TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሀዋሳ⬆️

የሃዋሳ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ በዛሬው ምሽት በሃዋሳ ከተማ ለሚገኙና በኢህአዴግ 11ኛው ጉባኤ ላይ ለታደሙ ጉባኤተኞች እና ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገር ለመጡ እንግዶች የእራት #ግብዣ አደረጉ።

በእራት ግብዣው ላይ የሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ለጉባኤው ስኬት ምርቃትና ጸሎት ያደረጉ ሲሆን የሃዋሳ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብም ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ የውጭ ዝርያ ያላት ከ40-60 ሊትር መታለብ የምትችል የ7ወራት ጊደር በስጦታ አበርክተዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩም ምስጋና በማቅርብ ንግግራችውን የጀመሩ ሲሆን: በንግግራቸውም ዶሮ ብዙ ጮሃ (አሽካክታ) አንድ ዕንቁላል ጠብ ስታደርግ ላም ግን ድምጽ #ሳታሰማ ብዙ ወተት ትሰጣለች። #ኢህአዴግም እንዲሁ ብዙ ሳያወራ ብዙ ልማት ወደማምጣት የሚሽጋገርበት ጉባኤ እንደሚሆና በስኬትም እንደሚጠናቀቅ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#CHINA

ቻይና የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መነሻን የሚመረምሩ ዓለም አቀፍ አጥኚዎችን አሁን ወደ ሀገርዋ እንደማትጋብዝ አስታውቃለች።

በጄኔቫ የቻይና አምባሳደር እንዳሉት ቻይና አጥኚዎቹን የምትጋብዘው ቻይና በኮሮና ቫይረስ ላይ ድል ከተቀዳጀች በኋላ ነው ብለዋል።

አምባሳደር ቼን ሹ ሀገራቸው አሁን ቅድሚያ የምትሰጠው ወረርሽኙን ማሸነፍ እና የቫይረሱን ጉዳይ ፖለቲካዊ ለማድረግ የሚሰነዘሩ ትርጉም የሌላቸው ውንጀላዎችን መቋቋም ላይ መሆኑን አስረድተዋል።

የዓለም የጤና ድርጅት በበኩሉ የቫይረሱን ምንጭ ለማጣራት በሚካሄደው ምርመራ ላይ ለመሳተፍ የቻይናን #ግብዣ እየተጠበቀ መሆኑን አስታውቋል።

ቻይና ግብዣውን መቼ ልታቀርብ እንደምትችል የተጠየቁት ሊቼን ሹ በአሁኑ ወቅት ቅድሚያ ሊሰጣቸው በሚችሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩሩ ተናግረው ፤ ይህን ለማድረግ ደግሞ ትክክለኛውን ድባብ እንፈልጋለን ብለዋል - #DW

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሶማሊያ እና ኤርትራ ምን መከሩ ? የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ወደ ኤርትራ አቅንተው የሁለት ቀን የስራ ጉብኝት አድርገው ወደ ሞቃዲሾ ተመልሰዋል። ፕሬዜዳንቱ ጉብኝታቸውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። በማብራሪያቸውም ፤ " ኤርትራን በተደጋጋሚ ጎብኝቻለሁ። ኤርትራ ለኛ እንደ ቤታችን ናት " ብለዋል። ወደ ኤርትራ የሄዱት ፦ - ኤርትራ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገች ባለችበት በሶማሊያ…
#Somalia #Eritrea

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼይክ ማሕሙድ ዳግም ወደ አስመራ ማቅናታቸው ተነግሯል።

ፕሬዝደንቱ ዛሬ አስመራ ሲደርሱ የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተቀብለዋቸዋል።

ሐሰን ሼይክ ማሕሙድ በፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ #ግብዣ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ወደ አስመራ እንደተጓዙ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ገልጸዋል።

የሶማሊያ ብሔራዊ የዜና ወኪል (SONNA) ሀሰን ሼይክ መሕሙድ ከፕሬዝደንት ኢሳያስ ጋር በሁለቱ ሀገሮች ትብብር ላይ እንደሚወያዩ አስታውቋል።

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ባለፈው ጥር ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ “የአጋርነት እና የትብብር የመግባቢያ ሥምምነት” በተፈራረሙ በቀናት ልዩነት ወደ አስመራ አቅንተው ከፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተገናኝተው ነበር።

መረጃውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር / SONNAን ዋቢ በማድረግ ያጋራው ዶቼቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

Photo Credit - Yemane G. Meskel

@tikvahethiopia