TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የፍርድ ቤት ውሎ⬇️

በሃገር ኢኮኖሚ ላይ #አሻጥር በመስራት እና በኢኮኖሚ ላይ #ጫና ማሣደር ወንጀል ተሣትፈዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የነበሩ 9 የሲቪል አቪዬሽን የአየር ትራፊክ ቁጥጥር ሰራተኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድን በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት በአቀረበው የምርመራ መዝገብ ተጠርጣሪዎች በቡድን በመደራጀት መንግሥትና ህዝብን ለማለያየት ተንቀሣቅሰዋል የሚለውን ጠቅሷል፡፡

ወርሀዊ ደሞዛቸው በአስር እጥፍ እንዲያድግና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች አልተከበሩልንም በማለት ከነሐሴ 21 ጀምሮ የሥራ ማቆም #አድማ ማድረጋቸውንም ፖሊስ ጠቅሷል፡፡

ለዚህም እንዲረዳቸው የሌሎች ሰራተኞችን ፊርማ በማስመሰል መፈረም እና ስራ እንዲያቆሙ አነሣስተዋል በሚል #ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር እንዲውሉ ካደረጓቸው ምክንያቶች ይጠቀሣል የሚለውንም የምርመራ ቡድኑ በመዝገቡ አካቷል፡፡

ቡድኑ ሌሎች የምርመራ ስራዎችን ለማከናወን 14 ቀን ጠይቋል። ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው የመብት ጥያቄዎችን ማንሣታቸውን በመጥቀስ ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸው እንዲያከብርላቸው አመልክተዋል፡፡

ግራቀኙን የተመለከተው ችሎት ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀን 8 ቀን በመፍቀድ ለመስከረም 2 /2ዐ11 #ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢንጂነር ስመኘው በቀለ⬇️

ኢንጅነር #ስመኘው_በቀለ ራሳቸውን ማጥፋታቸውን የፖሊስ የምርመራ ውጤት እንደሚያሳይ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። ኢንጅነር ስመኘው ራሱን ካጠፋ በኃላ በወቅቱ ህይወቱ ሳትወጣ እያጣጣረ ፖሊሶች በቦታው መድረሳቸውንም ገልጸዋል፡፡

በፖስታው ውስጥ የተገኘው መልዕክት ስለ ቤተሰባቸው #አደራና ያለባቸውን #ጫና የሚገልፅ ፣ እንዲሁም ወደ ውጭ ለመውጣት ፍላጎት እንደነበራቸው ቢወጡም ለህዝቡ የሚሰጡት ምላሽ እንዳሳሰባቸው የሚገልጽ እንደነበረም ተናግረዋል፡፡

የሚሞቱበትን #ምክንያት ግን በፖስታው መልዕክት አሳማኝ ሆኖ #አለመጠቀሱን ፖሊስ ገልጿል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተከራዮች ቅሬታ‼️

በቅርቡ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተደረገው የንግድ ቤቶች ኪራይ ዋጋ ጭማሪ በተገቢው ጥናት ያልተደገፈና በነጋዴው ላይም #ጫና እያሳደረ መሆኑን የተከራይ ነጋዴዎቹ ተወካዮች ተናግረዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በበኩሉ፣ የኪራይ ዋጋ ማሻሻያው በተገቢው ጥናት ተደግፎ የተከናወነ ቢሆንም ነጋዴዎቹ እንደ ችግር የቀረቡትን ጥያቄዎች ወስዶ በትኩረት እያየ መሆኑንና ለጥያቄዎቹም #መፍትሄ ይዞ እንደሚመጣ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን አደጋው ምርመራ ውጤት በዚህ ሳምንት ይፋ ይደረጋል፡፡ የአሜሪካው ናሽናል ትራንስፖርት ሴፍቲ ቦርድ እና ቦይንግ ኩባንያ ከመቅረጸ ድምጽና ከበረራ መረጃ መቅጃ #የተገለበጡ መረጃዎች እንዲሰጧቸው ቢጠይቁም የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ፍቃደኛ #አለመሆናቸውን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡ በዚህም ሳቢያ የአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣናት ዲፕሎማሲያዊ እና በምርመራ ሂደቱም ላይ #ጫና በመፍጠር ላይ ናቸው፡፡ ሰሞኑን የአሜሪካ ዐለም ዐቀፍ ሜዲያዎች ስህተቱን ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ #ለማላከክ ሲጥሩ ሰንብተዋል፡፡

Via ሪፖርተር(በዋዜማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ🇪🇹 ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችው የመግባቢያ ስምምነት አደጋ ይዞ ይመጣል ? የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ ያለ አንዳች ግጭት፣ ውጊያ ከባለቤቶቹ ተደርጓል ያሉት የመግባቢያ ስምምነት አደጋ እንደማያመጣ ገልጸዋል። አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦ " ኢትዮጵያ የባህር በር የላትም፤ እድገቷ በጣም ጨምሯል። በዙሪያዋ የሚተናኮሳት ፤ እሷን መተናኮስ…
#Ethiopia

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ ምንም ያህል #ጫና ቢደረግ የህዳሴውን ግድብ እንዳሳካነው የባህር በሩም በተመሳሳይ ይሳካል አሉ።

አምባሳደር ሬድዋን፤ " የህዳሴውን ግድብ ያሳካነው ተጨብጭቦልን ሳይሆን ከቅርብም ከሩቅም እየተላጋን፣ የሥጋት ከበሮ እየተደለቀ፣  ዛቻና ማስፈራሪያ በምድርም በአየርም ልምምድ እያስገመገመብን ፣ ሁሉንም ዓይነት ጫና ተቋቁመን ነበር " ብለዋል።

" የባህር በሩም እንዲሁ ይሆናል " ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#Canada #StudentVisa

ካናዳ በእ.ኤ.አ. 2024 የዓለም አቀፍ ተማሪዎች ቪዛን (የምትቀበላቸውን ተማሪዎች ቁጥር) ትቀንሳለች። ይህም ለሁለት ዓመታት ይቀጥላል።

ሀገሪቱ በ2024 ዕድገቷን ለማረጋጋት ስትል የምትቀበለው 360,000 ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን ብቻ እንደሆነ ይፋ አድርጋለች።

የካናዳ ኢሚግሬሽን ስደተኞችና ዜግነት ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዓለም አቀፍ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ብሏል።

አንዳንድ ተቋሞች ገቢያቸውን ለማሳደግ በሚል የቅበላ መጠናቸው በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል እንዲሁም ብዙ ተማሪዎች ለስኬታማነት ተገቢውን ድጋፍ ሳያገኙ ወደ ካናዳ እየመጡ ነው ሲል አስረድቷል።

ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ለካናዳ ማኀበራዊ፣ ኢኮኖሚያና ባህላዊ ለውጥ አንድ አካል ናቸው ሲል ገልጿል።

ይሁን እንጂ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ወደ ካናዳ መምጣት ፦
* በጤና አገልግሎት
* በቤት አቅርቦት ላይ #ጫና እየፈጠረ መጥቷል ነው የተባለው።

በመሆኑም፣ " ተማሪዎችን ከሕገ ወጦች ለመከላከልና የሀገሪቱን የሕዝብ ቁጥር ተመጣጣኝ ለማድረግ አዲስ ሕግ አስፈልጓል " ነው ያለው፡፡

የካናዳ ኢሚግሬሽን ስደተኞችና ዜግነት ሚኒስትር ማርክ ሚለር፣ " አዲሱ ሕግ ለሁለት ዓመት ይቆያል። በ2024 የ360,000 ማመልከቻ ብቻ እንቀበላለን " ብለዋል፡፡

" ይህም ከባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በ35% ይቀንሳል" ብለዋል ሚለር፡፡

" ከመጠን በላይ እየጨመረ የመጣው የዓለም አቀፍ ተማሪዎች ቁጥር በካናዳ ያልተረጋጋ እድገት እያሳዬ " ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ ይህን ችግር ለመቅረፍም ከየግዛት አስተዳዳሪዎች ጋር መምከራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ካናዳ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለትምህርት እንዲሁም ለስራ ከሚመርጧትና ለመሄድም ጥረት ከሚያደርጉባት ሀገራት አንዷ እንደሆነች ይታወቃል።

More : https://t.me/ThiqaMediaEth/185

@tikvahethiopia @thiqamediaeth