الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.4K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
925 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
#ምንም_ነገር_ቢከሰት_ለኸይር_ነዉ

አንድ ቀን የሆነች ሴት ወደ ነብዩሏህ ዳውድ ዐለይሂ ሰላም እያለቀሰች መጣች፤ እንዲህም አለቻቸው ፦አንተ የአላህ ነብይ ዳውድ ሆይ! ጌታህ ፍትሃዊ ነው ወይስ በዳይ ነው? እርሳቸውም በአላህ እጠብቃለሁ ምንድነው የምትይው
አሏት ?

ምን እንደደረሰብኝ ተመልከት አለቻቸው ፡- እኔ ህፃናት ልጆች አሉኝ ፈትል ፈትዬ ሽጬ ነው የምመግባቸው ፡ፈትዬ በቀይ ፎጣ ጠቅልዬ ለመሸጥ ወደ ሱቅ ስሄድ በድንገት ከላይ ትልቅ አሞራ መጣና ፈትሌን ይዞብኝ ሄደ አያለች ታለቅሳለች ።

ነብዩላህ ዳውድም አንቺ የአሏህ ባሪያ ! አሏህን ፍሪ! ታገሽም እያሉ ያፅናኗታል፡ በድንገት በከተማዋ አሉ የተባሉ አስር ነጋዴዎች ገቡ፡፡እያንዳንዱ 100 ዲናር ምፅዋት ሊያደርጉ ነብዩ ዳውድም ለምን ብለው? ጠየቋቸው ፡እነርሱም እንዲህ አሉ ጀልባ ላይ ነበርን ጀልባዋ ተቀደደች ልንሰጥም ስንል አሞራ መጣና የሆነ ፎጣ ጣለልን በዛም ፎጣ ቀዳዳውን ደፈንነው ፤ ከዚህም ነፃ ከወጣን እያንዳንዱ 100 ዲናር ምፅዋት ሊሰጥ ቃል ገብተን ነበር አሉ፡፡

ነብዩ ዳውድም ዲናሮችን አንሰተው ሰጧትና በየብስና በባህር የሚመግበውን ጌታሽን በዚህ መልኩ ትገልጭዋለሽ?
በይ ይኸንን ይዘሽ ሂጂ አሏት ፡፡
ሱብሃን አሏህ ለአሏህ ጥራት ይገባው

እኛ ለራስችን ጥሩ ነው ያልነው መጥፎ ሊሆን ይችላል መጥፎ ነው ያልነው ደግሞ ጥሩ ሊሆንልን ይችላል በአሏህ ላይ መልካም ጥርጣሬ ይኑረን! አሏህም በተከበረው ቃሉ እንዲህ ብሎናል፦

وَعَسَىٰٓ أَن تَكْرَهُوا۟ شَيْـًۭٔا وَهُوَ خَيْرٌۭ لَّكُمْ ۖ وَعَسَىٰٓ أَن تُحِبُّوا۟ شَيْـًۭٔا وَهُوَ شَرٌّۭ لَّكُمْ ۗ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
አንዳች ነገርን እርሱ ለናንተ የበለጠ ሲሆን የምትጠሉት መኾናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አንዳችንም
ነገር እርሱ ለናንተ መጥፎ ሲሆን የምትወዱት መሆናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አላህም (የሚሻላችሁን) ያውቃል ግን እናንተ አታውቁም፡፡(አል-በቀራህ፣216)
 
            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam