TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56K photos
1.4K videos
202 files
3.79K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVID19

መቼ ነው ማስክ ማድረግ ያለብኝ ?

የኮሮና ስርጭት ካለባቸው የተለያዩ ሀገራት በተለይም ደግሞ ከቻይና የሚመጡ መንገደኞች ቢያንስ ለ14 ቀናት የፊት ማስክ በማድረግ እና አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ ይመከራል። እንዲሁም ከነዚህ ሰዎች ጋር ቀጥተኛ የሆነ ንክኪ ከማድረግ በመቆጠብ እንዲሁም በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወይም በጤና ሚኒስቴር ህብረተሰቡ እንዲጠቀም ሲታወጅ!

#EPHI
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ውድ ቤተሰቦቻችን ራሳችሁን ከኮሮና ቫይረስ ለመጠበቅ ማድረግ የሚገባችሁን ጥንቃቄዎች ከኤፍ ቢ ሲ ድረገፅ፦

- በሕይዎት ካሉም ሆነ ከሞቱ የቤትና የዱር እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ

- ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ

- የትኩሳትና የሳል ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ፣

- እጅን በሳሙናና ውሃ መታጠብ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ከፈጠሩ፣

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከማጂ ወረዳ ቲክቫህ ቤተሰቦች፦

በምዕራብ ኦሞ ዞን ውስጥ የማጂ ወረዳ ባለሥልጣን በመታሠሩ ባለሥልጣኑ መታሠሩ አግባብ አይደለም በማለት የቱም ከተማና የአካባቢው ህዝብ ተቃውሞ ማሰማቱን የቲክቫህ ቤተሰቦች አሳውቀዋል።

ከ19/6/2012 እስከ 20/6/2012 ማለዳ ድረስ በርካታ የተኩስ ድምፅ ነበር የሚሉት ቤተሰቦቻችን አርፍዶም በከተማዋ የጎማ ቃጠሎም ታይቷል፤ 2 ሰዎችም በተተኮሰ ጥይት ሞቷል ብለውናል።

ቲክቫህ አትዮጵያ ከማጂ ቤተሰቦቹ የሚመጡ መልዕክቶችን እንዲሁም ስለከተማው ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ አሰባስቦ ያጋራችኃል። #TikvahFamily #MajiWoreda

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ProsperityParty

ብልጽግና ፓርቲ [Prospertity Party] በትግራይ ክልል በሁሉም ወረዳዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በቅርቡ እንደሚከፍት የፓርቲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙት ኃላፊ ገለጹ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አወሉ አብዲ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ብልጽግና አገር አቀፍ ፓርቲ በመሆኑ ከትግራይ ክልል ጋር በሚኖረው ሕገ መንግሥታዊ ግንኙነት መሠረት አደረጃጀቱን በማስፋት በቅርቡ በክልሉ በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ጽሕፈት ቤቶችን ይከፍታል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል ነባራዊ ሁኔታ እስካሁን ትርጉም ባለው መልኩ እንቅስቃሴ እንዳልተደረገ የገለጹት አቶ አወሉ፤ ነገር ግን አሁን በአዲስ መልክ የትግራይ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ተቋቁሞ ሥራውን እየሰራ ስለሆነ በቅርብ ጊዜ በክልል፣ በዞኖች፣ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ እንቅስቃሴ ይደረጋል ብለዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#MinistryOfCultureAndTourism

በቅርቡ ከኔዘርላንድስ የተመለሰው የ18ኛው ክፍለ ዘመን ዘውድ በነገው እለት ለትግራይ ክልል ጨለቆት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ተመላሽ ይደረጋል። በዕለቱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የመገናኛ ብዙሃን በተገኙበት በብሔራዊ ሙዚየም ቅጥር ግቢ የርክክብ ሥነ ሥርዓትና ሽኝት እንደሚካሄድ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።

ለተጨማሪ መረጃ ፦ 0911360902
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ከእስር ተፈተዋል!

የኢትዮጵያ መንግስት ክሳቸው አንዲቋረጥ ካደረገላቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ኤርሚያስ ጠቅል አመልጋ በዛሬው ዕለት ከእስር ተፈተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸው ተሰምቷል።

PHOTO : JANO BAND
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል፦

ይህ አዲስ አበባ ከተማ ወሎ ሰፈር አደባባዩ ላይ ያለዉ የድልድይ አካል ቢወድቅ ከስር ባሉ በተላላፊዎች ላይ ጉዳት ስለሚያስከትል ይታሰብበት!

#DrivinginAddis #EliasMeseret

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ProsperityParty ብልጽግና ፓርቲ [Prospertity Party] በትግራይ ክልል በሁሉም ወረዳዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በቅርቡ እንደሚከፍት የፓርቲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙት ኃላፊ ገለጹ፡፡ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አወሉ አብዲ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ብልጽግና አገር አቀፍ ፓርቲ በመሆኑ ከትግራይ ክልል ጋር በሚኖረው ሕገ መንግሥታዊ…
#TPLF #ProsperityParty

ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል በሁሉም ወረዳዎች ቢሮ እንደሚከፍት ያስታወቀ ቢሆንም የክልሉ መንግስት ግን የሚያዉቀዉ ነገር እንደሌለ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸዉ ረዳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የተናገሩት፦

ብልጽግና ፓርቲ ለትግራይ ክልል የተሾሙ ግለሰቦች እንዳሉ ሰምቻለሁ እነማን እንደተሾሙ ግን ወደ ፊት የሚሆነዉን የምናይ ይሆናል፡

ብልጽግና በትግራይ ክልል ብዙ ደጋፊ አለው ብዬ አላምንም፤ ማንኛዉም ፓርቲ ህጋዊ እስከሆነ ድረስ ግን በትግራይ ክልል የመንቀሳቀስ መብት አለዉ።

#EthioFM #አባቱመረቀ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#attention አሁንም በአንዳድን የማንቡክ አካባቢዎች የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ እየተገለፀልን ከቤተሰቦቻችን እየተገለፅልን ነው። በአካባቢው የተፈጠረውንና እየተፈጠረው ያለውን ዝርዝር ጉዳይ ከቤተሰቦቻችን ጠይቀን፤ ተጨማሪ መረጃዎችን አካተን እንድታነቡት እናደርጋለን። ለሁሉም ግን የሚመለከታችሁ አካላት [የፀጥታ ኃይሉ] የአካባቢውን ደህንነት እንድታስጠብቁ የቲክቫህ ማንቡክ ቤተሰቦች አሳስበዋል።…
#UPDATE

በዳንጉር ወረዳ ተስተውሎ የነበረው የፀጥታ ችግር በቁጥጥር ስር መዋሉን የመከተል ዞን አስታወቀ፡፡ የፀጥታ ችግሩ 3 ሰዎችን ለህልፈት፣ 7ቶችን ደግሞ ለከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ሰለባ ከማድረግ ባለፈ የተወሰኑ ቤቶች እንዲቃጠሉ ምክንያት መሆኑንም ተገልጿል።

በፀጥታ ኃይሎች ፣ በሀገር ሽማግሌዎች እና በሐይማኖት አባቶች የተቀናጀ ስራ የተስተዋለው የፀጥታ ችግር በቁጥጥር ስር መዋሉንና ህብረተሰቡን የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል። በአካባቢው የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ችግሩ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይዘመትም በተቀናጀ መልኩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፤ ህብረተሰቡ ያቆየውን አብሮ የመኖር እሴት አክብሮ ለዘላቂ ሰላም መስፈን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል፡፡

[የክልሉ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከማጂ ወረዳ ቲክቫህ ቤተሰቦች፦ በምዕራብ ኦሞ ዞን ውስጥ የማጂ ወረዳ ባለሥልጣን በመታሠሩ ባለሥልጣኑ መታሠሩ አግባብ አይደለም በማለት የቱም ከተማና የአካባቢው ህዝብ ተቃውሞ ማሰማቱን የቲክቫህ ቤተሰቦች አሳውቀዋል። ከ19/6/2012 እስከ 20/6/2012 ማለዳ ድረስ በርካታ የተኩስ ድምፅ ነበር የሚሉት ቤተሰቦቻችን አርፍዶም በከተማዋ የጎማ ቃጠሎም ታይቷል፤ 2 ሰዎችም በተተኮሰ ጥይት ሞቷል…
#UPDATE

በማጂ ወረዳ ተቃውሞ የሰዎች ህይወት አልፏል!

በደቡብ ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን ማጂ ወረዳ ቱም ከተማ በዛሬው ዕለት በተደረገ ተቃውሞ ላይ የጸጥታ ኃይሎች በተኮሱት ጥይት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የሕክምና ተቋም ኃላፊ ለጀርመን ድምፅ ተናገሩ።

የዞኑ ባለሥልጣናት እና የዐይን እማኞችም ጸጥታ ኃይሎች በተኮሱት ጥይት ከተገደሉት በተጨማሪ ሌሎች ከአስር በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን አረጋግጠዋል።

ሰልፉ የተደረገዉ አዲስ በተዋቀረው በምዕራብ ኦሞ ዞን የምትገኘው የማጂ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ እና የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ መታሰራቸውን በመቃወም ነበር።

«አስራ አንድ ሰው [በጥይት] ተመቷል። ሶስቱ ሴቶች ናቸው። ትልልቅ ሰዎች እና ሕፃናትም አሉበት» የሚሉት የዐይን እማኙ «ሰልፍ ሲደረግ መንገድ ይዘጋል። መንገድ ሲዘጋ መከላከያ እና ልዩ ኃይል መጣ። ከዚያ በአካባቢው በተሰበሰበው ሕዝብ ላይ ምንም ነገር ሳያማክር ተኩስ ጀመረ» ሲሉ መነሾውን አብራርተዋል።

More : https://telegra.ph/Maji-02-28

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የማጂ ወረዳ ጤና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ አኩ፦

"ቱም በተባለችው ከተማ በተደረገው ሰልፍ ስድስት ሰዎች በጸጥታ አስከባሪዎች ተገድለዋል። ዛሬ ጠዋት በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የነበሩ አራት ሰዎች በልዩ ኃይል እና በመከላከያ ሠራዊት በተተኮሰ ጥይት ተመተው እኛ ጋ ተኝተዋል። የሞቱት ሬሳቸው ሳይነሳ እዚያው ነው ያለው። የሞቱት ወደ ስድስት የሚሆኑ ሰዎች ናቸው። በአራት ጥይት የቆሰሉ አንድ ሰው ለተጨማሪ ሕክምና ወደ ማጂ ተልከዋል።"

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከማጂ ወረዳ ቲክቫህ ቤተሰቦች፦ በምዕራብ ኦሞ ዞን ውስጥ የማጂ ወረዳ ባለሥልጣን በመታሠሩ ባለሥልጣኑ መታሠሩ አግባብ አይደለም በማለት የቱም ከተማና የአካባቢው ህዝብ ተቃውሞ ማሰማቱን የቲክቫህ ቤተሰቦች አሳውቀዋል። ከ19/6/2012 እስከ 20/6/2012 ማለዳ ድረስ በርካታ የተኩስ ድምፅ ነበር የሚሉት ቤተሰቦቻችን አርፍዶም በከተማዋ የጎማ ቃጠሎም ታይቷል፤ 2 ሰዎችም በተተኮሰ ጥይት ሞቷል…
የምዕራብ ኦሞ ዞን የሚሊሺያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን መኮንን፦

"በቱም ከተማ የተገደሉት ሰዎች ሁለት (2) ብቻ ናቸው። ችግሮችን ለማረጋጋት ዛሬ ቱም ማዕከል ላይ ልዩ ኃይል እና መከላከያ ሰራዊት ወደ ከተማው ከገባ በኋላ በተተኮሰው ጥይት አንድ ሴት፤ አንድ ወንድ ሞተዋል የሚል መረጃ አለን። አስር ወንዶች፤ ሁለት ሴቶች ቆስለዋል የሚል መረጃ ነው በስልክ እየደረሰን ያለው"

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቻይና ውሃን የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰቦች፦ እኛ ጥያቄያችን ገንዘብ ሳይሆን ወደሀገራችን መመለስ ነው፤ እኛ ገንዘብ አንፈልግም መንግስት ዜጎቻችን ናችሁ የሚለን ከሆነ በአስቸኳይ ወደሀገራችን ይመልሰን ሲሉ እየጠየቁ ነው። ባለፉት ሳምንታት በተደጋጋሚ ጥያቄያችንን እያቀረብን ቢሆንም መፍትሄ አልተገኘልንም ብለዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በዉሃን የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት 'ወደ አገራችን መልሱን' የሚለውን የተማፅኖ ደብዳቤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መላካቸውን ጠቁመዋል።

የቻይና መንግሥት በወረርሽኙ ምክንያት መውጣትም ሆነ መግባት ከከለከለባት የዉሃን ከተማ መውጣት የሚችሉበትን ሁኔታ ቢያመቻች አብዛኞቹ ተማሪዎች ወጪያቸውን ራሳቸው ሸፍነው ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እንደሚፈልጉ ኅብረቱ ለተማሪዎቹ አሰራጭቶት በነበረው መጠይቅ ለማረጋገጥ ችሏል።

ምንም እንኳ የሀገሪቱ [የቻይና መንግሥት] አስፈላጊ ነገሮችን እያቀረበላቸው ቢሆንም ተማሪዎች ከባድ የሥነ ልቦና ጫና ላይ በመሆናቸው የግድ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ለመፃፍ መገደዳቸውን ተናግረዋል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የኮሮና ቫይረስ [#COVID19] መተላለፊያ መንገዶች እንድታውቋቸው፦

የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የመተንፈሻ አካል የሚያጠቃ በሽታ ነው። ዋናው የመተላለፊያ መንገድ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በሚያስሉበት እና በሚያስነጥሱበት ወቅት ትንፋሽ ጋር በሚወጡ ፈሳሾች ጋር በሚደረግ ንክኪ ነው።

እንዴት መከላከል ይቻላል?

