TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVID19

በአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ግዛት አንድ ሰው በኮሮና ቫይረስ መሞቱን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል። ትላንት በግዛቷ የ71 ዓመት አዛውንት በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፤ አዛውንቱ ባለፈው ወር መነሻዋን ሳንፍራንሲስኮ ባደረገችው መርከብ ሳይሳፈሩ እንዳልቀረ ተገልጿል።

የአሁኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠርና የሚያደርገውን ጉዳት ለመቀነስ ያለመ ነው ተብሏል። ከዚህ ቀደም ዋሽንግተን እና ፍሎሪዳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸው ይታወሳል።

ከኋይት ሃውስ የወጡ መረጃዎች ደግሞ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በመላው አሜሪካ ለማድረግ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን ያመላክታል።

ለኮሮና ቫይረስ ምላሽ ለመስጠት የተቋቋመውን ቡድን የሚመሩት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ማይክ ፔንስ ማንኛውም አሜሪካዊ በህክምና ባለሙያ ከታዘዘ ግዴታ ምርመራ ማድረግ እንዳለበት ገልጸዋል።

#BBC #ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል። ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሀላፊም ሆነው ሰርተዋል። ከመቐለ ዩንቨርስቲ በህክምና ትምህርት ዲግሪ ያገኙ ሲሆን ከጣልያኑ ፓርማ ዩንቨርስቲ በአለም አቀፍ ጤና ላይ ያተኮረ ትምህርት ተከታትለው ከስምንት አመት በፊት ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

ምንጭ፦ fidelPost.com

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
42ኛው የካራማራ የድል በዓል የመታሠቢያ ቀን!

የዛሬ 42 አመት ተስፋፊው የመሀመድ ዚያድባሬ ኃይል ካራማራ ላይ አከርካሪው ተሠበረ። በውጤቱም በምስራቅ 700 ኪ.ሜ እንዲሁም በደቡብ 300 ኪ.ሜ ዘልቆ በወረራ ይዞት ከነበረው የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ተጠራርጎ ወጣ ።

ወድቃ የነበረችው ሰንደቃችንም ዳግም ተነስታ በክብር ከፍ አለች።

ይህን በአባቶቻችን ደምና አጥንት እና በእናቶቻችን ደጀንነት ያገኘነውን የመላ ኢትዮጵያውያን የጋራ ደማቅ የድል ታሪክ ለማክበር ድሉ በተገኘበት ዛሬ የካቲት 26 ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በኢትዮ ኩባ ወዳጅነት ፓርክ (በትግላችን ሐውልት) ላይ ለማክበር ዝግጅት ተጠናቋል።

በዝግጅቱ ላይ፦

- በጦርነቱ ወቅት በአመራር ላይ የነበሩ የቀድሞ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች (ጀኔራሎችን ጨምሮ ) ሌሎች መስመራዊ መኮንኖች

- ለድሉ መገኘት ቁልፍ ሚና የተወጡ የጀግናው አየር ኃይላችን አብራሪዎች

- በጦርነቱ የተሳተፉ ባለሌላ ማዕረግተኛ ወታደሮች (የጀብድ ሜዳይ የተሸለሙ ጭምር )

- በጦርነቱ ቤተሠቦቻቸውን ያጡ የኩባ ተማሪዎችና የህፃናት አንባ ልጆች

- ለኢትዮጵያ ድጋፍ በመስጠት በጦርነቱ የተሳተፉ ሀገራት አምባሳደሮች /ተወካዮቻቸው እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ።

በመሆኑም ታሪክና ሀገር ወዳድ የሆናችሁ ዜጎች በዕለቱ በቦታው ላይ ተገኝታችሁ የመታሠቢያ በዓሉን በድምቀት እንድታከብሩ ተጋብዛችሗል።

የበዓሉ ጊዜያዊ አስተባባሪዎች፣ ኮረማሽ የጉዞ ማህበር ከማይክ መላከ የኢትዮ- ኩባ ወዳጅነት ማህበር እና በኢትዮጵያ የኩባ ኤምባሲ ጋር በመተባበር።

#EliasMeseret
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ በሚል መሪ ቃል የተለያየ ሀሳብ ያላቸወን የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮችን፣ አክቲቪስቶችን፣ ታዋቂ ግለሰቦችንና አርቲስቶችን ያሳትፋል የተባለውና የካቲት 15 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሊካሄድ የነበረው ሩጫ መራዘሙ ይታወሳል፡፡

አዘጋጆቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት ውድድሩ መጋቢት 20 እንዲካሄድ ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የፍቃድ ደብዳቤ ማግኘቱን ገልጸውልናል፡፡

ይህን አስመልክቶም የፊታችን ቅዳሜ ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ በዮድ አቢሲኒያ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥና ሁሉም ሚዲያዎች በቦታው ተገኝተው የዚህን የሰላም ሩጫ ሂደቶች እንዲዘግቡ አዘጋጆቹ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ መረጃ ለቲክቫህ ቤተሰቦች፦

'ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ' የጎዳና ላይ ሩጫ አዘጋጆች በTIKVAH-ETH በኩል ለሚመዘገቡ የቤተሰቡ ተሳታፊዎች 250 ብር የነበረውን የቲቨርት ዋጋ 150 ማድረጋቸው ይታወሳል አሁንም ይኸው ምዝገባ ቀጥሎ ሩጫው ሲቃረብ ለተመዝጋቢዎች የቲሸርቶች የሚገኙባቸውን ቦታዎች የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

ለመመዝገብ፡- https://forms.gle/H3R8nxTamrMPyieN7

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጤና ሚኒስቴር፦

"የቀድሞ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሃላፊ ክቡር ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሾሙ:: መልካም የስራ ጊዜ!"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ እንዲሁም የባንኮች ማህበር ፕሬዝዳንት በመሆን ሲያገለግሉ ነበሩት አቶ አቢ ሳኖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ሆነ እንደተሾሙ ዋዜማ ሬድዮ ዘግቧል።

ምንጭ፦ ዋዜማ ሬድዮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በባሌ ዞን ጎባ ከተማ በህግ ጥላ ስር ለሚገኝ ተጠርጣሪ የአልኮል መጠጥ ደብቆ ለማቀበል የሞከረ ግለሰብ በአንድ ዓመት ከሁለት ወር እስራት እንዲቀጣ መደረጉን የጎባ ወረዳ ፍርድ ቤት ገለፀ።

የጎባ ወረዳ ፍርድ ቤት በአቶ ሄኖክ ዳምጤ ላይ የፍርድ ውሳኔውን ያሳለፈው የካቲት 25 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት ነው፡፡

ግለሰቡ ለቅጣት የተዳረገው የካቲት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ በጎባ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ተጠርጥረው በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ ጓደኞቹ በድብቅ የአረቄ መጠጥ ለማስገባት ሲሞክር በጥበቃ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ በመያዙ ነው፡፡

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ATTENTION

በአሁን ሰዓት በባሌ ሮቤ የአንበጣ መንጋ በስፋት እየታየ እንደሚገኝ የሮቤ ቲክቫህ ቤተሰቦች ሪፖርት አድርገዋል። መንጋው ጉዳት እንዳያደርስ ለመከላከል የሚደረግ ጥረት እየተመለከትን አይደለም ያሉት ቤተሰቦቻችን መንጋው ጉዳት ሳያደርስ ሁሉም አካል ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።

#Melaku
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GERD

የዓረብ ሊግ ሀገራት የህዳሴ ግድብ ስምምነትን እንዲደግፉ ግብፅ ያቀረበችውን ምክረ ሀሳብ ሱዳን ውድቅ ማድረጓ ተገልጿል።

ግብፅ በካይሮ በተካሄደው 153ኛ የዓረብ ሊግ ሀገራት የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ነው በህዳሴ ግድብ ድርድር ዙሪያ የሊጉ አባል ሀገራት ከሱዳን እና ከግብፅ ጎን እንዲሆኑ የሚጠይቅ ምክረ ሀሳብ ያቀረበችው።

ሱዳን በበኩሏ በግብፅ በኩል የቀረበውን የዓረብ ሊግ ድጋፍ ምክረ ሀሳብን ውድቅ አድርጋለች።

ስሟም ከዚህ ጋር ተያይዞ እንዲነሳ እንደማትፈልግ በይፋ ያስታወቀችው ሱዳን፥ ምክረ ሀሳቡ ብሄራዊ ጥቅሟን የሚጎዳ እንደሆነም ገልፃለች።

ሱዳን የዓረብ ሊግ ሀገራት በኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር አለመግባባት ውስጥ ጣልቃ እንዳይገቡ ፍላጎቷ መሆኑንም አስገንዝባለች።

#ኤፍቢሲ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የባልደራስ እና መኢአድ ቅንጅት...

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የካቲት 30፣ 2012 ዓ/ም ፓርቲዎች ጥምረታቸዉን እንዲያስገቡ ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት፣ በነገው ዕለት አርብ የካቲት 27/2012 ዓ/ም ከቀኑ በ5:00 ሰዓት የሚደረግ የሁለት ፓርቲዎች የ"ባልደራስ መኢአድ" ቅንጅት ይፈጥራሉ።

#ስንታየሁቸኮል
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#GONDAR "ተጠርጣሪዎቹ ምንም ዓይነት የህክምና ፍቃድ የላቸውም" - ፖሊስ በጎንደር ከተማ ጌዜ ያለፈባቸው መድሃኒቶችን ሲያሰራጩ የተያዙት ተጠርጣሪዎች ምንም ዓይነት የህክምና ፈቃድ እንደሌላቸው ተገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ ማራኪ ክፍለ ከተማ ልኡል አለማየሁ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚገኙ ተማሪዎች የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን መድሃኒቶች ሲያሰራጩ ነው የተያዙት። ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት…
#UPDATE

የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን መድኃኒቶች ሲያከፋፍሉ ነበሩ የተባሉ 13 ካናዳዊያን እና ሁለት ኢትዮጵያዊያን እያንዳንዳቸው በ20ሺህ ብር ዋስ መለቀቃቸውን በጎንደር የሦስተኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ደሳለኝ አበራ ለቢቢሲ ገለጹ።

15ቱ ግለሰቦች ትላንት የካቲት 25 ቀን 2012 ዓ. ም. በዋስ እንደተለቀቁ ገልጸዋል። 15ቱ ግለሰቦች ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 አካባቢ በሚገኝ ትምህርት ቤት የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን መድኃኒቶች በመስጠት ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አየልኝ ታከለው ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በምዕራብ ኦሮሚያ በመንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሸማቂ ተዋጊ ባለው ቡድን መካከል ያለውን ግጭት ለመፍታት ራሱን "ፍርቱ" ብሎ የሰየመ የእርቅ እና ሰላም ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራ መጀመሩን ዛሬ አስታወቀ።

ኮሚቴው በአራቱ የምዕራብ ኦሮሚያና ጉጂ ዞኖች ላይ እርቅ ወርዶ ከሚመሩበት ወታደራዊ እዝ እንዲወጡ፣ በሲቪል አስተዳደር ስር እንዲገቡም እሰራለሁ ብሏል። የክልሉ መንግስት ይህንን ጅምር በበጎ እንደሚመለከተው እና ኮሚቴው የወጠነውም እንዲሳካ ፍላጎቱ መሆኑን አሳውቋል።

ፍርቱ የእርቅ እና ሰላም ኮሚቴ በመንግስት እና በሸማቂ ተዋጊዎች አለመግባባት ምክንያት በህዝቡ ላይ የደረሰው እና እየደረሰ ነው ያለው እንግልት እንዲቆም የማቀርበውን የእርቅ ጥሪ በማይቀበለው ላይ የተለመዱ ዓለም አቀፍ የቅጣት ተሞክሮዎች እንዲተገበሩ ጫና አደርጋለሁ ብሏል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ችሎት

እነ አቶ በረከት ስምኦን በጤና መታወክ ምክንያት እየተሰቃየን በመሆኑ የክስ መዝገባችን ተመርምሮ አስቸኳይ ፍትህ ሊሰጠን ይገባል ሲሉ ለችሎት ጥያቄ አቀረቡ። 

በጥረት ኮርፖሬት በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ በረከት ስምኦን፣ አቶ ታደሰ ካሳና አቶ ዳንኤል ግዛው ዛሬ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፈርድ ቤት ቀርበው ነበር።

በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል መዝገቡ ተመርምሮ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። በተለይም አቶ በረከት እንዳሉት ቀደም ሲል የጀመራቸው የጤና መታወክ እየተባባሰ በመምጣቱ ጊዜ ሳይራዘም ፍትህ እንዲሰጣቸው አመልክተዋል።

አቶ ታደሰ ካሳ በበኩላቸው የክስ መስገቡ ሆነ ተብሎ እንዲራዘም እየተደረገ በመሆኑ ከተያዝንበት ጊዜ መርዘምና ከጤና ችግራችን አንፃር ታይቶ በአጭር ቀጠሮ እልባት እንዲሰጠን ሲሉ ጠይቀዋል።

More https://telegra.ph/ETH-03-05-3

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#GERD #EGYPT #ETHIOPIA #SUDAN

የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜሕ ሽኩሪ በካይሮ የሚገኙ የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮችን አነጋገሩ። ግብፅ በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ "ትክክለኛና ሚዛናዊ ስምምነት" ላይ ለመድረስ ቁርጠኛ መሆኗን እንደተናገሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ ገልጸዋል።

#EsheteBekele
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
"የግድቡ ሁለት ሦስተኛ ስራ ተጠናቋል!" - አቶ ደመቀ መኮንን [ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር]

በነገራችን ላይ ዛሬ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ አስተባባሪ ምክር ቤት 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል።

በጉባኤው የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ የምክር ቤቱ አባላት ተገኝተው ነበር።

በጉባኤው የግድቡ ግንባታ የደረሰበት ደረጃና የታችኛው ተፋሰስ አገራት የሦስትዮሽ ድርድርን የተመለከተ ገለፃና ውይይት ተደርጓል። የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአሁኑ ወቅት የግድቡ ሁለት ሦስተኛ ስራ መጠናቀቁን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተላለፈ መልዕክት፦

በ2012 የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲው በመማር ላይ እያሉ ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት ትምህርታቸውን አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎቹ መልዕክት አስተላልፏል።

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ እስከ መጭው ሰኞ የካቲት 30/2012 ዓ.ም ድረስ ብቻ ተማሪዎች በየትምህርት ክፍላቸው እንዲያመለክቱ የማካካሻ ትምህርት ተሰጥቷቸው የማጠቃለያ ፈተና እንዲወስዱ ወስኗል።

በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ግቢ ለቀው የወጡ ተማሪዎች ተመልሰው በየትምህርት ክፍላቸው ተገኝተው የማካካሻ ትምህርቱን እንዲጀምሩ አሳስቧል።

የጎንደር ዮኒቨርሲቲ
የካቲት 26/2012ዓ.ም
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የግብፁ ፕሬዘዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ማክሰኞ ዕለት ከሀገሪቱ ከፍተኛ የጦር አዛዦች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

ውይይቱ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በሀገሪቱ እና አካባቢው የፀጥታና የደህንነት ጉዳይ ላይ ነበር በተለይም ከአሸባሪዎች ጥቃት ጋር በተያያዘ የሀገሪቷን ደህንነት እና ፀጥታ ከማስጠበቅ አንፃር ሰፊ ውይይት እንዳደርጉ ነው የተሰማው።

ጉዳዩ ይህ ሆኖ ሳለ በሀገራችን ኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በጉዳዩ ላይ የተዛባ እና ሀሰተኛ መረጃ እያሰራጩ ነው።

"ግብፅ በህዳሴው ግድብ ምክንያት ኢትዮጵያን ልትወጋ ነው! ጥቃት ልትፈፅም ነው" በሚል የሚሰራጩት መረጃዎች ከእውነታው የራቁ እና የመረጃ ምንጭም የሌላቸው ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮሮና ቫይረስ ደቡብ አፍሪካም ገብቷል!

ዛሬ ከደቡብ አፍሪካ ጤና ሚኒስቴር እንደተሰማው በደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ግለሰብ መኖሩ ተረጋግጧል። የግለሰቡ ዕድሜ 38 ዓመት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ከባለቤቱ ጋር [March 1] ከጣልያን ወደ ደቡብ አፍሪካ የተመለሰ እንደሆነ ነው የተነገረው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia