TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianCatholicSecretariat የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ብፁዕ ካርዲናል ሊቀ-ጳጳስ ብርሀነ የሱስና የመርዋቸው መልእክተኞች ኤርትራ እንዳይገቡ መከልከላቸውን የቤተክርስትያንዋ ሴክረታርያት አርረጋግጧል። ካርዲናሉና ቡድናቸው የኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስተያን ባደረገችላቸው ጥሪ መሰረት ባለፈው ቅዳሜ ወደ ኤርትራ ተጉዘው እንዳነበር ነገር ግን የፀጥታ ኃይሎች አውሮፕላን ማረፍያ…
የኤርትራ መንግስት ማብራሪያ እንዲሰጥ ተጠየቀ!

ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ እንዳይገቡ አሥመራ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የታገዱት የኢትዮጵያው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳስ ካርዲናል ብርሃነእየሱስ ጉዳይን በማስመልከት የኤርትራ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የኤርትራ መንግሥትን ማብራሪያ መጠየቋን ቫቲካን ኒውስ ዘገባ አመልክቷል።

የኤርትራ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጥያቄ ያቀረበችው ለኤርትራው ብሔራዊ የሐይማኖት ጉዳዮች ቢሮ ነው። ለቢሮው የቀረበው 'ማብራሪያ ይሰጠን' ደብዳቤ በኤርትራ የጳጳሳት ጉባኤ ዋና ፀሃፊ አባ ተስፋጊዮርጊስ ክፍሎም የተፈረመ ነው።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WolloUniversity

ትላንት በቀን 24/06/2012 ከምሽቱ 1:20 አከባቢ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትውት የተማሪዎች መኝታ ብሎክ ውስጥ በሚገኝ ፑል ቤት በሁለት ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ጸብ ምክንያት የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉ ግቢው ለተማሪዎች በለጠፈው ማስታወቂያ ገልጿል፡፡ ለተማሪው ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆነው ተማሪም በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አያይዞ ገልጿል፡፡

[Tikvah-family]
@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
አጭር መረጃ ስለሞጆ-ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ!

- የሞጆ ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል የሆነው የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ 88 በመቶ ተጠናቋል።

- ከሞጆ መቂ ከሚዘልቀው 56 ኪሎ ሜትር ውስጥ የ50 ኪሎ ሜትሩ የግንባታ ሂደቱ ተጠናቋል።

- የሞጆ – ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ 202 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን 13 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በጀት ተይዞለታል።

- የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ከአምስት ወራት በኋላ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"የኤርትራ ህዝብ ከትግራይ ህዝብ ጋር መዋጋት አይፈልግም ፤ ኢሳያስ እና ጥቂት የህግደፍ አባላት ፍላጎት ሊኖራቸው ይችላል" - ሌ/ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳይ

📹#7MB #EthioForum #TPLF
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ኤክሳይስ ታክስ የተካተተበት አዲሱ ደረሰኝ ከመጋቢት 1 ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንደሚውል የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

አዲሱን የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ገቢራዊ ለማድረግ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የገቢዎች ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አስታውቋል።

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 የካቲት 5 ቀን 2012 ዓ.ም ፀድቆ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

'ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ኮሮናን በመዋጋት ሀላፊነታቸውን እየተወጡ ያሉ መሪ' ሲል ቢቢሲ አድንቋቸዋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በመሆንእያገለገሉ ያሉትን ኢትዮጵያዊ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በዚህ ከባድ ወቅት ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ያሉ ታላቅ ሰው በማለት ጠቅሷቸዋል።

ዶክተር ቴዎድሮስ የስርጭት አድማሱን እያሰፋና በተለያዩ የዓለም ሀገራት እየተስፋፋ ያለውን ኮሮና ቫይረስ አስጊ በሆነበት በዚህ ጊዜ ሃላፊ መሆን ፈታኝ ቢሆንም በትኩረት እየሠሩ ነው ብሏል ዘገባው፡፡

የዶክተር ቴድሮስ የሥልጣን ዘመን በመጀመሪያ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በተከሰተው ኢቦላ አሁን ደግሞ በኮሮና የተፈተነ ቢሆንም ዶክተር ቴዎድሮስ ግን ጠንክረው በመስራት ላይ መሆናቸው ሚያስመሰግናቸው ነው ሲል ገልጿል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ የሆኑት ዶክተር ቴዎድሮስ ከሁለት አመት በፊት ወደ ሃለፊነት የመጡ ሲሆን በየአመቱ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ህልፈት ምክንያት የሆኑትን ወባ፣ኩፍኝ፣የሳንባ ምች እና ኤችአይቪ ለመቀነስ እየሠሩ እንደሚገኙ ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

#ENA #BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወልቃይት ስኳር ፋብሪካ!

ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነውን የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ወደ ግል ይዘዋወራሉ ተብለው ከሚጠበቁ ፋብሪካዎች መካከል መሆኑን ተከትሎ፣ የትግራይ ንግድ እና ዘርፉ ማኅበራት ምክር ቤት ሀብት በማሰባሰብ ለመግዛት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ።

የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት አሰፋ ኃይለ ሥላሴ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ የአዋጪነት ጥናት በምክር ቤቱ ተጠንቶ በመጠናቀቁ የክልሉን ምሁራን፣ ባለሀብቶች እና በውጪ የሚኖሩ ዳያስፖራዎችን በማሳተፍ እና ሀብት በማሰባሰብ ጨረታውን ለማሸነፍ እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

ይህንን እቅድ ምክር ቤቱ ይፋ ካደረገ ገና አንድ ሳምንቱ መሆኑን የገለፁት የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት አሰፋ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ግን ከፍተኛ ፍላጎቶች መምጣታቸውን ገልፀዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በሠው ማገት ወንጀል በተሠማራ ግለሠብ ላይ የ12 ዓመት ፅኑ እሥራት መወሠኑ ተገለፀ። ወንጀለኛ ፈንታሁን ቡቃያ እድሜው 26ዓመት የሳርና ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን የተከሰሰበት የወንጀል ዓይነት ሠው አግቶ 33, ሽህ ብር በመቀበሉ ነው። ወንጀለኛውም በፈፀመው ወንጀል ምክንያት 27/3/2012 ዓ/ም በፀጥታ ሀይል ቁጥጥር ስር ወሎ በሶሮቃ ፍ/ቤት ክስ ተመስርቶበታል። ፍ/ቤቱም ተከሳሹ የፈፀመው ወንጀል በማስረጃ የተደገፈ በመሆኑ የ12 ዓመት ፅኑ እሥራት ውሣኔ የተፈረደበት መሆኑን ኢንስፔክተር መላክ ከሣ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ Tegedie Communication
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተናገሩት፦

"ግድቡን የምንገነባው በራሳችን መሬት ላይ፤ ከራሳችን ሀገር የመነጨ ውሃ ፣ በራሳችን ገንዘብ ፤ ውሃ እንዳትሞሉ ብሎ ነገር አሜሪካኖቹ ከእነሱ በሚፈሰው ወንዝ በየትኛውም ያላደረጉትን ኢትዮጵያ እንድታደርግ የሚጠይቅ ስለሆነ በምንም መንገድ ተቀባይነት የለውም። ተስፋ የምናደርገው ግን ይሄንን አባባል ያስተካክላሉ ብለን ነው። እኛ ግን ግንባታችን ይፋጠንና ለዛ ይድረስ እንጂ የእኛው የራሳችን ግድብ ስለሆነ እንሞላለን ማንን ፍቃድ እንጠይቃለን?"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ የማስታወቂያ አባት ስርዓተ ቀብር...

በኢትዮጵያ የማስታወቂያ ሥራ ፈር ቀዳጅነት የሚታወቁት አንጋፋው ሁለገብ የኪነጥበብ ባለሙያ ውብሸት ወርቃለማሁ የቀብር ሥርዓት ዛሬ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡

#ዋልተንጉስዘሸገር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሙስጠፌ ወንድም ለከፍተኛ ህክምና አ/አ መጡ!

የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዘዳንት ሙስጠፌ ዑመር መሐመድ ታናሽ ወንድም የሆኑት አብዲራህማን ዑመር በደገሃቡር ከተማ በደረሰባቸው በስለት የመወጋት አደጋ ለከፍተኛ ህክምና ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የፕሬዝዳንቱ ኮሚኒኬሽን አማካሪ መሐመድ ኦላድ ጥቃቱ የደረሰባቸው በትላንተናው እለት መሆኑን ገልፀው ለግዜው የጤንነታቸው ሁኔታ ላይ እና የጥቃቱን ምክኒያት በተመለከተ ማብራሪያ መስጠት እደማይችሉ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ተናግረዋል።

[በአዲስ ማለዳ ጋዜጣ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኦነግ መንግሥትን አስጠነቀቀ!

በሰላም ከምንኖርበት ስፍራ እጅግ በሚያስደነግጥ ሁኔታ በታጠቀ ኃይል በአመራሮቻችን ላይ ወረራ ተፈጽሞብናል። በወቅቱ የመጣብን ኃይል ጥቂት ሲቪሎችን ለመያዝ የመጣ ሳይሆን አንድ ጦር ለመማረክ የመጣ ይመስል ነበር።»

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ «በሀገሪቱ ታሪክ እስከ ዛሬ ያልተፈጸመ» ያለው ግፍ እየተፈጸመብኝ ነው ሲል አማረረ። ኦነግ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ «የፖለቲካ ምህዳሩ የሰፋ መስሎን ወደ ሀገር ቤት ብንመለስም፣ መንግሥት በጦር ሠራዊቱ እና በሃብቱ (በከፍተኛ መዋዕለ ንዋዩ) በመተማመን በፓርቲያችን ላይ ግፍ እየፈጸመብን ነው» ብሏል። 

More https://telegra.ph/ETH-03-04-4

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የካቲት 29 በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል እንገናኝ!

Feminist Front ሃገር በቀል በጾታ እኩልነት ላይ የሚሰራ የፌሚኒስት ወጣቶች ማህበር ነው። በአሁን ወቅት Feminist Front ከግጥማዊ ቅዳሜ ጋር በመተባበር ‘ላንቺ’ የተባለ የድጋፍ መዋጮ ለአይነ ስውራን ሴቶች በየካቲት 29, 2012 አዘጋጅቷል።

ይህ የድጋፍ መዋጮ እነዚህ ሴቶች የሚያሳልፉትን ተደራራቢ ችግር ለመጋፈጥ እና ከማህበረሰቡ የሚደርስባቸውን መገለል ለመዋጋት የሚደረግ ነው።

የኛ ማህበር የነዚህን ሴቶች ለራሳቸው እና ለማህበረሰባቸው ለውጥን የማበርከት ተስጦ ሲያምን፣ እርሶም የዚ ድጋፍ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል።

Contact us: @FeministFront to get your tickets

#Lanchi
#የእኩልነትትውልድ
#FeministFront
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HAWASSA

የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ፦

- ሐሰተኛ የብር ኖቶች ህትመት ሲያካሂድ የነበረ አንድ የውጭ ዜግነት ያለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሏል።

- ፖሊስ ሰሞኑን ባካሄደው ክትትል በተደራጀ መንገድ የተሰረቁ ስምንት ሁለት እግር ብስክሌቶች እና አራት መኪኖችም በቁጥጥር ስር በማዋል በ27 ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እያካሄደ ይገኛል።

- ተሸከርካሪዎቹ ከተሰረቁ በኋላ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ለማስመሰል ሰነድ ተዘጋጅቶላቸው ለአገልግሎት እንዲውሉ ይደረግ ነበር።

- ተለይቶ ያልተገለፀ የውጭ አገር ዜግነት ያለው ግለሰብም ሐሰተኛ የብር ኖቶች ህትመት ሲያካሂድ ከነሙሉ ቁሳቁሱ መያዙን መምሪያው ያስታወቀ ሲሆን ምርመራም እየተካሄደበት ነው።

- አብዛኞቹ የስርቆት ወንጀሎች በረቀቀ መንገድ የተፈፀሙ መሆናቸውን የጠቆመው ፖሊስ፤ ወንጀለኞቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው ጥረት የህብረተሰቡ ሚና ከፍተኛ እንደነበርም ተገልጿል፡፡

[የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ ኢቢሲ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ፈተና በታብሌት በመጠቀም የምንፈትን እንደሆነ ላበስር እወዳለሁ" - ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ [የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር]

#ArtsTv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና ኦላይን ይሰጣል ወይ?

አዲሱ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ በቅርቡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ አዳሪ ትምህርት ቤትን በመረቁበት ወቅት የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና በኦንላይን ይሰጣል ማለታቸውን ከአርትስ ቴሌቪዥን ሰምተናል።

ይህንን ተከተትሎ ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ፈተናዎች ኤጀንሲ አምርተን ነበር፡፡ በዛም አንድ የተቋሙን ሰራተኛ በጉዳዩ ዙሪያ ጠይቀን በሰጡን መረጃ መሰረት የሀገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ እስካሁን ፈተናው በወረቀት እንደሚሆን ታሳቢ አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልጸውልናል፡፡

ነገር ግን አሁን ላይ በተለይም ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ከመጡ በኀላ አገልግሎቱን መስጠት በሚቻልባቸው አከባቢዎች ፈተናውን በኦንላይን ለመስጠት የታሰበ ነገር እንዳለ እንጂ እስካሁን የተረጋገጠ ነገር እንደሌለና መስሪያቤታቸውም በዚህ ጉዳይ በሚዲያ አንዳንድ ነገሮችን ከመስማት ውጪ ምንም ተጨባጭ ነገር እንዳልደረሰው አክለው ነግረውናል፡፡

#TikvahFamily

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GERD

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና የግብፁ አቻቸው አብዱል ፋታህ አል ሲሲ በታላቁ ኅዳሴ ግድብ ድርድር ዙሪያ በስልክ መምከራቸው ተነግሯል።

በውይይቱም ትራምፕ ግብፅ ባለፈው ሳምንት በዋሽንግተን ተገኝታ በግድቡ ድርድር ሰነድ ላይ መፈረሟን አድንቀዋል። ይሁንና ካይሮ የፈረመችበትን ሰነድ አዲስ አበባ ካለማወቋም ባሻገር በጋራ የተዘጋጀ ባለመሆኑ እንደማትቀበለው ግልፅ አቋማን ማሳወቋ እና የዩናይትድ ስቴትስን ለግብፅ የመወገን አካሄድ መተቸቷ ይታወሳል።

ትራምፕ የኢትዮጵያ መንግሥት ያልተቀበለውን የስምምነት ሰነድ ግብፅ መፈረሟ በግድቡ ድርድር ላይ ለመስማማት ያላትን ጥሩ ፍላጎት እና የፖለቲካ ታማኝነት ያሳየ ሲሉ ማወደሳቸውን ከካይሮ ቤተ መንግሥት የወጣ መግለጫ አትቷል።

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#USA #EGYPT #GERD #SUDAN #ETHIOPIA

የግብፅ ፕሬዝዳንት ቃል-አቀባይ ባሳም ራዲ አሜሪካ የግድቡ ስምምነት በ3ቱም አገራት እስኪፈረም ከኢትዮጵያ ፣ ሱዳንና ግብፅ መተባበሯን እንደምትቀጥል ትራምፕ ለፕሬዝዳንት አል-ሲሲ በስልክ መናገራቸውን ገልፀዋል። የፕሬዘዳንቱ ቃል አቀባይ ግብጽ ስምምነቱን መፈረሟን አረጋግጠዋል።

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVOD19

የጣሊያን መንግስት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ትምህርት ቤቶችን እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ሊዘጋ ነው።

ትምህርት ቤቶቹ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ በሚል እንደሚዘጉ የሃገሪቱን ባለስልጣናት ዋቢ ያደረገው የሬውተርስ ዘገባ ያመላክታል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ለሁለት ሳምንታት ይዘጋሉ ነው የተባለው፤ አሁን ላይ የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ በሆነባቸው የሃገሪቱ ሰሜናዊ አካባቢዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል።

በጣሊያን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ይገኛል። እስካሁን ባለው መረጃም 79 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ ከ2 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

#ሬውተርስ #ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በነገራችን ላይ በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 11 ደርሷል፤ 10 ሰዎች የሞቱት ከዋሽንግቶን ስቴት ሲሆን አንድ ሰው ደግሞ ካሊፎርኒያ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia