TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVOD19

የጣሊያን መንግስት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ትምህርት ቤቶችን እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ሊዘጋ ነው።

ትምህርት ቤቶቹ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ በሚል እንደሚዘጉ የሃገሪቱን ባለስልጣናት ዋቢ ያደረገው የሬውተርስ ዘገባ ያመላክታል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ለሁለት ሳምንታት ይዘጋሉ ነው የተባለው፤ አሁን ላይ የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ በሆነባቸው የሃገሪቱ ሰሜናዊ አካባቢዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል።

በጣሊያን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ይገኛል። እስካሁን ባለው መረጃም 79 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ ከ2 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

#ሬውተርስ #ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia