TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም የ4G LTE አገልግሎት ተደራሽነትን እያሰፋ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞች ተግባራዊ የተደረገው የ4G LTE አገልግሎት በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ ዛሬ ተጀምሯል።

ጋምቤላ ከተማ በኢትዮ ቴሌኮም የ "ደቡብ ምዕራብ ምዕራብ ቀጠና" የሚገኝ ሲሆን የ4G እና LTE Advanced የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራውን ተጠናቆ ስራ ጀምሯል።

በዚህ ቀጠና 28,000 ደንበኞች የዳታ ተጠቃሚዎች ናቸው።

በጋምቤላ ከተማ አገልግሎቱን የማስጀመሪያ ስነስርዓት የተካሄደ ሲሆን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ተገኝተው ነበር።

በሌላ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በተያያዘ መረጃ ኢትዮ ቴሌኮም ከአፍሪካ የቴሌኮም አገልግሎት ኩባንያዎች ውስጥ በሁለተኛ ደረጃ መቀመጡ ተሰምቷል።

በአፍሪካ 195 የቴሌኮም ኦፐሬተሮች ያሉ ሲሆን፤ ኢትዮ ቴሌኮም በግዝፈት፣ በደንበኛ ቁጥር እና በአገልግሎት ደረጃ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ከዓለም ደግሞ 28ኛ ደረጃን ይዟል።

ይህን ያሳወቀው ግሎባል ሲስተምስ ፎር ሞባይል ኮሙኒኬሽንስ ወይም በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃል GSMA የተባለ ተቀማጭነቱ እንግሊዝ ሀገር የሚገኝ ተቋም ነው።

GSMA በዓለም ዙርያ ከ750 በላይ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ተቋሞችን በአባልነት አቅፎ የያዘና ኩባንያዎቹን በሥራቸው ልክ ጥራት እና ደረጃ መዝኖ ሪፖርት የሚያድርግ ዓለም አቀፍ ተቋም መሆኑን ሸገር አስነብቧል።

@tikvahethiopia
"...መደበኛ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምሩትን ግዜ በመስከረም መጀመሪያ አሳውቃለሁ" - ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ እረፍት ላይ የሚገኙ መደበኛ ተማሪዎቹ ትምህርት የሚጀምሩትን ግዜ በመስከረም መጀመሪያ አሳውቃለሁ ብሏል።

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች ከሐምሌ 22/2013 ዓ.ም ጀምሮ እረፍት ላይ ይገኛሉ።

በተቋሙ ይገኙ የነበሩ የጤና ተማሪዎች እና የ2013 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከነሐሴ 08/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ሳምንታት የክረምት እረፍት እንደተሰጣቸው መዘገባችን ይታወሳል።

ተቋሙ ነሐሴ 22/2013 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ የተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲ የመመለሻ ጊዜን በቀጣይ አሳውቃለሁ ማለቱ አይዘነጋም።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ እንዳሳወቀው በእረፍት ላይ የሚገኙ መደበኛ ተማሪዎቹ ትምህርት የሚጀምሩትን ግዜ በመስከረም የመጀመሪያ ሳምንት አሳውቃለሁ ብሏል።

More : @tikvahuniversity
ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ያደረጉት የደሴ ልጆች...

ኑሯቸውን በአሜሪካ፣ ካናዳ እና አውሮፓ ያደረጉ የደሴ ልጆች እና ወዳጆች ለተፈናቀሉ ዜጎች የ1.6 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል::

ድጋፉ ከሰሜን ወሎ እና አፋር አካባቢ ተፈናቅለው በደሴ ከተማ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የተደረገ ነው።

ድጋፉ በውጭ ሀገር ነዋሪ በሆኑት አቶ ሽመልስ መኮንን እና ሰለሀዲን እሸቱ አስተባባሪነት የተሰበሰበ ሲሆን÷
- 600 ብርድልብስ፣
- 400 ፍራሽ፣
- 60 ኩንታል ደዱቄት፣
- 60 ኩንታል መኮረኒ፣
- 260 ወተትናና በርካታ የንጽህና መጠበቂያ መሆኑ ታውቋል።

የተደረገው ድጋፍም በሁሉም ትምህርት ተቋማት ተጠልለው ለሚገኙ ከአማራ እና አፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ይውላልም ነው የተባለው፡፡

ድጋፉ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩት አቶ ብርሀኑ አሰፋ እና ወይዘሮ ሳባ ገ/ሥላሴ ለከተማዋ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል ማስረከባቸውን የከተማ አስተዳደሩ ኮሜኒኬሽን አሳውቋል።

ከትግራይ ክልል ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች የሰፋው ጦርነት በመቶ ሺዎችን ከቤት ንብረታቸው ፣ቄያቸው አፈናቅሏል፣ ንብረት አውድሟል፤ ነዋሪዎችም ተሰደው በየትምህርት ቤቱ እንዲጠለሉ አድርጓል።

@tikvahethiopia
#BahirDar

ዛሬ በባህርዳር ከተማ በአፄ ቴዎድሮስ ክፍለከተማ በህገወጥ መልኩ የተከዘነ በርበሬ በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

በርበሬው ተከማችቶ የተገኘው በአፄ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ በአዲስ አለም ቀበሌ መስኪዱ አካባቢ ነው::

በቁጥጥር ስር የዋለው በርበሬ በኩንታል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሲሆን በህብረተሰቡ ጥቆማ ነው ሊያዝ የተቻለው::

ባለሃብቱም ከንብረቱ ጋር በቁጥጥር የዋለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል።

በባህር ዳር ከተማ ህገወጥ ነጋዴዎች እና ስግብግብ ነጋዴዎች የኑሮ ውድነቱን እንዲባባስ መንስኤ በመሆናቸው ህብረተሰቡ የዚህ አይነት ተግባራትን ሲያገኝ ለፖሊስና ለሚመለከተው አካል በመጠቆም ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ተብሏል::

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#KENYA 🇰🇪 #ETHIOPIA 🇪🇹 የጎረቤት ሀገር ኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ራይሸል ኦማሞ ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል። ሚኒስትሯ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርዱ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ብርቱካን አያኖ ተቀብለዋቸዋል። የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ከሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋር ይመክራሉ።…
#Update

የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራይሸል ኦማሞን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን በይፋዊ የማህበራዊ ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት ከራይሸል ኦማሞ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ፣ ስለትግራይ ክልል ፣ ስለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንዲሁም ስለኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ መምከራቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪ ኬንያ በመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆሟ ለሃገሪቱ መንግስትና ህዝብ ታላቅ ምስጋናና አክብሮት እንዳላቸው ለራይሸል አማሞ ገልፀውላቸዋል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,643 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ19 ሰዎች ህይወት አልፏል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 8,627 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1,643 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል። በተመሳሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ 19 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።

የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር እጅግ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 663 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

@tikvahethiopia
#Afar

ህወሓት በአፋር ክልል በበህራሌ በኩል በመግባት በፈፀመው ድንገተኛ ጥቃት ንፁሃን ላይ ጉዳት መድረሱን የጉዳቱ ሰለባዎች ተናገሩ።

በአካባቢው ጥቃት መፈፀመ የተጀመረው ካለፈው ዓርብ አንስቶ ነው።

በተከፈተው ጥቃት ብዙ ሰው መገደሉን፣ ከተገደሉት መካከልም ሴቶች እና ህፃናት እንደሚገኙበት ከጥቃቱ የተረፉና በአሁን ሰዓት በህክምና እርዳታ ላይ የሚገኙ ሰለባዎች ገልፀዋል።

በሰው ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ የቡድኑ ታጣቂዎች በርካታ ቤቶች መሰበራቸውንና እቃዎችን መዝረፋቸውን፣ ግመሎች፣ ፍየሎች ፣ ላሞች ላይ ዝርፊያ መፈፀሙን አስረድተዋል።

ቡድኑ ጥቃት ያደረሰበት ቦታ ለሽፍትነት ተግባር ምቹ በመሆኑ ይህንን በመጠቀም ነው ንፁሃንን የገደለው ሲሉም ተጎጂዎቹ አክለዋል።

በአሁን ሰዓት የአብዓላ የፕራይመሪ ሆስፒታል ከ40 በላይ ተጎጂዎች ህክምናቸውን እየተከታተሉ ሲሆን ሆስፒታሉ በየቀኑ ከ10 እስከ 15 ተጎጂዎችን እያስተናገደ እንደሚገኝ ለኤፍ ቢ ሲ አሳውቋል።

ሆስፒታሉ እንዳለው ካለፈው አርብ ጀምሮ በተከፈተ ውጊያ በየዕለቱ ተጎጂዎች እርዳታ ፍለጋ እየመጡ ናቸው። የሚመጡት ተጎጂዎች ጉዳታቸው የከፋ በመሆኑ አንዳዶቹ ለማከም ከአቅም በላይ የሆኑትን ሪፈር የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሆነ አክሏል።

ከውጊያው በፊት ሆስፒታሉ የተለያዩ የህክምና አገልግሎቶችን ሲሰጥ የነበረ ሲሆን ከውጊያ በኃላ ግን ሌሎች ስራዎቹን አቁሞ ተጎጂዎችን ለማከመ ተገዷል።

የአፋር ክልላዊ መንግስት ከዚህ ቀደም በክልሉ ፈንቲ ረዱ ጋሊኮማ ህወሓት በከፈተው ድንገተኛ ጥቃት ህፃናት እና ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ንፁሃን መገደላቸውን ፣ መጎዳታቸውን ገልፆ እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopia
ታሪክ የማይረሳው ጥረት ተደርጓል !

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፦

"...እነዚህ ችግሮች ሳይከሰቱ በሰላምና በሽምግልና ለፍታት ፣ ወደ አላስፈላጊ ክስተት እንዳያመሩ በወቅቱ ለማረም እና ለማስተካከል ከፍተኛ ጥረት የተደረገ ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቷል።

በአጠቃላይ በሀገራችን አሁን እየሆነ ያለው ሁሉ ከመሆኑ በፊት የሀይማኖት አባቶች ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ አድርገዋል፤ በአካልም ከ700 ኪሎ ሜትር በላይ በመጓዝ መክረዋል፣ ገሥፀዋል፤ ጠንካራ መልዕክቶችን እና ጥሪዎች አስተላልፈዋል።

በተለይ የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል ላይ ያለ የህግ ማስከበር ዘመቻ ከማወጁ በፊት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፣ ከኢትዮጵያ የሀገር ሽማግሌ መማክርት ፣ ከታዋቂና ተሰሚነት ካላቸው ገለልተኛ ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር ችግሩን በሰላማዊ ውይይት፣ ምክክርና ድርድር ብቻ እንዲፈታ ታሪክ የማይዘነጋው ከፍተኛ ጥረት አድርጓል።"

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"ሀገር አቀፍ የፆምና የፀሎት ምህላ አዋጅ" የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አዲሱን አመት በሰላም ለመቀበል ያለመ ለ5 ቀናት የፀሎት መርሐግብር አወጀ። የፀሎት መርሐግብሩ ከጷግሜ 1 እሰከ 5 የሚቆይ መሆኑም ተገልጿል። ጉባኤው አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ የሰላም ጥሪን በሚመለከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። አገሪቱ ያጋጠማት ወቅታዊ ችግር በይቅርታና በፍቅር እንዲፈታ የተለያዩ እምነት…
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ :

"...ስለህዝብ ያገባናል ፣ እንታገላለን የምትሉ ሁሉ ከሁሉ በላይ #ሰብዓዊነትን አክብሩ፣ ንፁሃንን በፍፁም ኢላማ አታድርጉ፣ ለአንድ ወገን እንታገላለን በማለት የሌላውን ወገን መጉዳት እና ለጥቃት ማጋለጥ፣ የዜጎችን ደህንነት በተለይም የታዳጊ ህፃናትን ተስፋ ማጨለም ፣ ለግዳጅ ማሰማራት ተቀባይነት የሌለውና ተገቢ እንዳልሆነ ልናስታውሳችሁ እንወዳለን።

በተጨማሪ ለዘመናት ተጠብቀው የኖሩ እንደ ቅዱስ ላሊበላ ፣ አክሱም ፂዮን ፣ አልነጃሺ መስጊድ በመሳሰሉ የሃይማኖት ተቋማት እና የታሪካዊ ቅርሶቻችን ላይ የተቃጣውን ጥቃት በፅኑ እናወግዛለን።

ሁላችሁም አካላት ከግብዝነት ርቃችሁ፣ያነገታችሁትን ጠብመጃ ለሰላም ስትሉ ለማዘቅዘቅ ፣ ህይወት ቀጣፊ እና ንብረት አውዳሚ ከሆነ ተግባር ለመራቅ ልባችሁ ሁሌም የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።"

ነሃሴ 27 ቀን 2013 ዓ/ም

@tikvahethiopia
ቦረና ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን መቀበል ጀመረ።

ባለፈው ሰኔ የተመረቀው ቦረና ዩኒቨርሲቲ የ2013 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ዛሬ መቀበል ጀምሯል።

ሰኔ 04 ቀን 2013 ዓ / ም የተመረቀው የቦረና ዩኒቨርሲቲ ፤ 600 አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

ዩኒቨርሲቲው የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባን ነሐሴ 27 እና 28/2013 ዓ.ም የሚያከናውን ሲሆን ዛሬ 200 የሚጠጉ ተማሪዎች ምዝገባቸውን አድርገዋል።

ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊ የሆኑ የምግብ፣ የመኝታ እና ሌሎች መሠረታዊ አገልግሎቶች እንደተሟሉለት የተቋሙ የሬጅስትራር ዳይሬክተር ማሊቻ ሀርጌሳ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

4 ሺህ ተማሪዎችን በአንድ ግዜ የሚያስተናግድ ቤተ መፅሀፍት ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ የውሃ፣ መብራት እንዲሁም ኢንተርኔት አገልግሎቶች መሟላታቸውን ነግረውናል።

ለአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ ግንዛቤ ማስጨበጫ በቀጣይ ማክሰኞ ከተሰጠ በኋላ፤ ትምህርት ረቡዕ እንደሚጀምር ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

በ350 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ዩኒቨርሲቲው ፤ የአካባቢውን አርብቶ አደር ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ታምኖበታል፡፡

MORE : @tikvahuniversity
ድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

“ተማር ልጄ” በሚለው ዘመን ተሻጋሪ ዘፈኑ የብዙዎችን ቀልብ የማረከው ድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ነሐሴ 27፣2013 እኩለ ሌሊት በድንገት ማረፉ ነው የታወቀው።

"ተማር ልጄ ሌት ፀሀይ ነው ላልተማረ ሰው ግን ቀኑ ጨለማ ነው..." እያለ ሚሊየኖችን በዜማው መክሯል።

አንጋፋዉ ሙዚቀኛ አለማየሁ እሸቴ በሚጫወታቸው የሙዚቃ ስራዎቹ 'ኤልቪስ ፕሪስሊ' የሚል ቅፅል ስምም ተሰጥቶት ነበር።

ስቀሽ አታስቂኝ" ፣ " እንደ አሞራ ክንፍ አውጥቼ ልብረራ"፣ " ማን ይሆን ትልቅ ሰው" ፣ " ምሽቱ ደመቀ"፣ "አዲስ አበባ ቤቴ" ፣ "የወይን ሃረጊቱ" ፣ "የሰው ቤት የሰው ነው"፣ "ደንየው ደነባ"፤ "ትማርኪያለሽ"፣ "ወልደሽ ተኪ እናቴ" እና " ተማር ልጄ" ከአለማየሁ እሸቴ ሙዚቃዎች በዋናነት የሚጠቀሱለት ናቸው።

የድምፃዊው ድንገተኛ ህልፈት ተከትሎ ብሔራዊ ቴአትርን ጨምሮ አድናቂዎቹ ሀዘናቸውን እየገለፁ ይገኛል።

(FBC)

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በድምፃዊ ዓለማየሁ እሸቴ ማረፍ የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፤ "ሀገሩን አጥብቆ በመውደድና ለሀገሩ ከልብ በመሥራት ለብዙ ከያንያን አርአያ የሆነው ዓለማየሁ እሸቴ ማረፉን ሰምቼ እጅግ አዝኛለሁ" ብለዋል።

አክለውም ፥ "ሰሞኑን ወጣትና አንጋፋ ከያንያን ስለ ኢትዮጵያ ዘመኑን የዋጀ ሙዚቃ እንዲያወጡ ሲያስተባብር እንደነበር ዐውቃለሁ ሥራዎቹ ኢትዮጵያን ከፍ እንዳደረጉ ይኖራሉ። ለኢትዮጵያ የሠራ ያርፋል እንጂ አይሞትም" ሲሉ ፅፈዋል።

@tikvahethiopia