TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በቤንሻንጉል ጉሙዝ በሎ ጅጋንፎይ ወረዳ ነሃሴ 24 እና 25/2013 በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ከ50 በላይ ሴቶች መገደላቸውን የክልሉ ፖሊስ ሪፖርት አደረገ።

የክልሉ ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ምስጋናው ኢንጂፈታ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፤ከ50 በላይ ሴቶችን በጅምላ የገደሉት የ 'ጉህዴን' ታጣቂዎች ናቸው ሲሉ ከሰዋል።

'ጉህዴን' ከዚህ ቀደም በአካባቢው እንደነበር አስታውሰው የሰላም ትግላቸውን ትተው በአፈሙዝ ጥቃት እየፈፀሙ ነው ብለዋል፤ ኃይሉ ከመተከል ዞን ባለፈም ወደካማሺ ዞን መግባቱን ጠቁመዋል።

አካባቢው ላይ በስፋት የጉምዝ ማህበረሰብ እንዳለ በማንሳት ነሃሴ 23 እና ነሃሴ 24 ቡድኑ ከ50 በላይ ሴቶችን በጅምላ መረሸኑን ገልፀዋል።

ም/ኮሚሽነሩ፤ አጠቃላይ የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ እና አካባቢውን ከታጠቀው ኃይል ለማስለቀቅ ተጨማሪ ኃይል እየጠየቅን ነው ብለዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ የፀጥታ ኃይሎች በካማሺ 5 ወረዳዎች ከጉህዴን ታጣቂዎች ጋር ውጊያ እያካሄዱ መሆኑንም ም/ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

"እነዚህ ታጣቂዎች ጉምዝን ነፃ እናወጣለን፣ በመሰረተ ልማት ወደኃላ ቀርተናል፣ጉምዝ እራሱን በእራሱ ያስተዳደር የሚሉ...መዓት ነገር ነው የሚያነሱት ነገር ግን ጥያቄያቸውን በሰላም ከማቅረብ ይልቅ ኢ-ህገመንግስታዊ መንገድ ይዘው ነው የሚንቀሳቀሱት" ሲሉ አክለዋል።

ከቡድኑ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የክልሉ ፖሊስ በርካታ ተጠርጣሪዎችን ማሰሩን ጠቁመዋል። 

ምክትል ኮሚሽነሩ በአካባቢው ባለው የታጣቂዎች እንቅስቃሴ የሱዳን እጅ በጣም ረጅም መሆኑን ያነሱ ሲሆን "በሱዳን አካባቢ የነበረው የፀረ ሰላም እንቅስቃሴ ከፍተኛ ነው፤ በመሳሪያ በሃሳብ፣ እዛ አካባቢ ያሉ ወጣቶችን መልምሎ ሱዳን አስቀምጦ የሚደግፉበትና ሽፋን የሚሰጡበት ሁኔታ አለ" ብለዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/BG-09-03

@tikvahethiopia
የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በኢኮኖሚው ላይ :

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በይፋዊ የትዊተር ገፁ ዛሬ አመሻሽ ላይ ባሰራጨው አጭር ፅሁፍ ቀደም ብለው የተወሰዱ ርምጃዎች የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በሀገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ ከባድ ተጽዕኖ እንዳይፈጥር ማስቻሉን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ የሰብዓዊ ዕርዳታ ወጭውን እየተጋራ መሆኑን ገልጿል።

እያጠናቀቅን ባለነው በዚህ ነሀሴ ወር ብቻ የኢትዮጵያ መንግሥት ለአስቸኳይ ዕርዳታ 9 ቢሊዮን ብር ወጭ ማድረጉን ጠ/ሚ ፅ/ቤት የገለፀ ሲሆን ውጪው በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአስቸኳይ ጊዜ ሰብዓዊ አቅርቦት በኩል የወጣ መሆኑን ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ በሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ከ7 ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸውን በቅርቡ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁን የጠ/ሚር ፅህፈት ቤት አስታውሷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gambella በትላንትናው ዕለት ከጋምቤላ ከተማ 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከቀኑ 11 ሰዓት ከ30 አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቁ 5 ግለሰቦች በከፈቱት ተኩስ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰው ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የጋምቤላ ክልል የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶማስ ቱት አስታወቁ። ጉዳቱን ተከትሎ በከተማው በተከሰተው ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉንና ሶስት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት…
#Update

ከሰሞኑን በጋምቤላ ከተማ ተፈጥሮ ከነበረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 30 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ የክልሉ ፖሊስ ዛሬ አስታውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ፥ "በከተማዋ ሽብር ለመፍጠር የተቀነባበረው ሴራ ከሽፎ የአካባቢው ሰላም ወደ ነበረበት ተመልሶ ነዋሪው የተለመደውን የዕለት ተለት ስራውን እያከናወነ ነው" ብሏል ለኢዜአ በሰጠው ቃል።

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቡላ ኡቦንግ በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች በሽብርተኝነት በተፈረጁት ህወሓት እና ሸኔ ተላላኪነት በከተማው የጸጥታ ችግር ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ የተጠረጠሩ ናቸው ብለዋል።

ከሰሞኑን ከጋምቤላ ከተማ 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ 5 ግለሰቦች በከፈቱት ተኩስ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉ፤ ሁለት ሰው ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ይህን ጉዳቱን ተከትሎም በከተማው በተከሰተው ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉንና ሶስት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ሪፖርት መደረጉ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,354 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ20 ሰዎች ህይወት አልፏል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 6,954 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1,354 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል። በተመሳሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ 20 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።

የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር እጅግ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 696 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ እና የጋና ፍልሚያ !

የሀገራችን የእግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ከደቂቃዎች በኃላ የጋና ብሄራዊ ቡድንን ይገጥማል።

ግጥሚያው ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ የሚደረግ #ማጣሪያ ሲሆን በጋና ኬፕ ኮስት በተባለው ስታዲየም ነው የሚደረገው።

በቋሚ አሰላለፍ ሀገራችን #ኢትዮጵያን የሚወክሉት ተጫዋቾች የታወቁ ሲሆን እነማን ናቸው የሚለውን በ https://t.me/tikvahethsport/20410 መመልከት ይቻላል።

የሀገራችን ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን አረጓንዴ ቁምጣ ፣ ቢጫ ካሶተኒ ቀይ የሚለብሱ ሲሆን ተፋላሚያችን ጋና ሙሉ ነጭ መለያ ይለብሳል።

ጨዋታውን ጥሩ የኢንተርኔት ግንኙነት ያላችሁ በFIFA ይፋዊ የዩቲዩብ ገፅ በዚህ 👉 https://t.co/j55uaSRXkI መመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahethsport ደግሞ የጨዋታውን ሁኔታ እየተከታተለ በፅሁፍ ያሳውቃል።

መልካም ዕድል ለኢትዮጵያችን !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ እና የጋና ፍልሚያ ! የሀገራችን የእግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ከደቂቃዎች በኃላ የጋና ብሄራዊ ቡድንን ይገጥማል። ግጥሚያው ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ የሚደረግ #ማጣሪያ ሲሆን በጋና ኬፕ ኮስት በተባለው ስታዲየም ነው የሚደረገው። በቋሚ አሰላለፍ ሀገራችን #ኢትዮጵያን የሚወክሉት ተጫዋቾች የታወቁ ሲሆን እነማን ናቸው የሚለውን በ https://t.me/tikvahethsport/20410 መመልከት ይቻላል።…
#Update

ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የምድባቸውን የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታ ከጋና ብሄራዊ ቡድን ጋር ያደረጉት ዋልያዎቹ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት ተሸንፈዋል።

ዋካሶ ብቸኛዋን የጋና ብሔራዊ ቡድን ጎል በመጀመሪያው አጋማሽ ማስቆጥር ችሏል።

ዋልያዎቹ በነገው ዕለት አዲስ አበባ እንደሚገቡ ሲጠበቅ ወደ ባህር ዳር በዚሁ ዕለት የሚያቀኑ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቀናት በኋላ ማክሰኞ #ከዙምቧቡዌ አቻቸው ጋር በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የምድብ ማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ።

More : @tikvahethsport
#HappeningNow

የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የሁርሶ የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ምልምል አባላትን እያስመረቀ ይገኛል።

በሀገር መከላከያ ሚኒሰቴር የሰላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ዛሬ እያስመረቀ የሚገኘው ሶስተኛው ዙር በመሠረታዊ ወታደርነት ያሰለጠናቸውን ምልምል አባላትን ነው።

በምርቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ እንዲሁም ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትእ አቶ ደመቀ መኮንን እንደሚገኙ ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD #FDREDefenseForce ሀገር መከላከያ ሰራዊት፥ ኢትዮጵያ እየገነባች ያለውን ግዙፉን የታላቁ ሕዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረውን የህወሓት ቅጥረኛ ሃይል ደመሰስኩኝ አለ። የግድቡን ግንባታ ለማደናቀፍ ተልዕኮ ውስደው የተንቀሳቀሱና ሰራዊቱ የማያዳግም እርምጃ የወሰደባቸው ኃይሎች (የተገደሉ) በቁጥር 50 ሲሆኑ ፤ ከ70 በላይ የሚሆኑት…
ሱዳን ምላሽ ሰጠች...

ሱዳን በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል በኩል የኢትዮጵያ መንግስትን እየተዋጉ ለሚገኙት የትግራይ አማፅያን ድጋፍ ታደርጋለች መባሉን አጥብቃ አስተባበለች።

ትላንት ሀገር መከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያ እየገነባች ያለውን ግዙፉን የታላቁ ሕዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረውን የህወሓት ቅጥረኛ ሃይል መደምሰሱን (50 መግደሉን፤ 70 ደግሞ ማቁሰሉን) ሪፖርት ማድረጉ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር አል-ታሂር አቡ ሀጃ "መሰረተ ቢስ ውንጀላ" ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።

አቡ ሃጃ ፥ "ሱዳን እና ሰራዊቷ በአጎራባች ኢትዮጵያ ወይም በሌሎች ሀገሮችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቀ አይገቡም" ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው፤ "ይህ መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝብ የመብት ጥሰቶች በመቀጠላቸው ምክንያት የኢትዮጵያ አገዛዝ የገጠመውን ከባድ እውነታ ያንፀባርቃል” ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ሱዳን ለአማፅያን የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገችን እንደሆነ ሲገልፅ ነበር።

በትላንትናው ዕለት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከገለፀው በተጨማሪ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ፤ የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የታጣቂዎች እንቅስቃሴ #የሱዳን_እጅ በጣም ረጅም መሆኑን ገልጿል።

የክልሉ ም/ኮሚሽነር "በሱዳን አካባቢ የነበረው የፀረ ሰላም እንቅስቃሴ ከፍተኛ ነው፤ በመሳሪያ በሃሳብ፣ እዛ አካባቢ ያሉ ወጣቶችን መልምሎ ሱዳን አስቀምጦ የሚደግፉበትና ሽፋን የሚሰጡበት ሁኔታ አለ" ሲሉ አስረድተዋል።

ከሰሞኑን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ፤ በካማሺ ዞን ፤ በሎ ጅጋንፎይ ወረዳ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ከ50 በላይ ሴቶች በጅምላ በግፍ መገደላቸውን የክልሉ ፖሊስ ሪፖርት ማድረጉ፤ ለጥቃቱ ደግሞ "ጉህዴን"ን ተጠያቂ ማድረጉ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
ICRC በደሴ ድጋፍ እያደረገ ነው።

ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ግጭት ከቆቦ፣ ወልዲያ፣ መርሳ እና ላሊበላ ተፈናቅለው በደሴ ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ 36,000 ሰዎች መሰረታዊ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁስ ፣ የንጽህና መጠበቂያዎችን እና መጠለያን ያካተተ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

#ICRCEthiopia

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ 108 የመገበያያ ቦታዎችን እና ከ250 ሺህ ኩንታል በላይ ተጨማሪ የግብርና ምርት መዘጋጀቱን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አሳወቁ።

ምክትል ከንቲባዋ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ስራ የጀመሩት መሸጫዎቹ በከተማዋ የሚስተዋለዉን የኑሮ ዉድነት በማረጋጋት በተለይ የግብርና ውጤት የሆኑ የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን እንዲሁም እንደ እንቁላል ያሉ የእንስሳ ተዋጽኦ አቅርቦትን ይበጥል በማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።

ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ፥ በከተማዋ 56 የቁም እንሰሳት መገበያያ እንዲሁም 52 የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫዎች በሁሉም ክፍለከተሞች ስራ መጀመራቸውን ገልፀው ፤ መሸጫ ማዕከላቱ ለሸማቹ ህብረተሰብ ምርት በቀጥታ ከአርሶ አደሩ ማሳ ከማቅረባቸው በተጨማሪ ምርቶቻቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረባቸው ተመራጭ ያደርጋቸዋል ሲሉ አክለዋል።

@tikvahethiopia