- በሚያስነጥሱበት ወይም በሚያስሉበት ወቅት አፍና አፍንጫዎን በክንድ ወይም በሶፍት መሸፈን

- አይን፣ አፍንጫ እና አፍን ባልታጠበ እጅ አለመንካት

- በውሃ እና በሳሙና መታጠብ፣ አልኮል ነክ በሆኑ የንፅህና መጠበቂያዎች እጅዎን በአግባቡ ማሸት

- የተጠቀሙበትን ሶፍት በፍጥነት በጥንቃቄ መክደኛ ወዳለው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ መጣል

#ጤናሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19 #ETHIOPIA

ከጤና ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተገኘ መረጃ፦

ዛሬ በለይቶ ማቆያ ማእከል ውስጥ አንድ የተጠረጠረ ቻይናዊ እንደሚገኝ ተሰምቷል። ግለሰቡ እ.ኤ.አ. ፌብሩዋሪ 22 ከቤጂንግ የመጣ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በወቅቱ ምንም ምልክቶች እንዳልታዩበት፤ በቤት ውስጥ ተገልሎ የቆየ ነበር፡፡ ዛሬ ትኩሳት ፣ ሳል እና የጉሮሮ መቁሰል ገጥሞት ክትትል እየተደረገለት ይገኛል፡፡ የግለሰቡ ናሙና ውጤት ዛሬ ማታ ይፋ ይደረጋል።

የበሽታው ስርጭት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን 20 የተጠረጠሩ ኬዞች የነበሩ ሲሆን ሁሉም ከቫይረሱ ነፃ ናቸው። በአሁኑ ወቅት በአገራችን በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠ ግለሰብ የለም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19 #ETHIOPIA

የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፦

"ይህ መረጃ እስከ ተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በ አገራችን የተረገገጠ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ የለም ነገር ግን እስከ አሁን ድረስ 20 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረዉ በመለያ ማእከል ክትትል ተደርጎላቸዉ ከቫረሱ ነጻመሆናቸዉ ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ጊዜ አንድ ተጠርጣሪ በማለያ ማእከል ተለይቶ ክትትል እየተደረገለት ሲሆን ናሙና ተወስዶ ላብራቶሪ እየተሰራ ነዉ፡፡ ዉጤቱም እንደደረሰ እናሳዉቃለን፡፡ ሕብረተሰቡ በቫረይሱ መያዙ የተረጋገጠ ሰዉ አለመኖሩን አዉቆ ሳይዘናጋ የበለጠ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ ያሳስባል፡፡"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ...

በርካታ በሚባሉ የሀገሪቱ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ጥቆማ በማድረስ ላይ ይገኛሉ። በምን ምክንያት ይህ ሊሆን እንደቻለ የሚመለከታቸው አካላት ሚሰጡት መረጃ ካለ እንድታነቡት እናደርጋለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር እቶ ሞገስ መኮንን የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ለዚህ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ለአሁን እለመታወቁን፤ ነገር ግን ከግልገል ጊቤ ሦስት ከሚቀርበው የኃይል አቅርቦት መስመር ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል አቶ ሞገስ ግምታቸውን ተናግረዋል።

አክለውም የድርጅቱ ባለሙያዎች የኃይል መቋረጡን ምክንያት ለመለየትና አገልግሎቱን ለመመለስ እየሰሩ መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።

በአጭር ጊዜ ውስጥም በአዲስ አበባ ከተማ ያጋጠመው የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ እንደሚስተከል እና በተከታይነትም የሌሎቹም አካባቢዎች አገልግሎት እንደሚመለስ አቶ ሞገስ ገልጸዋል።

በአንዳንድ ስፍራዎችም ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እየተመለሰ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#UPDATE

አመሻሹ ላይ በመላው ሃገሪቱ የኤሌክትሪክ መቋረጡን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሰጡት ምላሽና ማብራሪያ :-

ምንጭ፦ ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪ ኃይል መመለሱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ከተማ ቤተሰቦች አሳውቀዋል። አሁንም ግን የኤሌክትሪክ ኃይል ያልተመለሰባቸው አካባቢዎች በርካታ ናቸው።

PHOTO : FILE
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፦

በኃይል ማስተላለፊያ ስርዓታችን ላይ በገጠመን ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ ኃይል ተቋርጧል።

በአሁኑ ወቅት ችግሩ የተከሰተው በዚህ ምክንያት ነው ለማለት አስቸጋሪ ቢሆንም ከጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

የጣና በለስና የፊንጫ ኅይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ከሲስተም ጋር ማገናኘት በመቻሉ የአዲስ አበባን የተወሰኑ አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል።

በቀጣይም በየደረጃው ሁሉንም የሀገሪቱ ክፍሎች ኃይል እንዲያገኙ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው።

በዚህ አጋጣሚ ለተፈጠረው ችግር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይቅርታ ይጠይቃል።

የካቲት 20/2012 ዓ/ም

#EthiopianElectricPower
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia