TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#HijraBank

ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ የሆነው ሂጅራ ባንክ ነገ ቅዳሜ ነሐሴ 29 ቀን 2013 የመክፈቻ ፕሮግራሙን እንደሚያካሂድ ታውቋል።

ባንኩ በዚህ የመክፈቻ ፕሮግራም የመጀመሪያውን ኦሎምፒያ-ነጃሺ ቅርንጫፍ የሚከፍት ሲሆን በተጨማሪም በዚሁ የመጀመሪያው ሳምንት በተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባና በተለያዩ የክልል ከተሞች 11 ቅርንጫፎቹን እንደሚከፍት ሪፖርት አድርጓል።

በሌላ በኩል ሂጅራ ባንክ የዋናውን ቅርንጫፉን ማብሰሪያ ፕሮግራም ምክንያት በማድረግ ለ200 አቅመ ደካሞች የምግብ ድጋፍና ለ200 ተማሪዎች የትምህርት ቤት ቁሳቁስ በአሁን ሰዓት በዋናው መስሪያ ቤቱ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።

@tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ ክልል የነበረው እርዳታ አቅርቦት ከተጠናቀቀ ሁለት ሳምንት እንደሆነ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ግራንት ሌይቲ አስታውቀዋል።

አስተባባሪው ባወጡት መግለጫ አስፈላጊ የሆኑ የሰብዓዊ እርዳታዎችን ማቅረብ አለመቻሉ፣ የነዳጅ እና የጥሬ ገንዘብ እጥረት መኖሩ በሰሜን ኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ በትግራይ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ብለዋል።

በትግራይ ክልል 90% ሚሆነው ነዋሪ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልገዋል፤ 400 ሺ ያህሉ ደግሞ ረሃብ በሚመስል ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ ሲሉ አስተባባሪው ገልጸዋል።

በአማራ እና አፋር ክልል ደግሞ 1.7 ሚሊዮን ሕዝብ ለረሃብ ሊጋለጡ ከጫፍ ደርሰዋል ብለዋል ሲሉ የሰብአዊ እርዳታ አስተባባሪው እንዳመለከቱ ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/UN-09-03

@tikvahethiopia
የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪት ቢለኔ ስዩም፤ መንግስት ወደትግራይ እርዳታ ለማድረስ ማነቆ ናቸው የተባሉ አሰራሮችን ማሰተካከሉን ገልፀዋል።

ቢልለኔ ስዩም እንዳሉት ፥ ወደትግራይ ክልል እርዳታ የሚቀርብባቸው መተላለፊያዎች እየቀነሰ መጥቷል፤ የTPLF ታጣቂዎች ጦርነቱን ወደአጎራባች ክልሎች ማስፋፋታቸውን ተከትሎ 4 የነበረው የእርዳታ ማስተላለፊያ መስመር አሁን ላይ በአንድ መወሰኑን አሳውቀዋል።

ይህም ሆኖ ግን በቀረው የእርዳታ ማስተላለፊያ መስመር (በአፋር በኩል) እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በጉዞ ላይ እንደሆኑ መረጃ እንዳላቸው ገልፀዋል።

"ስንቶቹ እንደደረሱ መረጃው የለኝም፤ ያመረጃ በሚመለከተው አካል እየተጠናቀረ ነው" ብለዋል።

የUN ዋና ፀሃፊ ረዳት ቃል አቀባይ ወደትግራይ እርዳታ ለማድረስ ብቸኛው መንገድ የአፋር መስመር ካለፉት አስር ቀናት ወዲህ ተደራሽ አልሆነም፤ እርዳታ ለማቅረብ የሎጂስቲክስ እና ቢሮክራሲው አቅርቦቱን ከባድ አድርጎታል ሲሉ ላሰሙት ቅሬታ ቢልለኔ ምላሽ ሰጥተዋል።

ቢልለኔ፥"ከሰብዓዊ ተቋማት ለቀረበው ጥሪ ትኩረት ለመስጠት እና በተለይ ቢሮክራሲያዊ ማነቆዎች በሚል ለጠቀሷቸው የሚደርስባቸውን ፈተናዎች በተመለከተ ምላሽ ተሰጥቷል፤ በእርግጥ ውጤታማ እና የተቀላጠፈ የሰብዓዊ እርዳታ ሂደት እንዲኖር የእርዳታ መኪናዎች ይፈተሽባቸው የነበሩ 7 የፍተሻ ጣቢያዎች ወደ3 ዝቅ እንዲል ተደርጓል" ብለዋል።

ቢልለኔ አሁንም አካባቢው ላይ የፀጥታ ስጋት መኖሩን የጠቆሙ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ተጠያቂው ጦርነቱን ወደአጎራባች ክልል ያመጣው አካል ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

"...አካባቢው ላይ በህወሓት የሚካሄደ ሰርጎገብነትና ጦረኝነት አለ ፤ ለሰብዓዊና እርዳታ ሰራተኞች ሁኔታውን አስቸጋሪ አያደረገ ያለው የህወሓት ጦረኛ ባህሪና ተፈጥሮ ነው" ሲሉ አክለዋል።

@tikvahethiopia
"... ከ65 ሺህ በላይ ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል" - የነፋስ መውጫ ከተማ ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ

የነፋስ መውጫ ከተማ የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ በንፋስ መውጫና በአካባቢዋ ከ65 ሺህ በላይ ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ሪፖርት አድርጓል።

ኮሚቴው፥ በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው 'ህወሓት' ሀብትና ንብረታቸውን የዘረፈባቸውና በከፋ ችግር ውስጥ የሚገኙ ከ65 ሺ በላይ የነፋስ መውጫ ከተማ እና የአካባቢዋ ነዋሪዎች አስቸኳይ የምግብ እንዲሁም የቁሳቁስ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል አመልክቷል።

እስካሁን ድረስ ባለው ሂደት ባለሀብቶች፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች አና ተቋማት ለተጎጂዎች ድጋፍ እያደረጉላቸው መሆኑን ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴው የገለፀ ሲሆን በህብረተሰቡ ላይ ከደረሰው ሁሉን አቀፍ ችግር አንፃር ሲታይ በቂ አለመሆኑን ገልጿል።

- የምዕራብ ጎጃም ዞን፣
- ፋሲል ከነማ፣
- አልማ እና የአማራ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት ለተጎጂዎች ልዩ ልዩ ድጋፍ እንዳደረጉላቸው ኮሚቴው ሪፖርት አድርጓል።

አምስት (5) እና ከዚያ በላይ ላለው ቤተሰብ 25 ኪሎ ግራም ዱቄት ብቻ ነው ለማዳረስ እያከፋፈልን ያለነው ያለው ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴው ፥ "ሰፊ ቤተሰብ ላለው ችግሩን የሚፈታ አይደለም፣ ህብረተሰቡ ሌሎች ተጓዳኝ ድጋፎችንም ስለሚሻ ይህ ብቻ በቂ አይደለም" ብሏል።

ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የአማራ እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ ባለሀብቶች፣ ተቋማት፣ ባለሀብቶችና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ወገናዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
"...አሁን ላይ እንደሀገር ባጋጠመው ችግርና በአካባቢው ባለው የፀጥታ ስጋት ምክንያት የዘንድሮው የሩፋኤል በዓል አይከበርም" - የደጀን ወረዳ ፖሊስ

አሁን ላይ ካለው ሀገራዊ ችግር እና የፀጥታ ስጋት አኳያ ከአራት ቀናት በኃላ (ጷግሜ 3 ቀን 2013 ዓ.ም) በደጀን ወረዳ አባይ ድልድይ ላይ የሚከበረው የሩፋኤል በዓል አይከበርም።

የደጀን ወረዳ ፓሊስ በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ አባይ በርሀ ውስጥ ህዳሴ ድልድይ ላይ በየአመቱ ጷጉሜ 3 ቀን በድምቀት የሚከበረው የሩፋኤል በዓል አሁን ላይ እንደ ሀገር ባጋጠመው ችግርና በአካባቢው ባለው የፀጥታ ስጋት ምክንያት የዘንድሮው በዓል እንዳይከበር የተወሰነ መሆኑን አስታውቋል።

በዓሉን ለማክበር ከየአቅጣጫው ወደአካባቢው የሚመጣ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ላልተገባ ወጭና እንግልት ከመዳረጉ በፊት ፤ በዓሉ እንዳይከበር የተወሰነ መሆኑንና ወደ ቦታው መግባት የማይቻል መሆኑን አውቆ ካለበት እንዳይንቀሳቀስ የደጀን ወረዳ ፓሊስ አሳስቧል ።

መረጃው የደጀን ወረዳ ፓሊስ ኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ክፍል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በደሴ ከተማ ተሰብስቦ ጫት መቃም እና ማስቃም ታገደ። የደሴ ከተማ አስተዳደር ለሀሰተኛ መረጃ መሰራጨት እና ለህዝቡ አለመረጋጋት ምክንያት እንደሆነ የገለፀውን ተሰብስቦ ጫት መቃም እና ማስቃም እንዲሁም ሺሻ ቤቶችን በይፋ ከልክሏል። ከትላንት ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው ይህን ውሳኔ የተላለፈ አካል በህግ ተጠያቂ ይሆናል። የደሴ ከንቲባ አበበ ገ/መስቀል ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ "ጫት ማስቃም እና ሺሻ ቤቶች…
"...ከዛሬ ጀምሮ በጎንደር ከተማ ጫት ከሌላ አካባቢ ማጓጓዝ ፣ መቸርቸር፣ ማከፋፈል፣ ማስቃምና መቃም ተከልክሏል" - ከጎንደር ከተማ የፀጥታ ም/ቤት

የጎንደር ከተማ የፀጥታ ም/ቤት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባስተላለፈው አስቸኳይ ውሳኔ ከዛሬ ነሃሴ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ ጫት ከሌላ አካባቢ ማጓጓዝ፣ መቸርቸር ማከፋፈል፣ ማስቃምና መቃም መከልከሉን አሳውቋል።

ም/ቤቱ፥ ሽብረተኛ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀው ህወሓት ከሌሎች ፅንፈኛ ፀረኢትዮጵያ ኃይሎች ጋር በመሆን በአማራ ክልል ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች ህዝቡ ላይ ሁሉንም አይነት ግፍ እየፈፀመ ነው፤ የበቀል በትሩንም ማሳረፍ ጀምሯል ብሏል።

ም/ ቤቱ ፤ "ወረራውን ሊመክት የሚችል የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ እንዲሆን የሚያደርግ መንፈሰ ጠንካራ ወጣት ሀይል በስነ ልቦና የተገነባ ትውልድ ደግሞ ሃገርን ከጥቃትና ከወረራ እንዲሁም ከጥፋት መታደግ የሚቻለው ከሱስ የፀዳ በስነ ምግባር የታነፀ በመሆኑ ይህንን ትውልድ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት መነሻ በማድረግ በከተማው በጫት አቅራቢዎች አጓጓዦች፣ አከፋፋዮች፣ ቸርቻሪዎች አስቃሚዎቾና ተጠቃሚዎች ላይ የክልከላ ውሳኔ ተላልፋል" ሲል አሳውቋል።

በመሆኑም ከነገ ጀምሮ ምክር ቤቱ ክልከላ ባደረገባቸው ተግባራት ላይ ሲሳተፍ የሚገኝ ተሽከርካሪ ግለሰብም ሆነ ድርጅት በህግ የሚጠየቅ መሆኑን ምክር ቤቱ አሳስቧል።

የተላለፈውን ክልከላ የከተማዎ የፀጥታ ሃይል ተከታትሎ እንዲያስፈፀም ታዟል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፀጥታ ምክር ቤቱ በጎንደር ከተማ በጫት ንግድ የተሰማሩ የከተማው ህብረተሰብ ክፍሎች ዘርፍ ቀይረው በሌሎች የንግድ የአገልግሎትና ማኒፋክቸሪንግ ዘርፎች ለመሰማራት በተቋቋመው ግብረ ሃይል አማካኝነት አስፈላጊውን ጥረት እና እገዛ ይደረግላቸዋል ብሏል።

@tikvahethiopia
#GERD #FDREDefenseForce

ሀገር መከላከያ ሰራዊት፥ ኢትዮጵያ እየገነባች ያለውን ግዙፉን የታላቁ ሕዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረውን የህወሓት ቅጥረኛ ሃይል ደመሰስኩኝ አለ።

የግድቡን ግንባታ ለማደናቀፍ ተልዕኮ ውስደው የተንቀሳቀሱና ሰራዊቱ የማያዳግም እርምጃ የወሰደባቸው ኃይሎች (የተገደሉ) በቁጥር 50 ሲሆኑ ፤ ከ70 በላይ የሚሆኑት ቁስለኛ ሆነዋል።

መከላከያ ሰራዊት ፥ እርምጃ የወሰደበት ኃይል የተለያዩ ፀረ ሰው እና ፀረ ተሽከርካሪ ፈንጂዎችን ለማጥመድ መሞከሩን ነገር ግን መቋቋም ተስኖት መበታተኑን አሳውቋል።

ይኸው ጥፋት ሊፈፅም የነበረው ኃይል ይጠቀምባቸው የነበሩ ቀላል እና ከባድ የቡድን መሳሪያዎች፣ ፈንጂዎች ወድመዋል ፤ የተቀሩትን ሰራዊቱ ተቆጣጥሯቸዋል።

የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ሃይል ኮማንድ ፖስት የኦፕሬሽን ዘርፍ አሰተባባሪ ኮ/ል ሰይፈ ኢንጊ ፣ "አሸባሪው ሕወሃት በግንባር ድል አልቀና ሲለው አብዛኝው ጦር ወደ ሰሜኑ ክፍል አቅንቷል በሚል ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ተቀናጅቶ የህዳሴ ግድባችንን ስራ ለማስተጓጎል ለማጥቃት ቢሞክርም አልተሳካለትም" ብለዋል።

በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሃይል፣ እግረኛና ሜካናይዝድ ክፍለጦሮች እንዲሁም የክልል ልዩ ኃይሎች አስፈላጊውን ዝግጁነት በማረጋገጥ ግዳጃቸውን እየፈፀሙ እንደሚገኙ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#አሁን

"የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ያልተቋጨ የቤት ሥራ" በሚል ርዕስ በዶክተር በለጠ በላቸው ይሁን ተፅፎ በ "ኢትዮጵያ አካዳሚክ ፕሬስ" የታተመ መፅሐፍ በሂልተን ሆቴል የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ፣ ሙሁራን ፣ የሚዲያ ባለሞያዎችና የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት በመመረቅ ላይ ይገኛል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የመክፈቻና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት የተላለፈ ሲሆን በደንበር ጉዳዮች ዙርያ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች የሚመረምሩና የሚያጠኑ እንዲሁም በተግባር ስራ የሚሳተፉ ባለሞያዎች በመፅሐፉ ዙርያ ግመገማ ቀርቦ ውይይት በመከናዎን ላይ ይገኛል።

Via Bereket H.

@tikvahethiopia
#NewsAlert

የዋጋ ንረት በህብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ ስንዴ ፣ ዘይት ፣ ስኳር እና ሩዝ ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆኑ ተወሰነ።

ፖስታ ፣ ማካሮኒ እና እንቁላል ደግሞ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንደተነሳላቸው የገንዘብ ሚኒስቴር ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የቀረጥ እና የታክስ ማሻሻያው ላልተወሰነ ጊዜ እንደሚቆይ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የዋጋ ንረት በህብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ ስንዴ ፣ ዘይት ፣ ስኳር እና ሩዝ ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆኑ ተወሰነ። ፖስታ ፣ ማካሮኒ እና እንቁላል ደግሞ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንደተነሳላቸው የገንዘብ ሚኒስቴር ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል። የቀረጥ እና የታክስ ማሻሻያው ላልተወሰነ ጊዜ እንደሚቆይ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ዛሬ በሰጡት መግለጫ…
በመሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች ላይ የተፈረገው የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ማሻሻያ፦

የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ከፊስካል ፖሊሲ አኳያ መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦችን የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ማሻሻያ በማዘጋጀት ከነሐሴ 28/2013 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ በሚከተሉት መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች ላይ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ማሻሻያ እንዲደረግ ወስኗል።

• ስንዴ ከውጭ ሲገባ ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆን፣
• የምግብ ዘይት ከውጭ ሲገባም ሆነ በአገር ውስጥ ግብይት ሲፈጸምበት ከማንኛውም ቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆን
• ስኳር ከውጭ ሲገባም ሆነ በአገር ውስጥ ግብይት ሲፈጸምበት ከማንኛውም ቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆን
• ሩዝ ከውጭ ሲገባም ሆነ በአገር ውስጥ ግብይት ሲፈጸምበት ከማንኛውም ቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆን
• ፓስታ እና ማኮረኒ ከውጭ ሲገባም ሆነ በአገር ውስጥ ግብይት ሲፈጸምበት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ እንዲሆን እንዲሁም
• የደሮ እንቁላል ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እንዲሆን

ማሻሻው ተግባራዊ ሲደረግ መንግስት በብዙ ቢሊዮን የሚገመት ገቢ እንደሚያጣ በተደረገ ጥናት ተረጋግጧል።

የዋጋ ንረት በታክስ ብቻ የሚፈለገውን የዋጋ መቀነስ ስለማያመጣ አቅርቦትን ለመጨመር መንግስት በከፍተኛ ወጪ በመግዛት በዝቅተኛ ዋጋ ለህብረተሰቡ ከሚያቀርባቸው ከነዚህ መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች በተጨማሪ በሌሎች አካላት የሚገባውን በማከል አቅርቦቱ በከፍተኛ ደረጃ ይጨምር ዘንድ ለስድስት ወር ተፈቅዶ የነበረው ያለውጭ ምንዛሬ ሸቀጦችን የማስገባት አስራር ለሌላ ተጨማሪ 6 ወራት እንዲራዘም ተደርጓል።

ከዚህ ተጨማሪም መንግስት የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጠር እና ገበያውን ለማረጋጋት ተጨማሪ የገንዘብ ፖሊሲን ጨምሮ ሌሎች የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ይወስዳል።

#DrEyobTekalgn #MinistryofFinance

@tikvahethiopia
#Amhara #OCHA

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አገኘሁ ተሻገር ከተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (UNOCHA) የኢትዮጵያ ኃላፊ ማርሲ ቪጎዳ ጋር ውይይት አድርገዋል።

አቶ አገኘሁ በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው "ህወሓት" በአማራ ክልል ወረራ ፈጽሞ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥቃት እየፈጸመ መሆኑን ለማርሲ ቪጎዳ ገልፀዋል።

ቡድኑ ንጹሐን ዜጎችን በአስቃቂ ሁኔታ እየገደለና እያሳደደ መሆኑን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ በክልሉ በከፈተው ጦርነት ከ550 ሺ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን አመልክተዋል።

ቡድኑ ሀገር የማፍረስ ተግባር እና በዜጎች ላይ ያደረሰውን ጥቃት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሊገነዘብ ይገባል ብለዋል።

የሽብር ቡድኑ እያሳደዳቸውና እያፈናቀላቸው ላሉ ዜጎቻችን ሰብዓዊ ድጋፍ ከማቅረብ ጀምሮ አጋርነታቸውን በተግባር ማሳየት አለባቸው ብለዋል።

"እየተሳደዱ እየተጠቁ ላሉት ዜጎቻችን ድምጽ የሚሆኗቸውና ከጎናቸው የሚሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማትን ማዬት እንሻለን" ያሉት አቶ አገኘሁ "የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮም የተፈናቀሉ ዜጎቻችንን ጉዳይ ተረድቶ ድጋፍ እንዲያደርግ እንፈልጋለን ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ የኢትዮጵያ ኀላፊ ማርሲ ቪጎዳ ተቋማቸው ለአማራ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 148 ሚሊዮን ብር መመደባቸውን ገልጸዋል፡፡

UNOCHA በፍትሐዊነት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ የሚያደርግ በመሆኑ በቀጣይ ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ለመርዳት ዝግጁ ነን ማለታቸውን ከአሚኮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia