TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"የሰላም ውድ ዋጋ በግልፅ የሚስተዋለው ላፍታ ሲጓደል ነው!" ም.ጠ.ሚ/ር አቶ ደመቀ መኮንን
~~~~~<>~~~©

ዘላቂ የሃገር ሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን መወጣት እንደሚገባው ም.ጠ.ሚ/ር አቶ #ደመቀ_መኮንን አሳሰቡ።

ም.ጠ.ሚ/ር አቶ ደመቀ መኮንን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና የሰላም አቀንቃኝ የሆኑትን አቶ #ኦባንግ_ሜቶን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በሰሜን አሜሪካ "ግድግዳውን እናፍርስ፤ ድልድዩን እንገንባ" በሚል መርህ ከወራት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ የቀረበውን ጥሪ አቶ ኦቦንግ በአክብሮት ተቀብለው ወደ እናት ሃገራቸው በመመለሳቸው ም.ጠ.ሚ/ር አቶ ደመቀ ምስጋና እና አድናቆት ቸረዋል።

አቶ ኦባንግ በሃገር ቤት የወራት ቆይታ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች እየተዘዋወሩ ሃገራዊ ለውጡ ቀጣይነቱ እንዲጎለብት ለትውልዱ የሚያስተላልፉት አነቃቂ መልዕክት ተቀባይነት ያለውና ሊጠናከር እንደሚገባ አቶ ደመቀ ተናግረዋል።

በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለመከላከል እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሚያደርገውን ሃገራዊ ጥረት ለማገዝ ፤ አቶ ኦባንግ በትውልዱ ዘንድ ያላቸውን ሰፊ የተደማጭነት እና የተቀባይነት ዕምቅ አቅም መንዝረው በቀጣይ እንዲደግፉ ም.ጠ.ሚ/ሩ
ጠይቀዋል።

የሰላም ውድ ዋጋ በግልፅ የሚታወቀው ላፍታ ሲጓደል በመሆኑ፤ በማህበረሰቡ ዘንድ ሰፊ የግንዛቤ እና የንቅናቄ ስራዎች እንደሚያስፈልጉ አቶ ደመቀ አስረድተዋል።

አቶ ኦባንግ በበኩላቸው በም.ጠ.ሚ/ር አቶ ደመቀ በተደረገላቸው አቀባበል እጅግ መደሰታቸውን በመግለጽ፤ ተስፋ የፈነጠቀው ሃገራዊ የለውጥ ጉዞ ዘላቂነት እንዲኖረው የግል ጥረታቸው እንደሚያጠናክሩ አረጋግጠዋል።

በውጭ ሃገር "ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ" የተሰኘ ድርጅት በመስራችነትና በዋና ዳይሬክተርነት የሚንቀሳቀሱት አቶ ኦባንግ፤ በሃገር ቤት በሚኖራቸው ስምሪት ድርጅቱ በሰብዓዊ መብት እና በሰላም ዙሪያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ አስረድተዋል።

በቀጣይ በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር ትርጉም ያለው ስራ መስራት ፍላጐት እንዳላቸው
አቶ ኦባንግ ገልጸዋል።

በሃገር ውስጥ ህጋዊ ዕውቅና እና ምዝገባ አጠናቀው ከመንግሥት ጋር በቅንጅት ለመስራት ሰፊ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑንም አብራርተዋል።

በመጨረሻም ለሃገራዊ ሰላም ግንባታ የጋራ ጥረት እና ዘላቂ ውጤት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ም.ጠ.ሚ/ር አቶ ደመቀ አረጋግጠዋል።

ምንጭ፦ Office of Deputy Prime Minister
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወራቤ🔝የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዎስ፥ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ወ/ማርያም እና በኢጋድ የሰላምና ደህንነት ተጠሪና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በይፋ ተመርቋል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምክትል ጠ/ሚ አቶ #ደመቀ_መኮንን...

"ውድ ተማሪዎች . . . [ቢያንስ ቢያንስ] ለሃገር ክብር በጋራ እንደተዋደቁት፤ ለሃገር ልዕልና በጀግንነት እንደተዋጉት፤ ለሃገር አንድነት ዕድሜ ልካቸውን እንደደከሙት እንዲሁም ለእናት ሃገራቸው ሲሉ በቁርጠኝነት ለውጥ እንዳራመዱት. . .የቀደሙ አያቶቻችን እና አባቶቻችን እንድትሆኑ #እለምናችኋለሁ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድና ም/ጠ/ሚር #ደመቀ_መኮንን በአማራ ክልል የሚገኘውን የኩሳኤ ቀበሌ ስንዴ ማሳ ክላስተር ጎበኙ። የሀገራችን የግብርና ኮመርሻላይዜሽን ክላስተር አሰራር አራት አላማዎች አሉት፡፡ እነርሱም የአነስተኛ አርሶ አደሩን ገቢ ማሣደግ፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ገበያን ማመቻቸት፣ የአግሮ ኘሮሰሲንግና የእሴት ጭማሪ ስራን ማሣደግ እና የሥራ እድልን መፍጠር ናቸው፡፡

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ5 ተማሪዎች ህይወት አልፏል‼️

በቅርቡ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በግለሰቦች ደረጃ ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት የቡድን መልክ በመያዝ ወደሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች #ተዛምቶ የአምስት ተማሪዎች ህይወት ማለፉን የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየመከሩ ናቸው።

በምክክር መድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ናቸው።

ምክክሩ ሲጀመር የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር #ሂሩት_ወልደማሪያም እንደተናገሩት፤ በዩኒቨርሲቲዎች ተከስቶ በነበረው ግጭት ለሰው ህይወት መጥፋት ጭምር የዳረገ ጉዳት ደርሷል።

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በግለሰቦች ደረጃ የተፈጠረ አለመግባባት ወደ #ቡድን መልክ በመቀየር በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተዛምቶ የነገ ተስፋ የሆኑ አምስት ተማሪዎችን ህይወት ቀጥፏል ብለዋል።

ችግሩን ለማርገብና ዘላቂ ሰላም  ለማስፈን ታልሞ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ግጭት ወደተከሰተባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተንቀሳቅሰው ባከናወኑት ተግባር አንጻራዊ ሰላም እንደመጣ ዶክተር ሂሩት ተናግረዋል።

አሁን ባለድርሻ አካላት በሚያደርጉት ምክክር ዘላቂ የሆነ ሰላም ሊያረጋግጥ የሚችል ሃሳብ እንደሚፈልቅ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደትን ሰላማዊ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካል ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ተባለ። በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የመማር ማስተመሩን ሂደት በሚያውኩ ችግሮች እና የመፍትሄ ሃሳቦችን በሚጠቁም ጥናት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው። በውይይቱም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን ጨምሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር🔝

በጎንደር የሰላምና እርቅ ጉባኤ እየተካሄደ ነው። በአማራ እና ቅማንት ማህበረሰብ የተፈጠረውን ቁርሾ መፍትሄ ለመስጠት ያለመ ህዝባዊ #የሰላምና #የእርቅ ጉባኤ በጎንደር እየተካሄደ ነው፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር #ደመቀ_መኮንን እና የሐይማኖት አባቶች በተገኙበት መድረክ የሰላምና ጉባኤው በዛሬው ዕለት ሲካሄድ ይውላል፡፡

ዓላማውም በጎንደር በተለይም ማዕከላዊና ሰሜን ጎንደር ዞኖች ማንነትን መሰረት አድርገው የሚነሱ ግጭቶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ #በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ነው፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አማራ 🕊 ቅማንት!

‹‹ድርጅት እና መሪዎች ያልፋሉ ህዝብና #ታሪክ ግን ይቀጥላል፤ የምናልፍ መሪዎች #የማያልፍ ጠባሳ ጥለን እንዳናልፍ ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡››

‹‹ማንነትን ማክበር እና ማስከበር ስንል አጥር ማጠር እና የልዩነት ግንብ መገንባት ማለት አይደለም ፡፡ህዝብን ማድመጥ እና ታሪካዊ ወሰኑን ማስከበር እንጅ ተመልሶ ያደረ ጥያቄ ነው እያሉ ማለፍ ታሪኩ ያለፈበት ሂደት ነው፡፡››

‹‹ልታከብረን እና ልናከብራት የምንችላት ሃገር ለመገንባት በመጀመሪያ በህግ የበላይነት ልንገዛ ይገባል፡፡›› ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን
.
.
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን ግጭት ለታላቅ ሃገር እና ተስፋ ለሰነቀ ህዝብ የሚመጥን አይደለም፤ እንዲህ አይነት ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት ስራ ዛሬ ሳይሆን በሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ወቅት አማራን የትኩረት ማዕከል አድርጎ ሲሰራበት ነበር ዳሩ የህዝቡን አንድንነት #ማፍረስ አልተቻላቸውም እንጅ ብለዋል፡፡

አማራን ከአገው፣ ቤተ እስራኤላዊያንን ከአማራ እንዲሁም ቅማንትን ከአማራ ለማጋጨት ጥረት ተደርጎ ነበር፤ ነገር ግን አባቶቻችን በብልጠት ሴራውን አክሽፈው እልፍ ዘመን የዘለቀ አብሮነትን አውርሰውናል ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

ማንነትን ማክበር እና ማስከበር ስንል አጥር ማጠር እና የልዩነት ግንብ መገንባት ማለት አይደለም ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝብን ማድመጥ እና ታሪካዊ ወሰኑን ማስከበር እንጅ ተመልሶ ያደረ ጥያቄ ነው እያሉ ማለፍ ታሪኩ ያለፈበት ሂደት ነው ብለዋል፡፡

ልታከብረን እና ልናከብራት የምንችላት ሃገር ለመገንባት በመጀመሪያ በህግ የበላይነት #ልንገዛ ይገባል፡፡ ሃገራችን ያከበረችንን ያክል አላከበርናትም ያሉት አቶ ደመቀ ሃገር ግንባታ ጊዜ ይወስዳልና በትዕግስት ሃገር ልንገነባ ይገባል ብለዋል፡፡

እኛ እና እናንተ አሉ አቶ ደመቀ ‹‹እኛ እና እናንተ ከግለሰብ እልፍ ያለ ኃላፊነት ስላለብን ስሜት ሳይገዛን እና ከንፈራችን እየመጠጥን እንዳናዳማ ትክክለኛ መሪ እና መፍትሄ ፈላጊዎች ልንሆን ይገባል ብለዋል፡፡››

ይህ ህዝብ አብሮ ኖሯል ፤ ተዋልዷል ፤ #ደም አስተሳስሮታል እና! ይህ ቀን አልፎ ነገ አብሮ መኖሩ ስለማይቀር ‹‹መሪና ድርጅት ያልፋሉ ህዝብና ታሪክ ግን በዘመናት መካከል ይቀጥላሉና በሚያልፍ የመሪነት ዘመናችን የማያልፍ የታሪክ ጠባሳ እንዳንተው ልንጠነቀቅ ይገባል››
ብለዋል፡፡

🔹በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ያለው የሰላም መድረክ እንደቀጠለ ነው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን ከጥር 3 – 4 ቀን 2011 ዓ.ም በሴራሊኒዮን ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡ ጉብኝቱ የሚካሄደው የሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ጁልየስ ማዳቢዩ ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት ነው፡፡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት እንዳስታወቀው የሴራሊዮን ኢትዮጵያን ወዳጅነት ሊያጠናክር የሚችል ምክክር የሚደርግ ሲሆን የመግባቢያ ስምምነት ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን በሴራሊዮን የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ከፍተኛ የመንግሥት ልዑክ በሴራሊዮን መዲና ፍሪታውን በደረሰበት ወቅት በሃገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ለ2 ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴራሊዮን የሚገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር #ደመቀ_መኮንን ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጁልየስ ማዳባዮ ጋር በፕሬዚዳንቱ ፅህፈት ቤት ተገናኝተው ተወያይተዋል። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ የሚመራው ከፍተኛ የመንግሥት ልዑክ የጉብኝት ተልዕኮ በኢትዮጵያ እና በሴራሊዮን መካከል ሊኖር የሚገባውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት እና የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው።

ምንጭ፡- ም/ጠ /ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጂንካ🔝

17ኛው የአርብቶ አደር ቀን በዓል #በጂንካ_ከተማ ስታዲየም ትከብሯል። በበዓሉ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠ/ሚ #ደመቀ_መኮንን ተገኝተው ነበር።

ምንጭ፦ Office of Deputy Prime Minister of Federal Democratic Republic of Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጋሞ ዞን ጉብኝት🔝

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን ቆላማ አካባቢ የስንዴ ግብርና ልማት የሙከራ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።

በሙከራ ደረጃ 200 ሄክታር የሸፈነው የስንዴ ግብርና ልማት በመስመር እና በመስኖ የተዘራ በመሆኑ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ አልሚዎቹ ተናግረዋል።

በሃገሪቱ መሰል ቆላማ እና ዝናብ አጠር አካባቢዎች ይህን ስኬታማ ተሞክሮ በሚገባ ሊማሩበት እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ አሳስበዋል።

በየአካባቢው የስንዴ ግብርና ልማት እየጎለበተ መሄድ ለሃገራዊ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ፥ ለዘርፉ መንግሥት ተገቢውን ድጋፍ እና ክትትል እንደሚያጠናክር አቶ ደመቀ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ Office of Deputy Prime Minister of Federal Democratic Republic of Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 19/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያስገነባው ስካይ ላይት ሆቴል ዛሬ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡
.
.
#ሐሰተኛ_የማስተርስና_የዶክትሬት ዲግሪዎች እንዲሰጡ አድርገዋል የተባሉት የሜቴክ ኃላፊዎች ላይ ክስ ተመስርቷል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ #የድሬዳዋ ተወላጆች በዛሬው ዕለት በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተገኝተው ያላቸው ተቃውሞ እና ቅሬታ አሰምተዋል። የፌደራሉ መንግስት ለድሬዳዋ ከተማ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥና ያሉ ችግሮችን እንዲፈታ ጠይቀዋል።
.
.
#የሰላሌ_ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትናንት ቅዳሜ "አንድ ቀን ለማህበረሰቤ" በሚል መሪ ሀሳብ #ፍቼ ከተማን ሲያፀዱ ውለዋል።
.
.
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን ቆላማ አካባቢ የስንዴ ግብርና ልማት የሙከራ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።
.
.

4ኛው የኢህአዴግ የወጣቶች ሊግ ድርጅታዊ ጉባዔ #በሃዋሳ_ከተማ ዛሬ ተጀምሯል። ጉባዔው "በተጠናከረ የወጣቶች ትግል ሀገራዊ ለውጡን ወደፊት" በሚል መሪ ቃል እስከ ጥር 19 እስከ 21 በተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ይቆያል፡፡
.
.
በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን አጎራባች ወረዳዎች በተከሰተው #ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች መልሶ በሚቋቋሙበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።
.
.
በጅማ ከተማ "ንግዳችንን እናዘምን" በሚል መሪ ቃል የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በዛሬ ዕለት ተካሂዷል።
.
.
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር ሼህ መሃመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ከእስር መፈታታቸው ተሰምቷል።
.
.
የቀድሞ ጦር ማህበር #የምስረታ_ጉባዔ ዛሬ #በደብረማርቆስ ፖሊስ ኮሌጅ ተካሂዷል።
.
.
ለአራት ቀናት በመቀለ ሲካሄድ የቆየው የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የአምስተኛው ዘመን 14ኛው መደበኛ ጉባኤ አዋጆችንና ሹመቶችን በማጽደቅ #ተጠናቋል
.
.
የድሬዳዋን ሰላምና ፀጥታ #አስተማማኝ በማድረግ የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱ እንደሚሰራ #በምስራቅ_ዕዝ_መከላከያ የሚመራው ጊዜያዊ የፀጥታ ጥምር ኮሚቴ አስታውቋል።
.
.
ምንጭ፦ ኢዜአ፣ DW፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ የጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ የምክትል ጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ etv፣ ዋልታ፣ ፋና፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
የነገ ሰው ይበለን!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“የህዳሴ ግድብን #ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ማራዘሚያ ጊዜ ሊኖር አይገባም” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር #ደመቀ_መኮንን
.
.
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተያዘው የጊዜ መርሃ-ግብር ለማጠናቀቅ ርብርብ መደረግ እንደሚገባ የግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

በአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዞለት የነበረው ግድቡ ስምንት ዓመታት አለመጠናቀቁን የተናገሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) መሰራት የነበረበት የግድቡ ኤሌክትሮ ሜካኒካልና ተያያዥ ተግባራት አፈፃፀም #በመጓተቱ ነው ብለዋል።

በዚህም የተነሳ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ አራት ዓመታት አስፈልጓል፤ ይሁንና አሁን ላይ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ፕሮጀክቱን በተያዘው የጊዜ ገደብ በጥራትና በብቃት ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ክትትል ያደርጋል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድና ም/ጠ/ሚር #ደመቀ_መኮንን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለዉጥ የጋራ ኮሚቴ ጋር የካቲት 6 ቀን 2011 ተወያዩ። ካለፈው የቀጠለው ይህ ውይይት በዋናነት የኮሚቴውን የስራ እንቅስቃሴዎችና የተገኙ ውጤቶችን ገምግሟል። ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድም ኮሚቴው ያስመዘገባቸውን ውጤቶች እንዲያጠናክር አቅጣጫ በመስጠት የበኩላቸውን ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢሳት የሚዲያ ቡድን🔝

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን የኢሳት ሚዲያ ቡድን አባላትን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ ለኢሳት ሚዲያ ቡድን አባላትም በሃገሪቱ #ተጨባጭ ሁኔታ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በለውጡ ጉዞ እየገጠሙ ያሉ ፈተናዎችን እና ዕድሎችን ያብራሩ ሲሆን #ሚዲያው ለለውጡ ስኬት ሚዛናዊ እና ገንቢ ሚናውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የኢሳት ሚዲያ ቡድን አባላት በበኩላቸው የተጀመረው ለውጥ ዳር እስከ ዳር እንዲሰርጽ ሙያዊ #ሃላፊነታቸውን በሚዛኑ አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ ህዝብን እና ሃገርን ባስቀደሙ አጀንዳዎች ዙሪያ የጎደለው እንዲታረም - የተሻለው ደግሞ እንዲጠናከር በትኩረት እንደሚሰሩ የኢሳት ሚዲያ ቡድኑ አባላት አረጋግጠዋል፡፡

ምንጭ፦ Office of Deputy Prime Minister of Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የገጠር መሬት አስተዳደር ስርዓት ግንባታ ሂደትን የ2ተኛ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ የምርቃት በዓል በደብረ ብርሃን ከተማ ተካሄደዋል። በዝግጅቱ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን፤ የመሬት ሃብት አጠቃቀም በላቀ ደረጃ እንዲሻሻል ፋና ወጊ ሚና እንዲጫወቱ ለተመራቂ አርሶ አደሮች የስራ መመሪያ አስተላልፈዋል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን 5ተኛው የኢትዮ~ሱዳን ከፍተኛ የጋራ ኢኮኖሚ ትብብር ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሱዳን~ካርቱም ገብተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ እንደደረሱ፤ የሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት #ኦስማን_መሃመድ_ዩሱፍ_ኪቢር በወታደራዊ ማርሽ የታጀበ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Via Office of Deputy Prime Minister of Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BREAKING

የኢፌዴሪ ምክትል ጠ/ሚ #ደመቀ_መኮንን የዶክተር ወርቅነህ ገበየሁን ቦታ #በመተካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሊሾሙ እንደሆነ ከታማኝ ምንጭ መረጃ ደርሶኛል ሲል THE FINFINNE INTERCEPT ዘገበ። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ-አቶ #ገዱ_አንዳርጋቸውን በዶክተር አምባቸው መኮንን ምትክ አማካሪያቸው አድርገው ሊሾሟቸው እንደሆነ THE FINFINNE INTERCEPT ዘግቧል።

---ተጨማሪ መረጃዎች ከሌሎች መገናኛ ብዙሃን የሚሰሙ ከሆነ ተከታትዬ አሳውቃችኃለሁ--
@tsegabwolde @tikvahethiopia