الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.4K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
925 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
☞ሱብሀን አላህ ልብ የሚነካ ነገር ነው

#ሼኽ_ናይፍ_እንዲህ_ይለናል

አላህ( سبحانه وتعالى) ሁላችንንም  ይጣራል ማረኝ በሉኝ ምህረትን  ጠይቁኝ ይላል

ከአንድ ወር ግማሽ በፊት እኔና ሸኽ ወሊድ  ሌሎችም ሼኾች  ከጅዳ ወደ ጣኢፍ  ለሙሃደራ  ለመሄድ አስበን መንገድ ላይ ሸኽ ወዲድ እንዲህ አለኝ የናይፍ አንድ እናት አለች ከጣኢፍ  አንድ ሳምንት ሆናት ስታናግረኝ ። እርሱም  አንድ ወንድ ልጅ አላት ። የልጁ እናትም እንዲህ አለችኝ የሸኽ ልጄን መታችሁ ብታውልኝ ዝያራ ብታደርጉለት አለች
። አመኛለሁ አላህ ብታስታውሱን  ከእናንተ ጋር ዳዕዋው ቦታ ብትወስዱልኝ እናንተ አላህን የምትዘክሩበት ቦታ አላህን ከምታስታውሱበት ቦታ  ውሰዱት ልጄ እንዲሰግድ እፈልጋለሁ ልጄ ወደ ጌታው እንዲመለስ እፈልጋለሁ  ልጄ  እደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ ሆኖ ቢሞትብኝ አልፈልግም ጌታውን ያውቅ ዘንድ እርዱኝ አለች ።
#ሼኽ_ወሊድም አለኝ የናይፍ ምን ይመስልሃል የዚህችን እናት ቃል ሰምተን ወደ ልጁ ብንሄድ አለኝ ። እኔም አልኩኝ መርሀባ የሼኽ ። ከዛም  ለልጁ  እናት ስልክ ወደልን  ። ልጁን ማናገር እንፈልጋለን አልናት  አናገርነውም ። አልነው ስማ  ወንድሜ  እኛ ከቤታችሁ ቅርብ ነን ። ከጂዳ ወደ ጣኢፍ የዳዕዋ የመጣን ሼኾች ነን  አልነው ። ቦታ ተቀጣጠርን እና ተገናኘን ።
ተሰላለምን ።ካላሰብነው በላይ መልካም ልጅ ሆኖም አገኘነው ። ከጌታው የራቀ ቢሆንም ግን አላህ ሙሉ አካል የሰጠው ሁሉ ነገሩ የተሟላ ነበር ። ከተሰላለምን በኃላም እንዲህ አልነው
። የምንልህ ነገር አለ ። እርሱም እሺ ምንድን ነው አለ ። እኛም አልነው ።

ዛሬ ጣኢፍ  ሙሀደራ አለ እናም ከእኛ ጋር እንድትሄድ እንፈልጋለን አልነው ።እርሱም አለ ስሙኝ መምጣታችሁ ለእኔ ወድጄዋለሁ ። ወላሂ እመጣለሁ ። የእህቴን ልጅ ይዤ አብረን እንመጣለን ሙሀደራውን አብረን እንከታተላለን አለን ።
ወላሂ በሙሀደራው ውስጥ ከ2000 በላይ ህዝብ ነበርና ሙሀደራ በምናደርግ ሰአት ልጁን እረሳነው ። ከሙሀደራው መጨረሻ ላይም ያ ልጅ ቀስ እያለ ወደ እኛ መጣ  አቀፈኝ እና ያለቅስ ጀመር ።ለጌታው  ስጁድም ወረደ ።

ጌታዬን አመሰግነዋለሁ እያለ ስጁድ ላይ ተደፋ ። ወላሂ ከ4 ቀን በፊትም መሞቱን ሰማን እናቱንም አላህ ያፅናሽ አልናት ። ሰው ሁሉ ይሞታል ። ግን ይሄ ልጅ እንዴት ሞተ የሚለው ነገር ። እናቱም አለች ወላሂ ከሙሀደራው  ወዲህ  የእናቱን ሀቅ ሲወጣ ነበር  አለች ።

ኡምራም አድርጎ መጣ አለች ። ከዛም የሱቢህ ሰላትን ሰገደ  ከመካ ወደ ጣኢፍ እየመጣ ከቤቱ ሲደርስ ሞተ ። አላህ  አዛኝ ነው አላህ መሀሪ ነው አላህ የባሮቹን መክፈር አይወድም ።
አላህ ምህረትን ይሻልናል አላህ ጀነትን ይወፍቀናል ። አላህ ለምንድን ነው ጥሩኝ ምህረትን ጠይቁኝ ያለው እኛ ምህረትን እናገኝ ዘንድ ነው ""!
የረብ የአላህ አንተ ተገዢዎች ሆነን እንጂ አትግደለን ። አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን አሚን ።

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam