TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ALERT🚨

"ዴልታ" የተሰኘው የኮቪድ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ ተገኘ።

አደገኛው የኮቪድ ዴልታ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰጡት መግለጫ “በኢትዮጵያ ባለፉት ሳምንታት በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች፣ የሚሞቱና ፅኑ ህሙማን ቁጥር በጣም አሻቅቧል” ብለዋል።

አዲሱ ዝርያ ሁሉንም የዕድሜ ክልል የሚያጠቃ፣ ለከባድ ህመምና ሞት የሚዳርግ በተለይም ባልተከተቡ ሰዎች ላይ የሚበረታ ዝርያ መሆኑን ገልፀዋል።

ክትባት በየጤና ተቋማቱ በመገኘት እንዲወስዱ፣ የኮቪድ ፕሮቶኮልን ከሁሉም ተቋማትና ግለሰቦች እንደሚጠበቅም አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ብቻ 8 ሺህ 300 ሰዎች በወረርሽኙ ተይዘዋል።

እስካሁን በአገሪቱ 313 ሺህ ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል። ከ4 ሺህ 700 በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል።

በኮቪድ ወረርሽኝ የመያዝ ምጣኔውም ከ1 በመቶ ወደ 20 በመቶ አሻቅቧል ፤ ባለፈው ሳምንት 118 ሰዎች ሞተዋል። #ENA

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ስርጭት እየተባባሰ ይገኛል።

በወረርሽኙ ሳቢያ የኮቪድ-19 ህክምና መዕከሎች እየሞሉ መሆኑንም የጤና ባለሞያዎች እየጠቆሙ ናቸው።

የፅኑ ህሙማን ክፍሎችም ሞልተው ታካሚዎች የሚስተናገዱት በወረፋ ነው።

#DrYaredAgidew

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በኮቪድ-19 ሳቢያ በአንድ ቀን የ47 ዜጎች ህይወት አለፈ።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 47 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 9,379 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,489 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 789 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

በየዕለቱ በኮቪድ19 ምክንያት ህይወታቸው የሚያጡ ዜጎች ቁጥር በእጅጉ እያሻቀበ በመሆኑ መላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጥንቃቄያችሁን እንድታጠናክሩ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በአንድ ቀን የ49 ዜጎች ህይወት አለፈ።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በኮቪድ-19 ምክንያት 49 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,366 የላብራቶሪ ምርመራ 799 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 780 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

በየዕለቱ በኮቪድ19 ምክንያት ህይወታቸው የሚያጡ ዜጎች ቁጥር በእጅጉ እያሻቀበ በመሆኑ መላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጥንቃቄያችሁን እንድታጠናክሩ አደራ እንላለን።

#TikvahFamily😷

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WFP የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከመደበኛ እርዳታ ውጪ ለ62,900 አባዋራዎች የምግብ እርዳታ አቀርባለሁ ብሏል። ከቀናት በፊት የሶማሊ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገው ነበር። ውይይቱ በሶማሊ ክልል ውስጥ በአንድ አንድ ቦታዎች የተከሰተዉን ድርቅ ለመቋቋም ያለመ ነው። በዉይይቱ ላይ አቶ ሙስጠፋ ፥ በተለይ ዳዋ ዞን ከፍተኛ የድርቅ አደጋ…
#ALERT🚨

የዓለም ምግብ ፕሮግራም አሁኑኑ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ የማያገኝ ከሆነ በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል በተከሰተው ከባድ ድርቅ ምክንያት በሚቀጥሉት 3 ወራት ውስጥ እስከ 3.3 ሚሊዮን ሰዎች ለከፍተኛ ረሃብ ይጋለጣሉ ብሏል።

ከቀናት በፊት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ኃላፊዎች ከሶማሊ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ጋር ውይይት ካደረጉ በኃላ ያወጡት የጋራ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በሀገራችን ኢትዮጵያ በቀን 2,323 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 10,016 የላብራቶሪ ምርመራ 2,323 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ የ5 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 2,992 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 10,828 የላብራቶሪ ምርመራ 2,992 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ3 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ወረርሽኙን ለመከላከል የምታደርጉትን ጥንቃቄ እርምጃ ከመቼውም ጊዜ በላይ ታጠናክሩ ዘንድ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 3,793 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 13,147 የላብራቶሪ ምርመራ 3,793 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ5 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

በሌላ በኩል ፤ ኦሚክሮን የተሰኘው የኮቪድ-19 አዲሱ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ መከሰት አለመከሰቱን ለማረጋገጥ ናሙና በመውሰድ ምርምር እየተካሄደ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ዛሬ አስታውቀዋል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 4,573 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 12,348 የላብራቶሪ ምርመራ 4,573 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ3 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 5,013 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 14,027 የላብራቶሪ ምርመራ 5,013 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ6 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

193 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ከፍተኛ_ጥንቃቄ

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 6,262 የላብራቶሪ ምርመራ 1,864 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ6 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

210 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 5,185 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 13,280 የላብራቶሪ ምርመራ 5,185 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ7 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር በእጅጉ የጨመረ ሲሆን አሁን ላይ 232 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 14,035 የላብራቶሪ ምርመራ 4,998 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ10 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

260 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 13,409 የላብራቶሪ ምርመራ 4,899 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ11 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 👉 10,861
• ቫይረሱ የተገኘባቸው 👉 2,269
• ህይወታቸው ያለፈ 👉 24
• ከበሽታው ያገገሙ 👉 1,416
• ፅኑ ታማሚዎች 👉 443

ዛሬ እና ትላንት በድምሩ የ48 ሰዎች ህይወት አልፏል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 👉 10,073
• ቫይረሱ የተገኘባቸው 👉 2,131
• ህይወታቸው ያለፈ 👉 19
• ከበሽታው ያገገሙ 👉 835
• ፅኑ ታማሚዎች 👉 433

ዛሬ እና ትላንት በድምሩ የ43 የሰዎች ህይወት አልፏል።

@tikvahethiopia
#Alert

የጤና ሚኒስቴር የትዊተር አካውንት ተጠለፈ።

ከ204 ሺ በላይ ተከታዮች ያሉት የሚኒስቴሩ የትዊተር አካውንት ተጠልፏል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጤና ሚኒስቴር ይፋዊ የትዊተር አካውንቱ #FMoHealth ዛሬ መጋቢት 24 መጠለፉን (ሃክ መደረጉን) አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ በትዊተር ገጹ ላይ የሚለቀቁ ማንኛውም መረጃዎች እንደማይወክሉት ገልጿል።

@tikvahethiopia
#Alert🚨

በራስ ጠቆሮ ጥብቅ ደን ላይ የተነሳውን እሳት መቆጣጠር አልተቻለም።

በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ 016 ቀበሌ በተለምዶ ራስ ጠቆሮ እየተባለ በሚጠራ ጥብቅ ደን ላይ ሰኔ 6/2014 ሌሊት ጀምሮ የተከሰተው የእሳት አደጋን እስካሁን ድረስ መቆጣጠር አልተቻለም።

በጥብቅ ደኑ ውስጥ ወይራ፣ ጥድ፣ ኮሶ፣ ዝግባና ሌሎች የደን ሐብቶች እንዲሁም የተለያዩ እንሰሳትና አዕዋፋት እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

ከመልክዓ ምድራዊ አቀማመጡ አመቺ አለመሆን እና በደኑ ውስጥ ተቀጣጣይ ሳር ከመብዛቱ ጋር ተያይዞም የእሳት አደጋውን ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት ሥራውን ፈታኝ እንዳደረገው ተገልጿል።

የአደጋው መንስኤ በተመለከተ እሳቱ ከግለሰብ ማሳ ተነስቶ ወደ ደኑ እንደተዛመተ የአምባሰል ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

" ሰባ ሰባት እንኳን አንዲህ አልነበረም "

ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ በከባድ ድርቅ መመታቱ ተገልጿል።

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ስር ያለው ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ 13 ቀበሌዎች አሉት።

ወረዳው የ2015/2016 የምርት ዘመን #ድርቅ ክፉኛ መትቶታል።

ወረዳው በከፊል አርብቶ አድር የሚታወቅ ሲሆን ከማሳው በሚያገኛት ጥቂት ኩንታል እህል በይበልጥ ለገለባው ዋጋ ሰጥቶ በእንሰሳቱ ኑሮውን የሚገፈ አርሶና አርብቶ አደር አካባቢ ነው።

በወረዳው ከፍተኛ የእንስሳት ሀብትም ይገኛል።

ጠቅላላ ካለው የእንስሳት ሀብት የዳልጋ ከብት 104,430፣ የጋማ ከብት 22,121 በግ እና ፍየል 465,428 ይገኙበታል።

ከዚህ ውስጥ ለድርቅ የተጋለጡ የዳልጋ ከብት 92,430፣ የጋማ ከብት 16,121፣ በግ እና ፍየል 396,760 ናቸው።

ወደአጎራባች ዞን የተሰደዱ የዳልጋ ከብት 20,328 ፣ በግ እና ፍየል 116,900 ሲሆኑ እስካሁን በድርቅ ምክንያት የሞተ የዳልጋ ከብት 1320 ፣ የጋማ ከብት 71 በግ እና ፍየል 2457 ናቸው።

በወረዳው ከ52 ሺህ በላይ ህዝብ የሚኖርበት ሲሆን 46ሺ የሚሆነው አፋጣኝ እርዳታ ካለገኘ አደጋ ውስጥ እንደሆነ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ብሩ ተናግረዋል።

አቶ ሲሳይ፤ " ምንም እንኳን ድርቅ ቢሆንም ከዚህ በፊት ለእንስሳት የሚሆን ሳር አይጠፋም ነበር። ዛሬ ግን የተቃጠለ መሬት ብቻ ነው የሚታየው፤ ለጥርስ ስጋ ማውጫ የሚሆን የሳር ስንጥር እንኳን አይታይም፤ የወረዳው ነዋሪዎች እንደነገሩን እንደ ወረዳችን እንዲህ አይነት ድርቅ አይተን አናውቅም፤ ሰባሰባት እንኳን አንዲህ አልነበረም " በማለት የድርቁን አስከፊነት ገልጸዋል።

በወረዳው የአርሶ አደሩ ማሳ ርቃኑን ቀርቷል፣ እንስሳት ቆዳቸው ከስጋቸው መጣበቅ ብቻ ሳይሆን ነፍሳቸው በጣዕረሞት ላይ ናት፣  ህጻናት፣ እናቶችና አረጋውያን በርሀብ ተገርፈው ነፍሳቸው ከጉንጫቸው ተጣብቃ ይዛቸው ልትጠፋ አፋፍ ላይ ነች። ተሎ መድረስ ካልተቻለ አሳዛኝ ክስተት በሰሀላ ሰዬምት ወረዳ ሊከሰት ይቻላል።

የአስተዳደሩ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ጉዞ አዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን የብሄረሰቡ ከፍተኛ አመራሮችና አንዳንድ ግብረሰናይ ድርጅቶች በወረዳው ተገኝተው ቀበሌዎቹን ጎብኝተው ከነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

የቀበሌው ማህበረሰብ በውይይቱ ላይ " ከእግዚአብሄር በታች መንግስት ነበር ለሰው ልጅ ዋስትና፣ ዛሬ ግን መንግስትም ፊቱን አዞረብን " ብለዋል።

" በዚህ ሳምንት ውስጥ የሚበላ ካልቀረበ ልጆቻችን አናገኛቸውም ፤ አሁንም ቢሆን አንዲት እንጀራ ለ10 ሰው ነው የምንሻማው፤ ከዛ ውጭ ግን ጨው በውሀ በጥብጠን ነው የምንጠጣው " ብለዋል።

እስካሁንም በወረዳው በርሀብ ምክኒያት የ2  ሰዎች ሂይወት አልፏል ሲሉ አሳውቀዋል።

እንስሳትን በተመለከተ " በወረዳችን ትንሽ እህል ካገኘን እንሰሳ ስለምናረባ ከብት እና ፍየሎቻችንን ሸጠን እህል ስለምንሸምት ብዙም አያሳስበንም ነበር፤ ዘንድሮ ግን ለከብቶችም ሆነ ለፍየሎችና በጎች የሚሆን የሚጋጥ ሳር ስለሌለ ተስፋ አስቆርጦናል " ብለዋል።

የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ምህረት መላኩ፤ የተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ቃል ከመግባት የዘለለ በመንግስት በኩልም ምንም የቀረበ ነገር የለም።

ለክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ሪፖርት ከማድረግ ባለፈ የችግሩን አሳሳቢነት ብንገልጽም እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም ብለዋል።

መረጃው ከዋግኽምራ ኮሚኒኬሽን ነው የደረሰን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ALERT🚨 " ሰባ ሰባት እንኳን አንዲህ አልነበረም " ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ በከባድ ድርቅ መመታቱ ተገልጿል። በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ስር ያለው ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ 13 ቀበሌዎች አሉት። ወረዳው የ2015/2016 የምርት ዘመን #ድርቅ ክፉኛ መትቶታል። ወረዳው በከፊል አርብቶ አድር የሚታወቅ ሲሆን ከማሳው በሚያገኛት ጥቂት ኩንታል እህል በይበልጥ ለገለባው ዋጋ ሰጥቶ በእንሰሳቱ ኑሮውን…
#ALERT🚨

አንድ አንጀራ ለ10 ተሻምተው የሚበሉ ወገኖቻችን እንዳሉ እናውቅ ይሆን ?

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ስር ያለው ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ በከፍተኛ ድርቅ ተመቷል።

ነዋሪው ችግር ላይ ወድቋል።

ሰው በረሃብ #ሞቷል ፣ እንስሳት ሞተዋል ፣ ተሰደዋል።

ወገኖቻችን በቂ ምግብ አጥተው 1 እንጀራ ለአስር እየተሻሙ እየበሉ ነው። ካዛ ውጭ ጨው በውሃ በጥብጠው ነው የሚጠጡት።

" በዚህ ሳምንት የሚበላ ካልቀረበ ልጆቻችንን አናገኛቸውም " ብለዋል።

የግብረሰናይ ድርጅቶች ቃል መግባት እንጂ ጠብ የሚል ነገር አላደረጉም። መንግሥትም ለገዛ ዜጎቹ እየደረሰ አይደለም።

ከፈጣሪ በታች ለህዝቡ ዋስትና ነው የሚባለው መንግሥት ፊቱን እንዳዞረባቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ሁኔታው ከሰባ ሰባቱም የከፋ ነው።

via @BirlikEthiopia

@tikvahethiopia