐይናቸዉ እሱ ማየትን ናፍቀዋል፣ ልባቸዉ በሱ ዉዴታ ረፍት አግኝተዋል።

በዱንያ ላይ ልባቸዉ እሱን ማየትን ናፈቀችና አላህም በዚያኛዉ ዓለም የሱን ዉብ ፊትን ማየትን ወፈቃቸዉ።

እህቴ ከነሱ ሁኚ! ልባቸዉ በሀራም ፍቅር ከታወሩ ሰዎች አትሁኚ!

በቂያማ ቀን በአላህ ዉዴታ ላይ ከተገናኙ ሰዎች በቀር ሌሎች አብዘሀኛዉ ሰዎች ፍቅራቸዉ ወደ ከባድ ጥላቻ ይቀየራል። አንዱ አንዱን ይረግማል። «ምናለ እገሌን ጓደኛ ባላረኩ!» እያለች ነፍስ በቁጭት ትዋጣለች። ጓደኛ ስል በሴትና ሴት መሃል ብቻ ሳይሆን በሴትና በወንደ መሃል ሚፈፀመዉን የሀራም ግኑኝነትንም ይይዛል።

እናም ከሀራም ፍቅር እንድትጠነቀቂ አደራ እልሻለሁ!!

ወደ ሀራም ግንኙነት ከሚመሩ ነገሮች መሃል አንዱ ፊልም ነዉ። በየፊልሞች የሴትና የወንድን አንድ ላይ መሆን እየደጋገመ የሚያይ ሰዉ በህይወት ዉስጥም የወንድና ሴት አንድ ላይ መሆን ኖርማል ነገር ይመስለዋል። ከዚያም ህይወቱን ምታደምቅለትን ፍቅረኛ፣ እሷም ህይወቷን ሚያደምቅላትን ፍቅረኛ መፈለግ ይጀምራሉ።

በተለይ ፊልሙ ኢክቲላጥ ከበዛበት.. በዉስጡ ፍቅር መገላለፅ፣ መነካካት፣ መደባበስ፣ መሳሳምና መሰል ነገሮች ካሉበት በነፍስ ዉስጥ ሰክኖ የነበረን ስሜት ይቀሰቅስና መጨረሻዉ ወደ ማያምር ነገር ይወስዳል።

እንደዚሁ የሀራም ፎቶዎችን የሚያይ ሰዉ.. ነፍሱ ያን ነገር መስራት ላይ ማነሳሳቱ አትቀርም። ያ ነገር ወደ ከባድ ሀራም ሊመራዉ ይችላል።

በጣም ሚገርመዉ አላህ ራሱ ሀራምን አትፈፅሙ ሳይሆን አትቅረቡት ነዉ ያለዉ። ሱብሀነላህ!!

ረሱልም «አይን ዝሙት ትፈፅማለች፣ የዐይን ዝሙት እይታ ነዉ።» ብለዋል።

ወደ ሀራም ፍቅር ከሚወስዱ ነገሮች መሃል ሌላኛዉ ዘፈን ነዉ። ኢብን መስዑድ እንዲህ ይላል.. «ዘፈን የዝሙት መንገድ ነዉ።»

ኢብኑ መስዑድ እንደዛ ያሉት እዛኔ ዘፈን በሴት ባሪያዎችና በሚገራርሙ የአረበኛ ግጥሞች ብቻ በሚባልበት ወቅት ላይ ነዉ። የዚህን ዘመን ዘፈንን ቢመለከት ምን ይል ይሆን??!

የዚህ ዘመን ዘፈን ሸህዋን የሚቀሰቅስና ለሀራም መንገድ ዋና በር ነዉ። አላህ ይጠብቀን!!

ከሀራም ፍቅር የሚያርቁ ነገሮች ደግሞ..
ዒልም፣ አላህን መፍራት፣ ሞትን ማስታወስ፣ ነፍስ አኼራን እንድታስታዉስ ማድረግና መሰል ነገሮች ይገኙበታል። በተጨማሪም መልካምና ምርጥ የአላህ ባሮችን መጎዳኘት አንዱ ነዉ።

መልካም ጓደኞች የዱንያም የአኼራም ብርሀኖች ናቸዉ። ጀነት ዉስጥ ቢያጡሽ እንኳን ይፈልጉሻል። «ጌታዬ ጥፍጥናዉ ከሷ ዉጪ አይሞላም።» ይሉታል።

[[አላህና አኼራን በሚያስታዉሱሽ መልካም እህቶች አደራ እልሻለሁ!!]]
#ይቀጥላል_ኢንሻአላህ

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
☞ጥርጣሬ በትዳር ዉስጥ‼️

☞በትዳር ውስጥ ተገቢ ያልሁኑ ጥርጣሪዎችን ከቀልብ ማውጣት ለቀልብም ሰላም በህይወትም ላይ እረፍትን ይሰጣል።

⇨ባልም ምስቱን ምስትም ባልዋን በተገቢ መልኩ ነገር ግን ከጥርጣሬ ራቅ ባለሁኔታ መጠያየቅነ ከምቀኝነት እና አስፈላጊ ካልሆነ ቅናት በመጥራት  መከታተላቸው ችግር የለውም ነገር ግን አለመተማመን እስከ ሚያሻክር ድረስ መጠራጠር አሰፈላጊ አይደለም ።

ባልን የት እንደ ሚሄድ ከማንጋር እንደሚውል ሰላይ የቀጠሩ ማስጎብኘት ውድ እህት ትዳርሽን አደጋ ላይ ይጥለዋልና ይህን ድርጊት ወደጎን ተይው

📌ባልም ብትሆን ባለቤትህን መቆጣጠር እና መከታተል እንዳለበክ ሳለ  ነገር ግን በጥርጣሬ በሽታ ውስጥህን አትልከፍ ጥርጣሬ ውስጥህ ላይ የሰፋ በመጣ ቁጥር መረጃ ለማግኝት ስትል አደጋ ላይ ትዳርህን ትጥል አለክ

☞☞⇝ለምሳሌ እንዲህ የሚያደርጉ አይጠፉም በሄደችበት ሁሉ መከታተል ይህም አልበቀ ሲላቸው ሄዳለው ያለቺው ቦታ ነው የሄደቺው ወይስ ሌላ ቦታ በማለት ወደ ቦታው የደወሉ ለማረጋገጥ መሞከር በዚህ ወቅት ምሰት አልታመንም እንዴ? የሚል ስሜት ውስጧ ላይ ይጫርባታል ፣ ቦርሳዎችዋን መፈተሽ፣ የስልክ ሜሴጆችዋን መከታተል፣ የድሮ ታሪኳን መፈተሽ በተለይ ወጣት የትዳር ጥንዶች ከዚህ በሽታ ተቆጠቡ

⇨⇨በተለይ ምስትህን ከዘመዶችዋ ጋር አትጠርጥር ከወንድሞቿና ከአጎት ከአባትዋ ጋር ስትጫወት ስታይ አትቅና  አንዳንድ ጉዞ የሚያበዙ ባሎች ምስታቸውን እስከ ዝሙት ድረስ የሚጠረጥሩ አሉ። በትዳር ላይ የማይገባ እና ከልክ ያለፈ ቅናትን ማስወገድ ይኖርባችዋል

☞አላህ እንዲህ ይላል "እናንተ ያመናቸሁ ሰዎች ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙውን ራቁ። ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጥያት ነውና።"

☞⇉መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሐሰት ጥርጣሬን አስመልክቶው እንዲህ ብለዋል "አንድ ንፁህ ወንድ ወይም ሴት በሐሰት የወነጀለ ሰው የፍርዱ ቀን አላህ እሳት ውስጥ ይከተውና ለሰራው ጥፍት ቅጣቱን ይሰጠዋል"

📌ወንድም ደግሞ በተቃራኒው ግድ የለሽ ሁን ማለት አይደለም በተገቢው ቦታ ላይ ሆነክ ተገኝ ዐሊይ (ረዲየላሁ ዓንሁ ) ልጆቸውን  ሀሰንን (ረዲየላሁ ዓንሁ) እንዲህ ሲሉ መክረውታል።

☞መሆን በሌለብህ ቦታ ላይ ሆነህ ከመገኘት ተቆጠብ ምክንያቱም ይህ ነገር ጥሩ ሰዎችን ወደ መጥፎ ተግባራትና ኃጥያት ሊያመራቸው ይችላል።

በትዳር ላይ የሚትገኞው አላህ እስከጀነት ያዝልቃችሁ ትዳርን ለምትናፍቁ አላህ ሷሊህ የሆነው ትዳር ይወፍቃቹሁ አሚን🌷

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
ብዙን ጊዜ የኛ ሴቶች ነገር ግርም ይለኛል!!

በጣም የምንሸወድበት ነጥብ ቢኖር

በዐረብኛ ፊደል አቡ ፉላን ኢብኑ ፉላን ኡስታዝ ፉላኖች ላይ

በጣም እንሸወዳለን ለእነሱ ልባችን ደቂቃ እንኳን አይፈጅባትም ቶሎ ይከፈታል። ወልዒያዙ ቢሏህ

ላኢላሀ ኢለሏህ

ያ ኡኽቲ የሰው ስሙ ሳይሆን ተግባሩ ነው። ሰምተሽኛል ኣ???

ስለዚህ አንቺ ሁሌም አሏህ ለወደደልሽና ለፃፈልሽ(ለሰጠሽ) ሰው ብቻ ልብሽን እንድትከፍችለት ዱዓ ኣድርጊ።የምትፈልጊውን ሳይሆን የሚያስፈልግሽን እንዲሰጥሽ ዱዓ አድርጊ።!!

ስንመከር እንኳ የቀኑብን የሚመስለን አለን። አሏህ
ቴሌግራማችን

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
‏لماذا ذُكرت الزوجة قبل ذكر الجنة في آية " وَقُلْنَا يَا آدَمُ اسْكُنْ أَنْتَ وَزَوْجُكَ الْجَنَّةَ"؟!

قالوا، الرَّفيق قبل الطَّريق، وهي مَسكَن القلب، والجَنَّة مَسكَن البَدن، ومن الحكمة تقديم الأول علىٰ الثاني.

•تفسير الإمام ابن كثير
وَقُلْنَا يَا آدَمُ اسْكُنْ أَنتَ وَزَوْجُكَ الْجَنَّةَ “

«አደም ሆይ! አንተ ከነሚስትህ በገነት እርጉ»
በሚለው አንቀፅ ላይ ከጀነት በፊት ባለቤት ለምን ቀደመች?
ለእሱም እንዲህ አሉ:-የመንገድ አጋር ከመንገድ ይቀድማል...እሷ የልብ መርጊያ ስትሆን ጀነት ደግሞ የአካል መርጊያ ናት።ከሁለተኛው ይልቅ አንደኛን ማስቀደም ደግሞ ከብልሃት ነው።

ተፍሲሩ ኢብኑ-ከሲር|•

ቴሌግራማችን

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::::እህቴ::::::::::☜ ክፍል ስምንት/⑧ የጀነት ሰዎች ነፍሳቸዉ ከፍጥረቱ ዉዴታ ተሳንፋ ወደ ፍጥረቱ ፈጣሪ የተጠናከረች ናት። ጌታቸዉ ከንብረታቸዉ፣ ከቤተሰባቸዉ፣ ከነፍሳቸዉ በላይ እነሱ ዘንድ ተወዳጅ ነዉ። ምናልባትም በሌሊት ተነስተዉ ለሱ አንሾካሽከዋል፣ ቀንም በሱ ፍራቻ አንብተዋል፣ ዐይናቸዉ እሱ ማየትን ናፍቀዋል፣ ልባቸዉ በሱ ዉዴታ ረፍት አግኝተዋል። በዱንያ ላይ ልባቸዉ እሱን…
☞::::::እህቴ::::::::☜

ክፍል ዘጠኝ/⑨

ዛሬ የእዝነትና የፍቅር የአታክልት ስፍራ በሆነዉ (በአቡ ደህዳህ) የአታክልት ስፍራ ዉስጥ ቆይታ እናረጋለን። ያቺ የአታክልት ስፍራ ልብን በሀሴት ምትሞላ፣ ደስታ የምትሰጥ፣ ሰላማዊ አየር ያላት ዉብ የአታክልት ስፍራ ናት። ያየዉን ሰዉ ድንገት ሳያስተዉል ‛ሱብሀነላህ!’ እንዲል ታስገድዳለች። የመዲና ሰዎች አዉርተዉላት የማያበቁ እጅግ ዉብና ምርጥ የአታክልት ስፍራ ነበር።

ከዕለታት በአንዱ ቀን የምድር ሰዎችን እንዳስገረመዉ ሁሉ የሰማይ መልዕክተኞችን አጀብ ማሰኘት የሚችል የሚገርም ክስተት ተከሰተ። ንፁህ ዐይኖችን በእንባ ያጠበ፣ እዚያ የነበሩትን ብቻ ሳይሆን ታሪካቸዉን የሰማዉን ሰዉ በእንባ ያራጨ ገራሚ ክስተት ተከሰተ።

ክስትቱ ወዲህ ነዉ..

አንድ ቀን (አቡ ደህዳህ) በነቢያችን አጠገብ ሲያልፍ የአንድን ታዳጊ ልጅ ለቅሶ ይሰማል። ልጁ የቲም መሆኑን ሲያዉቅ አዘነለትና ቆሞ የልጁን ጉዳይ መስማት ፈለገ። ልጁም ሀዘን በጎዳዉ አንደበት እንባዉ እየቀደመዉ ረሱሉን እንዲህ አላቸዉ..
«አንቱ የአላህ መልዕክተኛ! በአታክልት ስፍራዬ ዙሪያ ግንብ እየሰራሁ እያለ (ግንዱ) የጎረቤቴን አንዲት የተምር ዛፍን ቆረጠበት። እንዲተዉልኝ ወይም እንዲሸጥልኝ ጠየኩት። እሱ ግን እምቢ አለ።»

ረሱሉም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሰሀቦችን ያን ጎረቤቱን እንዲጠሩት አዘዙትና መጣ። ረሱሉም ልጁ የቲም ስለሆነ እንዲሰጠዉ ሌላዉ ቢቀር እንዲሸጥለት ጠየቁት። እሱ ግን እንደማያረገዉ ተናገረ።

ረሱሉም በጣም የሚገርምን ንግድ አመላከቱት.. «ሽጥለት! ለአንተ ደግሞ በምትኩ መቶ የተምር ግንዶች ጀነት ዉስጥ አሉልህ!» አሉት። (ዐዉ ከማ ቃለ)

ሁሉም ሰሀባ በድንጋጤ ክዉ አሉ። ይሄን የመሰለ ግብይት ወደ ቀረበለት ሰዉ ጆሮዎች ዞሩ። እንደሚቀበል ማንም ሸክ አልነበረዉም።

እሱ ግን እምቢ አለ።

የቲሙም ልጅ እንባ በእንባ ሆነ። የሰሀቦች ዐይንም ወደ ሰዉዬዉ በግርምት ማየት ጀመሩ። እሱ ግን ምንም አቋሙን አልቀየረም ነበር።

ይሄኔ ነዉ (የአቡ ደህዳህ) ታሪክ ሚጀምረዉ። አቡ ደህዳህ ይሄንን ምልልስ ከሰማ ብኃላ ነፍሱ ወደ ጀነት ናፈቀች። ረሱልንም እንዲህ ሲል ጠየቀ..

«አንቱ የአላህ መልዕክተኛ! የአታክልት ስፍራዬ ሽጬ ለልጁ የተምር ግንዱን ባስመልስለት በጀነት ዉስጥ የተምር ዛፍ አገኛለሁ?»

ረሱሉም ደስታ ፊታቸዉን አፈካዉ። «አዎ!» አሉት። አቡ ደህዳህም ወደ ሰዉዬዉ ዞረና «የአታክልት ስፍራዬን ታዉቀዋለህ?!» አለዉ። ሰዉዬዉም «አዎ!» አለ።

አቡ ደህዳህም «የተምር ግንድህን በአታክልት ስፍራዬ ሽጥልኝ!» አለዉ። ተስማማ ንግዱ ተፈፀመ። (ሱብሀነላህ!)

የልቡ ምት የእግሩን ፍጥነቶች እየቀደመ ወደ አታክልት ስፍራዉ ሮጠ። የመዲና ቤቶች በመላለሱት በተቆራረጠ ድምፅ..
«ኡመ ደህዳህ!..» ብሎ ሚስቱን ተጣራ።

«..ከአታክልት ስፍራዉ ዉጪ! እሱ ለአላህ!» አላት። የደህዳህ እናትም ወዲያዉ ከግዛቷ ተነሳች። እጆቿን ከፍራፍሬዎቹ ላይ አነሳች። በልጆቿ እጅ ላይ የቀሩትን ፍራፍሬ ሳይቀር ቀማቻቸዉና አማና ነዉና አስቀመጠችዉ። የባሏን ትዕዛዝ ከመፈፀሟ በፊት የአላህን ትዕዛዝ «ለበይክ!» አለች። ምንም ሳትጠይቅ፣ ምንም ሳታጣራ በንፁህ ልብ ዉሳኔዉን ተቀበለች። አንድ ነገር ብቻ ነዉ ምታቀዉ። «ለአላህ!» መሆኑን።

ከዚያም ወደ ባሏ ዞረችና..

«ትርፋማ ንግድ ነዉ አቡ ደህዳህ! ትርፋማ ንግድ ነዉ።» አለች።

እቺ እህትሽም የጀነትን ፀጋ በማሠብ ከዱንያዊዉ የአታክልት ስፍራ ወጣች።

ምን አይነት ሚገራርሙ ባልና ሚስት ናቸዉ?!

ልቧ በአታክልት ስፍራዉ ላይ የተንጠለጠለ ቢሆንም ያለ አንዳች ኪላፍና ሙሉ በሆነ ዉዴታ የባሏን ትዕዛዝ አከበረች። ወደደች።

ዛሬ እኔ ምንም አላወራም። ታሪኩ ብቻዉን ለሚገሰፁት በቂ ትምህርት ነዉ።

[[እህቴ! የፈለገዉን ያህል ፈታኝ ቢሆንም ከዱንያ የአታክልት ስፍራሽ ዉጪና ለአላህ መንገድ ደስ ከሚልሽ ነገር ላይ ለግሺ! ከንብረትሽ፣ ከወቅትሽ፣ ከእድሜሽ ለዚህ ዲን መፅዉቺ!! የአላህን ዉዴታና የጀነቱን የአታክልት ስፍራ በማሰብ በደስታ ካለሽ ላይ ስጪ!!]] የመጨረሻዉ ክፍል ይቀጥላል ኢንሻአላህ

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
ጋብቻ በኢስላም ቅንጭብ ድምጽ
በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን
👆👆👂👂 ይደመጥ
#ጋብቻ በኢስላም
#የጋብቻ ጥቅም
የጋብቻ አስፈላጊነት❗️

🎤በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
❗️ወደ መጥፎ ነገሮች የሚጠራህ ጓደኛ  ጓደኛህ ሳይሆን ጠላትህ ነውና ተጠንቀቀው❗️ አላህ መልካም ጓደኛ ይስጠን አሚን

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::እህቴ::::::::☜ ክፍል ዘጠኝ/⑨ ዛሬ የእዝነትና የፍቅር የአታክልት ስፍራ በሆነዉ (በአቡ ደህዳህ) የአታክልት ስፍራ ዉስጥ ቆይታ እናረጋለን። ያቺ የአታክልት ስፍራ ልብን በሀሴት ምትሞላ፣ ደስታ የምትሰጥ፣ ሰላማዊ አየር ያላት ዉብ የአታክልት ስፍራ ናት። ያየዉን ሰዉ ድንገት ሳያስተዉል ‛ሱብሀነላህ!’ እንዲል ታስገድዳለች። የመዲና ሰዎች አዉርተዉላት የማያበቁ እጅግ ዉብና ምርጥ የአታክልት…
☞::::::::::እህቴ :::::::☜

ክፍል አስር/⑩ የመጨረሻዉ ክፍል


..ከዱንያ ግብግብ ርቀሽ፣ የጌታሽን ዉዴታ ናፍቀሽ፣ ዉዱዕ አድርገሽ፣ ሁለት ረከዓ ሰግደሽ.. ወንጀልሽን ለአላህ እየተናዘዝሽ አልቅሰሽ አላህ ደግሞ የዉስጥ እርካታን፣ የመንፈስ ደስታን ሲሰጥሽ..

እንዴት ደስ ይላል?!

አቅልሽ፣ ልብሽና መላዉ አካላትሽ  ከሚያዉቁት ወንጀሎች ቶብተሽ፣ ነገር ግን የቂያማ እለት የማታስታዊሻቸዉ ወንጀሎችሽ አላህ ገልፆልሽ.. ያ ዱንያ ላይ የሰተረሽ አላህ አኼራም ላይ ሰትሮልሽ እንደዉም ወደ ሀሰና ቀይሮ ሚዛንሽን ከፍ ሚያረግ ከሆነ..

እንዴት ደስ ይላል?

ጥም ሊገልሽ ተቃርቦ፣ ድንብርብርሽ ጠፍቶ ወደቀኝና ግራ ስትመላለሺ ድንገት ሀዉድን አይተሽ ሰዎች ሲጋፉና ሲሽቀዳደሙ አንቺ ምንም ማረግ ባለመቻልሽ በታላቅ ድምፅ እይጮህሽ ባለበት ሁኔታ ላይ.. ከሩቅ ያ የፍጥረቱ ዐይነታ የሆኑትን የዓለሙን ብርሀን ፈገግ ብለዉ አይተሻቸዉ፣ በፊት አይተሻቸዉ ባታዉቂም በአንዴ ለይተሻቸዉ ሀዉዳቸዉን ጠጥተሽ ከዚያ መቼም ማትጠሚ ከሆነ..

እንዴት ደስ ይላል?!

«ያ አህለል ጀና!» ተብሎ በሚጠራበት ወቅት ላይ ያንቺም ስም እዛ ዉስጥ ሰፍሮ ከሆነ..

እንዴት ደስ ይላል?!

«እከሊት የእከሌ ልጅ!» ተብለሽ ተጠርተሽ ጀነትን ያለሂሳብና ያለቅጣት ምትወርሺ ከሆነ..

እንዴት ደስ ይላል?!

አላህ ፊት መቆምን ከናፈቅሽ፣
የሱን ንግግር መቅራትን ከናፈቀሽ፣
ሌሊትን እሱን ለመገናኘት ከናፈቅሽ፣
ቀንንም የሱን ትዕዛዛት ለመፈፀም ከናፈቅሽ፣
አዛን የሱ ጥሪ ነዉና እሱንም ከናፈቀሽ፣
ረሱሉን ከናፈቅሽ፣
ጀነትን ከናፈቅሽ፣
አላህን መገናኘትን ከናፈቅሽ..

እንዴት ደስ ይላል?!

እነዚህን ፅሁፎች አንብበሽ ዱዓ መቅቡል ሚሆንባቸዉን ወቅቶች መርጠሽ ለራስሽ ዱዓ እንደምታደርጊዉ ይህን ፅሁፍ ለፃፈ ሰዉም ዱዓ ምታደርጊ ከሆነ..

እንዴት ደስ ይላል?!

እህቴ ከላይ የተመኘሁትን በሙሉ አላህ ይወፍቅሽ!

ይህንን ከኸይር እጅግ በጣም ትንሽ እንጂ ምንም የሌለዉን ደካማ ባሪያንም አላህ በእዝነቱ እንዲያካብዉ ዱዓ አድርጊለት። አላህ የሱን ይቅርታ፣ የሱን ሙሀባ፣ የሱን ጀነትን ከሚወፈቁት ያደርገዉ ዘንድ ለምኚለት!!

የስንብት ወቅት ደርሷል!
ሀሳብ፣ አስተያየት፣ ቅሬታ ካላችሁ  አድርሱኝ

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
#ምንም_ነገር_ቢከሰት_ለኸይር_ነዉ

አንድ ቀን የሆነች ሴት ወደ ነብዩሏህ ዳውድ ዐለይሂ ሰላም እያለቀሰች መጣች፤ እንዲህም አለቻቸው ፦አንተ የአላህ ነብይ ዳውድ ሆይ! ጌታህ ፍትሃዊ ነው ወይስ በዳይ ነው? እርሳቸውም በአላህ እጠብቃለሁ ምንድነው የምትይው
አሏት ?

ምን እንደደረሰብኝ ተመልከት አለቻቸው ፡- እኔ ህፃናት ልጆች አሉኝ ፈትል ፈትዬ ሽጬ ነው የምመግባቸው ፡ፈትዬ በቀይ ፎጣ ጠቅልዬ ለመሸጥ ወደ ሱቅ ስሄድ በድንገት ከላይ ትልቅ አሞራ መጣና ፈትሌን ይዞብኝ ሄደ አያለች ታለቅሳለች ።

ነብዩላህ ዳውድም አንቺ የአሏህ ባሪያ ! አሏህን ፍሪ! ታገሽም እያሉ ያፅናኗታል፡ በድንገት በከተማዋ አሉ የተባሉ አስር ነጋዴዎች ገቡ፡፡እያንዳንዱ 100 ዲናር ምፅዋት ሊያደርጉ ነብዩ ዳውድም ለምን ብለው? ጠየቋቸው ፡እነርሱም እንዲህ አሉ ጀልባ ላይ ነበርን ጀልባዋ ተቀደደች ልንሰጥም ስንል አሞራ መጣና የሆነ ፎጣ ጣለልን በዛም ፎጣ ቀዳዳውን ደፈንነው ፤ ከዚህም ነፃ ከወጣን እያንዳንዱ 100 ዲናር ምፅዋት ሊሰጥ ቃል ገብተን ነበር አሉ፡፡

ነብዩ ዳውድም ዲናሮችን አንሰተው ሰጧትና በየብስና በባህር የሚመግበውን ጌታሽን በዚህ መልኩ ትገልጭዋለሽ?
በይ ይኸንን ይዘሽ ሂጂ አሏት ፡፡
ሱብሃን አሏህ ለአሏህ ጥራት ይገባው

እኛ ለራስችን ጥሩ ነው ያልነው መጥፎ ሊሆን ይችላል መጥፎ ነው ያልነው ደግሞ ጥሩ ሊሆንልን ይችላል በአሏህ ላይ መልካም ጥርጣሬ ይኑረን! አሏህም በተከበረው ቃሉ እንዲህ ብሎናል፦

وَعَسَىٰٓ أَن تَكْرَهُوا۟ شَيْـًۭٔا وَهُوَ خَيْرٌۭ لَّكُمْ ۖ وَعَسَىٰٓ أَن تُحِبُّوا۟ شَيْـًۭٔا وَهُوَ شَرٌّۭ لَّكُمْ ۗ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
አንዳች ነገርን እርሱ ለናንተ የበለጠ ሲሆን የምትጠሉት መኾናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አንዳችንም ነገር እርሱ ለናንተ መጥፎ ሲሆን የምትወዱት መሆናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አላህም (የሚሻላችሁን) ያውቃል ግን እናንተ አታውቁም፡፡(አል-በቀራህ፣216)
 
            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam