TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርስቲ በቃሉ ወረዳ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ለሁለተኛ ጊዜ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ዳይሬክተሮች እና የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ከ8 በላይ በሚሆኑ አውቶቢሶች ከ900 በላይ ተማሪዎች በመያዝ ከደጋን እስከ 17 ኪሎሜትር በእግር በመጓዝ የሰብል ስብሰባ እና የአንበጣ መከላከል ስራ እየተሰራ ይገኛል።

ምንጭ፦ ወሎ ዩኒቨርስቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ(ደሴ ካምፓስ) የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠል ዛሬ ከተማሪ ተወካዮች ጋር ውይይት እንደሚደረግ ተነግሮናል። አብዛኛው ተማሪ ትምህርት ፈላጊ ነው፤ ዛሬ ውይይት ከተደረገ በኃላ ነገ ትምህርት ይጀምራል የሚል ተስፋ አድሮብናል ብሎናል አንድ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ተወካይ። በሌላ በኩል አሁንም ስጋታቸው ሙሉ በሙሉ እንዳተቀረፈ፤ ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ እንደሚፈልጉ መልዕክቶቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ ተማሪዎች ገልፀዋል።

በተመሳሳይ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒስቨርሲቲ ዛሬ ተማሪዎቹ ተመልሰው ትምህርታቸው እንዲማሩ ድጋሜ ማስታወቂያ ቢያወጣም በማህበራዊ ሚዲያዎች ውስጥ ለውስጥ የሚሰራስጩ የማስፈራሪያ መልዕክቶች ስጋት አጭረውብናል ብለዋል የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ተማሪዎች። ዩኒቨርሲቲው እንዲህ ያሉ ነገሮችን እንዲቆጣጠር አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት ትምህርት የተቋረጠባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየሰሩ እንደሆነ እየገለፁልን ይገኛሉ። በአንፃሩ ችግር ላይ ነን የሚሉ ተማሪዎች ድምፃችን ይሰማ፤ ወደቤተሰቦቻችን፣ ወደ እናትና አባታችን በሰላም መልሱን እያሉ ይገኛሉ።

የዩኒቨርሲቲ ሁኔታዎች(07/03/2012)👇
https://telegra.ph/TIKVAH-11-17

አዳዲስ ጉዳዮች ሲኖሩ እናሳውቃለን!

@tikvahethiopiabot @tikvahethiopia
#WolloUniversity

ትላንት በቀን 24/06/2012 ከምሽቱ 1:20 አከባቢ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትውት የተማሪዎች መኝታ ብሎክ ውስጥ በሚገኝ ፑል ቤት በሁለት ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ጸብ ምክንያት የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉ ግቢው ለተማሪዎች በለጠፈው ማስታወቂያ ገልጿል፡፡ ለተማሪው ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆነው ተማሪም በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አያይዞ ገልጿል፡፡

[Tikvah-family]
@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ4 ሺህ በላይ ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 200 ተማሪዎች ነው ለ12ኛ ጊዜ እያስመረቀ የሚገኘው። ~ AMMA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WolloUniversity

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተቋርጦ የቆየውን የ2014 ዓ.ም የአንደኛ ሴሚስተር #የኤክስቴሽን ትምህርት ከየካቲት 05/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለማስቀጠል ወስኗል።

በመሆኑም ቀደም ሲል የተመዘገቡ ነባር የመጀመሪያ እና የ2ኛ ዲግሪ የኤክስቴሽን ተማሪዎች ምዝገባ ያደረጉበትን ስሊፕ በመያዝ ሪፖርት እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

አዲስ መመዝገብ የሚፈልጉ የመጀመሪያ እና የ2ኛ ዲግሪ የኤክስቴሽን አመልካቾች ጥር 28 እና 29/2014 ዓ.ም ያለቅጣት መመዝገብ እንደሚችሉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

@tikvahuniversity @Tikvahethiopia