ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
15.5K subscribers
335 photos
80 videos
146 files
208 links
This channel is not operated by Deacon Yaregal Abegaz

https://youtube.com/@yaregalabegaz?si=1f5NHTaQ2l2LbxWQ

“ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።”
— 2ኛ ቆሮ 11፥28
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"በቁም ላለመቀበር መንቂያው ጊዜ አሁን ነው"
#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
ጌታችን በተግባር እንዳስተማረን መንፈሳዊ ሕይወት በትንሹ ተጀምሮ ከዚያ ቀስ በቀስ እያደገና እየጠነከረ የሚሄድ እንጂ በአንድ ጊዜ ተጀምሮ በቅጽበት ፍጹም የሚሆንበት አይደለም፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትን ከተለያየ ሁኔታና ሕይወት ከጠራቸው በኋላ ወዲያውኑ ዕለቱን ወደ ፍፁምነት ደረጃ አልደረሱም፡፡ ብዙ ድክመቶች ነበሩቸው። እርሱ ስለ ሰማያዊ መንግስት ሲነግራቸው ስለ ምድራዊ መንግስት የሚጠይቁበት ጊዜ ነበር።የሚነገራቸውን ባለማስተዋላቸው፣ ለእርሱ የቀኑና የተቆረቆሩ ምስሎአቸው እሳት ከሰማይ ወርዶ እርሱን ያልተቀበሉትን ሰዎች እንዲያጠፋቸው በመጠየቃቸው፣ ስለ ሞቱና መከራው ሲነግራቸው “አትሙትብን” በማለታቸው ÷ ስለ እምነት ማነስ ሁሉ ብዙ ጊዜ ተገሥጸዋል፡፡ እነርሱም ከዚህ የተነሳ “ጌታ ሆይ እምነት ጨምርልን” እስከማለት ደርሰዋል ። ጌታችንም ብዙ ጊዜ ይገስጻቸውና ስሕተታቸውን እንዲያስተካክሉ በአባትነቱ ይመክራቸው ነበር፤ ሦስት ዓመት ከእርሱ ጋር ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት እያደሩ በቃልም በተግባርም ተምረው እንኳ ፍጹማን መሆን አልቻሉም ነበር። ጌታችን በሰጣቸው ተስፋ መሰረት መንፈስ ቅዱስን ሲቀበሉ ነበር ፍጹማን የሆኑት። እንግዲህ ሐዋርያት በእንዲህ ዓይነት ሂደትና ውጣ ውረድ ውስጥ ያለፉ ከሆነ ወደ ፍጹምነት ደረጃ መድረስ በአንድ በኩል በራስ ጥረት በዋናነትም በእግዚአብሔር ቸርነት በሂደትና ቀስ በቀስ እንጂ በአንድ ጊዜ በቅጽበት የሚሆን ነገር አይደለም ማለት ነው፡፡ በክርስትና የሕይወት ጉዞ ውስጥ የሕይወትን አካሄድ÷ ስልትና ዘዴ ማወቅ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ የጉዞውን ርዝመትና ጠባይ እንዲሁም በሂደቱ ውስጥ ያሉና ሊገጥሙ የሚችሉ ነገሮችን አስቀድሞ ሳያውቁ የሚጀመር ጉዞ መሰናሎች ሲገጥሙት የመውደቅ ዕድሉ የሠፋ ነው፡፡ ከዚህም አንዱ የአካሄድን ፍጥነት መወሰን ነው፡፡ አንዳንዶች ክርስትና በተወሰነ ጊዜ ተሰርቶ ማለቅ እንዳለበት የሥራ ዕቅድ (ፕሮጀክት) ወዲያውኑ እንደ ጀመሩ አካሄዳቸው የጥድፊያና የችኮላ ይሆናል፡፡ ሰውነቱ ጾምን በሚገባ ሳይለማመድ እስከ ማታ ድረስ በመጾም ይጀምራል። «የክርስቶስ ክቡር ደም በፈሰሰባት ምድር በጫማ አልሄድም» እስከ ማለት ይደርሳል፡፡ ይህን ዓለም በሙሉ የመጸየፍና የምናኔ ነገር ብቻ ይታሰበዋል። ሌሎች ሰዎች ኀጢአተኞችና ደካሞች ሆነው ይታዩታል። አንዳንዶች ሥራቸውን እስከ መተው ደርሰው በየገዳማት መዞርን ብቻ ስራዬ ብለው ይይዛሉ:፡ በአጠቃላይ ነገሮችን ሁሉ እንዳይሆን እንዳይሆን አድርገው ይይዟቸዋል፡፡ በየቦታው በመዞር ብቻ በረከትና ጽድቅ የሚገኝ ይመስለዋል። ከትምህርት ቤት ወደ ትምህርት ቤት እየተዘዋወረ መምህር ሲያማርጥና የተመቸ ሁኔታን ሲፈልግ አንድ ቁም ነገር ሳይማር ጊዜውን የሚያጠፋውን ተማሪ አበዉ ’እግረ ተማሪ’ ይሉታል፡፡ዛፍ እንኳን ፍሬ የሚያፈራው ከተተከለበት ቦታ ሲኖር ነው:: ነገር ግን በየጊዜው እየተነቀለ የሚተከል ከሆነ ወይ ይደርቃል፤ ባይደርቅ እንኳ ፍሬ ማፍራት አይችልም።ጊዜውን በዙረት ብቻ የሚጨርስ ሰውም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም፡፡ ቢያፈራም እንኳ በአንድ ቀን በቅላ በአንድ ቀን አብባ በአንድ ቀን ታፈራለች እንደምትባለው ዕፀ ከንቱ÷ ፍሬው ምትሐታዊ ይሆንና ከመታየቱ ወዲያውኑ ይረግፋል። በእንዲህ ያለ ሕይወት የሚጓዙ ሰዎች የማይመች አካሄድ ውስጥ ይወድቃሉ፡፡ ይህ ዓይነት ሕይወት ብዙ ችግሮችን ሊያስከትል የሚችል አስቸጋሪ አካሄድ ነው፡፡
....................

ክርስትና የክርስቶስ ፍቅር እንደ ተረዳውና እንዳከበረው መጠን ከውስጥ በሚመነጭ ፍቅር የሚመሠረት እንጂ በተጽዕኖ ከውጭ የሚጫን ሸክም አይደለም። ሐዋርያው «የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል» አለ እንጂ ሌላ ማንም ያስገድደናል አላለም። በሰዎች ላይ ከባድና እስቸጋሪ ሸክም የሚጭኑ ጸሐፍትንና ፈሪሳውያንን ጌታችን እንዲህ በማለት ገሥጾአቸዋል « ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፥ እነርሱ ግን በጣታቸው እንኳ ሊነኩት አይወዱም»:: ማቴ 23÷4። እንዲህ በሌሎች ላይ መጫን ገድልና ትሩፋት መስሎ የሚታያቸው ሰዎች ሁሉን ከሚያውቅና ሁሉን በጊዜው ከሚያደርግ ጌታ ጋር ያሉትን ቅዱሳን ሐዋርያትን የግድ፥ እንዲጸሙ ለማደረግ ወደ ጌታችን ቀርበው: « እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጾመው ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጸሙት ስለ ምንድነው?» እስከማለት ደርሰዋል፡፡ ለጾም ከራሱ ከባለቤቱ የበለጠ ተቆርቋሪዎች በመምሰል በሌሎች ላይ ለመወሰን ቀረቡ፡፡ ማቴ.9÷14። አባቶቻችን ሐዋርያትንም እንጀራ ሲበሉ፡ “እጃቸውን አይታጠቡም በሰንበት ቀን እሸት ቆርጠው በሉ» ወዘተርፈ እያሉ ይከሷቸውና ይነቅፏቸው ነበር:: ጌታችን ከሰው የሚፈልገው ግን ከባድና አስጨናቂ የሆኑ ነገሮችን አይደለም፤ « እናንተ ደካሞች፥ ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፉችኀለሁ… ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና» በማለት የእርሱ ቀንበር ቀላልና የማይጎረብጥ መሆኑን ነገረን። የተለያዩ ሰዎች መጥተው ምን አናድርግ?» እያሉ በጠየቁት ጊዜ ዮሐንስ መጥምቅ የነገራቸዉ በዚያው በአቅማቸው ሊሠሩት የሚችሉትን እንጂ ከባድ የሆኑ ነገሮችን አላዘዛቸውም ሉቃ.3፥10-14:: ምክንያቱም ገና በመንፈስ ያላደጉ ስለነበሩ ከበድ ያለ ነገር ቢነግራቸው አይችሉትምና፡፡ ጌታችንም፦ «ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና በማለት ለሁሉም በሚቻልና በማይከብድ ሁኔታ አዘዘ ማቴ.7÷1። ሌሎች ለእኛ ሊያደርጉልን የምንወደውን ነገር እኛም ያንን ለሌሎች ማድረግ እንችላለንና። ሌሎች እንዲያደርጉልን ከምንፈልገው ነገር እኛ ለሌሎች ማድረግ የማንችለው ካለ ከሌሎች የምንፈልገው እኛ የማንችለውን ነው ማለት ነው። እኛ የማንችለውን ከሌሎች መጠበቅ ደግሞ ተገቢ አይደለም፡ እንዲሁም ራሳችን ከሌሎች የምንፈልገውን ጠንቅቀን እንደ ምናውቅ ሁሉ ሌሎች ከእኛ የሚፈልጉትንም በእኛው ፍላጎት አንጻር በቀላሉ ማወቅ እንችላለን፡ ስለዚህ ይህን ማወቅም ሆነ መፈጸም ከባድ አይደለም።
...................

ወደ ክርስትና የገቡት አይሁዶች እንኳ ኦሪታዊ ልማዳቸው አልተዋቸው ብሎ ከቤተ አሕዛብ እያመኑ ወደ ክርስትና የሚመጡትን አማንያን «ያንኑ የኦሪቱን ሕግና የሙሴን ትእዛዛት በሙሉ ሊጠብቁ ይገባል» እያሉ ስላስቸገሩ በዚህ ምክንያት የመጀመሪያው የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ በኢየሩሳሌም ተደርጓል። በዚህ ጉባኤም ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ «እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን እግዚአብሔርን አሁን ስለምን ትፈታተናላችሁ?» በማለት የጉባኤ መግቢያ ሐሳብ ተናገረ። ከዚያም ቅዱሳን ሐዋርያት ከተወያዩ በኋላ፦ ለጣዖት ከተሰዋ ከደምም ፥ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና ክዚህ ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ» ሲሉ በአንድነት ወሰኑ። የሐዋ. 15፥29።

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

#በየጥቂቱ_ማደግ

ሐመር መስከረም/ጥቅምት ፲፱፻፺፰ ዓ.ም
👆👆👆👆👆
ሃይማኖት እና እምነት
* ሃይማኖት ምንድን ነው?
* እምነት ምንድን ነው?
* የእምነት አይነቶች በመጽሀፍ ቅዱስ
ሃይማኖት አያስፈልግምን ?
* ክርስትና ሃይማኖት አይደለምን?
* ድህነት በሃይማኖት አይደለምን?
* በሞተልን ጌታ የምንገኘው እንዴት ነው?
* ወንጌል በየትኛውም ሃይማኖት ቢሰበክ ችግር የለውምን?
* ዶግማ ማለት ምን ማለት ነው?
* ኦርቶዶክስ ተዋህዶበሰው የተመሰረተች ነችን?
* የሃይማኖት ክፍልፋይ ስም ነው ችግራችን? ወይስ የመጽሀፍ ቅዱስ አረዳድ?
* የመጽሀፍ ቅዱስ ክርስትና እንደምን ያለ ነው?
* በሃይማኖቶች መካከል ያለው የአስተምህሮ ልዩነት ችግር የለውምን?

#መድሎተ_ጽድቅ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
ኑፋቄ (በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ) (1).pdf
330.5 KB
ኑፋቄ

* ኑፋቄ ምንድን ነው?

በዘመናት የነበሩ ዋና ዋና መናፍቃንና ኑፋቄያቸው በአጭሩ

* ግኖስቲኮች/ ኖስቲኮች
* አርዮስ
* ንስጥሮስ
* ሄልቪዲየስ
* ጆቪኒያን
* ቪጂላንቲየስ
* አርዮስ ዘሴባስቴ
* ማርቲን ሉተር

#መድሎተ_ጽድቅ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጠቀሜታ

* ተግባራዊ ተሞክሮ ነው
* ጥንታዊውንና ትክክለኛውን ሃይማኖት ለማወቅ ይረዳል
* ለመልካም ምግባር የሚያነሳሱ ምሳሌ የሆኑ ቅዱሳን ህይወት አለው
* ለተግባራዊ ክርስትና ይረዳል
* ያለ ምስክር ላለመቅረት ያግዛል
* የማንም መሞከሪያ ላለመሆን ይረዳል
* ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን በአግባቡ ለመፍታት ይጠቅማል

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ህይወቱና_ትምህርቱ_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
214.8 KB
ወደ ቤተ ክርስቲያን ስላልመጡ ምዕመናን

የሚያስጨንቅህ የዚህ ዓለም ጉዳይ አለብህ? እዚህ በምታሳልፈው ጊዜ የእግዚአብሔርን ርዳታና ምሕረት ታገኝ ዘንድ፣ በመረጋጋትና በመጽናናት መንፈስ ሆነህ ትሄድ ዘንድ ስለዚህ ምክንያት ወደዚህ ና፡፡ እርሱ ኃይልሀና ጋሻህ ይሆን ዘንድ፣ በሰማያዊ ሥልጣን በመጠበቅ ለጠላቶችህ ለአጋንንት የማትሸነፍ ትሆን ዘንድ ወደዚህ ወደ ጸጋው ዙፋን ና፡፡ በአባቶች ከሚደርሰው ጸሎት ሱታፌ ካለህ፣ በማኅበር ጸሎት ከተሳተፍክ፣ ቅዱስ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ከሰማህ፣ የእግዚአብሔርን ርዳታ ካገኘህ፣ እነዚህን መሣሪያዎች ከታጠቅህ የትም ብትሄድ እንዳንተ ያሉ ሥጋ የለበሱ ጠላቶችህ ክፉዎች ሰዎች ይቅርና ዲያብሎስ ራሱ ፊትህን ማየት አይችልም፡፡ ነገር ግን ከቤትህ እንደ ተነሣህ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሳትመጣ ወደ ገበያ፣ ወደ ሥራ፣ ወዘተ ብትሄድ ብቻህን ያለ ምንም መንፈሳዊ ትጥቅና ጸጋ እግዚአብሔር ስለምትሆን ሁሉም ነገር በአንተ ላይ ይበረታብሃል፤ ጠላቶችህም በቀላሉ ያጠቁሃል

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ህይወቱና_ትምህርቱ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"መጽሀፍ ቅዱስ ብቻ"

* መለያየትን ያመጣል
* የጋራ እውነትን ያጠፋል
* ክርስትናን ያዳክማል
* እንደተፈለገ መተርጎምን ያስከትላል
* ሃይማኖትን አንፃራዊ ያደርጋል
* ሥነ ምግባርን ያጠፋል
* ሁሉም እምነት ያስኬዳል ወደሚል ክህደት ይወስዳል


#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
ለካህን_መናዘዝና_ቀኖና_መቀበል_ለምን_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
333.1 KB
ለካህን መናዘዝና ቀኖና መቀበል ለምን?

* የተሐድሶዎች ትምህርት ለካህን ስለመናዘዝና ቀኖና ስለመቀበል
* በዚህ ጉዳይ ላይ የተሐድሶዎች መሠረታዊ ስህተቶች
* ለንስሐ አባት መናዘዝና ቀኖና መቀበል በመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት
* ቀኖና የሚሰጥባቸው ምክኒያቶች
* ንስሐ አባትና ቀኖና በአበው ትምህርት

~ +++++ ~~

“ነቢዩ ናታን ንጉሥ ዳዊትን ኃጢአቱን ከነገረው በኋላ ወዲያውኑ ኃጢአቱን እንዳመነ አጽናንቶት ነበር፡፡ ሆኖም ብፁዕ ዳዊት ግን ምንም እንኳ እግዚአብሔር ደግሞ ኃጢአትህን አርቆልሃል፡ ኣትሞትም' (2 ሳሙ. 12፡13) የሚለውን የነቢዩን ቃል የሰማ ቢሆንም ንስሐ ከመግባት ግን አልተመሰለም፡፡ ንጉሥ የነበረ ቢሆንም በልብሰ መንግሥት ፋንታ አመድ ለበሰ በወርቅ ዙፋን ላይ በመቀመጥ ፋንታ በመሬት ላይ፣ ያውም በአመድ ላይ ተቀመጠ፡፡ በአመድ ላይ የተቀመጠ ብቻ ሳይሆን አመድንም ምግቡ አደረገ፤ እርሱ ራሱ “አመድን እንደ እህል ቅሜያለሁና፣ መጠጤንም ከእንባዬ ጋር ቀላቅያለሁና” (መዝ 101፡9) ብሏልና፡፡ ወደ ኃጢአት የተመለከተው ዓይኑ በዕንባ እስኪሟሟ ደረሰ፤ “ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ፣ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ፤ ዓይኔ ከቍጡ ዕንባ የተነሣ ታወከች” እንዳለ፡፡ መዝ. 6፡6-7 መኳንንቱ እህል እንዲቀምስ በለመኑት ጊዜ እንኳ አልሰማቸውም፡፡ ጾሙን እስከ ሰባት ሙሉ ቀናት አራዘመ፡፡ ንጉሥ የነበረው እርሱ እንዲያ ባለ ሁኔታ ንስሐ ከገባ ተራ ግለሰብ የሆንከው አንተ ንስሐ ልትገባና ልትናዘዝ አይገባህምን?” (ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም፣ ትምህርት 2 በእንተ ንስሐ ወሥርየተ ኀጢአት፣ ቁ 12)


#መድሎተ_ጽድቅ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
ሁሉም_ክርስቲያን_ካህን_ነውን_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
323.4 KB
ሁሉም ክርስቲያን ካህን ነውን?

* የ1ኛ ጴጥሮስ 2፥9 እንዲሁም የዮሀንስ ራዕይ 1፥6 ማብራሪያ እና ከ ዘጸአት 19፥6 አንፃር
* ክህነትን የተዳፈሩ ሰዎች
* ካህናት ትሆኑ ዘንድ ምን ማለት ነው?
* የክርስቲያኖች ሁሉ አጠቃላይ ክህነት

++++ ~~ +++++

እዚህ ላይ ጳውሎስ “ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ” ሲል አሳሰበን። ሰውነት መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበው እንዴት ተደርጎ ነው? ብሎ የሚጠይቅ ይኖር ይሆናል። ዓይን ክፉ ነገርን አይመልከት፣ እንዲህ ካደረግህ ዓይንህ መሥዋዕት ሆኖ ቀርቧል ማለት ነው፤ እጅህ ሕገ ወጥ የሆነ ተግባርን አያድርግ፣ ይህ ከሆነ የተቃጠለ መሥዋዕት ሆኗል ማለት ነው። ወይም ይህም ብቻውን በቂ አይደለም፣ በዚህ ላይ መልካም ሥራን መሥራትም ይገባናል እንጂ። እጅ ምጽዋትን ይስጥ፣ አንደበት የሚረግሙትን ይመርቅ፣ ጆሮም የቅዱሳት መጻሕፍትን ትምህርት በመስማት ደስ ይሰኝ። መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብ ነገር አንዳችም ነውርና ነቀፋ ያለው ሆኖ ሊቀርብ አይችልምና። መሥዋዕት የሌሎች ተግባራት ሁሉ ቀዳምያት ነውና። ስለዚህም ከእጃችንም፣ ከእግራችንም፣ ከአንደበታችንም፣ ከሌላውም አካላችን ሁሉ ለእግዚአብሔር ቀዳምያትን እናቅርብ። ይህ ዓይነቱ መሥዋዕት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ነው። (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)


#መድሎተ_ጽድቅ
#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
ከበረሐውያን አንደበት.pdf
16.4 MB
ከበረሐውያን ሕይወትና አንደበት

ጥበብ ወምክር ዘአበው ቀደምት

++++++~+++++

#ጸሎት_ከበረሓውያን_አበው


ሁሉም ነገር ለፈቃድህ የሚገዛልህና የሚታዘዝልህ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ያደረግሁትን ነገር ሁሉ ይቅር በለኝ፣ ኃጢአተኛ
የሆንኩትን እኔን ከአሁን በኋላ እንዳልበድል አድርገኝ፡፡ ጌታ ሆይ፣ የማይገባኝ መሆኔን
ባውቅም ከኃጢአቴ ሁሉ ልታነጻኝ ትችላለህ። ጌታ ሆይ፣ ሰው ፊትን እንደሚያይ፣ አንተ ግን ልብን እንደምታይ አውቃለሁ፡፡ ቅዱስ መንፈስህን ወደ ውስጤ ጥልቅ ላክልኝ፣ ነፍሴንና ሥጋዬን ይኖርበትና ገንዘቡ ያደርገው ዘንድ፡፡ ያለ አንተ ልድን አልችልም፤ በምትጠብቀኝ በአንተ ግን ማዳንህን እናፍቃለሁ፡፡ እናም አሁን አንተን ማዳንህን እለምንሃለሁ፡፡ የአንተን ጥበብ እሻለሁ፣ የሚረዳኝንና የሚጠብቀኝን ታላቁን ደግነትህንና ቸርነትህን እማጸናለሁ፡፡ ሁሉን ቻይ ታላቅ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ በቀንና በሌሊት የአንተን መኖር አስታውስና አንተን ሁል ጊዜ በፊቴ አደርግህ ዘንድ ልቤን ምራልኝ፡፡

+ አሜን +


#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
ምጽዋት (በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ).pdf
199 KB
ምጽዋት

* ምጽዋት በመጽሀፍ ቅዱስ ትምህርት

* ምጽዋት በአበው ትምህርት

++++++++~~++++++

ከጥምቀት በኋላ የሚሠሩ ኃጢአቶችን ማስወገጃና ማጠቢያ መንገድ ማግኘት መቻል ምን ያህል ታላቅ ነገር መሆኑን ልብ በል! ምጽዋት መስጠት ምን ያህል ታላቅ ዋጋ እንዳለው አስተውል፡፡ እርሱ ምጽዋት ስጡ ባይለን ኖሮ፣ 'ገንዘብ መስጠትና ከሚመጣው ክፉ ነገር በምጽዋት አማካይነት መዳን የሚቻል ቢሆን ኖሮ እንዴት ጥሩ ነበር' የሚሉ ስንት ሰዎች በኖሩ ነበር! ነገር ግን አሁን እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ቸርነት የተነሣ በምጽዋት አማካይነት ከሚመጣው ክፉ ነገር መዳን የምንችልበትን ዕድል ስለ ሰጠንና ይህን የሚቻል ስላደረገልን እንደገና ብዙዎች ተመልሰው ግድ የለሾች ሆነው ይታያሉ፡፡ አይ፣ እኔ ምጽዋት እሰጣለሁ እኮ ትል ይሆናል፡፡ ይህ ምንድን ነው? ሆኖም ግን መቀነቷን ፈትታ ሁለት ሣንቲሞችን እንደ ሰጠችው ሴት ያህል አልሰጠህም፡፡ ኧረ የእርሷን ግማሽ ያህል፣ እርሷ ከሰጠችው ጥቂቱን ያህል እንኳ አልሰጠህም፡፡ ካለህ ገንዘብ ብዙውን ክፍል ጥቅም በሌለው ነገር ላይ ታባክነዋለህና፡፡ በመጠጥ፣ በመባልዕት ቅጥ ባጣ አባካኝነት እያዋልክ ራስሀን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም እንደ አንተ እንዲያባክኑና ገንዘባቸውን በማይጠቅማቸውና ተገቢ ባልሆነ ነገር ላይ እንዲያጠፉት ፈተና ትሆንባቸዋለህና፡፡ በዚህም ቅጣትህ እጥፍ ድርብ ይሆንብሃል፤ የራስህ ጥፋት አንሶህ ሌሎችንም ወደ ጥፋት መርተሃቸዋልና፣ የኃጢአት ምክንያት ሆነሀባቸዋልና፡፡ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ ትርጓሜ ወንጌለ ማቴዎስ፣ ክፍለ ትምህርት 67፣ ቁ. 5)


#መድሎተ_ጽድቅ
#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ኦርቶዶክስ መሆን በራሱ ኋላ ቀርነት እንደሆነ ተደርጎ ነው የተሰበከው"

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
ክህነት_በሀዲስ_ኪዳን_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ_.pdf
247.5 KB
ክህነት በሀዲስ ኪዳን

* የተለየ ክህነት
* አዲስ ክርስቲያን ካህን መሆን ይችላል?
* ሽማግሌ ወይስ ካህን ?

++++++++++~~~~~+++++++++

ኃጢአትን ይቅር የማለትን ሥልጣን ለራሱ ለእግዚአብሔር ብቻ የሚገባ ሥልጣን ስለሆነ ይህን ለሌላ ለማንም አንሰጥም በማለት፣ እግዚአብሔርን ታላቅ በሆነ አክብሮት እናከብረዋለን ይላሉ። ሆኖም ግን እርሱ በግልጽ የተናገረውን ትእዛዙን እንደሚሽሩትና ለካህናት የሰጠውን ሥልጣን አንቀበልም እንደሚሉት እንደ እነርሱ አድርጎ የሚያቃልለው ሌላ ማንም የለም። ራሱ ጌታችን “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፣ ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል” ያላቸው ከሆነ፣ እግዚአብሔርን የሚያከብረው የእርሱን ትእዛዝ ተቀብሎ የሚታዘዘው ነው? ወይስ ትእዛዙን አልቀበልም የሚለው? .. " (ቅዱስ አምብሮስ በእንተ ንስሐ፣ መጽሐፍ 1፡6-7)

#መድሎተ_ጽድቅ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
አንድ ወንድም ወደ ቅዱስ መቃርዮስ ሄደና “እድን ዘንድ የሚረዳኝን ምክር ምከረኝ" አለው፡፡ መቃርዮስም "ወደ መቃብር ቦታ ሒድና ሙታንን ስደባቸው" አለው፡፡ ያ ወንድምም ወደዚያ ሄዶ ሰድቧቸውና ድንጋይ ወርውሮባቸው ተመለሰና ይህንኑ ማድረጉን ነገረው፡፡ መቃርዮስም “ምን አሉህ?” ሲለው እርሱም “ምንም ነገር አላሉኝ" አለው። አረጋዊውም “ነገ ተመልሰህ ሒድና
አመስግናቸው” አለው፡፡ ያ ወንድምም ተመልሶ ሔደና “እናንተ እናንተ ሐዋርያት፣ ቅዱሳንና ጻድቃን ሰዎች ናችሁ" እያለ ሲያመሰግናቸው ውሎ ተመለሰ፡፡ አረጋዊውም “ምንም አልመለሱልህም?" አለው፡፡ እርሱም “የለም” አለ፡፡ መቃርዮስም “ሙታንን እንደ ሰደብካቸውና ምንም እንዳልመለሱልህ፣ እንደ
ገናም እንዳመሰገንካቸውና ምንም ነገር እንዳልተናገሩህ አይተሃል፡፡ አንተም ልትድን ከፈለግህ እንዲሁ ማድረግና የሞትህ መሆን
አለብህ። ልክ እንደ ሙታን የሰዎችን ነቀፌታቸውንም ሆነ ምስጋናቸውን ከቁም ነገር አትቁጠረው፣ ቦታም አትስጠው፣ እንዲህ ብታደርግ ትድናለህ” አለው፡፡

++++++++~++++++


በአንጾኪያ የነበረ አንድ ደግ መነኩስ እንዲህ አለ፦ “እጸልይ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ሄድሁ፤ በዚያም የምመገበው ስላልነበረኝ እንደ ራበኝ አዝኜ ተኛሁ:: ክርስቶስ ሌሊት ታየኝና «ጎልጎታ
ወዳለ ቄስ ሂድና አንዲት ዲናር ትሰጠኝ ዘንድ ክርስቶስ ወዳንተ ልኮኛል፣ እርሱ መጥቶ ይከፍልሃል በለው» አለኝ:: በነቃሁ ጊዜ
ወደ ቄሱ ሄድሁና ነገርሁት:: እርሱም «ክርስቶስ የሚመጣና ገንዘቤን የሚሰጠኝ መቼ ነው?» አለኝ፡፡ እኔም እርሱ ያለኝን ነግሬሃለሁ፣ ከዚህ በኋላ የወደድከውን አድርግ አልሁት፡፡ እርሱም
«ጻፍልኝ» ኣለኝ፡፡ እኔም እኔ የአንጾኪያው ዮሐንስ ከኢየሩሳሌሙ ቀሲስ እስጢፋኖስ አንድ ዲናር ወስጃለሁ፤ ክርስቶስ መጥቶ ዲናሩን እንደሚከፍለው ይኸው በእጄ ጽፌአለሁ ብዬ ጻፍሁለት፡ እርሱም ሰጠኝ። በዚያው ሌሊት ክርስቶስ ታየውና «ዲናርህን ውሰድና ያ መነኰስ የጻፈውን ጽሑፍ መልስልኝ» አለው᎓᎓ እርሱም «ክርስቶስ መጥቶ ይመልስልሃል ብሎኝ አልነበረምን?» አለው፡፡ እርሱም «ዲናርህን ውሰድና የዚያን መነኰስ ጽሑፍ መልስልኝ የምልህ እኔ ራሴ ክርስቶስ ነኝ» አለው:: ያም ቄስ እየፈራና እየተንቀጠቀጠ ከእንቅልፉ ነቃ፡፡ ወደዚያ መነኰስም ወደ እርሱ በፍቅር ይመጣ ዘንድ ላከበት፡፡ መነኲሴው ግን ያቺን ዲናር አምጣ ሊለኝ ነው ብሎ ፈራ፡፡ ኣብረው ሲበሉም «ከገንዘቤ የፈለግከውን ሁሉ ውሰድ» አለው፡፡ መነኲሴው ግን ከታዘዘልኝ በቀር ሌላ አልፈልግም” አለው፡፡ ቄሱም በሀልሙ የሆነውን ነገር ነገረውና “አሥር መክሊት ወርቅ ውሰድና ጻፍልኝ” አለው። እርሱ ግን “ከአንድ ዲናር በቀር ሌላ እወስድ ዘንድ አምላኬ አላዘዘኝም፡፡ ነገር ግን በፍጹም ልብህ
ካመንህ ብዙ ነዳያንን ታገኛለህ፤ እነርሱም እንዲህ ይጽፉልሃል” አለው::

++++++++++++~~~~+++++++++

ነፍስህ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ ስትሰለች ፣ ቃለ እግዚአብሔር ማንበብና መስማት ደስ የማይላት ሲሆንና ሲያስጠላት፣ እንዲሁም መንፈሳዊ ተግሳፅን ስታቃልል ካየሀት በክፉ ደዌ ላይ እንደወደቅህ ተገንዘብ፤ ሰዎች የሞትን ፍሬ የሚቀጥፉበት መጀመሪያው ይህ ነውና።

#ከበረሐውያን_አንደበት

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
ወላዲተ_አምላክ_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
352.7 KB
ወላዲተ አምላክ

*እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም "ወላዲተ አምላክ" ትባላለችን? ለምን?

* "ወላዲተ አምላክ" የቃሉ ትርጉም

* የቃሉ ነገረ መለኮታዊ ፋይዳ

* የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክነት በመጽሀፍ ቅዱስ ትምህርት

* የእመቤታችን ወላዲተ አምላክነት-በቀደምት አበው ትምህርት

+++++++++~~~+++++++

ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስ “ወላዲተ አምላክ” የሚለውን መቃወሙ በነገረ ክርስቶስና በነገረ ድኅነት ላይ የሚያስከትለው ነገር መሠረታዊ የሆነ ኑፋቄ መሆኑን በሚገባ አስረድቷል፡፡ እነዚህን ነገሮችም እንደሚከተለው በሚገባ ለይቶ አውጥቷቸዋል፡-

ከድንግል ማርያም የተወለደው አካላዊ ቃል የእኛን ባሕርይ ነሥቶ (ተዋሕዶ) ሥግው ቃል ካልሆነና ሰው ብቻ (ዕሩቅ ብእሲ) ከሆነ መዳናችን አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ ምክንያቱም ክርስቶስ የተቀበላቸው ሕማማትና መከራዎች የሥግው ቃል (ሥጋን የተዋሐደውና የእኛን ባሕርይ ባሕርዩ አድርጎ ሰው ሆኖ በሥጋ የተገለጠው አካላዊ የእግዚአብሔር ቃል) ሕማማትና መከራዎች ሳይሆኑ የዕሩቅ ብእሲ (የስው ብቻ) ይሆናሉና፡፡ ፍጡር በሆነ በሰው ብቻ መዳን አይቻልምና ስለዚህ ድነናል ማለት አይቻልም፡፡ ስለዚህ ወላዲተ አምላክ የሚለውን ቃል መካድ የአምላክን ሰው የመሆን ምሥጢር (ምሥጢረ ሥጋዌን) እና የሰውን መዳን መካድ ነው፡፡

እንደዚሁም አካላዊ ቃል አዲሱን ሰው ዳግማዊ አዳምን ለመፍጠር አካላዊ ቃል ከእኛ ባሕርይ ጋር ሊያደርግ የሚያስፈልገው ተዋሕዶ፡ ንስጥሮስ እንዳለው ዓይነት አፍኣዊና የጉርብትና ዓይነት ዝምድና ሳይሆን፣ ውሳጣዊና ባሕርያዊ የሆነ ጥብቅ እና አማናዊ የሆነ ተዋሕዶ ያስፈልገው ነበር፡፡ ይህ አይደለም ከተባለ የባሕርያችን መታደስ፡ በሐዲስ ተፈጥሮ የመዳናችን ነገር ሁሉ ከንቱ ይሆናል፡፡

#መድሎተ_ጽድቅ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